Heaven — and Hell — are Real
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሮሜ ፡ 23) የሚነግረን “ የኃጢዓት ደሞዝ ሞት ነው “ ፤ ሁልጊዜ ኃጢዓት ወደ ሞት ይመራል ፡፡ ዛሬ እንደ ሚያስከፋ ነው ሉቃስ 16 እንደ ጥናት ሞት እና ሲዖል ላይ እናዉጠነጥናለን ፤ መልካም ዜና ሊኖረን የቻለበት ምክንያት መጀመሪያ መጥፎ ዜና ስለነበረን ነው ፡፡ ለጠፉት በጎች ስለሚመጣው ዘላለማዊ ቅጣት ከማዉራት አሁንም እናፍራለን ፡፡
ትምህርት
ሉቃስ (16፡ 19)፡ በዚህ ምሳሌ ኢየሱስ አንድ ቀይ ልብስ እና ቀጭን የተፈተለ ልብስ የለበሰን ባለጠጋን ሰዉ ገለፀ - አለባበሱ ብቻ ባለፀጋ እንደነበር እንድታዉቁት ይፈቅድላችኋል ፡፡ እያንዳንዷን ቀን ከመጠን በላይ ይጠግባል ፡፡
ሉቃስ (16፡ 20)፡ ቀጥሎም ኢየሱስ አልዓዛር የሚባለዉን አንድ ድሀ ሰዉዬ ገለፀው ፤ በመፅሀፍ አንድ ሰዉ የተሰየመበት ቦታ ይህ ብቸኛው ምሳሌ ነው ነገር ግን ይህ አልዓዛር የማሪያም እና የማርታ ወንድም አልነበረም ፡፡
ሉቃስ (16፡ 21)፡ “ ከባለ ጠጋዉም ማዕድ ከሚወድቀዉ ፍርፋሪ ሊጠግብ ይመኝ ነበር “ ፤ ኢየሱስ ሰዎችን ወደ ግብዣዉ እንዲመጡ ጋበዛቸው ሀብታሙ ግን አላደረገዉም ፡፡ በዚያ ፈንታ ዉሻዎች መጥተዉ ቁስሎቹን ላሱለት ፡፡
ስለ ድሆች ሚናችን ምንድን ነው ? ምናልባት ይህ ባለፀጋ ሁልጊዜ በሩ ላይ ድሀዉን አይቶታል እርሱን በመርዳት ፈንታ ግን ምናልባት እየተበሳጨ እንደ ነበር እና በሚኖረዉ እየተደነቀ ያስባል ፡፡ ምሳሌ በተደጋጋሚ ለሚያስፈልጋቸዉ እንዲከባከቡዓቸዉ ሰዎችን ተጣርቷል፡ “ ባልንጀራዉን የሚንቅ ይበድላል ፤ ለድሀ ግን የሚራራ ምስጉን ነው “ (ምሳ 14፡ 21) ፤ “ ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሄር ያበድራል በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል” (ምሳ 19፡ 17) ፡፡ ለድሃ ምግብ፣ አስፈላጊ ነገሮች ወይም በመስጠት ርህራሄ በምናሳይ ጊዜ እግዚአብሄር ሽልማት እንደሚሰጠን ይናገራል ፤ ምሳ (21፡ 13) የሚለው “ የድሀዉን ጩኸት እንዳይሰማ ጆሮዉን የሚደፍን ሰው እርሱ ራሱ ይጮኻል አይሰማለትምም “ ፤ ምሳ (28፡ 27) የሚመሳሰል ነው “ ለድሃ የሚሰጥ አያጣም ዓይኖቹን የሚጨፍን ግን እጅግ ይረገማል “ ፡፡ ባለፀጋዉ ሰዉዬ ከአልዓዛር መዞሩን በቀጠለ ጊዜ ራሱ ላይ በደንብ ያተኮረ ይሆናል ፡፡ በፍፁም ከእግዚአብሄር ስጦታ ዉጭ እንደ ማንችል የምናስታዉስ መሆን ያስፈልገናል ፤ በዙሪያችሁ ያሉትን “ አልዓዛሮች “ ለመርዳት እምቢ ካልን ምንም ይቅርታ አይኖረንም ፡፡
ሉቃስ (16፡ 22-23)፡ “ ድሀዉም ሞተ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት ፤ ባለ ጠጋዉ ደግሞ ሞተና ተቀበረ “ ፤ ከሞት በኋላ ኑሮአቸዉ ቀጠለ ፤ ባለፀጋው ሰዉዬ “ በከፍተኛ ስቃይ ዉስጥ ሆነ “ ወይም ቋሚ ስቃይ ዉስጥ ሆኖ አሻቅቦ ሲመለከት አብርሃምን አየው ፡፡ የሆነ ሰዉ በሰማይ ነዉ ብለን ማሰብ ችግር የለዉም ነገር ግን በሞት በስቃይ መሆንን አንቀበልም ፤ ይልቁንም ሲዖል እዉነት ነዉ ብለን እንጠራጠራለን ፡፡ የዚህ ባለፀጋ ሰዉዬ አኳኳን ኢየሱስ ያለዉን ያሳያል “ እዉነት እላችኋለሁ ለባለጠጋ ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት ጭንቅ ነው “ (ማቴ 19፡ 23) ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ማን ሊድን ይችላል የሚለዉን ለማወቅ በፈለጉ ጊዜ ኢየሱስ “ ይህ በሰዉ ዘንድ አይቻልም በእግዚአብሄር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው “ (ማቴ 19፡ 26) ፡፡ ሀብታሙ ቀረጥ ሰብሳቢ ዘኪዎስ ቆይቶ ለሀብታም ሰዉ ወደ መንግስተ ሰማይ መግባት የሚቻል እንደ ነበር አረጋግጣል (ሉቃ 19፡ 1-10) ፡፡
ሉቃስ (16፡ 23-24)፡ አሁን ሁኔታቸዉ ተገለበጠ ፤ አሁን ሀብታሙ ሰዉዬ ከሩቅ ሆኖ አልዓዛር ከነበረው ነገር ጓጓ (ፈለገ) ፤ ሀብታሙ ሰዉዬ አብርሃም እንደሚያውቀው “ አብርሃም አባት ሆይ “ ብሎ ጠራው ፤ አስተዉሉ “ አልዓዛርን ላክልኝ “ ነዉ ያለው ፤ አሁንም እንኳን ድሀዉ ሰዉዬ እንዲያገለግለዉ ፈለገ ፡፡ ሀብታሙ ሰዉዬ ከዘላለማዊዉ ነበልባል እና እሳት ስቃይ ማስታገሻ ፈለገ ፡፡ ሲዖል ባይኖር በኢየሱስ የመስቀል ሞት ላይ ትርጉም አይኖርም ነበር ፡፡ ኢየሱስ በኢሳያስ 53 በተተነበየዉ ህመም እና ጭንቀት ዉስጥ ለምን ሄደ ? በሲዖል ካለው ከእሳት፣ ከነበልባል እና ከስቃይ ነፃ ሊያወጣን መጣ ፡፡ ብዙ መፅሀፍት ሲዖል እዉነት እንደሆነ ይናገራሉ ፡፡
- ማቴ (25፡ 41, 46)፡ “ በግራዉ ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል እናንተ ርጉማን ለሰይጣንና ለመለዓክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ !.....እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ ፡፡ “ በዘላለማዊ ህይወት ካመናችሁ በዘላለማዊ ቅጣት ማመን አለባችሁ ፤ የተወሰነ ነገር ከመፅሀፍ ዉስጥ ማስወጣት እና ከዚህ በኋላ አይተገበርም የሚል ቅሬታ ማቅረብ አትችሉም ፡፡ መፈለግ ያለብን እና የጠፉትን ማግኘት ያለብን ምክንያት እግዚአብሄርን ለማያዉቁት የዘላለም ቅጣት ስላለ ነው ፡፡
- ኢሳ (66፡ 24)፡ “ ወጥተዉም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸዉን ያያሉ ፤ ትላቸዉ አይሞትምና እሳታቸዉም አይጠፋምና “ ፤ መንፈሳቸዉ ያለሟቋረጥ በስቃይ ዉስጥ ይሆናል ምክንያቱም በእግዚአብሄር መገኘት በፍፁም አይሆኑም ፡፡
- ይሁዳ 7፡ “ እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ስጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸዉም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል ፡፡ “
- ይሁዳ 13፡ “ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው ! “ ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ ክፍል ዉስጥ ሆናችሁ ታውቃላችሁ ? ከእግዚአብሄር መገኘት ተለይቶ በሙሉ ጨለማ ዉስጥ ለዘላለም መኖርን አስባችሁታል ?
