The Gospels John

The First Sign

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 180 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ስለ ኢየሱስ እንደ እግዚአብሄር ልጅ ማዉራታችን እንቀጥላለን ፡፡ በሉቃስ ኢየሱስን እንደ ሰዉ ልጅ አይተናል ፤ አሁን በኢየሱስ እንደ እግዚአብሄር ልጅ እንለየዋለን ፤ ዛሬ መፅሀፉን ወደ ሁለት አካል እንከፍለዋለን ፡ ኢየሱስን እንደ ተዓምር ሰራተኛ እና ኢየሱስን በሁሉም ስልጣን ፡፡

ትምህርት

ዮሐንስ (2፡ 1)፡ የዚህ ምዕራፍ የመጀመሪያዉ ግማሽ በዮሐንስ ወንጌል ላይ ብቻ የተከሰተዉን ታሪክ ብቻ በቃና ሰርግ ላይ ያተኩራል ፡፡ ሰርጉ ሰዎስተኛዉ ቀን ላይ ነበር ይህም ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ ሁለት ቀናት ይጓዛሉ ፡፡

ዮሐንስ (2፡ 2)፡ ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ ሰርጉ ላይ ተገኝተዉ ነበር ፤ እንዲሁም የኢየሱስ እናት ማሪያም እና ምናልባትም ብዙ ቤተሰቦቹ ሰርጉ ላይ እየታደሙ ነበር ፡፡ የኢየሱስ ወንድም የያዕቆብ ሰርግ ነበር ? እርግጠኞች መሆን አንችልም ግን በእርግጠኝነት ማሪያም በሰርጉ ላይ ሚና ነበራት ፡፡ ይህ ሰርግ የማንም ይሁን ከኢየሱስ ጋር ባቻ ሳይሆን ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ተገናኝተዋል ፡፡

ዮሐንስ (2፡ 3-4)፡ ማሪያም ወደ ኢየሱስ በመሮጥ ወይን እንዳለቀባቸዉ ነገረችዉ ፡፡ ኢየሱስ እናት እንደ ነበረው እና የተለየ ግንኙነት እንደ ነበራቸዉ ማስታወስ አስፈላጊ ነው ፤ የኢየሱስ መልስ በእዉነት የንቀት ወይም የጨዋታ ፌዝ እርጋታ እንደ ነበር ማሰብ ትችላላችሁ ፤ የኋለኛው እንደ ነበር እና የተለየ ግንኙነት እንደ ነበራቸዉ አስባለሁ ፡፡ ማሪያም በትክክል ኢየሱስ ማን እንደ ነበር አዉቃለች ፡፡ ኢየሱስ ጊዜ ገና እንዳልመጣ ቢናገርም ከፍቅር የተነሳ ግን የእናቱን ጥያቄ በማክበር ታዘዘ ፡፡

ዮሐንስ (2፡ 5-7)፡ ይህ የኢየሱስን እና የማሪያምን የጨዋታ ቅርርብን እንደ ሚያሳይ አስባለሁ ፡፡ ማሪያም ወደ አገልጋዮቹ በመሄድ ኢየሱስን እንዲሰመት ነገረቻቸው ፤ ማሪያም በዚህ ሰርግ ላይ ቁልፍ ሚና እንደ ነበራት ግልፅ ነው ፡፡ ሰዎች እርሷን በሚያደምጡት ትንሽ የአገልጋይነት ሚና ነበራት ፤ እዉነታው ኢየሱስ ያላቸዉን ሰዎቹ በማድረግ ሚያስደነግጥ(የሞኝነት) የእምነት ደረጃ አሳዩ ፡፡

ሰርጉ ላይ የማንፃት ማድጋዎቸው ነበሩአቸው ፤ እነዚህ ማድጋዎች ከድናጋይ እንደ ተሰሩ የበዓላት ማንፂያ ማድጋዎች ብቻ ናቸው ፤ ትልቆች ነበሩ ፤ እንግዶች እጆቻቸዉን ይታጠቡባቸዋል በዚህም ከመብላታቸዉ በፊት ንፁህ ይሆናሉ ፤ ይህ የሚጠጣ ዉሃ አልነበረም ፡፡

ዮሐንስ (2፡ 8-10)፡ የሚያስደነግጠዉ የማሪያም እና የአገልጋዮቹ የእምነት ደረጃ የነበረው ይህን ዉኃ ለአሳደሪዉ በመስጠት በእነርሱ ታይቷል ፡፡ ከየት እንደ መጣ ምንም ኑሀዉ አልነበረውም ምናልባትም ይህ ጥሩ ነገር ነው ፤ ሙሽራዉን በመጥራት ለመጨረሻ መልካሙን ወይን ስለ ማስቀረቱ ተቆጣው ፡፡ ይህ በበሩ ስለ ኢየሱስ ትክክለኛ መምጣት ነበር እርሱ የህይወት ወይን ነው ፤ ትንቢታዊ ድርጊት ነበር ፡፡

