The Gospels John

The One From Heaven

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 181 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለዮሐንስ መፅሀፍ ሀረጋችን የእግዚአብሄር ልጅ ነው ፤ በዮሐንስ ወንጌል ኢየሱስ ማን እንደ ሆነ ማሳየት ቀጠለ ፡፡

ትምህርት

ዮሐንስ (3፡ 1)፡ የአይሁዶች መሪ እና የካህናት አለቃ የነበረ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰዉ ነበር ፤ ሁልጊዜ በቤተሰብ የዘር ግንድ ወይም በፖለቲካ ዝምድና ምክንያት ይህ ስልጣን የተመረጠ ነበር ምክንያቱም ፈሪሳዉያን የአይሁዶች ዋና መሪ አካል አድርገዉ ስለ ሚመለከቱት ፡፡ “ ፈሪሳዉያን “ የሚለዉ ስም “ የተለየ “ ማለት ነው ፡፡ እዚህ ፈጣን የሆነ ታሪክ አለን ! ክርስቶስ ሰዉን ለራሱ እየሳበ ነበር ፡፡ ዮሐ (1፡ 24-27)፡ “ የተላኩትም ከፈሪሳዉያን ነበሩና እንኪያስ አንተ ክርስቶስ ወይም ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካይደለህ ስለ ምን ታጠምቃለህ ? ብለዉ ጠየቁት ፡፡ ዮሐንስ መልሶ እኔ በዉኃ አጠምቃለሁ ! ዳሩ ግን እናንተ የማታዉቁት በመካከላችሁ ቆሞአል ፤ እኔ የጫማዉን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ ይልቅ የሚከብር ይህ ነዉ አላቸው ! “

ፈሪሳዉያን በብልጫ የሚመጣ አንድ ሰዉ እንደ ነበር ዮሐንስ ያለዉን ሰሙ ፤ ብላክቤይ የሚለው “ አንድ ጊዜ የት እየሰራ እንዳለ ብታዉቁ በመለኮት አላማዉ ከእርሱ ጋር ለመገናኘት ህይወታችሁን ማስተካከል ትችላላችሁ “ ፤ ኒቆዲሞስ እያደረገ የነበረዉ ይህን ነበር ፡፡

ዮሐንስ (3፡ 2)፡ ኒቆዲሞስ በምሽት ወደ ኢየሱስ መጣ ፤ ለምን ? በከፍተኛ ማንነት(ማዕረግ) ስለ ነበር ፈርቷል ፡፡ ዮሐ (12፡ 42) የሚገልፀው “ ከዚህም ጋር ከአለቆች ደግሞ ብዙዎች በእርሱ አመኑ ፤ ነገር ግን ከምኩራብ እንዳያስወጡአቸው በፈሪሳዉያን ምክንያት አልመሰከሩለትም “ ፡፡ እንደ መሪ ስለሚፈፅም ሌሎች ኒቆዲሞስ ከኢየሱስ ጋር እንደ ተገናኘ ሲያገኙት መልካም ዕድል ነበር ፡፡

የኒቆዲሞስን የህይወት ፍፃሜን ላይ እንመልከት ፤ በዮሐ (7፡ 50) ኒቆዲሞስ በአቻዎቹ መካከል በመቆም ስለ ክርስቶስ ቆመ ፡፡ ፍራት በመጨረሻ ወደ እምነት እንደ ሚመራን አስባለሁ ፤ የምትሰሩትን ፍራት እንዲያስገድዳችሁ አትፍቀዱለት ! ለወዳጆቻችሁ ለማዉራት በደንብ ደፋር ሁኑ ! በዮሐ (19፡ 39) ኒቆዲሞስ ለኢየሱስ አካል እንደ ማዘጋጂያ የእሬት እና የከርቤ ቅልቅል አመጣ ፤ ከኃይማኖተኝነት መንፈስ ሰብሮ ነፃ ሆነ ! ለኒቆዲሞስ እንዴት እንዳለቀ እናውቃለን ፤ እዚያ እንዴት ተገኘ ?

