The Gospels John

Witnesses for the Son of God

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 183 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ወደ ዮሐንስ ምዕራፍ 5 ዘለናል ፤ ስለ ዮሐንስ ወንጌል የምወደዉ አድስ እና ትኩስማሰማቱ ነው ፡፡ ትናትና ምንጩ ላይ ስለ ኢየሱስ እና ሳምራዊቷ ሴት አዉርተናል ፤ ኢየሱስ ሁሉንም ልምድ ሲሰብር አይተናል ፡፡ መንገዱን በጠቅላላ ከአይሁድ አዋቂዎች ጋር መስተጋብር ከማታደርገዉ ሴት ጋር ለማገልገል፣ ለመዉደድ፣ ለመስማት እና ለመመለስ ሄደ ፡፡ ኢየሱስ ሰዎችን እንዴት እንደ ሚወድ ለሞደልነት ቀጠለ ፡፡ ዮሐ (5፡ 1-15) ሁሉም ስለ ምልክት ናቸው ፤ ኢየሱስ ሰዎስተኛዉን ምልክት አድርጎ ነበር ፤ ሰባት ምልክቶች እንዳሉ እናስታዉሳለን ፤ እዚህ ኢየሱስ አንድ የታመመ ሰዉ በመፈወስ አንድ ተዓምራት እያደረገ ነበር ፡፡ ዮሐ (5፡ 16-23) ሁሉም አባቱን(አብን) እና ልጁን ስለ ማክበር ናቸው ፤ እነዚህ ጥቅሶች ከአብ እና ልጁ ወደ ህይወት እና ፍርድ እንደ ሽግግር ያገለግላል ፡፡ ለዮሐንስ መፅሀፍ ሐረጉ የእግዚአብሄር ልጅ ነው ፡፡

ትምህርት

ዮሐንስ (5፡ 30)፡ ይህ የመሸጋገሪያ ጥቅስ ነው ፤ ዶር. ቶም ኮንስታብ የፃፈው “ የኢየሱስ ሀሳብ ከአባቱ ዉጪ ማንኛዉንም ነገር ማድረግ አለመቻሉ ነበር (በራሱ መነሳሳት ) ለእርሱ ባለዉ መታዘዝ ምክንያት (የራሴን ፍቃድ አልፈልግም ) ፤ ፍርዱ ወደ አባቱ (አብ) የማዳመጥ ዉጤት ነው ፤ ፍርዱ ትክክል ነዉ ምክንያቱም ለራሱ ክብር ፍላጎቱ አይሸትም (አይበክልም) ፤ የልጁ ፈቃድ(ፍላጎቱ) ሙሉ በሙሉ የአባቱ ፈቃድ ለማሻሻል (ለመቅደም) ነው ፡፡” ስለ ልጁ የአባቱ ምስክርነት አለላችሁ ፤ እግዚአብሄር “ ልጄ ነው ! በእርሱ ደስ የሚለኝ “ አለ አባቱ (አብ) የክርስቶስን ማንነት ለማረጋገጥ ከሰዎስቱ አንዱ ምስክር ነው ፡፡ ዘዳ (19፡ 15) ለማንኛዉም ቅሬታ እዉነት እንደ ሆነ ለመመልከት ሁለት ወይም ሰዎስት ምስክሮች ለማረጋገጥ ያስፈልጉ ነበር ፡፡

ዮሐንስ (5፡ 31-32)፡ ኢየሱስም “ እኔ ስለ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እዉነት አይደለም “ (ቁጥር 31) ፤ ይህ ከዮሐ (8፡ 14) ጋር ይፃረራል ? ይሆናል ብዬ አላስብም ፡፡ በዮሐ (8፡ 14) ኢየሱስ ስለ ግሉ እዉቀት እያወራ ነበር እዚህ ኢየሱስ አብ ስለ ሚያዉቃቸዉ ነገሮች እየተናገረ ነበር ፤ ኢየሱስ ስለ እርሱ የሚመሰክር ሌላ አለ በሚል ጊዜ ስለ አባቱ (ስለ አብ ) እያወራ ነበር ፡፡

ዮሐንስ (5፡ 33-35)፡ የመጀመሪያዉ ምስክር መጥምቁ ዮሐንስ ነበር ፡፡ አስታዉሉ ኢየሱስ ለአይሁድ ኃይማኖት መሪዎች እያወራ ነበር ፤ ኢየሱስ ለቃለ ምልልሱ የኃያማኖት መሪዎች ከመጥምቁ ዮሐንስ ጋር የነበራቸዉን ጠቀሰ (ዮሐ 1፡ 7, 19) ፡፡ ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ማንነት እዉነት ተናገረ ፤ ኢየሱስ ህያዉ አምላክ ነበር ፡፡

