The Gospels Luke

Keep Watch; Be Ready.

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of Man Luke 12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 166 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ሉቃስ የኢየሱስን ስዕል እንደ ሰዉ ልጅ ተጠቀመበት ፡፡ ዮሐ (1፡ 1) የሚለው “ በመጀመሪያው ቃል ነበር ቃልም በእግዚአብሄር ዘንድ ነበር ቃልም እግዚአብሄር ነበር ፤ ቀጥሎም ዮሐ (1፡ 14) የሚጨምረው “ ቃልም ስጋ ሆነ ጸጋንና እዉነትም ተመልቶ በእኛ አደረ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነውን አየን “ ፡፡ ኢየሱስ የሰዉ ስጋ ሆነ ስለዚህም ከእኛ ጋር መገናኘት ቻለ እንዲሁም ከእርሱ ጋር መገናኘት ቻልን ፡፡ በቁጥር 1-3 ኢየሱስ የፈሪሳዉያንን ኃይማኖታዊ ግብዝነት አስጠነቀቀ ፤ በቁጥር (4-7) ኢየሱስ የሚየደምጡትን ወደ ሲዖል ሰዎችን የመወርወር ስልጣን ያለዉን እግዚአብሄርን እንዲፈሩ ነገራቸው ፤ በቁጥር (8-12) ኢየሱስ አድማጮቹን የሰዉን ልጅ የምታከብሩት ከሆነ በእግዚአብሄር መለዓክት ፊት እንደሚያከብራቸዉ ነገራቸው ፤ ነገር ግን የሚክዱትን በመለዓክቱ ፊት የሚክዳቸዉ ይሆናል ፤ ቁጥር 13-21 የሞኙን ሀብታም ምሳሌን ይይዛል ቁጥር 22-24 ደግሞ ለጭንቀት መፍትሄን ይመለከታል ፡፡ ቁጥር 31 ለዚህ ፅሁፍ ቁልፍ ጥቅስ ነው ፡፡

ትምህርት

ሉቃስ (12፡ 35-40)፡ ዛሬ ለክርስቶስ መመለስ እንዴት የተዘጋጀን መሆን እንደምንችል በተለያዩ አረት መልክ ላይ እንመለከታለን ፡፡

ወገባችሁን ታጠቁ፡ በመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን የተለበሰዉ ልብስ ለለባሹ ትክክለኛ ስራ እንዲሰራ አይፈቅድም ስለዚህ የተሸለ እንቅስቃሴ እንዲፈቅድ በእግሮቹ አስገብቶ ወደ ላይ በመሳ መሀከሉ ላይ የሚታሰር ይሆናል ፤ ሂደቱ ብዙ እርምጃ እና ለመስራትም የተወሰነ ጊዜ ይፈጃል ስለዚህም ሰዉዬዉ በፍጥነት መመለስ አልቻለ ፡፡ በአሁን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሚመመጣዉ ዉጊያ እያሰበች ዘና ብላለች ነገር ግን በሚገባ አልተዘጋጀችም ፤ ኢየሱስ የተዘጋጀ እንደትሆን በሚገባ ገለፀ (ቁጥር 35, 40) ፡፡

የሚበራ ብርሀና ይኑራችሁ፡ መብራታችሁ እየበራ ዝግጁ መሆን ያስፈልገዋል ፤ ክብሪት ወይም የተዘጋጀ የኩራዝ ክር ለመፈለግ ጊዜ አይኖርም (ማቴ25፡ 1-13) ፡፡

