The Gospels Luke

Jesus Seeks the Lost

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 15 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 169 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

አንደ ማስታወስ ለሉቃስ ወንጌል ሀረጉ የሰዉ ልጅ ነው ፡፡ ኢየሱስ ከሰዎች ጋር እንደ ሰዎ ልጅ መስተጋብር አደረገ ፤ በወደዳቸዎ ሰዎች ላይ ባደረገዉ ኢየሱስ በግልፁ ሁሉንም ነገር እንደሚያደርግ አሳዬ ፡፡ በሉቃስ 15 ኢየሱስ ከሁሉም ነጠላ ልብ ጋር ተገነኜ ፡፡

ትምህርት

ሉቃስ (15፡ 1)፡ ሁሉም ቀረጥ ሰብሳቢዎች እና ኃጢዓተኞች እርሱን ለመስማት ኢየሱስን ቀረቡት ፤ ሁላችንም ኃጢዓተኞች አይደለንም ? ሮሜ (3፡ 23) የሚለው “ ሁሉ ኃጢዓትን ሰርተዋልና የእግዚአብሄር ክብር ጎድሎአቸዋልና“ ፤ ሁላችንም አላማዉን ስተናል በእግዚአብሄርም ላይ ኃጢዓት ሰርተናል ፡፡

ሉቃስ (15፡ 2)፡ ፈሪሳዉያን እና ፃፎች ኢየሱስ ከኃጢዓተኞች ጋር ይቀርባል ምግብም እንኳን ይበላል በማለት አጉረመረሙ ፤ ቅር መሰኘታቸዉ ራሳቸዉን ኃጢዓተኞች እንደልሆኑ ማሰባቸዉን ያመለክታል ፤ በሀሳባቸው ፃድቅ እና ፍፁም ነበሩ ፡፡ ኃጢዓተኞች በነበሩበት ስፍራ ወደ ግብዣዉ የማይመጡ የህግ ሰዎች ነበሩ ፤ ከከሀዲ(ተገቢ) ሰዎች ጋር አይተባበሩም ፡፡ ኢየሱስ ግብዣዉ ላይ ከእነርሱ ጋር ስለበላ የኃጢዓተኞችን ተቀባይነት ስላመለከተ ተበሳጩ ፡፡ የማንጠነቀቅ ከሆነ እዚያ ሰፈር በፍጥነት በጥሩ እንወድቃለን ፡፡

ሉቃስ (15፡ 3-4)፡ ኢየሱስ ስለ በግ ምሳሌ ነገራቸው “ 100 በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋው 99 በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘዉ ድረስ ሊፈልገዉ የማይወድ ከእናንተ መነው ? ይሁን እንጂ ይህ የፈሪሳዊያን እና ፃፎች አመለካከት አልነበረም ፡፡ በሕዝ (34፡ 1-2) እግዚአብሄር ለሕዝቅኤል የነገረው “ የሰዉ ልጅ ሆይ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር ….. ራሳቸዉን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው ! እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸዉምን ? “ ኢየሱስ ፈሪሳዉያንን እና ፃፎችን ከጠፋዉ አንዱ ይልቅ በብዙ ስለራሳቸዉ እና ስለ 99 ያሰቡ በመሆናቸዉ ከሰሳቸው ፤ ሕዝ (34፡ 4-5) የሚቀጥለው “ የደከመዉን አላፀናችሁትም የታመመዉንም አላከማችሁትም የተሰበረዉንም አልጠገናችሁትም የባዘነዉንም አልመለሳችሁትም የጠፋዉንም አልፈለጋችሁትም” ፤ ኃያማኖታዊ መሪዎች በመሄድ የጠፋዉን ለመፈለግ ምንም አላደረጉም ነበር መንፈሳዊ የሰቡ በመሆን ሁሉንም ነገር ያደርጋሉ ፡፡ በሕዝ (34፡ 10) እግዚአብሄር ያለው “ እነሆ በእረኞች ላይ ነኝ ….ከዚያም ወዲያ እረኞች ራሳቸዉን አያሰማሩም ፤ በጎቼንም ከአፋቸው አድናለሁ መብልም አይሆኑላቸዉም “ ፤ እግዚአብሄር መንጋዉን ከኃያማኖተኞች አድናለሁ አለ ፡፡ በሕዝ (34፡ 11-12) እግዚአብሄር መንጋዉን በራስ እንደሚፈልጉ ተናገረ “ እነሆ እኔ ራሴ በጎቼን እሻለሁ እፈልግማለሁ ፤ እረኛ በተበተነበት በጎች መካከል ባለ ጊዜ መንጋውን እንደሚፈልግ እንዲሁ በጎቼን እፈልጋለሁ “ ፤ እግዚአብሄር የጠፉትን በጎች ከጠፉበት እንደሚያድናቸው ተናገረ ፡፡ ሰዎችን ወደ መቅደስ፣ ወደ ድንኳኑ ማደሪያ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጡ እንደምናቸኛዉ እናስባለን ፤ ነገር ግን ሰዎች ልክ እንደዚያ አይመልሱም ፡፡ የሚከታተለን ጌታ ያስፈልገናል ፤ በሕዝ (34፡ 23) እግዚአብሄር “ በላያቸዉም አንድ እረኛ አቆማለሁ እርሱም ባሪያዬ ዳዊት ነው “ አለ ፡፡

