ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሉቃስ ወንጌል መጨረሻ ላይ በነበሩበት ኢየሱስ የሰዎችን መብት አቀረበ(አጨ) ፡፡ ዮሐንስ ዮሐንስ ኢየሱስ ያደረጋቸዉን ብዙ ተዓምራቶች አይቷል ነገር ግን አንዱ የመዘገበው (ያሰፈረው) አንዱ በዮሐንስ 4 የተካተተው ተፅፏል በዚህ ምክንያትም “ ኢየሱስ መሲህ እንደሆነ ታምናላችሁ “ (ዮሐ 20፡ 31) ፡፡ በዮሐንስ 4 ኢየሱስ ለወንጌል አራት ቃላት አቀራረቦችን ቀርፃል (አዘጋጅቷል)፡ ፍቅር, ማዳመጥ, መለየትን እና መመለስን ፡፡
ትምህርት
ዮሐንስ (4፡ 1-4)፡ ኃያማኖታዊያን አይሁዶች በፍፁም በሰማሪያ በኩል አይጓዙም ፤ በሰማሪያ በኩል ከይሁዳ ወደ ገሊላ መጓዝ ቀላል ቢሆንም አይሁዶች መስመሩን አስወግደዉታል (አይሄዱበትም) ምክንያቱም ሰማሪያዉያንን ስለ ሚንቁ ፡፡ አይሁዶች ሰማሪያዊያንን ይንቃሉ ምክንያቱም የሰማሪያዊያን የአምልኮ ድርጊት(ልምድ) ንፁህ ያልሆነ እና ፍፁም እንዳልሆነ ይታሰብ ስለ ነበር ፤ ነገር ግን ኢየሱስ በሰማሪያ በኩል እጓዛለሁ አለ ምክንያቱም ለሰዎች ፍቅር ስለ ነበረው (ዮሐ 3፡ 16) ፡፡
ዮሐንስ (4፡ 5-6)፡ ኢየሱስ ተጠምቶ ነበር ነገር ግን ለአገልግሎቱ ፍላጎቱን ወደ ጎን አስቀመጠ ፡፡
ዮሐንስ (4፡ 7-8)፡ ሳምራዊቱም ሴት ወደ ጉድጓዱ እንደ ቀረበች ኢየሱስ ዉሀ ለመጠጣት ጠየቃት ፡፡ እዚህ ጋር የኢየሱስን ሰብዓዊነት እና መደገፍ እናያለን ፡፡ ይህ በሰማሪያ የቀኑ ግለት አካል ነበር ፡፡ ኢየሱስ ደግሞና ተጠምቶ ነበር ፤ ዉሃ ለመቅዳት ምንም መንገድ አልነበረው ስለዚህም ለመጠጣት ሳምራዊቱን ሴት ጠየቃት ፡፡ ለሳምራዊቱ ሴት ኢየሱስ ወደፊት በመሆን ያስተላልፍ የነበረው መጀመሪያ ብቻቸዉን ስለ ነበሩ እና ሁለተኛው አይሁዳዊ ስለ ነበር መስሏታል ፤ ነገር ግን ባህልም ሆነ ልምድ ወይም ማንኛዉም ሌላ ነገር የሚወዳቸዉን ሰዎች ከማገልገል አያስቆመዉም ፡፡
ዮሐንስ (4፡ 9-15)፡ እንደ ሳምሪዊ ሴት ለኢየሱስ በጥያቄ መለሰለችለት ወደ እርሷም በጥንቃቄ አዳመጠ ፤ ስቴፈንኮቬይ “ ብዙ ሰዎች ለመረዳት በጥንቃቄ አያዳምጡም ፤ ለመመለስ በጥንቃቄ ያደምጣሉ “ ፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሷን ለመረዳት ወደ ሳምራዊቷ ሴት አደመጠ ፡፡ የሆኑን ሰዎች የምትወዱ ከሆነ ወደ እነርሱ አድምጡ ፡፡ ኢየሱስ ስለ ህያው ዉሃ ተናገረ ነገር ግን ሳምራዊቱ ሴት በተፈጥሮ መረዳት ሰማችዉ (1ቆሮ 2፡ 14) ፤ ምናልባት አሁንም በቁጥር 15 መልሷ ተፈጥሮአዊ ነበር ፡፡ ኢየሱስ አቅርቦት ስለ ነበረው ህያው ዉሃ ሳምራዊቱ ሴት አልተረዳችዉም ፡፡ ህያዉ ዉሃ የኢየሱስ ትምህርት ዋና(ጭብጥ) ነበር ፡፡ በዮሐንስ 7 በምኩራብ ላይ በመቆም “ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ ፡፡ በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለው የሕይወት ዉኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ “ (ዮሐ 7፡ 37-38) ፡፡
ዮሐንስ (4፡ 16-20)፡ የአንድን ሰዉ ጥያቄ ስትሰሙ ወደ ታሪካቸዉ ልታዳምጡ ይገባችኋል ፡፡ ሴቲቱ ኢየሱስን እንደ ነቢይ ተረዳችዉ (አወቀችዉ) ስለሆነም በአይሁዶች እና በሰማሪያዊያን መካከል ያለዉን አንዱን ትልቅ ልዩነት ጠየቀችው ፡፡
ዮሐንስ (4፡ 21-22)፡ ኢየሱስ ለሳምሪዊቷ ሴት ወደ እርሷ በማዳመጥ ፍቅሩን ማሳየት ከጀመረ በኋላ ግልፁን ተናገረ (ጠቀሰ) ፡፡ ተመሳሳይ ነገር ለማድረግ መንፈስ ቅዱስ እንዲመራን መፍቀድ መማር እንችላለን ፤ ይህ የሌላ ሰዉ ኃላፊነት አይደለም ፤ የኛ ነው !
ዮሐንስ (4፡ 23-24)፡ ኢየሱስን ለማምለክ ወደ ገበታዉ በምንመጣ ጊዜ በእግዚአብሄር ቃል(እዉነት) መሰረት መምጣት ይጠበቅብናል ፤ በተመሳሳይ ጊዜ(በዚያኑ ጊዜ) በመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ ወደ ገበታዉ (ግብዣዉ) እንመጣለን ፡፡ መንፈስን በመናቅ(በመተው) በእዉቀት መምጣት አንችልም በመንፈስ መምጣት ስለማንችል እዉነትን እንገፋለን ፡፡
ዮሐንስ (4፡ 25-26)፡ ኢየሱስ ሳምራዊቱን ሴት ወደዳት ወደ እርሷም አዳመጠ ምን እያለች እንደ ነበር ተረዳ ከዚያም መለሰላት ፡፡ ሳምራዊቱ ሴት ህይወትን እየሸሸች ነበር እንዲሁ የማንጠነቀቅ ከሆነ በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ እንደ ሌሎች ተመሳሳይ ወጥመድ ዉስጥ እንወድቃለን፡
ዘጸ (14፡ 13)፡ እስራኤላዊያን ከግብፅ እንደ ወጡ ፈርዖን ከኃላቸዉ ለመምጣት ወሰነ ፤ እስራኤላዊያን በፈርዖን ጦር እና በቀይ ባህር መካከል ወጥመድ ዉስጥ ነበሩ ፡፡ እግዚአብሄር ተገለጠ ፡፡
ዘፍ (41፡ 14-15)፡ የፈርዖንን ህልም ለመፍታት በመጣ ጊዜ ዮሴፍ ለአመታት በእስር ቤት ተቀምጦ ነበር ፤ እግዚአብሄር ተገለጠ ፡፡
ሳምራዊቷን ሴት የምትመስሉ ከሆነ እና ከሁኔታዉ ለመዉጣት ኢየሱስ ካስፈለጋችሁ ይህን አድርጉ፡
- በተስፋችሁ ላይ ፅኑ (ኢሳ 40፡ 8; ማቴ 5፡ 17-18) ፡፡