ጌታቸዉን የሚጠብቁ አገልጋዮች፡ ጌታው ከሙሽራዉ ጋር በሚደርስ ጊዜ ላለመቆለፍ እና በሩን ለመክፈት የተዘጋጃችሁ ሁኑ ፤ ዋይርስቤ የፃፈው “ የአይሁዶች ሰርግ ማታ ላይ ይደረጋል እናም የሙሽራዉ አገልጋዮች ለጌታቸው ከሙሽራዉ ጋር ወደ ቤቱ ሲመጣ በር አጠገብ ላይ ይጠብቃሉ “ ፤ ኢየሱስ ሲመለስ ዝግጁ ሆነዉ የተገኙት ስለ እምነታቸዉ እና ስለ መታዘዝ አገልግሎታቸው የተባረኩ ይሆናሉ (ቁጥር 37; ሮሜ 14፡ 10; 2ቆሮ 5፡ 10) ፡፡ አገልጋዮቹ ጌታቸዉን ለማገልገል ዝግጁ ነበሩ ስለዚህ ሊያገለግላቸዉ ይመጣል ፡፡ ዮሐ (13፡ 3-8) በደቀ መዛሙርቱ የኢየሱስን የእንክብካቤ አገልግሎት ምሳሌ ያጋራል ፤ ይህ ኢየሱስ እንዴት ሊያገለግለን እንደመጣ የሚያሳይ (ዉልብታ) ነው ፡፡ ታማኝነት ያሻልማል ፡፡

በምሽት ላለዉ ሌባ ዝግጁ ሁኑ፡ዋይርስቤ “ በሮማዉያን ስርዕት ሁለተኛዉ እና ሰዎስተኛዉ ስዓት ከምሽት 9ሰዓት እስከ ቀን 3ሰዓት ይሆናል ፤ በአይሁድ ዘዴ ከምስት 10ሰዓት እስከ ቀን 6ሰዓት ይሆናል “ በማለት ይገልፃል ፡፡ እዉነታው ኢየሱስ በማንኛዉም ጊዜ ሊመጣ ይችላል ማለት ነው ፤ የቤት ባለቤቱ ሌባዉ መቼ እንደ ሚመጣ አዉቆ ቢሆን ሌባዉ እንዲገባ አይፈቅድለትም (ቁጥር 39) ፡፡

1ተሰ (5፡ 2) የሚገልፀው፡ “ የጌታ ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁን አጥብቃችሁ አዉቃችኋልና ፡፡ “

2ጴጥ (3፡ 10)፡ “ የጌታዉ ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል ፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኩሳት ይቀልጣል ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል ፡፡”

1ዮሐ (2፡ 28)፡ “ አሁንም ልጆች ሆይ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ ፡፡ “

ሮሜ (13፡ 11)፡ “ ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአል ፡፡ “

በማቴ (26፡ 40) ኢየሱስ ሲፀልይ በመጠበቅ ፋንታ የተከተሉት ደቀ መዛሙርት ተኝተዉ ነበር ፤ ካመንነዉ በላይ በቅርብ ኢየሱስ ተመልሶ የመምጣቱን እዉነት ቤተ ክርስቲያን የምትቀበልበት ጊዜ አለ ፤ የተኛን ደቀ መዛሙርቶች መሆን አንችልም ፡፡

መዝጊያ

በቁጥር 41 ጴጥሮስ፡ “ ጌታ ሆይ ይህን ምሳሌ ለእኛ ወይስ ደግሞ ለሁሉ ትናገራለህን ?” ብሎ ጠየቀ ኢየሱስም ስለ መታመን ደረጃ በመናገር መለሰ ፤ ታማኝ ከሆናችሁ ትሸለማላችሁ ፤ ነገር ግን ኢየሱስ ተመልሶ እንደሚመጣ እያወቃችሁ እንኳን በግልፅ የማትታዘዙ ከሆናች ወደ ማያምኑት ቦታ ትመደባላችሁ ፡፡ የሚመስለኝ ከማያምኑት ጋር ከተመደባችሁ(ከተቀመጣችሁ) የማታምኑ ናችሁ ማለት ነው ፡፡ የሽልማት ደረጃዎች አሉ ኢየሱስ በሚመለስ ጊዜ የሚገኘዉን ሙሉ ሽልማት እንድታገኙ እፈልጋለሁ ፤ “ ብዙም ከተሰጠው ሰዉ ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል “ (ቁጥር 48) ፡፡

ስለዚህ በዚህ ሁሉ መረጃ ምንድን ታደርጋላችሁ ? Bible.org ሰዎስት ምክሮችን ይሰጣል፡ 1) እርሱ የእናንተ ጌታ ይሆናል ፤ 2) የእርሱ አገልጋዮች ትሆናላችሁ ፤ 3) በእርሱ መመለስ ተስፋ መኖር ይጠበቅባችኋል ፡፡ ሉቃ (12፡ 40) የሚለው “ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ የሰዉ ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣል “ ፤ የተዘጋጃችሁ ሁኑ ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 222.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1279.