ዮሐንስ ኢየሱስ እርሱን ሲቀርበዉ በመሰከረ ጊዜ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ ወዲያዉኑ አወቀ፡

  • ዮሐ (1፡ 29)፡ “ በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ እነሆ የዓለምን ኃጢዓት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ ፡፡ “
  • ዮሐ (1፡ 33)፡ “ እኔም አላዉቀዉም ነበር ዳሩ ግን በዉኃ አጠምቅ ዘንድ የላከኝ እርሱ መንፈስ ሲወርድበትና ሲኖርበት የምታየው በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እርሱ ነዉ አለኝ ፡፡ “
  • ዮሐ (1፡ 34)፡ “ እኔም አይቻለሁ እርሱም የእግዚአብሄር ልጅ እንደ ሆነ መስክሬአለሁ ፡፡ “

ኢየሱስ እነዚህ ኃይማኖት መሪዎች በወቅቱ በዮሐንስ ብርሀን ለመዝናናት ፍቃደኞች እንደ ነበሩ አመለከተ ፤ (መዝ 132፡ 17; 2ቆሮ 4፡ 7) ፡፡

ዮሐንስ (5፡ 36)፡ ሁለተኛዉ ምስክር የኢየሱስ ስራ ነበር ፡፡ “ የዮሐንስ መልካም ነበር ነገር ግን እኔ የተሸለ ምስክር አለኝ ! ስራዬን ተመልከቱ “ አለ ( ኢሳ 35፡ 5-6; ኢሳ 61; ሉቃ 4; ዮሐ 10፡ 25; ዮሐ 14፡ 11) ፡፡ በግልፅ የኢየሱስ ስራ በእርሱ በኩል ወደ አብን ስራ ያመለክታል ፡፡ ኢየሱስ የተለመዱ ቋንቋዎችን ሲጠቀም ነበር ፡፡

ዶር. ኮንስታብል የፃፈው “ እነዚህ ስራዎች ሁሉንም የኢየሱስን እንቅስቃሴዎች ያካትታሉ፡ ተዓምራቱን፣ በፍፁም መታዘዝ የሆነዉን ህይወቱን እና መስቀል ላይ ያለዉን የመዋጀት ስራዉንም ፤ ተዓምራቶች ብቻቸዉን የኢየሱስን አምላክነት አያረጋግጥም ሙሴ፣ ኤልያስ እና ኤልሳም በብዙ ተዓምራትን አድርገዉ ስለ ነበር ፤ ኢየሱስ ያደረገዉ ሁሉም ነገር በቀላሉ የአብ ስራ መስፋፋት ነበር (ቁጥር 19-30) “ ፡፡ ዮሐ (17፡ 4) “ እኔ ላደርገዉ የሰጠኸኝን ስራ ፈጽሜ በምድር አከበረርሁህ “ ፤ የምናደርገዉ ሁሉም ነገር ወደ ክርስቶስ ማመልከት ወይም መመስከር አለበት !

ዮሐንስ (5፡ 37-38)፡ ሰዎስተኛዉ ምስክር ራሱ አብ ነበር ፡፡ ዶር. ኮንስታብል የፃፈው “ ምናልባትም ኢየሱስ ማለት ለኢየሱስ የአብ ጠቅላላ ምስክርነት ማለት ሲሆን የሚያካትተው፡ ብሉይ ኪዳን ትንቢቶችን እና ትንቢታዊ ክስተቶችን እና ተቋማትን ጨምሮ - በኢየሱስ ጥምቀት ላይ የእርሱን ምስክርነት በማካተት “ ፡፡ በአብ እና በመፅሀፍ መካከል ልዩነት እንዳለ አምናለሁ ፤ ኮንስታብል የፃፈው “ ምናልባትም ኢየሱስ ማለት ስለ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ቅድመ መገለጥ ነው “ ፡፡ ዕብ (1፡ 1) የሚገልፀው “ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሄር በብዙ አይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ “ (ዘፍ 32፡ 30-31; ዘጸ 33) ፡፡

ዮሐንስ (5፡ 39-47)፡ የመጨረሻዉ ምስክር መፅሀፍት ነው ፡፡

ዮሐ (3፡ 34)፡ “ እግዚአብሄር የላከው የእግዚአብሄርን ቃል ይናገራልና ፤ እግዚአብሄር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥማን ፡፡ “