- አይናችሁን ኢየሱስ ላይ አድርጉ (መዝ 25፡ 15; ዕብ 12፡ 2) ፡፡
መዝጊያ
ኢየሱስን የምትከተሉም ሁኑ ወይም ሳምሪዊት ሴት ሁኑ ችግር የለዉም ፤ በዮሐ (4፡ 27) ኢየሱስ ከሳምራዊቷ ሴት ጋር መስተጋበር በማድረጉ ተደንቀዉ የነበሩትን ደቀ መዛሙርቶቹን የምትመስሉ እንዳትሆኑ ፡፡ ሁላችንም ከሳምራዊያን ጋር መስተጋብር ማድረግ ያስፈልገናል ፡፡ የታሪኩ መጨረሻ በከተማዋ ያሉ ሁሉም ሰዎች ከኢየሱስ ጋር በሳምራዊቱ መስተጋብር በኩል ስለ ኢየሱስ ለማዎቅ ሁሉም መምጣታቸዉ ነው ፡፡
Stephen Covey, The 7 Habits of Highly Effective People (Kindle e-book: Franklin Covey, 2017), p. 250.
ጥያቄዎች
-
በቁጥር 10 “ የህይወት ዉሃ “ ምንጭ ምንድን ነው ? (ኢሳ 55፡ 1, ኤር 2፡ 13, 17፡ 13) ፤ እንዴት ታገኙታላችሁ ? (ሮሜ 10፡ 9-10)
-
በግል አስተያየታችሁ አብን (አባቴን) በእዉነት እና በመንፈስ ማምለክ ማለት ምን ማለት ነው ? (1ሳሙ 16፡ 7, ሉቃ 18፡ 9-14, ሮሜ 12፡ 1) ፤ ምንድን እንደ ሚመስል ምንድን ታስባላችሁ ?
-
በዮሐ (4፡ 26) ኢየሱስ በግልፅ ሳምራዊቱን ሴት መሲህ እንደ ሆነ ነገራት ፤ በዮሐንስ 3 ኒቆዲሞስን ሳይነግር በግልፅ ለምን እንደ ነገራት ምን ታስባላችሁ ?
-
በዮሐ (4፡ 35-38) ኢየሱስ በዘር እና በሰብሳቢ ላይ ተናገረ ፤ በሁለቱ መካከል ልዩነቶቻቸዉ ምንድን ናቸው? ዘርታችሁ ወይስ አጭዳችሁ ታዉቃላችሁ ? ባልዘራችሁበት ስፍራ አጭዳችኋል ? ዘርታችኋል እንጂ አላጨዳችሁም ?
-
በዮሐ (4፡ 47) ሰራተኛዉ ኢየሱስን ልጁን እንዲፈዉስለት በጠየቀዉ ጊዜ ኢየሱስ ድንቅ እና ምልክቶችን ካላዩ እንደ ማያምኑ ጠቀሰ (ዮሐ 4፡ 48) ፤ ልጁም ተፈወሰ በዚያች ቅፅበት መላዉ ቤተሰቡ አመኑ ፤ ለእናንተ ለማመን ድንቅ እና ምልክት ተቀብላችኋል ? ለምን ወይስ ለምን አልተቀበላችሁም ?
-
በዮሐንስ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin John 4:6–8 ESV
“Jacob’s well was there; so Jesus, wearied as he was from His journey, was sitting beside the well. It was about the sixth hour. A woman from Samaria came to draw water. Jesus said to her, ‘Give Me a drink.’ (For his disciples had gone away into the city to buy food.)”