ኢየሱስ ሕዝቅኤል የተነበየዉን በግልፅ እያደረገ ነበር ፤ የጠፉትን እየተከታተለ ነበር ፤ ነገር ግን የአይሁድ ሀይማኖት መሪዎች እያጉረመረሙ ነበር ፡፡ በራሳቸዉ ፅድቅ ደልበዉ ተቀምጠዉ ነበር ፡፡

ሉቃስ (15፡ 4)፡ እረኛዉ 99 ትቶ ከጠፈዉ ከአንዱ ኃላ ይሄዳል ፤ በጴጥ (3፡ 9) የእግዚአብሄር ልብ ማንም እንዳይጠፋ እንደሆን እንማራለን ፤ እግዚአብሄር አንዷ በግ እንዲጠፋ መተዉ ፍቃዱ አይደለም ፡፡ ካልተጠነቀቅን አንድ ሰዉ ጥቅም የለዉም በምንል ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ጨዋታዉን ትጫወታለች ስለሆነም እነርሱን አለመከተልን እንመርጣለን ነገር ግን ያ በዮሐ (3፡ 16) ኢየሱስ ካለዉ ጋር ይጋጫል ፡፡ እግዚአብሄር ማንኛዉም ሰዉ እንዲጠፋ አይፈልግም ፤ እርሱን የማያዉቁት እንዲሞቱና ሲዖል እንዲገቡ አይፈልግም ፤ ይህም ሙስሊሞችን፣ ሂንዱዚሞችን እና ቡዲሂስቶችን ያካትታል ፡፡ የእግዚአብሄር ግድየሌሽ ፍቅር ወደኃላ አይዝም ፤ በ 1ጢሞ (2፡ 4) ጳዉሎስ እግዚአብሄር “ ሁሉ እንዲድኑና እዉነትን ወደ ማወቅ እንዲመጡ እንደሚፈልግ “አብሯርቷል ፡፡ የሆነ አካል ካልዳነ ከእርሱ ኃላ መሄድ ይጠበቅብናል ፤ ኢሳ (40፡ 11) የሚለው እግዚአብሄር “መንጋዉን እንደ ያሰማራል ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል “ ፤ የጠፉትን የምንፈልግበት ምክንያት ስለ ምንወዳቸዉ ነው ፤ እንወዳቸዋለን ምክንያቱም መጀመሪያ ስለ ወደደን ፡፡

