ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በምዕራፍ 13 በእግዚአብሄር መንግስት ዉስጥ ትብብር ላይ እንመለከታለን ፡፡
ትምህርት
ሉቃስ (13፡ 6-9)፡ በሁሉም የኢየሱስ ታሪኮች የመንግስቱ መርሆች ናቸው ፤ ይህም የተለዬ አይደለም ፡፡ የበለስ ዛፍ ወደ ሚያድገዉ ዛፍ ሁሉም ምግቦች በተቀመጡለት ጊዜ የማደጊያ ጊዜ ያለዉ የፍሬ ዛፍ ነው ፤ ከዚያም ፍሬዉ ይመጣል ፡፡ አንድ የፍሬ ዛፍሬ ከጥሩ ምልከታዉ ጎን ለጎን ጥቅም እንዲያመጣ የተቀመጠ(የተለየ) ነው ፡፡ ይህ ፅሁፍ ዛፉ በሰዎስተኛዉ አመት መጨረሻ ፍሬ ማፍራት እንደሚገባው ወይም የፍሬ ዛፍነት ተፈጥሮ እንደሌለው ያመለክታል (ቁጥር 7) ፡፡ የሰዎስት አመቱ አስፈላጊነት ምን ነበር ? የበለስ ዛፏ የአይሁድ ሰዎችን ስትወክል ምናልባት ሰዎስቱ አመት ምድር ላይ ከኢየሱስ አገልግሎታ ጋር ይዛመዳል ፡፡ ጠባቂዉ ለበለስ ዛፏ ሌላ አመት ፍቃድ ማድረግ ፈለገ አሁንም ግን የማታፈራ ከሆነች እንደ ከፉ ዛፍ ትታያለች (ቁጥር 8-9) ፡፡
የእግዚአብሄርን ልጅ እና የሰዉን ልጅ ማነፃፀር አላማው ምንድን ነው ? ኢየሱስ አምላክነቱን ትቶ ተረጋጋ፣ አምላክ መሆን መብቱ ነው አምላክ እንደሆነ ያውቃል በተጨማሪም እንደማይቀየርም ያዉቃል ፡፡ ኢየሱስ ራሱን ከሴት የተወለደ ለማድረግ፣ እንደ ልጅ ለማደግ እና የሰዉ ልጅ ለመሆን ወደ ምድር አካባቢ መጣ ፤ ይህ ኢየሱስ በአለም ከፈጠረው የተፈጥሮ ህግ ጋር ለመተባበር የመማሩን መረዳት ይሰጠናል ፡፡ ወደ ነበሩ ነገሮች ላይ የተናገረዉን ተመልከቱ መጀመሪያ በእግዚአብሄር ሀሳብ ዉስጥ የነበር ነው ፤ የበለስ ዛፏ ምንድን ትወክል እንደ ነበር ማን ያውቅ ነበር ? ምድር ላይ የሚጓዘዉ ኢየሱስ ፍጥረት ምን እንዲሆኑ እና እንደሚሰሩ እንደ ተቀመጡ(እንደ ተሸሙ) ያውቃል በዚህም ለአድማጮቹ መግለፅ ይችላል ፡፡
