The Gospels John

The Word Became Flesh

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 179 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የዮሐንስ ጥናታችንን ስንጀምር ልታዉቁት የሚገባዉ አንድ ነገር ማስረጃዎቹ 98 ፐርሰንትለዮሐንስ የተለየ ነው ፡፡ በጥናታችን የምናየዉ ሁሉም አድስ እና ትኩስ(ንፁህ) ነው ፡፡ በማቴዎስ፣ በማርቆስ እና በሉቃስ ያያችሁትን ማስረጃዎች በጣም በጥቂቱ በዮሐንስ ታያላችሁ ፤ ዋይርስቤ የሚለው “ የመጀመሪያዎቹ ሰዎስት ወንጌል በዋናነት በክርስቶስ ህይወት ክስተቶች ላይ ሲገልፁ ዮሐንስ የእነዚህን ክስተቶች ትርጉም አብራርቷል “ ፡፡ የዚህ ወንጌል ፀሀፊ ዮሐንስ ራሱን “ ኢየሱስ እንደ ሚወደዉ ደቀ መዝሙር “ ብሎ ገልፆታል ፡፡ የዮሐንስ ታላቅ ወንድም ያዕቆብ ነበር ፤ በአንድ ላይ እንደ ነጎድጓድ ልጆች ይታወቃሉ (ማር 3፡ 17) እና እንደ ዘብድዮስ ልጆች በመባል ይታወቃሉ ፡፡ በተጨማሪም ዮሐንስ ሐዋሪያ ነበር ፡፡ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ በማቴዎስ እንደ ኢየሱስ የቅርብ ጓደኞች ተገልፀዋል ፡፡

ዮሐንስ የጴጥሮስ የቅርብ ተባባሪ እና ብዙ ጊዜ እንደ አይን ምስክር የተጠቀሰ ነው ፤ በተጨማሪም 1ዮሐንስ፣ 2ዮሐንስ፣ 3ዮሐንስ እና ራዕይን ፅፏል (ራዕ 1፡ 1-4) ፡፡ ዮሐንስ የመፅሀፍ ቅዱስ አምስት መፅሀፍትን ፅፏል ፤ አንዱ የመጀመሪያዉ ገላጭ ሰዉ ነው ፤ ወንጌሉ ከ80 እስከ 90 ከክርስቶስ ሞት በኋላ ተፃፈ በጥቂት “ ከአምሳ አመታት በኋላ ዮሐንስ የኢየሱስን የምድር አገልግሎት መሰከረ “ ፡፡ በተለዩ ብዙ መጠን መግለጫዎች ምክንያት ዮሐንስ ለሌሎቹ ወንጌላት አጋዥ(የሚያብራራ) ሰጥቷል ፤ ከአራቱ ወንጌላት ዮሐንስ በጣም ስነ መለኮታዊ ሲሆን ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ ያብራራል ፡፡

የመፅሀፉ አላማ በዮሐ (20፡ 30-31)ላይ ይገኛል፡ “ ኢየሱስም በዚህ መፅሀፍ ያልተፃፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ ፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደ ሆኑ ታምኑ ዘንድ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል ፡፡ “ በዮሐንስ ወንጌል ዉስጥ ምልክት እና ድንቅ ቀርበዋል ፤ ማክአርቱር ለመፅሀፉ ሁለት ጭብጦች አመልክቷል፡ ወንጌላዊነት (በመፅሀፉ“ ማመን “ 100 ጊዜ የተጠቀሰ ነው) እንዲሁም ይቅርታ ጠያቂ ( የኢየሱስ ማንነት የማይታየው(የእዉኑ) እግዚአብሄር እንደሆነ ለአንባቢዎቹ ለማሳየት ) ፡፡ ማክአርቱር ከታች በሚጠቀምበት ዮሐንስ (1፡ 1-18) ወደ ስድስት ዋና ዋና ሀሳብ ያስቀምጠዋል (ይዘረዝረዋል) ፡፡