ኢየሱስ በገሊላ መንገዱ በሰማርያ በኩል ተጓዘ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ በሌሎች አይሁድ ብዙም ጉዞ የማይደረግበትን መንገድ መረጠ እና የያዕቆብ ጉድጓድ ጋር ውሃ ሊጠጣ ቆመ፡፡ ከመንገዱ ደክሞ ነበር፡፡ ከደቀመዛሙርቱ ውጪ ብቻውን ነበር፥ ይሄ ለእርሱ ያልተለመደ ነው፡፡ ከዚያም አንዲት ሳምራዊት ሴት ውሃ ልትቀዳ ወደ እርሱ ቀረበች፡ ፡ ራሱም ደክሞት እና ወሃ ጠምቶት ቢሆንም፥ ኢየሱስ የእርሱን ፍላጎት ወደ ጎን በማድረግ የውሃ ጉድጓዱ ጋር የነበረችውን ይህቺን ሴት ለመውደድ፥ ለመስማት፥ ለማወቅ፥ እና ለእርሷ ለመመለስ ጊዜ ወሰደ፡፡ በዚያን ቀን፥ ኢየሱስ ለዚህች ሴት ፍቅርን ለማሳየት ጊዜ እንደወሰደ ፥ የእግዚያብሔር ልጅ የሆነውን ኢየሱስን በማመኗ ህይወቷ ለዘላለም ተለወጠ፡፡ ከተማው ራሱ ተፅዕኖ አደረበት እና ብዙ ሳምራዊያን በኢየሱስ ማመን ጀመሩ፡፡
ከመንገዱ የተነሣ ደክማችኋል? ቁጭ ብላችሁ የሚጠጣ ውሃ የምትስተናገዱበት ጊዜ የሚያስፈልጋችሁ እንደሆነ ተሰምቷችሁ ያውቃል? ኢየሱስ በተመሳሳይ መንገድ ተሰምቶታል፡፡ ይሁን እንጂ፥ በዚያ የድካም ጊዜ መካከል፥ ኢየሱስ የሚወደው አንድ ሰው መጣ፡፡ በመዋኛ ገንዳ አጠገብ ተቀምጣችሁ እረፍት ስታደርጉ ወይም ደግሞ በቡና መሸጫ ውስጥ መፅሀፍ ስታነቡ፥ እንደ ኢየሱስ ትወዱት ዘንድ ጌታ በመንገዳችሁ ለሚያመጣው ማንኛውንም ሰው አይናችሁን ክፍት አድርጋችሁ እንድትቆዩ አስታውሱ፡፡ በቤታችሁ ራሱ ሆናችሁ እግራችሁን ዘርግታችሁ ማረፍን ብቻ ፈልጋችሁ ይሆናል፥ ነገር ግን ልጃችሁ ይመጣ እና ይፈልጋችኋል፡፡ በነዛ አይነት የድካም ጊዜዎች፥ ለመውደድ እና ፀጋን ለማሳየት ብርታት እንዲኖራችሁ ወደ ጌታ ተጣሩ፡፡ በነዚህ የድካም ጊዜዎች፥ የኢየሱስ ፍቅር በብርቱ መንገድ ያበራል፡፡ በማይጠበቁ እና በማይመቹ ጊዜያት በእናንተ ውስጥ እና በእናንተ በኩል ሆኖ የሌሎች ህይወት ላይ ተፅእኖ እንዲያመጣ በፍቅሩ መደገፋችሁን ቀጥሉ፡፡ የኢየሱስ ፍቅር በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ የሚያደርገውን ተፅእኖ ምን እንደሚሆን አታውቁም፡፡
“በዚያም የያዕቆብ ጕድጓድ ነበረ። ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ ደክሞ በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ያህል ነበረ።ከሰማርያ አንዲት ሴት ውኃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም፦ ውኃ አጠጪኝ አላት፤ ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበርና። ”
— ዮሐንስ 4:6–8
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ትንቢተ ኢሳይያስ 40:8 – “ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች። ”
- ትንቢተ ኢሳይያስ 40:31 – “እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”
- 2ኛ ቆሮንቶስ 2:14 – “ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን”
የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 72
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።