Banquet Lessons and Cross Carrying
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ ሳምንት በሉቃስ 14 መጀመሪያ ላይ አሁኑ ወደ ትልቅ ግብዣ ዘለናል ፤ ሉቃ (14፡ 1-24) በፈሪሳዊዉ ቤት ላይ የተለመደ የትልቅ ግብዣ ሁኔታዎች ይይዛል ፡፡
ትምህርት
ሉቃስ (14፡ 1-6)፡ ሰንበት ላይ ኢየሱስ ከፈሪሳዊያን መሪዎች አንዱ ቤት ለመብላት ሄደ ፤ ሌሎቹ ፈሪሳዉያንን በጥንቃቄ ይመለከቱት ነበር ፡፡ ሰዉነቱ በፈሳሽ የተነፋዉን ምናልባትም በተለያዬ የሰዉነት ክፈሉ ላይ በዉሃ ክምችት ተፈጥሮ በነበረዉ በሽታ የዉሃ መቋጠር የነበረበትን አንድ ሰዉ አመጡለት ፤ በሽታዉ በጣም የሚያስጨንቅ፣ የሚያም እና በተለምዶ የማይድን ነበር ፡፡ ይህ ሰዉ የፈሪሳዊዉ መሪ ዘመድ እንደነበር አድል አለው ፤ ሰዉዬዊ እዚያ ስለተቀመጠ ፡፡ ግብዣዉ ላይ ያሉት ሰዎች በኢየሱስ እና በሰዉዬዉ መካከል ወደኃላ እና ወደ ፊት መመልከት ቀጠሉ፡፡
ኢየሱስ የህግ አዋቂዎቹን እና ፈሪሳዉያንን በሰንበት መፈወስ የተፈቀደ እንደሆን ጠየቃቸዉ ነገር ግን አልመለሱለትም ፤ ስለዚህ ኢየሱስ ሰዉዬዉን ፈዉሶ በራሱ መንገድ ላከው ፡፡ የማይመች፣ ግራ የሆነ እና የሚያስደንቅ ክስተት ነበር ፡፡ ኢየሱስ ፈሪሳዉያንን በሰንበት ልጃቸዉ ወይም በሬአቸዉ ጉድጓድ ዉስጥ ቢወድቅባቸዉ ከጉድጓዱ ዉስጥ ልጃችሁን ወይም በሬአችሁን አታወጡትም ? ብሎ ጠየቃቸው እንደገና መልስ አልነበራቸውም ፡፡ በክፍሉ የተሰራጨዉን የማይመች ዉጥረት ሊሰማችሁ አይችልም ?
ሉቃስ (14፡ 7-11)፡ በግብዣዉ ዙሪያ በሉቃስ ብዙ መስተጋብሮች ሆነዋል ፡፡ ኢየሱስ ይህን የሚያጃጅል የማይመች ክስተትን በመዉሰድ ሌላ ምሳሌ ነገራቸዉ በዚህ ጊዜ ምክር ሰጣቸው ፤ የመጨረሻዉን ዘመን ጥበቃ እንደ ማሳያነት በብሉይ ኪዳን እና በአድስ ኪዳን በሁለቱም ተጠቅሞ የነበረውን የሰርግ ግብዣ ተጠቀመ ፤ ወደ ግብዣዉ በገባችሁ ጊዜ በግብዣዉ ላይ ምርጡን መቀመጫ መዉሰድ እንደሌለባቸው ምክንያቱም ሌላ የተሸለ ቆይቶ ይመጣ ይሆናል እናም ከግብዣዉ ወደ ታች ትወርዳላችሁ ከዚያም የተዋረዳችሁ ትሆናላችሁ ብሎ ነገራቸው ፤ በዚያ ፈንታ ዝቅ ባለዉ ስፍራ ላይ መቀመጥ እና ወደ ተሻለ መቀመጫ የተጋበዙ ለመሆን መጠበቅ በጣም የተሸለ ነበር ፤ ዋናዉ መልዕክት እግዚአብሄር ትሁታንን ማስበለጥ እና ኩራተኞችን ማሳፈር ነበር - ለራሳቸዉ ክብር ለማግኘት የሚሞክሩ ትህትናን ይተዋሉ ቀጥሎም ይዋረዳሉ ፡፡ “ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል “ (ቁጥር 11) ፡፡
ሉቃስ (14፡ 12-14)፡ ከዚያም ኢየሱስ ወደ አዘጋጂዉ ተመለሰ- እርሱን ጋብዞት ወደ ነበረዉ አንድ ፈሪሳዊ መሪ ጋባዙን እንዴት ግብዣዉን እንደሚጥለዉ ነገረዉ ፤ ኢየሱስ አዘጋጁን ሁሉንም ሰዉ እንዲጋብዝ ከዚያም የተባረከ እንደሚሆን እና “ በጻድቃን ትንሳኤ እንደሚመለስለት “ (ቁጥር 13-14) ነገረው ፡፡ ኢየሱስ በአንድ ቤተሰብ ወይ ጓደኛ ግብዣ ላይ ምንም አልያዘም ነበር - እግብዣዉ ላይ ራሱ ሄደ (የሐ 2፡ 1-11) ፤ ኢየሱስ ስለ ተጨባጭ ምድራዊ ሽልማት መልካም የማድረግ አስተሳሰብ ይዞ ነበር ፡፡ በምላሹ ምንም ሊሰጡን ለማይችሉት መልካም ማድረግ አለብን የሽልማት ጥያቄዉን ለእግዚአብሄር ተዉት ፡፡
ሉቃስ (14፡ 15-21)፡ ግብዣዉ ላይ አንዱ ሌለኛዉ እንግዳ “ በእግዚአብሄር መንግስት እንጀራ የሚበላ ብፁዕ ነው አለው “ (ቁጥር 15) ፤ ኢየሱስ በሌላ ምሳሌ “ አዎ ሀሳቡን ታደንቃለህ ነገር ግን ለመተግበር አልተዘቻጀህም “ በማለት መለሰለት ፡፡ ኢየሱስ የተናገሩ ሁለተኛዉ ግብዣ የቀድሞዉ ልምድ የነበረዉን ነገር ለእንግዳዉ ተሰጠው ፤ ግብዣዎቹ ብዙ ጊዜ R.S.V.P ነበሩ የተጋበዙትም እንግዶች እየመጡ እንደ ነበር አረጋግጠዉ ነበር ፡፡ በማስታወቂያ ግብዣዉ እንደተዘጋጀ የመጨረሻዉ ጥሪ በደረሳቸዉ ጊዜ የተጠሩት እንግዶች ለምን መምጣት እንዳልቻሉ ምክንያት መስጠት ይጀምራሉ ፤ ያልመጡበት እነዚህ ምክንያቶች ለኢየሱስ አድማጮች በጣም የሚያሳምም ጠንካራ ሀሳብ ይሆናል ፡፡ በኢየሱስ አይን (እይታ) እስከሚያዉቁት ድረስ በታሪኩ የጨዋታ ለዛ ተዝናንተዉ ይሆናል ለእነርሱ የእግዚአብሄርን ግብዣ እንዴት እየተቀበሉት እንደ ነበር ይህ ነበር ፡፡