ላይፍልድ ያመለከተው “ ለእረኛ ሁልጊዜ ማታ በጎቹን መቁጠር የተለመደ ነበር “ ለምን ? ምክንያቱም እያንዳንዷ በግ ስለምታሳስበው ፤ በዮሐ (10፡ 7) ኢየሱስ “ እዉነት እዉነት እላችኋለሁ እኔ የበጎች በር ነኝ “ አለ ፤ ኢየሱስ እንደ በር አገለገለ የጠፋዉን እንዲያገኝ ለማንኛዉም አይፈቅድም ፡፡ በዮሐ (10፡ 11) ኢየሱስ በመቀጠል “ መልካም እረኛ እኔ ነኝ ፡፡ መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል “ ፤ በሌላ ቃል አንድ ጊዜ የጠፋዉን በግ ካገኛችሁት በበረት ዉስጥ ለመጠበቅ የምትችሉትን ሁሉንም ነገር ታደርጋላችሁ ፡፡ በዮሐ (10፡ 16) ኢየሱስ “ ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ ፡፡ “ ሁሉም ትንንሽ በጎች የኢየሱስን ድምፅ ይሰማሉ ፤ አንዷ ብታመልጠው እረኛዉ የግሉን በሚችለው በፅናት ይከተላል ፤ በዘፍ (31፡ 38-39) ያዕቆብ ስለ አጣቸዉ የላባ በጎች ከራሱ እንስሳ መንጋ ከፍሏል ፡፡ እረኛ ከነበራችሁ ትከፍላላችሁ ፡፡ በዘጸ (22፡ 10-12) የአንድ ሰዉ እንስሳ በሌላ እረኛ ጥበቃ ስር እያለ ከተሰረቀ እረኛው ካሳ ያደርጋል ፤ በጉ ከተሰረቀ ተጠያቂ ነበር ፡፡

ኢየሱስ ከበጎቹ ለእያንዳንዳቸው ጫናቸው፣ ርህራሄ እና ፍቅር ይሰማዋል ፤ አንድ በግ ቢወጣ እና በዙሪያችን ቢንከራተት እንጠነቀለታለን ? መፅሀፍት ከእነርሱ ዉስጥ ለእያንዳንዳቸዉ መጠንቀቅ እንዳለብን ይናገራል ፤ ነገር ግን ፈሪሳዉያን በአንድ ላይ ይዘዉት ነበር በራሳቸዉ ፅድቅ ደልበዋል ከጠፉ በኃላ ስለ መፈለግ አይጠነቀቁም ፡፡ በአሞ (3፡ 12) እግዚአብሄር ያለው “ እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት እግርን ወይም የጆሮን ጫፍ እንደ ሚያድን እንዲሁ በሰማሪያ በአልጋ ማዕዘን በደማስቆ በምንጣፍ ላይ የተቀመጡት የእስራኤል ልጆች ይድናሉ ፡፡ “ እረኛዉ ሁኔታዉ አስቸጋሪ ቢሆንም ችግር የለዉም በጎቹን መልሶ ይናጠቃል ፤ እረኛ ያለማቋረጥ የጠፋዉን በግ እስኪያገኙ ድረስ ከኋላዉ ይከተላል ፤ ነገር ግን እንድንሄድበት ያልተፈቀደልን ቦታ አለን ፡፡

ሉቃስ (15፡ 5-6)፡ እረኛዉ የጠፋዉን በግ ባገኘዉ ጊዜ በትካሻዉ ላይ አስቀምጦ ይወስደዋል ትልቅ ግባዣ ያደርጋል ፤ ደስ ይለዋል ምክንያቱም የጠፋበትን በግ ስላገኘው ፡፡ በእግዚአብሄር በተገኘው በእያንዳንዱ ሰው መደሰት እና ማክበር ይጠበቅብናል ምክንያቱም ከሞት ወደ ህይወት ስለ ገባ ፡፡ በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን በዝግታ እየሞተች ነው ምክንያቱም ሰዎች እግዚአብሄርን ወደ ማወቅ ሲመጡ ግብዣ አናከብርም ፤ ስናገኛቸው አንከብርም እናም የጠፉትን አንፈልግም ፤ ሁሉንም መሰብሰብ እና መደሰት ያስፈልገናል ፤ ግብዣ የለንም ምክንያቱም ሰዎች የተገኙ ስላልሆነ ፡፡