ማር (11፡ 12-24) ስለ ባዶዋ በለስ ዛፍ ሌላ ፅሁፍ ነው ፡፡ ከሞት የአልዓዛር መነሳት ኢየሱስ ከመታሰሩ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሆነ ፤ ሰዎች በቢታኒያ እና በኢየሩሳሌም መካከል እየተመላለሱ ነበር ምክንያቱም ከአልዓዛር ሞት እዉነት በተጨማሪ በቢታኒያ ነገሮች እየተከሰቱ ስለ ነበር ፤ ኢየሱስ በደረሰ ጊዜ በጣምብዙ ህዝብ ተገኝቶ የነበረዉ ለዛ ነው ፡፡ ኢየሱስ በደረሰ ጊዜ አልዓዛርን ከሞት አስነሳዉ ትንሳኤ እና ብርሀና እንደ ነበር አወጀ ፤ ከዚያም ሰዎች ኢየሱስ አድርጎት የነበረዉን ለማየት የፋሲካን ድግስ በመተው ከኢየሩሳሌም እየወጡ ወደ ቢታኒያ መምጣት ጀመሩ፡፡ ኢየሱስም ሁል ቀን በቢታኒያና በኢየሩሳሌም መካከል ይመጣና ይሄድ(ይመላለስ) ነበር ፡፡
ከቀናቶቹ አንድ ቀን ላይ ነበር የፍሬ ዛፏን አየ ተርቦም ነበር ፤ ፈጣሪዉ ኢየሱስ ምንድን እንደሚሆን የተፈጥሮን ስርዓት ያውቃል - በለሷዛፍ ላይ ፍሬ እንደሚኖር መጠበቅ እንደሚችል ያውቃል ፡፡ በመንግስቱ የተፈጥሮ ተፍጥሮአዊ ስርዓት(ቅደም ተከተል) በምድር ኃጢዓት አጥፍቶታል ፤ እግዚአብሄር ዘላለማዊ ነው፣ በሰዉ ያለ መንፈስ ዘላለማዊ ነው፣ ህይወት ምድር ላይ ጊዜያዊ ነው ፡፡ የህይወት ዛፍ በመንፈሳዊ መንግስት በወቅቱ ያለማቋረጥ ፍሬ እንዲያፈራ ተፈጥሯል ነገር ግን የምድር ዛፎች የህይወት እና የሞት ወቅት አላቸው ፤ ሀሉን ነገር የፈጠረዉ ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች እንዴት እንደ ፈጠራቸዉ ያውቃል ፡፡ በኢየሱስ መንፈስ የዛፊቱን የወደቀዉን ተፈጥሮ ባየው ጊዜ ረግሟታል ከስሯም ሞታለች ፤ ከምድር ተፈጥሮ ላይ ተቆርጣ እንደ ነበር ተናገረ ፡፡ ኢየሱስ በመፅሀፍት ዉስጥ ወዳለዉ ግጭት እየጠራን ነበር ፡፡
ሉቃስ (13፡ 18-19)፡ ፈጣሪዉ፣ የስርዓት አስቀማጪዉ ኢየሱስ ወደ ምን እንደሚሆኑ ምንድን መሆን እንደ ሚችሉ የተናገረዉን ያውቃል ፤ ዜጋ ከዚያም በመቀጠል አምባሳደር ስለ መሆን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ አስተምራለሁ ፡፡ በእዉነት ዜግነት ላይ ስመለከት “ የእግዚአብሄር መንግስት ምን ትመስላለች በምንስ አስመስላታለሁ ? (ቁጥር 18) በዚህ ጥያቄ ላይ እመለከታለሁ ፤ የሚያካትተው “ ምንድን እንደሆነ በዚያስ ምክንያት መረዳት እችላለሁ ?