- 2ተሰ (1፡ 9)፡ “ ከጌታ ፊት ከኃይሉም ክብር ርቀዉ በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ “ ፤ እግዚአብሄርን ከሚመስለዉ ዘላለማዊ መለየትን መጠኑን መረዳት ያስፈልገናል ፤ አልዓዛር በዘላለማዊዉ ጥንካሬ በእግዚአብሄር ፊት ነበር ፡፡
- ማቴ (13፡ 50)፡ “ ወደ እቶን እሳትም ይጥሉአቸዋል ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል “ ፤ ሲዖል ጥሩ እንዳልሆነ የሚነግሩን በጣም ብዙ ስዕሎች አሉን ፡፡ አንድ በግ እንዲሄድ መፍቀድ አንችልም ምክንያቱም እግዚአብሄርን ካለወቁት መጨረሻቸዉ ይህ ቦታ ነው ፡፡ ስለ ሆነ ሰዉ ይህን እንዲቀምስ ራሱን/ዋን እንዲፈቅዱ ምን ያክል አታስቡም ?
ሲዖል የለም ብሎ የሚነጋገር ማንኛዉም ሀሰተኛ አስተማሪ ይሆናል ምክንያቱም ክርስቶስ ለሚያደርገዉ እና ላደረገዉ የሚሆን ምክንያት ስለ ማይኖር ፡፡
ሉቃስ (16፡ 25-26)፡ አብርሀም ሀብታሙን ሰዉዬ “ አንተ በህይወት ሳለህ መልካም እንደ ተቀበልህ አስብ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይፅናናል አንተም ትሰቃያለህ “ ብሎ ነገረው ፤ ተግባራቸዉ ተገለባበጠ ፤ “ ታላቅ ገደል ተቀመጠ “ ማለትም ማንም በየትኛዉም አቅጣጫ ማቋረጥ አይችልም ፤ ጊዜያዊ ማረፊያ የለም ፤ ሁለተኛ እድሎች የሉም ፡፡ መፀለይ ወይም የሆነን ሰዉ ወደ መንግስተ ሰማይ አሻግረን መላክ አንችልም ፡፡
ሉቃስ (16፡ 27-31)፡ ሀብታሙ ሰዉዬ ቤተሰቦቹን እንዲነግራቸዉ አንድ ሰዉ እንዲልክ አብርሃምን ለመነው ያ ከሆነ ወደዚህ ወደ ስቃይ ስፍራ አይመጡም ፤ ነገር ግን አብርሃም “ ሙሴና ነቢያት አሉላቸዉ ፤ እነርሱን ይስሙ አለው “ ፡፡ ቢያንስ 300 ጊዜ በብሉይ ኪዳን ሙሴና ነቢያት ወደ መሲሁ አመልክተዋል ፤ ኢየሱስ ያለው “ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ልፈፅም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም “ (ማቴ 5፡ 17) ፡፡ ሀብታሙ ሰዉዬ ያን በመቃወም ከሞቱት አንድ ሰዉ ወደ እነርሱ ቢሄድ ይመለሳሉ ፤ ነገር ግን አብርሃም መልሶ “ ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ ከሙታንም ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሳ አያምኑም አለው “ ፡፡
መዝጊያ
በመንግሰተ ሰማይ እና በሲዖል እንደ ማጠቃለያ ማርክ ቤይሌይ ስለ ሞት አምስት ንግግሮች አድርጓል፡