ዮሐ (17፡ 7-8)፡ “ የሰጠኸኝ ሁሉ ከአንተ እንደ ሆነ አሁን ያዉቃሉ ፤ የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና ፤ እነርሱም ተቀበሉት ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእዉነት አወቁ አንተም እንደ ላከኸኝ አመኑ ፡፡”

ሰዎስተኛዉ እና አራተኛው ምስክሮች በፍፁም በአንድ ላይ እንደ ሚሄዱ ማየት ትችላላችሁ ፤ እነዚህ ኃይማኖት መሪዎች ከክርስቶስ በሚበልጥ በመፅሀፍ ተስፋ እንደ ነበር አምነዋል ፡፡

የአይሁድ መሪዎች ወደ መፅሀፍት ፈሰሱ (1ቆሮ 8፡ 1) ፤ የክርስቶስን ፍቅር ማየት ካልቻላችሁ እዉቀታችሁ ዋጋ ቢስ ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የሚናገረው “ በአሁኑም ጊዜ በመፅሀፍት ማስተር(አዋቂ) የሆኑ አሉ ነገር ግን መፅሀፍት ማስተር (አዋቂ) እንዲያደርጋቸዉ አይፈቅዱም “ ፡፡ ኢየሱስ የሚፈልገው መፅሀፍን ከማንበብ በይበልጥ መፅሀፍ ቅዱስን ማክበርን(መረዳትን) ይፈልጋል (ያዕ 1፡ 22-25) ፡፡ ለእግዚአብሄር ፍቅር ሳይኖራችሁ ለምን መፅሀፍን ታነባላችሁ ?

ኢየሱስ “ ከሳሻችሁ(የሚወቅሳችሁ) ሙሴ ነው “ አለ ፤ ሙሴ ሁል ጊዜ ወደ እግዚአብሄር ልጅ ያመለክት ነበር ፡፡ እነዚህ ኃይማኖት መሪዎች ወደ ሙሴ ያዳምጡ አልነበረም ፤ በሙሴ አምነዉ በነበር በኢየሱስ ያምናሉ (ሉቃ 24) ፡፡ ኢየሱስ እነዚህ ሰዎች በእዉነት በእግዚአብሄር ቃል ከነበሩ የእግዚአብሄር ልጅ እንደ ነበር እንደ ሚያዩት አመለከተ ፡፡

መዝጊያ

ዋረን ዋይርስቤ “ የመፅሀፍ ቅዱስ እዉቀታችን ትልቅ እዉቀት ወይስ የሚቃጠል ልብ ይሰጠናል “ ብሎ ይጠይቃል ጳዉሎስ “ ሁላችን እዉቀት እንዳለን እናዉቃለን ፡፡ እዉቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንፃል “ (1ቆሮ 8፡ 1) በማለት አብራቷል ፡፡

ትልቅ እዉቀት ነዉ ያላችሁ ወይስ የሚቃጠል ልብ ? ስለ እዉቀት ከሆነ ስታችሁታል ፤ ሁሉም ነገር ስለ ልብ መቀየር ነው ፡፡ የዚህን መፅሀፍት ገፅታ የመፈተሸ ጊዜ ብቻ አለን ፡፡ ወደ እነዚህ ጥቅሶች ተመልሳችሁ በመሄድ እንድትቆፍሩ አበረታታችኋለሁ ፡፡

  1. Dr. Thomas Constable. Dr. Constable’s Bible Study Notes: John, p. 115; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/john.pdf.

  2. Constable, p. 117.

  3. Constable, p. 117.

  4. Constable, p. 117.

  5. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publications, 1999), p. 1326.

  6. Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2007), p. 224.

ጥያቄዎች

  1. ሰው የፈለገዉን እንደ ሚያገኙ ኢየሱስ ለምን እንደ ጠየቀ ምን ታስባላችሁ ? (ማቴ 7፡ 7)
  2. ኢየሱስ “ በመሄድ ክፉ የሆነ ነገር ሲያደርግ የባሰ ነገር በእርሱ ላይ ይመጣል “ ለምን አለ ? (ዘሌ 26፡ 23-24, ማቴ 12፡ 45)
  3. አባቱ ለልጁ ሁሉንም ፍርድ ለምን ሰጠው ? (ፊል 2፡ 5-10)
  4. ኢየሱስ “ ስለ እራሴ የምመሰክር ከሆነ ምስክርነቴ እዉነት አይደለም “ ለምን አለ ? (ዘዳ 19፡ 15, 2ቆሮ 13፡ 1)
  5. ኢየሱስ ሙሴ በአባቱ ፊት የሚከሳቸዉ እንደ ሆነ ለምን አላቸው ? (ዮሐ 5፡ 45)
  6. በዮሐንስ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin John 5:36

“I have testimony weightier than that of John. For the works that the Father has given me to finish—the very works that I am doing—testify that the Father has sent me.”