ዮሐንስ (2፡ 11-12)፡ ይህ የኢየሱስ የመጀመሪያ ተዓምራት ነበር ፤ ከዚያም ኢየሱስ፣ ደቀ መዛሙርቱ፣ እናቱ እና ሌሎቹ የቤተሰብ አባላት ወደ ቅፍርናሆም ተጓዙ ፤ ምናልባትም ይህ ሰርግ የቤተሰብ ጉዳይ እንደ ነበር ይህ ሌላ ጥልቅ አመልካች ነው ፡፡

ዮሐንስ (2፡ 13)፡ ከዚያም ኢየሱስ ለአይሁዶች ፋሲካ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ ፡፡ በጊዜ ክስተቶችን ከሌሎቹ ሰዎስት ወንጌላት በመቀጠል በምናገናኘዉ ጊዜ የዮሐንስ ወንጌል ቅደም ተከተሉ የተዘበራረቀ የሚሆን ይመስላል ፤ ስነ መለኮታዊያን የዮሐንስ ወንጌል ከቅደም ተከተል ዉጪ እንደሆነ እና ይህም ስህተት እንደሆነ ይስማማሉ ፤ አንድ ቲዎሪይ ሳይፃፍ የወደቀ እና ገፁ በተሳሳተ ቅደም ተከተል ከኋላ የተቀመጠ ነው ፡፡ ሌሎቹ በጣም በርቀት በተወሳሰብ ቲዎሪዎች መጥተዋል ልክ እንደ እያንዳንዶቹ ወንጌል ፀሀፊዎች የተለየ የአፃፃፍ ዘዴ ነበረው ሌሎች ስነ መለኮታዊያንም ሁሉንም ችግሮች ሙሉ በሙሉ አልተቀበሏቸዉም ፡፡ የመጨረሻዉ መስመር ይህ ነው - ታሪኩ ከሌሎች ወንጌሎች ጋር በመዋሀድ ነው ፡፡

ዮሐንስ (2፡ 14-17)፡ ኢየሱስ በመቅደሱ ላይ በደረሰ ጊዜ የሚሸጡ ከብቶችን እና ሁሉም ቦታ ገንዘብ ለዋጮችን አገኘ ፤ ኢየሱስ ጅራፍ በመስራት ከመቅደሱ ከብቶቹን እና ገንዘብ ለዋጮቹን አስወጣቸው (መዝ 69፡ 9) ፡፡

ኢየሱስ ለምን ነበር በጣም የተበሳጨዉ ? መጀመሪያ አመልኪዋች በጉዞ ላይ ወደ ኢየሩሳሌም ከሩቅ ርቀት እንስሳት ይዘዉ መምጣት አይችሉም ፤ እንስሳትን የሚሸጡት በዋጋቸዉ ለእነዚህ አምልኮ ተጓዦችን በከፍተኛ ዋጋ እያስከፈሉዓቸዉ ስለ ነበር ፤ ሁለተኛ እነዚህ ድርጊቶች የፀሎት ቤት ይሆናል በተባለበት እየተደረጉ ስለ ነበር ፤ ሰዎስተኛ ለገዣዎቹ እንደ ርካሽ ፀጋ ስለ ነበር ፤ መስዋዕት ለሚያደርግቱ ሰዎች ትንሽ ስራ ነበር ፡፡

ዮሐንስ (2፡ 18)፡ አይሁዶችም “ ማን እንደሆንክ ታስባለህ ? ምንድንስ ትክክል ነገር ትሰጠናለህ ? አሉት ፡፡

ዮሐንስ (2፡ 19-21)፡ በምላሹም ኢየሱስ “ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሰዎስት ቀንም አነሳዋለሁ አላቸው “ (ቁጥር 19) ፤ ነገር ግን ህዝቡ ኢየሱስ እያለ የነበረዉን አልተረዱትም ! ኢየሱስ ስለ ራሱ አካል እየተናገረ ነበር ፡፡ በሴሚንቶ እና በብሎኬት ላይ አትኩረዉ ነበር ፤ ጭፍኖች እና ዝንጉዎች ነበሩ ፡፡ ይህን ምልክት ማድረግ የሚችለዉ አንዱ የእግዚአብሄር ልጅ ብቻ ነው ፤ በዮሐ (11፡ 25) ኢየሱስ “ ትንሳኤ እና ህይወት እኔ ነኝ “ አለ ፡፡