ኢየሱስ ልክ እንደ ሰናፍጭ ዘር ፍረሬ እንደ ነበር ተናገረ ፤ በተፈጥሮዉ ዉስጥ ወደፊት ለሚሆነው ለመሆን ሁሉንም ነገር ያስፈልገዋል ፡፡ የሰናፍጭ ዘር መጠን በጣም ትንሽ ነው ወደ ብዙ መጠንም ያድጋል ፤ ነገር ግን የዘሩ መጠን ጉዳይ አይደለም ፡፡ ቀያይ እንጨቶች (በካሊፎርኒያ የሚገኙ ትልልቅ ዛፎች) ከፓይኮኖች ዘር ያድጋሉ ፤ ይህ በዘር ተፈጥሮ ዉስጥ ያለ ነው ፤ በፓይኮን ዉስጥ በሺዎች ዘር አለ ፤ አንድ ሚሊዮን ቀይ እንጨት ዘሮች ስምንት ፓዉንድ አካባቢ ይመዝናሉ ከ300 ጫማ ርዝማኔ በላይ ማደግ ይችላሉ ፡፡ ዉጤቱን በሚወስነዉ በላዉ ላይ ማስቀመጥ እንደ ቻለው እግዚአብሄር በዘር መጠን አይገደብም ፤ በዘሩ ዉስጥ ስርዓት እና ዱካ(የተቀመጠ ነገር) አለ ከአፈር ጋር እና በዙሪያዉ ካሉ ነገሮች ጋር በሚተባበር(በሚጣመር) ጊዜ ለሚሆነዉ ተፈጥሮዉን ይከተላል ፡፡ የሰማይ መንግስት ከፈጣሪዉ እንደ መጣ ተፈጥሮዉ የሚመስል ነው ፡፡
ኢየሱስ በረገማት በዛፊቱ የክርስቲያን ህይወት ምንድን ይመስላል ? የሚያስደንቅ ቅጠሎች ያሏት ዛፍ ነገር ግን ፍሬ የሌለው ፤ ፍሬያማነት በታወጀ በእግዚአብሄር ስርዓት ይመጣል ፤ ስለሆነም በአማኞች ዉስጥ ከማንኛዉም ነገር በይበልጥ አማኞቹ የሚያዉቁት ብቅ የሚል እና የሚሆን ነገር አለ ፡፡ አማኞች ምን ያክል ቢያንሱም ወይም ባይጠቅሙም ችግር የለዉም ምክንያቱም የእግዚአብሄር ዱካ(ምልክት) አማኞቹ ላይ አለ ፡፡
ሉቃስ (13፡ 20-21)፡ እንጀራ(ዳቦ) በመስራት ዉስጥ እርሾ በጣም ትንሹ አካል ነው ፤ በመቀልቀል ላይ እያለ ማንያዉንም ልዩነት ማየት አትችሉም ነገር ግን ተፈጥሮአዊ ዉጤቱን እንጀራዉ(ዳቦዉ) ሲነሳ የምትመለከቱት ይሆናል ፡፡ መረዳቱን የምናመጣዉ ከሆነ የሚታየዉን በኃይል ተፅዕኖ የሚያደርገዉ ያልታየ ተፈጥሮ አለው ፡፡ በተፈጥሮዉ አለም በተገናኜ ጊዜ መንግሰቱ ተፈጥሮአዊ መልስ አለው ፤ በእርሾዉ ዉስጥ ባለዉ ነገር እና በተቀመጠበት አካባቢ መካከል ስላለዉ ትብብር ነው ፡፡
በእግዚአብሄር እምነት አላችሁ ! ለእናንተ እና በእናንተ የተናገረዉን እንደሚያደርገዉ እመኑ ፤ ፍሬ እንድናፈራ ተሰርተናል ፤ የማሳደጊያ ሂደት ጊዜ አለ ነገር ግን ለፍሬአማነት እርግጠኛ አድርጎ የሚያስመስል የሚፈትን ጊዜ አለ ፡፡
ማቴ (7፡ 17-20)፡ “ እንዲሁ መልካም ፍሬ ያደርጋል ክፉም ዛፍ ክፉ ያደርጋል ፡፡ መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለዉም ፡፡ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል ፡፡ ስለዚህም ከፍሬያቸው ታዉቋቸዋላችሁ ፡፡ “
መዝጊያ
እግዚአብሄር ማን እንደሆነ በመከተሌ እና ምን እንድሆን እግዚአብሄር እንደሚፈልግ እንዴት አድርጌ ፍሬአማ መሆን እችላለሁ ? የቀይ ዛፍ ዘርን ትልቅ አድርጎ ማሳደግ እግዚአብሄር ከቻለ በእርግጠኝነት በእግዚአብሄር መንግስት ከእኛ ዉስጥ እያንዳንዱን ታላቅ ፍሬ ተሸካሚዎች መጠቀም ይችላል ፡፡ ዮሐ (15፡ 8) የሚለው “ ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከብራል ፡፡ “
ጥያቄዎች
-
ኢየሱስ ሰዎቹ በኃጢዓት እና በሞት መካካል ስላለዉ ግንኙነት በጠየቁት ጊዜ ለሰዎቹ ለማሳየት የሞከረበት ሀሳቡ ምን ነበር ?
