Jesus Fed the 5,000
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ደስ ብሎኛል ምክንያቱም ዛሬ የመጀመሪያዉን “ እኔ “ የሚለዉን ንግግር ስለ ምናጠና ፤ በወንጌላት ሰባት “ እኔ “ የሚሉ ንግግሮች አሉ ፡፡ በዮሐ (6፡ 35) ኢየሱስ “ እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ “ ባለ ጊዜ ምን ማለቱ እንደሆነ እንፈታዋለን ዛሬ የምናጠናቸዉ ፅሁፎች የቀሩትን ሰዎች እዉቀት የሚያክክ እና በእዉነት ክርስቶስን መከተል ይችሉ እንደ ሆነ የሚጠይቅ ጥቂት ጠንከር ያለ እዉነት ይይዛሉ ፡፡ ዮሐ (6፡ 1-21) ኢየሱስ ከህዝቡ እና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ላለዉ ቃለ ምልልስ መነሻ ያስቀምጣል ፡፡
ትምህርት
ዮሐንስ (6፡ 22-24)፡ዋረን ዋይስርቤ የፃፈው “ በዮሐንስ 6 ለጌታ ኢየሱስ የህዝቡን አራት መልሶች እናያለን፡ መፈለግ (ቁጥር 22-40)፣ ማጉረምረም (ቁጥር 41-51)፣ መራብ (ቁጥር 52-59) እና መለየት (ቁጥር 60-70) “ ፡፡ ከአንድ ትልቅ እግር ኳስ ጨዋታ በኋላ እንዳለ ትልቅ ዋንጫ በዚህ ጊዜ ከአንድ ትልቅ ተዓምራት በኋላ ሰዎች ወደ መቋመጥ ያዘነብላሉ ፡፡ ህዝቡ ኢየሱስን ማግኘት ባልቻሉ ጊዜ ወደ እርሱ መስመር ለመዉረድ ጀልባዎችቸዉን ወሰዱ ፤ ዕብ (11፡ 6) የዚህ መፈለግ ጭብጥ አለው ፡፡ እንደ ተከታይ በሁሉም ኢየሱስን የምንፈልግ መሆን ይጠበቅብናል ፤ (ኤር 29፡ 13) ፤ የህዝቡ ኢየሱስን የመቅረብ ይህኛዉ ፍላጎት መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነው (ምሳ 8፡ 17; ማቴ 6፡ 33) ፡፡
ዮሐንስ (6፡ 25-26)፡ ህዝቡ በመጨረሻም ኢየሱስን አገኙት ፤ ባገኙትም ጊዜ ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀመሩ ፡፡ በመጀመሪያዉ በኢየሱስ መልስ በቀጥታ ለድካማቸዉ(ለስስ ብልታቸዉ) ሄደ “ የተከተላችሁኝ ምክንያቱ ለእናንተ እንጀራ መስጠት እንደ ምችል ስላሰባችሁ ነው “ ፤ ዋይርስቤ የፃፈው “ ኢየሱስ ሁለት አይነት ምግቦች እንዳሉ አመለከተ፡ ጠቃሚ ስለሆነዉ ነገር በጣም ስለማያስፈልገዉ ለአካል የሚሆን ምግብ እና በጣም የሚያስፈልገዉን ለዉስጠኛዉ ሰዉ ለመንፈስ የሚሆነዉን ምግብ “ ፡፡
ዮሐንስ (6፡ 27)፡ ኢየሱስ “ ለሚጠፋ መብል አትስሩ ፤ ነገር ግን ለዘላለም ህይወት ለሚኖር መብል የሰዉ ልጅ ለሚሰጠው ስሩ አለ “ ፡፡ በጥናታችን ደግመን ደግመን እንዴት አብ ልጁን እየመሰከረ እንደ ነበር ማየት እየጀመርን ነው ፤ይህ ዘላለማዊ አስተሳሰብ ሊኖረን ያስፈልጋል (ማቴ 6፡ 20; 2ቆሮ 4፡ 18) ፡፡ ይህ ሁኔታ ዓይነተኛ ነበር - ህዝቡ ኢየሱስን ለተሳሳ መነሳሳት ፈለጉት ፡፡