በምሽት ጊዜ ጣሪያ ላይ መቀመጥ ለሰዎች የተለመደ ነው ፤ ኢየሱስ እና ኒቆዲሞስ ለማዉራት ተቀምጠዋል ፤ መጀመሪያ ኒቆዲሞስ ኢየሱስን አመሰገነ ከዚያም በመቀጠል እርሱን ጠየቀዉ ፡፡

ዮሐንስ (3፡ 3-5)፡ ኢየሱስ ኒቆዲሞስን ዳግም ካልተወለደ በስተቀር የእግዚአብሄርን መንግስት ማየት እንደ ማይችል ነገረው ፤ ኒቆዲሞስም “ ምን ! “ አለ ኢየሱስም እንደ ገና ማንም ዳግም ካልተወለደ ወደ እግዚአብሄር መንግስት መግባት አይችልም አለ ፤ ኢየሱስ “ ከዉኃና ከመንፈስ ልትወለድ ያስፈልግሀል “ አለው (ቁጥር 5) ፡፡ ይህ ቁጥር ፈታኝ(አስቸጋሪ) ነዉ ምክንያቱም ብዙ ነገሮችን ሊል ይችላል ፤ ሊሆን የሚችለዉ፡ አካላዊ መወለድ እና መንፈሳዊ መወለድ ወይም የዉሃ ዉልደት ንስሀን እና ቀጣይነትን ሊወክል ይችላል ደግሞም ዉልደት መንፈሳዊ ዉልደትን ሊገልፅ ይችላል ፡፡

ዮሐንስ (3፡ 6-7)፡ ኢየሱስ “ ይህን ስላልኩህ አትደነቅ “ አለው ፤ ዳግም መወለድ ማለት “ ከላይ ካሉት መወለድ “ ማለት ነው ፡፡ 2ቆሮ (5፡ 17)፡ “ ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አድስ ፍጥረት ነው ፤ አሮጌዉ ነገር አልፏል ፤ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆኗል “ ፤ አድስ ሰዉ ትሆናላችሁ ፡፡ ቲቶ (3፡ 5) የሚለው “ እንደ ምህረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆን መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ስራ አይደለም፡፡” ከዚህ ጋር ኒቆዲሞስ ይታገል የነበረዉ ለምን ነበር ?

1ቆሮ (2፡ 10)፡ “ መንፈስም የእግዚአብሄርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሄር በመንፈሱ በኩል ገለጠው ፡፡ “

1ቆሮ (2፡ 13-16)፡ “ መንፈሳዊን ነገር ከመንፈሳዊ ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰዉ ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም ፡፡ ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሄር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነዉና አይቀበለዉም ፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያዉቀው አይችልም ፡፡ መንፈሳዊ ሰዉ ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም ፡፡ እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አዉቆት ነው ? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን ፡፡

ከላይ ባሉት ዳግም በተወለዳችሁ ጊዜ እነዚህ ነገሮች ትርጉም የሚሰጡ ይሆናሉ ፤ በዚህ ክስተት ኒቆዲሞስ እንኳን ብዙ ለመማር የተራበ ነው ኢየሱስ እርሱን የነገረዉን ለመያዝ ዝም አላለም ፡፡

ሕዝ (36፡ 25-26)፡ “ ጥሩ ዉኃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ ከርኩሰታችሁም ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ ፡፡ አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በዉስጣችሁ አኖራለሁ ፤ የድንጋዩንም ልብ ከስጋችሁ አወጣለሁ የስጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ ፡፡ “

ኒቆዲሞስ ትንቢቶቹን ለማስታወሱ እና መረዳት ለመጀመሩ እዚህ በቂ ቋንቋዎች ነበሩ ፡፡

ሕዝ (37፡ 11-14)፡ “ እርሱም እንዲህ አለኝ የሰዉ ልጅ ሆይ እነዚህ አጥንቶች የእስራኤል ቤት ሁሉ ናቸው ፤ እነሆ አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል ፈጽመንም ተቆርጠናል ብለዋል ፡፡ ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል ሕዝቤ ሆይ እነሆ መቃብራችሁን እከፍታለሁ ከመቃብራችሁም አወጣችኋለሁ ወደ እስራኤልም ምድር አገባችኋለሁ ፡፡ ሕዝቤ ሆይ መቃብራችሁን በከፈትሁ ጊዜ ከመቃብራችሁም ባወጣኋችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሄር እንደ ሆንሁ ታዉቃላችሁ ፡፡ መንፈሴንም በዉስጣችሁ አሳድራለሁ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ በገዛ ምድራችሁም አኖራችኋለሁ ፤ እኔም እግዚአብሄር እንደ ተናገረሁ እንዳደረገሁም ታዉቃላችሁ ይላል እግዚአብሄር ፡፡ “