አይሁዶች እያወሩበት የነበረዉ መቅደስ በ515 ከክርስቶስ ልደት በፊት ያለቀ ነበር ፤ ለመስራት 46 አመት ፈጅቷል (ቁጥር 20) ፡፡ (1ቆሮ 6፡ 19 የእናንተ አካል የመንፈስ ቅዱስ መቅደስ እንደሆነ ይናገራል ) ፤ ኢየሱስ “ የመንፈስ ቅዱስ መቅደስ እንደሆንሁ አዉቃለሁ “ እያለ ነበር ፤ የክርስቲያን ህይወት ምንድን እንደ ሚመስል በዉልብታ እያሳየን ነበር፡፡

ዮሐንስ (2፡ 22-23)፡ ሮሜ (10፡ 9) የሚለው “ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሄርም እግዚአብሄር ከሙታን እንዳነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ “ ፤ ይህ ሁሉ ለዚያ ነው ፡፡ ወንጌል ያ ነው ደቀ መዛሙርቱም በዚህ ቀላል እምነት አለምን ቀየሩ ፡፡

ዮሐንስ (2፡ 24-25)፡ ኢየሱስ ሁሉንም ነገር ያብራራላቸዉ ጥቂት ሰዎች ነበሩ ፤ ኢየሱስ ራሱን ለጴጥሮስ፣ ለዮሐንስ እና ለያዕቆብ በተራራዉ መልክ መቀየር ላይ ገልጦላቸዋል ፤ ሊያምናቸዉ የሚችለዉ ሌሎች ነበሩ ነገር ግን በመቀራረብ አይደለም ምሳሌ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ፡፡ ለኃይማኖት መሪዎች ኢየሱስ በምክናታዊነት ካርዱን ዘግቶ ያዘባቸው ፡፡ ቁጥር 25 ሌላ የኢየሱስ የልጅነት መለኮታዊ ባህሪይ ተገልጣል፡ “ ስለ ሰዉም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገዉም ነበርና አይተማመናቸዉም ነበር ፤ ራሱ በሰዉ ያለዉን ያዉቅ ነበርና ፤ አብ የሰዉን ልብ ለእርሱ ይገልጥለታል - መልካሙን፣ መጥፎዉን እና አስከፊዉን ገልጦለታል ፡፡

መዝጊያ

ስለዚህ እናንተ እና እኔ ? እግዚአብሄር ሊያምነን የሚችል ሰዎች ነን ? ለሰዎች እግዚአብሄር ራሱን ሊገልጥ ይችላል ? ምልክቶችን እና ድንቆችን ለማሳደድ እርሱን እንከተላለን ? ስለ ነፃ ምግብ እርሱን እንከተላለን ? ለታአምራት ? ለፈዉስ ?

ማቴ (16፡ 13-17)፡ “ ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሳሪያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ሰዎች የሰዉን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል ? በሎ ጠየቀ ፡፡ እነርሱም አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ ሌሎችም ኤልያስ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት ፡፡ እርሱም እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆኑህ ትላላችሁ ? አላቸው ፡፡ ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ አንተ ክርስቶስ የሕያዉ የእግዚአብሄር ልጅ ነህ አለ ፡፡ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለዉ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማያት ያለዉ አባቴ እንጂ ስጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ ፡፡ “

ዮሐ (1፡ 50)፡ “ ናትናኤልም መልሶ መምህር ሆይ አንተ የእግዚአብሄር ልጅ ነህ ፤ አንተ የእስራኤል ንጉስ ነህ አለው ፡፡ “

ዮሐ (6፡ 66-69)፡ “ ከዚህም የተነሳ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም፡፡ ኢየሱስም ለአስራ ሁለቱ እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን ? አለ ፡፡ ስምዖን ጴጥሮስ ጌታ ሆይ ወደ ማን እንሄዳለን ? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ ፤ እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያዉ የእግዚአብሄር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አዉቀናልም ብሎ መለሰለት ! “