ትምህርት

ዮሐንስ (1፡ 1-3)፡ ዘላለማዊዉ ክርስቶስ ፤ “ በመጀመሪያ “ (ቁጥር 1) ወደ ኋላ ዘፍጥረት (1፡ 1) ይገናኛል ፡፡ ቃልም በመጀመሪያ ነበር በእግዚአብሄርም ዘንድ ነበር እግዚአብሄርም ነበር ፡፡ “ የግሪክ ግንባታ ቃሉ የአምላክነት ሁሉም መሰረት ወይም ባህሪይ ነበሩት ያ ማለት መሲሁ ኢየሱስ በሙሉ እግዚአብሄር ነበር “ ፡፡ በዮሐንስ የዘር ሀረግ የለም ምክንያቱም አንዱ አያስፈልገዉም ፤ ኢየሱስ በመጀመሪያ ነበር ሁሉም ነገር በእርሱ በኩል ተፈጥረዋል ፡፡ በዘላላማዊነት ኢየሱስ ከመጀመሪያ በፊት ጀምሮ አለ እያልን ነው ማለት ነው ፡፡

ቆላ (2፡ 9)፡ “ በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰዉነት ተገልጦ ይኖራልና ፡፡ “

ዮሐ (17፡ 5)፡ “ አሁንም አባት ሆይ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ ፡፡ “

ኤፌ (3፡ 9)፡ “ ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሄር ከዘላለም የተሰወረው የምስጢር ስርዓት ምን እንደሆነ ለሁሉ እገልጥ ዘንድ ይህ ፀጋ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ለማንስ ለኔ ተሰጠ ፡፡ “

ዕብ (1፡ 2)፡ “ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን ፡፡ “

ዮሐንስ (1፡ 4-5)፡ የክርስቶስ ስጋ መልበስ(እንደ ሰዉ መሆን) ፤ ዮሐ (5፡ 26)፡ “ አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታል “ ፤ ስለዚህ በእግዚአብሄር ህይወት አለ ፡፡ በእግዚአብሄር የምትሰሙት ቋንቋ በክርስቶስ ከምትሰሙት ጋር ተመሳሳይ ቋንቋ ነው ፡፡ ዮሐ (10፡ 28) የሚለው “ እኔም የዘላለም ህይወትን እሰጣቸዋለሁ ለዘላለምም አይጠፉም ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም “ ፡፡ ቁጥር 4-5 የብርሃንን እና የጨለማን ንፅፅር ይሰጣል ፤ ብርሃን መፅሀፍ ቅዱሳዊ እዉነት ነው ጨለማ ደግሞ ሀሰት ነው ፤ ብርሃን ቅዱስነት እና ንፁህነት ነው ጨለማ ደግሞ ኃጢዓት እና የተሳሳተ ስራ ነው ፡ ይህ ንፅፅር “ የጨለማ ኃይል በሰዉ ልጅ በመስቀል ሞት ተሸነፈ “ ወደ ሚለዉ እዉነት ይመራል ፡፡

ዮሐንስ (1፡ 6-8)፡ የክርስቶስ ቀደምትነት ፤ መጥምቁ ዮሐንስ ወደ አለም መጥቶ ስለ ነበረው ብርሀን ለመመስከር ከ400 አመት ዝምታ በኋላ መጣ ፤ ይህ የኢየሱስ መምጣት የወንጌልነት ተፈጥሮዉን ያመለክታል፡ “ ለሁሉም ሰዉ ብርሃን የሚሰጥ “ (ቁጥር 9) ፤ ዮሐንስ ለሚመጣው ብርሃን መንገድ እያዘጋጀ ነበር ፡፡ ቁጥር 8 ዮሐንስ ብርሀን እንዳልነበር ነገር ግን ስለ ብርሃኑ ሊመሰክር መምጣቱን አመልክቷል ፡፡