የመንፈስ ነገር ብቻ ከመንፈስ ቅዱስ ሊመጣ ይችላል ፡፡

ዮሐንስ (3፡ 8-11)፡ መንፈስ ቅዱስ በመምጣት ልክ እንደ ንፋስ ይሄዳል ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በፍፁም አይተዋችሁም ነገር ግን በህይወታችሁ በተለያዬ መንገድ ይጓዛል ፡፡ ኒቆዲሞስ እንደ ገና “ ምን ?! “ አለ ኢየሱስም “ መምህር አይደለህምን ? የምናዉቀዉን እንናገራለን ያየነዉንም እንመሰክራለን ምስክራችንንም አትቀበሉትም “ በማለት ገፀው ፡፡ ኢየሱስ እንደ አብ፣ እንደ ወልድ እና እንደ መንፈስ ቅዱስ እየተናገረ ነበር ፡፡

ዮሐንስ (3፡ 12)፡ የመንግስተ ሰማያትን ነገሮች እንዴት ልትረዱ ትችላላችሁ ?

ዘኁ (21፡ 8-9)፡ “ እግዚአብሄርም ሙሴን እባብን ሰርተህ በዓላማ ላይ ስቀል ፤ የተነደፈዉም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው ፡፡ ሙሴም የናሱን እባብ ሰርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ እባብም የነደፈችዉ ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ ፡፡ “

ይህ የኢየሱስ ዘላለማዊ ህይወት ማሳያ ጅማሬ ነበር ፡፡

ዮሐንስ (3፡ 16)፡ “ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሄር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶዓልናል ፡፡ “

ኢየሱስም “ ኒቆዲሞስ እንደ ምትሰማኝ አዉቃለሁ ፤ ልብህ ላይ አንድ ነገር እንድታስቀምጥ እጠይቅሀለሁ ፤ በእኔ እመን ፤ እንደ ምነሳ እኔ ላይ አይንህን አድርግ “ አለው ፡፡

ዮሐ (19፡ 39-40)፡ ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ ፡፡ የኢየሱስንም ስጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዘ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት ፡፡ “

መዝጊያ

አሁን ፍራታችሁን የምታሸንፉበት ጊዜ ነው ፤ ፍቅሩ ኃጢዓታችሁን ጠርጎ አርቆታል ፡፡ ይህን ስጦታ በተቀበላችሁ ጊዜ ዘላለማዊ ህይወት ይኖራችኋል ፡፡ የበረታችሁ ሁኑ ፡፡

  1. Henry T. Blackaby. Experiencing God: Knowing and Doing the Will of God (Nashville, TN: B&H Publishing, 2008), p.70.

ጥያቄዎች

  1. ራሳችሁን በኒቆዲሞስ ጫማ ዉስጥ አድርጉ ፤ ቃለ ምልልሱ ከእናንተ እንዴት የተለዬ ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ይመሳሰላል ?
  2. ለአንድያ ልጁ በመስጠት እግዚአብሄር የተናገረው በጣም የተጠቀሰዉ አንዱ መፅሀፍ ዮሐ (3፡ 16) ነው ፤ ይህን ቁጥር ባሰባችሁት ጊዜ ለአለም ላጃችሁን ለመስጠት ማሰብ ትችላላችሁ ? አንድ ልጃችሁን ? ሀሳቡ ለመያዝ ለምንድን ነዉ በጣም አስቸጋሪ የሆነው ?
  3. ቁጥር 19-21 የእግዚአብሄር ብርሃን እና ጨለማን ይናገራል ፤ ስለ ትክክለኛዉ ብርሃን እየተናገረ ነበር ወይስ ስለ ሌላ ? ምንድን ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? (መዝ 119፡ 105, ዮሐ 1፡ 9)
  4. የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቶች ወደ እርሱ መጡና ሁሉም ከእርሱ ይልቅ ወደ ኢየሱስ እየሄዱ እንደ ሆነ ነገሩት ፤ በእዉነት የዮሐንስ ደቀ መዛሙርቶች ኢየሱስ ማን እንደ ነበር አዉቀዉታል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡም ?
  5. መጥምቁ ዮሐንስ እኔ ላንስ እርሱ ሊልቅ ይገባል ባለ ጊዜ ምን ማለቱ ነበር ? (ቁጥር 30) ፤ ለእናንተ ቁጥር 31 ምን ማለት ነው ?
  6. በዮሐንስ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin John 3:16–17