“ ከሞት በኋላ ወዲያዉኑ ንቃተ ህሊና አለ “ ፤ የሀብታሙ ሰዉዬ ህይወት ቀጥሏል ፍፃሜዉ የሆነበትን ስፍራ አልወደደውም ፡፡
“ ከሞት ቦኃላ ማረፊያዎች የማይቀየሩ ናቸው “ ፤ ማረፊያ ቦታ ወይም ሁለተኛ እድል የለም ፡፡
“ ከሞት በኋላ ማንም ድነትን ሊያገኝ ወይም ሊያጣ አይችልም ፡፡ “
“ ዘላለማዊ ማረፊያን ስቃይን ወይም ደግሞ በረከትን የሚወስኑት ፍርዶች አሁን ናቸዉ “ ፤ አንድ ሰዉ በስቃይ ዉስጥ የሚሆነዉ የእግዚአብሄር ስሕተት አይደለም ምክንያቱም ወደ ግብዣዉ መምጣት እንደምንችል በግልፅ አሳይቶናል ፡፡ በክርስቶስ ፍቅር በኩል መዉጣትን ሰጥቶናል ፡፡
“ ለእግዚአብሄር ቃል እንደ ተቀያሪ የሚሆን ምልክት በፍፁም አታዩም “ ፤ እግዚአብሄር እዉነት እንደሆነ ቃሉ ያረጋግጣል ነገር ግን ሰዎች ወደ እግዚአብሄር ቃል ከመመለስ ይልቅ ታዓምራቶች ይኖሯቸዋል ፡፡
መንግስተ ሰማይ አለ ሲዖል አለ አሁን እዚህ ምድር ላይ እንደ ለመድነዉ አይደለም ፤ ከሚመጣዉ ጋር ሲወዳደር ይም ምንም አይደለም ፡፡ ሌዊስ .ሲ.ኤስ ከመቃብር ድንጋይ በተፃፈው ተምሯል፡ “ እዚህ የተኙት ሁሉም የሰሩት በእግዚአብሄር የማያምኑት የትም አይሄዱም “ መልሶም “ ያ የተሸለ እንደ ነበር እንደሚመኝ እወራረዳለሁ “ ፤ ስለዚህ ምንድነዉ ትልቁ ስዕል(መልክ) ? በጣም ከመርፈዱ በፊት የጠፉትን በጎች መፈለግ ፡፡ በየቀኑ ዘላለማዊ አስተሳሰብ(አመለካከት) ሊኖረን ይገባል ፤ ቆላ (3፡ 1-4) የሚለው ኑሮአችንን ከሁለቱ በአንዱ አለም መኖር እንደ ምንችል ነው - በምድራዊ ወይም በዘላለማዊ ፡፡ አይምሮአችን፣ አሳባችን፣ ድርጊታችን እና ቃላታችን ሁሉም ዘላለማዊ ላይ የተመሰረቱ ናቸው ፤ ይህን አስተሳሰብ ለጠፉት ብዙ በጎች፣ እንደ ብዙዎች ሀብታሞች እንደ ቻልን እናስተዋዉቃቸው ፡፡
Mark Bailey and Tom Constable, Nelson’s New Testament Survey (Nashville: Thomas Nelson, 1999), n.p.
C. S. Lewis, Christian Reflections, edited by Walter Hooper (Grand Rapids, Wm. B. Eerdmans Pub. Co., 1967), p. xii.
ጥያቄዎች
-
የባላደራነት ትርጉሙ ምንድን ነው ? ንብረታችንን እንዴት እናስተናግደዋለን ? (መዝ 24፡ 1; ምሳ 3፡ 9)
-
የጊዜ፣ የችሎታ ወይም የንብረት ባላደራነት መግለጫ ከተሰጣችሁ እንዴት ታደርጋላችሁ ? (ሉቃ 16፡ 2)
-
በሉቃ (16፡ 13) ኢየሱስ ለምን ሁለት ጌቶችን ማገልገል አትችልም አለ ? ከእግዚአብሄር በላይ ገንዘብን እያገለገላችሁ እንደሆነ እንዴት ታውቃላችሁ ?