ዮሐንስ (1፡ 9-11)፡ ዕዉቅና ያልተሰጠዉ ክርስቶስ ፤ ዮሐንስ ኢየሱስ ወደ “ አለም “ መጥቶ እንደ ነበር ፅፏል ፡፡ ማክአርቱር “ ዮሐንስ የትርጉሙን ብዙ ጥላዎች ይሰጣል ፡ 1) በአካል የተፈጠረው ዩንቨርስ; 2) በጠቅላላ ሰበዓዊነት እና 3) የክፈዉ በሰይጣን የተዋጠው የማይታየው መንፈሳዊዉ ስርዓትን እና ከእግዚአብሄር በተቃራኒ የሚያቀርባቸው ሁሉም ነገሮች ቃሉን እና ሰዎቹ “ ይገልፃል ፡፡ ኢየሱስ በፈጠረው አለም በእነዚህ አካባቢዎች መጥቶ ነበር - እርሱ ዘላለማዊ ክርስቶስ ነው ፤ ነገር ግን የፈጠረው አለም አላወቀዉም ፡፡ ዮሐንስ ኢየሱስ ወደ እራሱ ወደ አይሁዶች እንደ መጣ ነገር ግን እንዳልተቀበሉት ተናግሯል (ቁትር 11) ፡፡ ኢየሱስ በተደጋጋሚ ከአይሁድ ሰዎች መገፋት ነበር የተቀበለው ፡፡

ዮሐ (10፡ 25)፡ “ ኢየሱስም መለሰላቸው እንዲህ ሲል ነገርኋችሁ አታምኑምም እኔ በአባቴ ስም የማድርገው ስራ ይህ ስለ እኔ ይመሰክራል ፡፡ “

ዮሐንስ (1፡ 12-13)፡ ምንም የማይሳነዉ ክርስቶስ ፤ ዮሐንስ የአይሁድ ሰዎች ክርስቶስን ሳይቀበሉት ቢቀርም ያመኑ ቅሪቶች ነበሩ ፡፡

ዮሐንስ (1፡ 14-18)፡ የሚያኮራው(የከበረ) ክርስቶስ ፤ በትክክል ቃሉ ክርስቶስ እንደ ነበር እንዴት እናውቃለን ? ምክንያቱም ቃሉ ስጋ ሆኗል (ቁጥር 14) ፡፡ ጳዉሎስ ለጢሞቲዋስ ያን እዉነቱን አረጋግጦለታል፡ “ እግዚአብሄርንም የመምሰል ምስጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው ፤ በስጋ የተገለጠ፣ በመንፈስ የፀደቀ፣ ለመላእክት የታየ፣ በአሕዛብ የተሰበከ፣ በዓለም የታመነ በክብር ያረገ “ (1ጢሞ 3፡ 16) ፡፡ “ ቃልም ስጋ ሆነ በእኛ አደረ “ የሚለው ፅሁፍ በግሪክ “ በድንኳኑ ማደሪያ ስፍራ “ ማለት ነው ፤ ይህ ማለት ኢየሱስ በድንኳኑ ማደሪያ ኖሯል ፡፡ በብሉይ ኪዳን “ የእግዚአብሄር ሁሉን ቻይነት መገኘት ጠቅላላዉን መዋቅር ሞላው ፤ ቃሉ ስጋ በሆነ ጊዜ የአምላክነቱ ክብር መገኘት በእርሱ ዉስጥ የነበር ነበር “ ፡፡ ይህን የሰሙት አይሁዶች ወዲያዉኑ ዘጸ (25፡ 8) ያስባሉ፣ እግዚአብሄር በድንኳን ከእስራኤል ጋር ሲገናኝ ዘጸ (33፡ 11)፣ እግዚአብሄር ፊት ለፊት ሙሴን በተናገረው ጊዜ እና በዘጸ (40፡ 34) የእግዚአብሄር መገኘት የድንኳኑን ማደሪያ በሞላ ጊዜ ፡፡ በትንቢታዊነት በዘጸዓት እነዚህ ጥቅሶች ወደ ዮሐንስ (1፡ 14) ያመለክታሉ ፡፡

መዝጊያ

በመጨረሻም የእግዚአብሄር ክብር ከእስራኤል አለመታዘዝ ተለየ (ሕዝ 9፡ 3; 10፡ 4, 18; 11፡ 22-23) ፤ ከአመታት በኋላ ቃሉ ስጋም ሆነ “ ክብሩንም አየን “ (ቁጥር 1፡ 14) - ከአባቱ የመጣው ክብር እዉነት እና ፀጋ የሞላው ነው ፡፡ ሁሉም ኢየሱስ መልስ እንደ ሆነ አመልክተዋል ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: John (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 284.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1339.