“For God so loved the world in this way: He gave His one and only Son, so that everyone who believes in Him will not perish but have eternal life. For God did not send His Son into the world that he might condemn the world, but that the world might be saved through Him.”

እግዚያብሔር አለምን ከመውደዱ የተነሣ አንድያ ልጁን ኢየሱስን ወደ ምድር ላከው፡፡ የኢየሱስ አላማ በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ የዘላለምን ህይወት እንዲያገኙ ወደ ምድር መምጣት ነው፡፡ ኢየሱስ አለምን ለማዳን እንጂ በአለም ሊፈርድ አልመጣም፡፡

እግዚያብሔር ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ ልጁን አሳልፎ ሰጠ፡፡ አንድ ነገርን መስጠት ኖሮባችሁ ያውቃል? ምናልባት ልጃችሁ ከወላጅ አልባ ልጆች ጋር እንዲሰራ ወደ ውጪ ሀገር ልካችሁት፥ ካደገው ልጃችሁ ጋር በቅርበት የመኖር ህልማችሁን አሳልፋችሁ ሰጥታችኋል፡፡ ሆኖም ልጃችሁን እና ህልማችሁን አሳልፋችሁ በመስጠታችሁ ምክንያት፥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወላጅ አልባ ልጆች ህይወት ላይ ተፅዕኖ አድሯል፡፡ ምናልባት የአገልግሎቱ ቤተሰብ የሚሰራ መኪና እንዲኖረው መኪናችሁን አሳልፋችሁ እንድትሰጡ ጌታ መርቷችኋል፡፡ እናንተ መኪናችሁን ስለሰጣችሁ፥ ይሄ ቤተሰብ አንድ ከተማ ላይ ለወንጌሉ ተፅዕኖ ፈጥረዋል፡፡ መስዋዕትነቱ የተገባ ነው፥ አይደል? እግዚያብሔር አንድያ ልጁን ሰጠ፥ ስለዚህ አሁን አለም ሁሉ መዳን እና የዘላለምን ህይወት ማግኘት ይችላል፡፡ ነገር ግን ልክ መኪናውን እንደ ስጦታ እንደሚቀበለው ቤተሰብ፥ የእግዚያብሔርን ልጅ እንደ ስጦታ፥ ለድነት የሆነ ነፃ ስጦታ፥ መቀበል አለባችሁ፡፡ ይህንን ስጦታ ስትቀበሉ፥ በኢየሱስ ህይወት ከሞት እና ከኃጢያታችሁ ትድናላችሁ፡፡ ዛሬ፥ ይህንን ውሳኔ ካላደረጋችሁ የመዳንን ስጦታ ተቀበሉ፡፡ ካደረጋችሁ ደግሞ፥ ፍቅሩ፥ ፀጋው፥ እና ሀይሉ ለሌሎች እንዲዳረስ አሳልፋችሁ እንድትሰጡ የሚፈልገው ነገር ካለ ጌታን ጠይቁት፡፡

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።”

— ዮሐንስ 3:16–17

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ሮሜ 10:9–10 — “ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ”
  • 1ኛ ዮሐንስ 4:8 — “ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። ”
  • የዮሐንስ ራእይ 22:17 — “መንፈሱና ሙሽራይቱም፦ ና ይላሉ። የሚሰማም፦ ና ይበል። የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 71