በመጀመሪያዉ ምክንያት እንግዳው ገዝቶት የነበረዉን ማሳ መመልከት እንደሚያስፈልገዉ ተናገረ ፤ እዉነቱ በፊት ማሳዉን ይመረምራል እንዲሁም ግዥዉን ሄዶ ለመፈፀም እንኳን በህግ ተገድዶ ይሆናል ፤ ነገር ግን ዘግይቶ ማስታወቁ ለአዘጋጁ ክብር እንደ ፅኑ ስድብ እንደ ሚያገለግል እንደ ደካማ ምክንያት የሚሰማዉ ይሆናል ፡፡ ሌለኛዉ ምክንያት እንግዳዉ ገዝቷቸዉ የነበረዉን አምስት ጥማድ በሬዎች መሞከር ያስፈልገኛል ማለቱ ነበር ፤ መጀመሪያ አምስት ጥማድ በሬዎች ማለት ሰዉዬዎ የበለፀገ የመሬት ባለቤት ነበር ፤ እንግዳዉ በአንዱ አገልጋዩ ከማሰራት ይልቅ ስራዉን በራሱ መስራቱ የማይታመን(የማያሳምን) ነው ፡፡ ሰዎስተኛዉ ምክንያት እንግዳዉ ማግባቱ ነበር ፤ ይኸኛው ህጋዊ ምክንያት ለመሆን የቀረበ ነው ፤ ዘዳ (20፡ 7; 24፡ 5) የሚለው አንድ ሰዉ በመጀመሪያው የትዳር አመቱ ወደ ጦርነት ከመሄድ ነፃ ይደረግ ነበር ነገር ግን ለመገኘት ቃል ገብቶበት በነበረዉ ድግስ አይዘልም (አያልፍም)፡፡ “ ይቅር እንድት ለኝ እጠይቅሀለሁ “ የሚለዉ ንግግር “ ይቅር እንዳልኩህ እኔም እነግርሀለሁ “ በማለቱ የተሸለ መረዳት ነው ፡፡ የመጀመሪያዉ ምክንያት ስለ ንብረት፣ ሁለተኛዉ ስለ ስራ መኖር እና ሰዎስተኛው ስለ የግል ወዳጅነት(ፍቅር) ነበር (የሰዎስቱ ሰዎች ነገር አሁንም ከእግዚአብሄር መንግስት በላይ አስቀድመዋል ) ፤ ኢየሱስ በመሰረቱ “ ምክንያቶቻቹሁ ይሸፍኗችኋል “ ብሏል ፡፡
ከዚያም የአዘጋጁ አገልጋይ መንገድ ላይ ወጥቶ ማግኘት የሚችለዉን ሁሉንም እንዲያመጣ ተላከ - ጎስቋሎችን፣ የተናቁትን እና ለማኞችን ማለት ነው ፤ ይህ ተሰምቶ አይታወቅም ነበር ነገር ግን ስዕሉ የኢየሱስ ምሳሌ በጣም ኃይለኝ እንደሆነ ነው ፡፡ የኢየሱስ መልዕክት ለጎዳና ሰዎቹ ለተዋረዱት እና ለማይታወቁት(ለተናቁት) ወደ የመንግስቱ ግብዣ ላልተጋበዙት የተገለጠ ነበር ፡፡
ዛሬ እንድትሰሙኝ የምፈልገዉ እነዚህ የግብዣ እዉነታዎች ናቸው፡
- እግዚአብሄር ግብዣዉን ለሁሉም አቅርቦ አገልጋዩን እንዲጋብዛቸዉ እን እንዲያመጣቸው ይልከዋል (ቁጥር 23) ፤ ሰዎች ወደ ግብዣዉ የመምጣት ወይም ከግብዣዉ የመዞር ምርጫ አላቸው ፤ ለጌታ የዘገዩት ምክንያቶቻችሁን ተመልክታችኋል ?