ዮሐንስ በፍርድ ቤት ውስጥ እንደነበረ እና ኢየሱስ እግዚያብሔር ወልድ በመሆኑ ከእግዚያብሔር አብ ጋር እኩል መሆኑን ለማሳየት በፍርድ ላይ እንደነበር አይነት ጽፏል፡፡ ኢየሱስ አራት ምስክሮች ለማያምኑት መግለጫቸውን እንዲሰጡ አድርጓል ፦ መጥምቁ ዮሐንስ፣ የኢየሱስ ስራዎች፣ የአባቱ ምስክርነት፣ እና መጻሕፈት፡፡ ሕዝቡ ምስክሮቹ እርሱ የዘላለም ህይወት ማስገኛ እንደሆነ የተናገሩለትን ኢየሱስን በማመን ወይም እርሱን በመካድ፥ አለማመንን በመምረጥ መካከል ምርጫ ነበራቸው፡፡ በጣም ብዙ ጊዜ ሕዝቡ፥ በኢየሱስ ዙሪያ ያሉትም እንኳን፥ አለማመንን መረጡ፡፡

እናንተ የኢየሱስ እውነት ምስክር ናችሁ፡፡ ኢየሱስ በህይወታችሁ ኃይሉን፥ ምህረቱን፥ ወይም ፀጋውን ሲገልጽ ስታዩ ፥ በዙሪያችሁ ላሉት አካፍሉት፡፡ ጌታን ለተመራቂ ተማሪ ገንዘብ እንዲያዘጋጅ ጠይቃችሁት ተአምራዊ በሆነ መንገድ ስኮላርሺፕ አዘጋጅቷል? ለአንድ ሰው ተናገሩ! ጌታን አዲስ ቤት ለመግዛት ጥበብን ጠይቃችሁት እርሱም ሰጥቷችኋል? ለስራ ባልደረቦቻችሁ ተናገሩ! አንድ ሰው እንድትፈወሱ ፀልዮላችሁ ተፈውሳችኋል? ሂዱ እና በማህበራዊ ድህረ ገጽ ላይ አካፍሉት! በጨለማ ውስጥ ጠፍታችሁ፥ ለኃጢያት እና ለአለም መንገድ ታስራችሁ ከዚያም በሕይወታችሁ የኢየሱስን ፍቅር እና ብርሃን ተቀብላችሁ አሁን በነጻነት እየተመላለሳችሁ ነው? አካፍሉት! ይህን በማድረግ ክብሩን ለእግዚያብሔር ትሰጣላችሁ! ኢየሱስን እና ኃይሉን እናም ክብሩን ሌላ ሰው እንዲያይ ትፈቅዳላችሁ! ደብቃችሁ ለራሳችሁ ብቻ ከያዛችሁት፥ በውስጣችሁ ላለው የእግዚያብሔር ኃይል ስጦታ ባላደራነትን ታጣላችሁ፡፡ ዛሬ፥ ሂዱ እና ኢየሱስ ያደረገላችሁን ፥ለሚሰማ ለማንኛውም ሰው፥ አውጁ፡፡ ህይወታችሁን ምን ያህል እንደነካው መስክሩ!

“እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክር የሚበልጥ ምስክር አለኝ፤ አብ ልፈጽመው የሰጠኝ ሥራ፥ ይህ የማደርገው ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራልና።”

— ዮሐንስ 5:36

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 71:15–16 – “ሥራን አላውቅምና አፌ ጽድቅህን ሁልጊዜም ማዳንህን ይናገራል። በእግዚአብሔር ኃይል እገባለሁ፤ አቤቱ፥ ጽድቅህን ብቻ አስባለሁ። ”
  • ማርቆስ 5:19 – “ኢየሱስም አልፈቀደለትም፥ ነገር ግን፦ ወደ ቤትህ በቤተ ሰዎችህ ዘንድ ሄደህ ጌታ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገልህ እንዴትስ እንደ ማረህ አውራላቸው አለው። ”
  • 1ኛ ዮሐንስ 5:11 – “እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 73