ዋይርስቤ የተናገረው “ የጠፉት ኃጢዓተኞች ወደ አዳኛቸዉ በመጡ ጊዜ የተገለፀ አራት እጥፍ ደስታ አለ “ ፤ 1) የተገኘዉ ሰዉ ደስተኛ ይሆናል(ደስታ ይቀምሳል) ፤ 2) የተመለከቱት ሰዎች እንደ ገና ይደሰታሉ ምክንያቱም የጠፋዉን ሰዉ ስላገኙት ፤ 3) ሌሎች ወደ ደስታው ይገባሉ ( አንዱ የመገኘቱን ታሪክ መስማት ማነዉ የማይወደው ? ) ፤ 4) በሰማይም ደስታ ይሆናል(ይገኛል) ፡፡ ሁሉንም ደስታ በዚህ ሂደት ተመልከቱት ፡፡

ሉቃስ (15፡ 7)፡ “ እንዲሁ ንስሀ ከማያስፈልጋቸው ከ99 ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢዓተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል “ ፤ በዚህ አገባብ (ሀሳብ) ፈሪሳዉያን እና ፃፎች እያጉረመረሙ ነበር ፤ ንስሀ እንደሚያስፈልጋቸው አያስቡም ምክንያቱም ጠፍተዉ እንደ ነበር እንኳን ስላልተረዱ ፡፡ ከራሳቸዉ ማንነት ጋር እየታገሉ ነበር ሁልጊዜ የጠፉትን ለማግኘት፣ ከቦታ ዉጪ የሆኑትን ፣ መንጋዉ ዉስጥ መሆን ያለባቸዉን ነገር ግን በዙሪያ የሚንከራተቱትን፣ ከእግዚአብሄር አገልግሎት ዉጪ የሆኑትን እና ምንም ዋጋ እንደሌላቸዉ የሚያስቡትን ለማግኘት መንገዶችን እንወድዳለን ፡፡ እነርሱን መልሰን በማምጣት ከእግዚአብሄር ጋር በማስታረቅ ወደ በረቱ በመመለስ አላማቸዉን የምንሰጣቸዉ አካላት ነን ፡፡ እግዚአብሄር ለእናንተ የተለያየ ማንነት፣ አላማ እና እቅድ አለው ፤ እግዚአብሄር ስለ ጠፉት ይፈልጋል ፡፡ ኃይማኖተኞቹ ተሰናከሉ ምክንያቱም የጠፉት ልክ እንደኛ አይመስሉም ወይም አይሸቱም ፤ አዳም እና ሒዋን በጠፉ ጊዜ እግዚአብሄር አገኛቸው ፡፡ እግዚአብሄር ሁልግዜ ተፃራሪ ልጆቹን የሚንከባከብ አባት ነው ፡፡

መዝጊያ

ዮሐንስ ዌስልይ ያለው “ ቤተ ክርስቲያን የምትሰራዊ የላትም ነገር ግን ነፍሳትን ታድናለች ፤ ስለዚህ በዚህ ስራ ያሳለፋችሁ እና የምታሳልፉ ሁኑ ፡፡ “ በሁሉም መፅሀፍት ዉስጥ ኢየሱስ ከአንድ ኋላ እንድንሄድ ያዝዘናል ፤ መጀመሪያም ወደፊትም ፈተናችን እነርሱን መዉደድ ነው ፤ በወደዳችኋቸዉ ጊዜ ስለ ምታገኙአቸዉ ሰዎች አስቡ ፤ በዙሪያችሁ ያሉትን ሌሎቹን እንዴት ተፅዕኖ ማድረግ እንደሚችል አስቡ ፤ ከዚያም በሰማይ ደስታ(ግብዣ) አለ ፡፡

  1. Walter L. Liefeld, “Luke,” in The Expositor’s Bible Commentary: Matthew–Luke (Grand Rapids: Zondervan, 1984), p. 981; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Luke, p. 238; available at www.planobiblechapel.com.