ከማንኛዉም ነገር በላይ እንድንወደው ይጠራናል ፡፡ ቁጥር 27 “ መጥላት “ የሚለዉን ቃል ይጠቀማል ነገር ግን እንደ “ ያነሰ ፍቅር “ ወይም “ የራስ የሆነን መተዉ “ በመጀመሪያ የታማኝነት ጊዜ ምርጡ መረዳት ይሆናል (ሉቃ 6፡ 27) ፡፡ ለኢየሱስ የሆነዉ ፍቅር መብለጥ አለበት ፡፡
የራሳችንን መስቀል መሸከም አንችልም ፡፡ አድማጮቹ እዉነቱን ተረድተዉታል ምክንያቱም ስቅለት የተለመደ ክስተት ስለ ነበር ፤ “ መስቀሉን መሸከም “ ማለት በግልፅ ለሰማእትነት ዝግጁ መሆን ማለት ነው፡፡ የሰሙት የመተግበር ደረጃዉን ተረዱት ፤ ኢየሱስ አጥብቁ እንዲይዙት እንዲረዳቸዉ ሁለት ታሪኮችን ነገራቸው (ቁጥር 28, 31) ፡፡
መጀመሪያ ገንዘቡን በመጨረሱ ምክንያት የግንባታ እቅዱን መጨረስ ያልቻለዉ ግንበኛ(ሰራተኛ) እንዴት ሞኝ ነው ? በዓ.ዓ 27 በደካማነት የተሰራዉ የትያትር ቤት 50,000 በሚገመቱ መጥፎ አጋጣሚ ምክንያቶች ፈርሶ ነበር ፤ አድማጮቹ ያስታዉሱታል ፡፡ ሁለተኛ በዉጊያ ጠንካራ ጠላቱን ከመግጠሙ በፊት የጦሩን ጥንካሬ የማያሰላ የቶር መሪ እንዴት ሞኝ ነው ? የኢየሱስ ሀሳብ የነበረው የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ለመሆን የሚያስወጣዉን ዋጋ ማወቅ አለበት የሚል ነበር ፤ የሄሮድ ጥላቻ በቅርቡ ከሮማዉያን የመሬት ባለቤቶች ጋር በነበረዉ ጦርነት ተሸንፎ ነበር በዚህም የኢየሱስ አድማጮች የአጉል ጦርነት ስዕልን ተረዱት ፡፡
ግብዣዉን ለመቀበል ዋጋ አለው በጣም ያስከፍላል (ቁጥር 33) ፤ በኑሮአችን በኢየሱስ በሚቀጥል ጥሪ ቁጥጥር ስር እንሆናለን እንጂ በነገሮች እና በሁኔታዎች አይደለም ፤ ይህ ሰዎቹን እና ቤተ ክርስቲያንን ለማሳደግ የእግዚአብሄር እቅድ ነው ዘላለማዊም አንደምታ አለው ፡፡
መዝጊያ
ይህ ትዕዛዝ እና ሂደት ሁለቱንም ነው ፤ ከመለወጥ ልምድ ባለፈ ለመሄድ እና የቤተ ክርስቲያንን ተልዕኮ ለመፈፀም ከክርስቶስ እና ሌሎች ጋር መጓዝ የራስ ትጋት(ዉሳኔ) ነው ፤ ማለትም በኑሮአችን ከመቀኘቱ ዉጪ ምንም ዋስትና እንደሌለ ኢየሱስ እየተናገረ ነበር ፡፡ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ለመሆን ምንድን ዋጋ ትከፍላላችሁ ?
በስቴቭ ካምፕ “ ዋጋዉን ማሰብ “ ከሚለዉ መዝሙር እነዚህ ቃሎች ላይ አስቡ፡
ከአባት ወይም ከእናት በላይ እርሱን መዉደድ
ከራሳችሁ ስጋ በላይ እርሱን መዉደድ
ያላችሁን ሁሉንም ለእርሱ ለሆነው ሁሉ ስጡት
እንደ ኢየሱስ ወንጌል ይሄ ነው ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1263.
ጥያቄዎች
-
ኢየሱስ በሰዎች በቅርበት ሲታይ እንዴት የተሰማዉ እንደሆነ ምን ታስባላችሁ (ሉቃ 14፡ 1) ? ሰዎች እንደ ክርስቲያን የምናደርገዉን እና የምንለዉን ለማየት ይህ እንደ ሚመስል ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡም ?