  3. MacArthur, p. 1339.

  4. MacArthur, pp. 1343–1346.

  5. MacArthur, p. 1343.

  6. MacArthur, p. 1344.

  7. MacArthur, p. 1345.

  8. MacArthur, p, 1346.h

ጥያቄዎች

  1. በመጀመሪያዎቹ አምስት የዮሐንስ 1 ቁጥሮች ዉስጥ ወዲያዉኑ ዮሐንስ ኢየሱስን እንዴት ሳለው ?
  2. ኢየሱስን እንደ ዘላለማዊ አምላክ ለመለየት በምዕራፍ 1 ዮሐንስ የተጠቀማቸዉ ሰባት ስሞች ወይም ርዕሶች ምንድን ናቸው ? (ዮሐ 1፡ 1-3, 14, 4-13, 29-34, 35-42, 48-49, 50-51)
  3. የመጥምቁ ዮሐንስ አስፈላጊ ስራ ምን ነበር ? አይሁዶች ማን እንደ ነበር እና በመፅሀፍት መሰረት ምንድን ሊያደርግ እንደ መጣ ተረድተዉታል ?
  4. በዮሐ (1፡ 29) ወደ እርሱ እየመጣ እንዳለ ኢየሱስን መጥምቁ ዮሐንስ እንዴት አድርጎ አቀረበው ? ይህን ባለ ጊዜ በሰዎቹ ሀሳብ ዉስጥ ምንድን ሆነ ? (ዘፍ 22፡ 7-8፣ ዘኁ 28፡ 19)
  5. ለናትናኤል የመሰከረለት ማን ነበር ? ናትናኤል ኢየሱስን እንዲከተል ምንድን አሳመነው ?
  6. በዮሐንስ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin John 1:4–5

“In Him was life, and the life was the Light of men. The Light shines in the darkness and the darkness did not comprehend it.”

ዮሐንስ ወነጌሉን ኢየሱስ ህይወት ነው ይህም ህይወት የሰዎች ብርሃን ነው በሚለው መልዕክት ጀመረ፡፡ ኢየሱስ እንደ ብርሃን በጨለማ ውስጥ ያበራል፡፡ እነዚህን የእውነት ሐረጎች በቀናችሁ ሁሉ ብትናገሩስ፥ "ኢየሱስ ህይወቴ ነው፣ ኢየሱስ ብርሃኔ ነው፡፡"?

ኢየሱስ ህይወታችሁ በሆነበት መንገድ ጣልቃ የሚገቡ አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው? ስራ ህይወታችሁ ነው? ግብይት ህይወታችሁ ነው? የምትወዷቸው ሰዎች ህይወታችሁ ናቸው? ዛሬ፥ ኢየሱስን ህይወታችሁ አድርጉት፡፡ ፍቅራችሁን በሙሉ ስጡት እና በእርሱ ብቻ የሚገኘውን የተትረፈረፈ ህይወት ተቀበሉ፡፡ ደግሞም ኢየሱስ ብርሃን ነው፡፡ ብርሃኑ በጨለማ ውስጥ ያበራል፡፡ በኢየሱስ ውስጥ ጨለማ ፈፅሞ የለም፡፡ በህይወታችሁ የክርስቶስ ብርሃን ከደበዘዘ እና ጨለማ በዙሪያችሁ እየጨመረ ከመጣ፥ ከኢየሱስ ጋር ጊዜ አሳልፉ፡፡ ከእርሱ ጋር ተራመዱ እና እውነቱን ተለማመዱ፡፡ ብርሃኑ በውስጣችሁ ያድግ እና ነፃ ያወጣችኋል፡፡

“በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች። ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም። ”

—ዮሐንስ 1:4–5

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ዮሐንስ 14:6 — "ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። ”
  • ሮሜ 8:2 — “በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና። ”
  • 1ኛ ዮሐንስ 1:5–7 — “ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት። ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 69