  2. Wiersbe, p. 233.

  3. Wiersbe, p. 234.

ጥያቄዎች

  1. ሉቃ (15፡ 2) ኢየሱስ ኃጢዓተኞቹን ተቀበለ ከእነርሱም ጋር እንደ በላ ይናገራል ፤ ፈሪሳዉያን ይህን አላፀደቁትም ፡፡ በማያምኑ የሚተገሩ ችግሮች እና ምጭበርበሮች ምንድን ናቸው ?
  2. ስለ ኢየሱስ ተልዕኮ አላማ ሉቃ (15፡ 4) ለእናንተ ምን ይላችኋል ? (ሕዝ 34፡ 11-16)
  3. በሉቃ (15፡ 7) ኢየሱስ “ ፃድቅ ሰዉ ንስሀ እንደ ማያስፈልገው “ አመለከተ ፤ በአሁኑ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሄዱ የፃድቅን መልክ በመልበስ ንስሀ እንደማያስፈልጋቸዉ የሚሰማቸው እንዳሉ ታስባላችሁ?
  4. አባትዬው የወጣት ልጁን የውርስ ድርሻዉን ለምን ሰጠው ? (ሉቃ 15፡ 12) የተሰጣችሁን ማንኛዉንም ዉርስ እንዴት አባከናችሁት ?
  5. በሉቃ (15፡ 28) ለተመለሰዉ ልጅ አባትዬዉ ግብዣ ባደረገ ጊዜ ታላቅ ወንድሙ የተበሳጨ ሆነ ፤ ለምን እንደ ሆነ መረዳት ትችላላችሁ ? የተበሳጨ እንዲሆን ተጨማሪ ምክንያት አለው ?
  6. በሉቃ (15፡ 32) አባትዬው “ ይህ ወንድምህ ሞተ ነበር አሁን ግን ህያው ነው “ አለ ፤ ከሞተዉ ጋር ለምን እራሱን አወዳደረ ?
  7. በሉቃስ 15 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Luke 15:7

“I tell you, in the same way, there will be more joy in heaven over one sinner who repents than over 99 righteous people who don’t need repentance.”

ኢየሱስ መቶ በግ ስለነበረው እና አንዱ ስለጠፋበት ሰው ምሳሌ ነገራቸው፡፡ ይህ ሰው ዘጠና ዘጠኙን ትቶ አንዱን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው ወጣ፡፡ አንዱን በግ ካገኘው በኋላ፥ ወደ ወዳጆቹ እና ቤተሰቦቹ በመሄድ የጠፋውን አንዱን በግ ስላገኘ ከእርሱ ጋር አብረው ደስ እንዲላቸው ጠየቃቸው፡፡

በዚህ ታሪክ ውስጥ፥ ኢየሱስ ለእናንተ ያለውን ታላቅ ፍቅር ገልጿል፡፡ ኢየሱስ እያንዳንዱን ሰው በጥልቀት ስለሚወድ፥ ወደ እርሱ ያልመጣ እና ንሰሐ ያልገባ አንድ ሰውን እንኳን ለመፈለግ እንደሚሄድ ታስተውላላችሁን? ያ አንድ አያመልጠውም፥ አንዱን ይፈልጋል፡፡

እንደ ኢየሱስ እንድትወዱ ተጠርታችኋል፡፡ እንደ ኢየሱስ መውደድ ከመቻላችሁ በፊት ግን፥ ለእናንተ ያለውን ታላቅ ፍቅር ልትቀበሉት ያስፈልጋል፡፡ ራሳችሁን ሆናችሁ ይወዳችኋል የሚለውን እውነት በመያዝ፥ የእግዚያብሔር ልጅ መሆናችሁን በማመን ቀኑን ጀምሩ፡፡ ፍቅሩ ረጅም እና ሰፊ፥ ጥልቅ እና ከፍ ያለ ነው፡፡ ዛሬ፥ ለእናንተ ካለው ፍቅር የተነሣ ፥ ሌሎችን መውደድ እንድትችሉ እና በህይወታችሁ ያለውን አንዱን ነገር እንድትፈልጉ ፥ ለእናንተ ያለውን ትልቅ ፍቅር ተቀበሉ፡፡

“እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።”

— ሉቃስ 15:7

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 103:11 — “ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጠነከረ። ”
  • ኤፌሶን 3:17–18 — “ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ ”
  • 1ኛ ዮሐንስ 4:19 — “እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን። ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 59