-
እንደ ኢየሱስ በንጉሱ ግብዣ ላይ ድግሱ ላይ ስንጋበዝ ሀሳባችን ምን መሆን አለበት ? ቁጥር 11 ማለት ምን ማለት ነው ? (ምሳ 29፡ 23; ያዕ 4፡ 6; 1ጴጥ 5፡ 5-6)
-
ሰዎች ታላቁ ግብዣ ላይ ስላለመምጣታችዉ ያቀረቡት ጥቂት ምክንያቶች ምንድን ናቸው ? አሁን ሰዎች ወደ ኢየሱስ ላለመምጣት የሚሰጡዓቸዉ ጥቂት ምክንያቶች ምንድን ናቸው ?
-
ኢየሱስ አንዳንድ ጊዜ ለህዝቡ ከባድ ነገሮች ይነግራቸዋል ፤ በሉቃ (14፡ 26) ለእነርሱ ምን እያለ ነበር ? (ማቴ 6፡ 33)
-
ኢየሱስን የመከተል ዋጋ መቁጠር ማለት ምን ማለት ነው ? የኢየሱስ ማመሳሰል ጨዉ ላይ ከዚህ ጋር እንዴት ይግባባል(ይጣጣማል) ? (ማቴ 5፡ 13; ሉቃ 14፡ 28-35)
-
በሉቃስ 14 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Luke 14:11
“For everyone who exalts himself will be humbled, and the one who humbles himself will be exalted.”
ኢየሱስ የሰርግ ግብዣ ላይ ስለታደሙ እንግዶች ምሳሌ ተናገረ፡፡ አንዳንድ እንግዶች ገብተው የከበሬታን ሥፍራዎችን መርጠው ነበር፡፡ ከዚያም ጠሪው፥ በሚያሳፍር መንግድ፥ ከዚያ ተነስተው ዝቅተኛ ቦታ ላይ እንዲቀመጡ ነገራቸው፡፡ ነገር ግን፥ በግብዣው ላይ ዝቅተኛውን ሥፍራ የመረጡ ሰዎች ወደ ላይ እንዲወጡ ተጠሩ፡፡
እንደ ክርስቶስ ተከታይ፥ በትህትና እንድትራመዱ እና ከራሳችሁ በፊት ስለሌሎች እንድታስቡ ተጠርታችኋል፡፡ ክፍት የመኪና ማቆሚያ ቢኖር እና ሌላ መኪና በዛው ሰአት ሊቆም ቢመጣ፥ ትህትና ያ ሰው ከእናንተ በፊት እንዲቀድም እና ቦታውን እንዲወስድ ይፈቅዳል፡፡ በጣም የምትወዱትን ኬክ ከጓደኞቻችሁ ጋር እየጠበቃችሁ፥ የምትወዱት የኬክ ጣዕም አንድ ብቻ ቢቀር፥ ትህትና እናንተ አዲስ ነገር ስትሞክሩ ጓደኛችሁ የቀረውን ኬክ እንዲወስድ ይፈቅዳል፡፡ ዛሬ፥ ስለራሳችሁ ከማሰባችሁ በፊት ስለሌሎች አስቡ፡፡ በዚህ አይነት መንገድ ስትኖሩ፥ በክርስቶስ ፍቅር ትራመዳላችሁ፡፡ በትህትና ስትራመዱ ጌታ ልባችሁን ያከብራል፡፡ ራስ ወዳድ ላልሆነው እና ትሁት ለሆነው አመለካከታችሁ እናንተን የሚባርክበትን መንገድ እንድታዩ አይኖቻችሁን ክፈቱ፡፡
“ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል።”
— ሉቃስ 14:11
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ምሳሌ 11:2 — “ወዳጁን የሚንቅ እርሱ አእምሮ የጐደለው ነው፤ አስተዋይ ግን ዝም ይላል። ”
- ፊልጵስዩስ 2:3-4 — “ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ። ”
- 1ኛ ጴጥሮስ 5:6 — “እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 58
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።