ለማን ነዉ የምንሄደዉ ? በእዉነት ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ እዉቅና እንሰጣለን ? ሌላ የት ልንሄድ እንችላለን ? በመጨረሻም የዘለላም ህይወት ቃል አለው ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ሰርጉ ራት ግብዣ ላይ ማሪያም አገልጋዮቹን ኢየሱስ የሚነግራቸዉን ሁሉ እንዲያደርጉ ነገረቻቸው (ዮሐ 2፡ 5) ፤ ይህ ጊዜዉ እንዳልነበር ከነገራት በኋላ ነበር ፡፡ ኢየሱስ እንኳን አይሆንም ካላት በኋላ ማሪያም ያን ንግግር እንድታደርግ ስለ መራት ምን ታስባላችሁ ?
  2. በቁጥር 19 ኢየሱስ ስለ መቅደሱ መልሶ እንደ ሚገነባው በሚያወራ ጊዜ ስለ ትክክለኛዉ ህንፃ ሳይሆን ስለአካሉ እንደ ሆነ ለምን አልተናገረም ? (ኢሳ 6፡ 9፣ ማቴ 13፡ 14፣ ዮሐ 1፡ 14)
  3. በዮሐንስ 2 በቁጥር 23-25 ላይ አሰላስሉ ፤ እነዚህ ቁጥሮች በምንድን ለእናንተ ይናገራሉ ? ምን ማለት እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ?
  4. በዮሐንስ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ ያስረዳችኋል (ያሳያችኋል) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin John 2:5, 7-8

“His mother said to the servants, ‘Whatever He says to you, do it.’ ‘Fill the jars with water,’ Jesus told them. So they filled them to the brim. Then He said to them, ‘Now draw some out and take it to the chief servant.’ And they did.”

ኢየሱስ፥ እናቱ፥ እና ደቀመዛሙርቱ በገሊላ ቃና በነበረ ሰርግ ላይ ታዳሚዎች ነበሩ፡፡ እናቱ ወደ ኢየሱስ ዘወር አለች እና ጋባዦቹ የወይን ጠጅ እንዳለቀባቸው ነገረችው፡፡ የልጇን ሀይል በመረዳት፥ የኢየሱስ እናት ወደ አገልጋዮቹ ዘወር አለች እና አለቻቸው፥ " ኢየሱስ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ፡፡" ውሃን ወደ ወይንጠጅ በመለወጥ፥ ኢየሱስ የመጀመሪያውን ተአምር አደረገ፡፡ ኢየሱስ አገልጋዮቹ ምን እንደሚያደርጉ ነገራቸው፥ እነርሱም አደረጉት፡፡ በፍጥነት በሆነው ታዛዥነታቸው ምክንያት ፥ ውሃው ወደ መልካም የወይን ጠጅ ተለወጠ፡፡ ኢየሱስ በግልፅ ክብሩን ገለጠ፥ ደቀመዛሙርቱም በእርሱ አመኑ፡፡

እንደ አገልጋዮቹ ኢየሱስን ብትሰሙት ምን ይሆናል? አድርጉ ያላችሁን ማንኛውንም ነገር፥ እንዲያው ብታደርጉት፡፡ ማንኛውንም በእግዚያብሔር ቃል ውስጥ የምታነቧቸውን የእርሱን ተስፋዎች እና እውነቶች፥ ወዲያውኑ ታምናላችሁ፡፡ በነገሩ ጥያቄ አትጠይቁም፡፡ ሌሎች ምን እንደሚያስቡ አትጠይቁም፡፡ ይልቁንም፥ ትሰሙ እና ወዲያውኑ ትታዘዛላችሁ፡፡ ልክ ውሃው ወደ ወይንጠጅ ሲቀየር እንዳዩት አገልጋዮች፥ ወዲያው በሆነ ታዛዥነት በመራመድ፥ ኢየሱስ ተአምራዊ በሆነ መንገድ ሲሰራ ማየት ትጀምራላችሁ፡፡ ቢጠብቁ፥ ቢከራከሩ፥ ቢያመዛዝኑ ወይም ሌላ ሰው እንዲያደርግ ቢጠይቁ፥ ተአምራቱ ያመልጣቸው ነበር፡፡ ዛሬ፥ የጌታን ድምፅ በመስማት ወዲያውኑ አድርጉ፡፡

“ እናቱም ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።. . .ኢየሱስም፦ ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው። አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም። ”

—ዮሐንስ 2:5, 7-8

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ዘፍጥረት 17:23 — “አብርሃምም ልጁን እስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ፥ በብሩም የገዛቸውን ሁሉ፥ ከአብርሃም ቤተ ሰብ ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ፥ የቍልፈታቸውንም ሥጋ እግዚአብሔር እንዳለው በዚያው ቀን ገረዘ። ”
  • ትንቢተ ኢሳይያስ 30:20ለ–21 — “ዓይኖችህ ግን አስተማሪህን ያያሉ፥ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ ብትል ጆሮችህ በኋላህ፦ መንገዱ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ የሚለውን ቃል ይሰማሉ። ”
  • ዮሐንስ 2:11 — “ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 70