-
ከንስሀችን በኋላ እግዚአብሄር ምንድን ይመለከታል (ሉቃ 13፡ 6-9) ? በእኛ ዉስጥ ሊመለከታቸዉ የሚችለዉ የሚቻሉት ጥቂት ፍሬዎች ምንድን ናቸው (ገላ 5፡ 22-23) ? ሌላ አንዳንድ የሚቻሉ ምንድና ናቸው ?
-
ፈሪሳዉያን እና የምኩራብ መሪዎቹ ኢየሱስ ሰንበት ላይ ሲፈዉስ በጣም የሚበሳጩት ለምን ነበር (ዘጸ20፡ 9-10; ዘዳ 5፡ 12-14; ሉቃ 13፡ 14) ? ኢየሱስ እንዴት መለሰ ? (ማር 2፡ 27; ሉቃ 6፡ 5)
-
በጠባቡ በር (መግቢያ) በሚገቡት እና በሰፊዉ መንገድ በሚገቡት ልዩነቱ ምንድን ነው (ማቴ 7፡ 13-14) ? በጠባቡ በር በኩል መግባት ለምንድን ነዉ የሚያስቸግረው ? ጠባቡ በር ማነው ? (ዮሐ 10፡ 7, 9)
-
በሉቃ (13፡ 34-35) የኢየሱስን ፍቅር፣ ርህራሄ እና ፍላጎት ለኢየሩሳሌም ለመጠበቅ እንዴት ታዩታላችሁ ? (ኢሳ 31፡ 5)
-
በሉቃስ 13 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Luke 13:13
“Then He laid His hands on her, and instantly she was restored and began to glorify God.”
ኢየሱስ ለሰዎች ርኅራሄ እና ህመምተኞችን የመፈወስ ኃይል ነበረው፡፡ የምኵራብ አለቆችን እጅግ በሚያበሳጭ መልኩ፥ ኢየሱስ በሳምንት ሰባት ቀናት ለህመምተኞች ርኅራሄን ያሳይ ነበር፡፡ በሰንበት ሲያስተምር ሳለ፥ በመንፈስ የታሰረች ሴትን ፈወሰ፡፡ በፈውሷ ምክንያት ጌታን ማክበር ቀጠለች፡፡ የምኵራብ አለቆች ኢየሱስ በሰንበት በመፈወሱ ተቆጡ፡፡ ነገር ግነ፥ ኢየሱስ ለጠፉት እና ለታመሙት ትልቅ ልብ ስለነበረው፥ በየትኛውም ቀን ይሁን- ይፈውሳቸው ነበር፡፡
ቀናችሁን ስታሳልፉ፥ አይናችሁን ክፈቱ እና በዙሪያችሁ ያሉትን ሰዎች ተመልከቱ፡፡ በሳምንቱ በእያንዳንዱ ቀናት ለሌሎች ርኅራሄን እንዲሰጣችሁ ጌታን ጠይቁት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለስሙ ክብርን እየሰጠ፥ ለእግዚያብሔር መንግስት በውስጣችሁ እንዲሰራ ፍቀዱለት፡፡ በጌታ እረፉ እና ብርታትን ከእርሱ አግኙ፡፡
“ያን ጊዜም ቀጥ አለች፥ እግዚአብሔርንም አመሰገነች።”
— ሉቃስ 13:13
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት30:2 — “አቤቱ አምላኬ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ ምሕረትም አደረግህልኝ። ”
- መዝሙረ ዳዊት 34:3-4 — “እግዚአብሔርን ከእኔ ጋር ታላቅ አድርጉት፥ በአንድነትም ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ። እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ። ”
- መዝሙረ ዳዊት 62:5-8 — “ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና። እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነውና፤ እርሱ መጠጊያዬ ነው አልታወክም። መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ የረድኤቴ አምላክ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው። የሕዝብ ማኅበር ሁላችሁ፥ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር ረዳታችን ነው። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 57
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።