ጥያቄዎች

  1. በሉቃ (12፡ 16-21) ኢየሱስ ስለ ባለጠጋው ሰዉዬ አንድ ምሳሌ ተናገረ ፤ በቁጥር 21 በእግዚአብሄር ባለጠጋ መሆን ማለት ምን ማለት ነው ?
  2. ሉቃ (12፡ 31) መንግስቱን መፈለግ ይላል ፤ ከመፈለግ እና ከማግኘት አንፃር ይህ ከሉቃ (11፡ 9-10) ይገናኛል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  3. ምዕራፍ 12 ስለ ዋጋ (ቁጥር 7 እና 24), ስለ ባለጠግነት (ቁጥር 15 እና 33) እና ስለ ሀብት (ቁጥር 21, 33 እና 34) ይናገራል ፤ ቁጥር 34 እንዴት ትገልፁታላችሁ ? ሀብታችን የት እንዳለ ምንድን ይገልፃል ? (ሉቃ 6፡ 45)
  4. “ ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁ የበራይሁን “ ምን ማለት ነው (ሉቃ 12፡ 35) ?
  5. በቁጥር 37 የሚያገለግሉት እነ ማን ነበሩ ጋደም ያሉትስ እነ ማን ነበሩ (ማቴ 20፡ 28; ሉቃ 22፡ 27) ? በመፅኀፍ የት ላይ ይህ ሲሆን ይታያል ? ዮሐ 13፡ 3-17)
  6. በሉቃስ 12 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Luke 12:40

“You also be ready, because the Son of Man is coming at an hour that you do not expect.”

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ እንዲዘጋጁ ደጋግሞ ነግሯቸዋል፡፡ መብራታችሁን አብሩ፡፡ ንቁ ምክኒያቱም የሰው ልጅ ይመጣል፡፡ እናንተስ? ለክርስቶስ ምፅአት ተዘጋጅታችሁ እየኖራችሁ ነው?

ዛሬ ማታ እንግዳ እንደሚመጣ ካወቃችሁ፥ ትዘጋጃላችሁ፥ ምግብ ታዘጋጃላችሁ፡፡ ነገ መኪናችሁ እንደሚሰበር ካወቃችሁ፥ ወድ እቃዎችን ታወጣላችሁ ወይም መስታዎቶቹ እንዳይጎዱ ልትከፍቷቸው እንኳን ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ ነገ እንደሚመለስ ብታውቁ፥ ዛሬ ምን ታደርጋላችሁ? ሕይወታችሁን ለክርስቶስ ካላስገዛችሁ እና እንደ ጌታችሁ እና አዳኛችሁ ካላመናችሁት፥ ከዚህ ቦታ መጀመር የተሻለ ነው፡፡ አማኞች ከሆናችሁ ደግሞ፥ ለምጽአቱ በመዘጋጀት መኖር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለልባችሁ እንዲናገር መንፈስ ቅዱስን ጠይቁት፡፡ እንድታደርጉ በሚጠይቃችሁ ነገር በእምነት እና በመታዘዝ ተራመዱ፡፡ መንፈስ ቅዱስ የምትራመዱበትን ቃላት እና ኃይልን ይሰጣችኋል፡፡ ምጽአቱን እንድትጠብቁ ኃይልን እንዲያስታጥቃችሁ ጌታን ታመኑት፡፡

“እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።”

—ሉቃስ 12:40

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ማቴዎስ 5:14–15 — “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።
  • ሮሜ 13:12 — “ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ።”
  • 1ኛ ዮሐንስ 2:5 — “ቃሉን ግን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር በእውነት ተፈጽሞአል። በእርሱ እንዳለን በዚህ እናውቃለን ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 56