-
በአብርሃም ልብ (ቅርብ ቦታ) አልዓዛር እንዴት አደረገ ሀብታሙ ያልሆነዉን ? ሞት የሁሉም መጨረሻ እንዳልሆነ እንዴት እናውቃለን ? (2ቆሮ 5፡ 6-8; ፊል 1፡ 21; ዕብ 9፡ 27)
-
ባለፀጋው ሰዉዬ አልዓዛርን በትሩ ሁኔታ አላየዉም እንደዉም ናቀዉ (ችላ አለው) ፤ ድሆችን ለማስተናገድ መፅሀፍ እንዴት ያስተምረናል ? (ምሳ 14፡ 21; 19፡ 17; 21፡ 13; 28፡ 27; ማቴ 25፡ 37-40)
-
በሉቃስ 16 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Luke 16:26
“Besides all this, a great chasm has been fixed between us and you, so that those who want to pass over from here to you cannot; neither can those from there cross over to us.”
ሉቃስ የባለጠጋውን ሰው እና የድሀውን ሰው ታሪክ አካፈለ፡፡ የቅንጦትን ህይወትን የኖረው እና በእየለቱ በደስታ ይመገብ የነበረው፥ ባለጠጋ ሰው ሲሞት፥ በሲኦል ይሰቃይ ነበር፡፡ በአንጻሩ፥ ህይወቱን በቁስል ተወርሶ ሲኖር የነበረው፥ ድሀ ሰው ሲሞት፥ መልአክት ወደ ሰማይ ወሰዱት፡፡ ባለጠጋው ሰው በሲኦል ሲሰቃይ ሳለ፥ ከሙቀቱ ያርፍ ዘንድ ምላሱን እንዲያበርድለት ጠየቀ፡፡ በተመሳሳይ መከራ ውስጥ እንዳያልፉ፥ ወደ አምስት ወንድሞቹ ሄዶ ስለሲኦል እንዲያስጠነቅቃቸው አብርሃምን ለመነው፡፡
መንግስተ ሰማይ እና ሰኦል እውን ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ምናልባት ሲኦል ያን ያህል መጥፎ አይደለም ብሎ ማሰብን ይወዳሉ፡፡ ግን አዎ፥ እንደተገጸው ሲኦል እጅግ አስፈሪ ቦታ ነው፡፡ ኢየሱስ በመንግስተ ሰማይ የዘላለም ህይወት እንዲኖራችሁ መጥቷል፡፡ የድነትን ሥጦታ ተቀብላችሁ ከተከተላችሁት፥ ለዘላለም በሲኦል መሰቃየት አያስፈልጋችሁም፡፡ ምርጫው የእናንተ ነው፡፡ ምድር ላይ ባሏችሁ ቀናት ውስጥ ኢየሱስን ታምኑታላችሁ? ወይስ የራሳችሁ አምላክ ራሳችሁ ትሆናላችሁ? ጌታ ፍቅሩን እንድትቀበሉ ይወዳል፡፡ ከእናንተ ጋር ለዘላለም ማሳለፍ ይፈልጋል፡፡ ኢየሱስን ማመን የመረጣችሁ እናንተ ደግሞ፥ ለሌሎች ከማካፈል አትቆጠቡ፡፡ ዘላለምን በሲኦል ከማሳለፍ እንዲተርፉ ትረዷቸው ይሆናል፡፡ ዛሬ፥ ሂዱ እና ኢየሱስን በማካፈል፥ የሰዎችን ህይወት አድኑ!
“ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ሊያልፉ የሚፈልጉ እንዳይችሉ፥ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጎአል አለ።”
—ሉቃስ 16:26
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ማቴዎስ 16:26 — “ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?”
- ቆላስይስ 3:2-4 — “በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም።”
- 1ኛ ዮሐንስ 5:11–12 — “እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 60
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።