ዮሐንስ (6፡ 28-29)፡ የህዝቡ አስተሳሰብ ይህ ነበር፡ ይህን ዘላለማዊ ምግብ ለመስራት እንድንለምድ ያሳየናል ፤ ዋይርስቤ የፃፈው “ ህዝቡ አገልጋይ የሚለዉን ቃል በማንሳት ለባርነት በማሳረት በተሳሳተ ተረድተዉታል “ ፤ (ኤፌ 2፡ 8-9) ፤ ኢየሱስም “ ይህ የእግዚአብሄር ስራ እንጂ የእናንተ ስራ አይደለም “ በማለት መለሰ ፤ እነዚህ ስራዎች ተፈፅመዋል ስለዚህ እንደ እግዚአብሄር ልጅ በኢየሱስ እናምናለን ( ዮሐ 14፡ 1; ሐዋ 16፡ 31) ፡፡
ዮሐንስ (6፡ 30)፡ ህዝቡም “ ስለዚህ ምን ምልክት ታደርጋለህ ? “ አሉ ህዝቡ ምልክቶችን እየፈለጉ ነበር ፤ (1ቆሮ 1፡ 22) ፡፡ ይህ ለምልክቶች ያለማቋረጥ መመልከት የአይሁድ ሰዎች የተለመደ አስተሳሰብ ነበር ፤ የ5000 ሰዎች መመገብን ምስክሮች ነበሩ እናም አሁን ደግሞ ሌላ ምልክት ፈለጉ ፡፡
ዮሐንስ (6፡ 31-32)፡ ሰዎቹ “ እግዚአብሄር ለአባቶቻችን መናን ከሰጠ ለምን አንተስ አትችልም (አትሰጠንም) ? “ ብለዉ ጠየቁ እያሉ የነበሩት ኢየሱስ መናን በመስጠት ሊያሳያቸዉ እንደሚያስፈልገዉ ነበር (መዝ 78፡ 24) ፡፡ መዝሙራትን እየዘረዘሩ ነበር ምክንያቱም በግልፅ ይህን ቀምሰዉት ስላልነበር ከአባቱ ይልቅ መና ከሙሴ እንደ ነበር እየገለፁ ነበር ፡፡
ዮሐንስ (6፡ 33)፡ “ ከሰማይ ወርዶ የመጣዉ “ የሚለዉ ሀረግ በዮሐንስ ወንጌል ብዙ ጊዜ የሚታይ ነው ፤ ኢየሱስ ለህዝቡ ያዩት የነበረዉ ይመጣ ስለ ነበረው እዉነተኛ ጥላ እንደ ነበር ኢየሱስ እያሳያቸዉ ነበር (ቆላ 2፡ 17) ፡፡ ኢየሱስ እያለ የነበረው ፍሬ ነገሩ መሲሁ እንደሆነ ነው ፡፡
ዮሐንስ (6፡ 34-36)፡ ህዝቡ “ ሁል ጊዜ ይህን እንጀራ ስጠን “ በማለት መለሱ ፤ በዮሐ (4፡ 15) ይህን ተመሳሳይ አስተሳሰብ የሚታይ ነው ፤ ህዝቡ ያስብ ከነበረዉ ጋር የሚመሳሰል ነው “ ይህ ታላቅ ይሆናል ! ለሌላ ተጨማሪ መሄድ አይጠበቅብንም “ ፡፡ ኢየሱስ “ እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ “ ባለ ጊዜ (ዮሐ 6፡ 35) በመፅሀፍ የመጀመሪያዉን “ እኔ “ የሚለዉን ተናገረ ፤ ይህ “ እኔ “ ከሚለዉ ንግግር አንዱ ነው ፡፡ ኢየሱስ “ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁል ጊዜ ከቶ አይጠማም “ እያለ ነበር ፡፡
ህዝቡ በእርሱ ለመምጣት ወደ ኢየሱስ መምጣት አስፈለጋቸዉ ፤ ዋይርስቤ የፃፈው “ ማመን ለሆነ አስተምሮ የአስተሳሰብ ስምምነት የሚሰጥ የምሁራዊ ዝም ብሎ ነገር አይደለም ፤ ማለትም ወደ ክርስቶስ ስትመጡ ለእርሱ ራሳችሁን ታኖራላችሁ ለት ነው “ ፡፡ ኢየሱስ እንደ ገና ራሱን ከእግዚአብሄር ጋር እያስተካከለ ነበር (ዘጸ 3፡ 14) ፤ ኢየሱስ “ አያችሁኝ ነገር ግን አለመናችሁም አለ “ ፤ የተቃወሰ ነገር ነዉን ? እርሱን እየፈለጉ ነበር ነገር ግን አላገኙትም ፡፡
ዮሐንስ (6፡ 37-40)፡ እነዚህ ጥቅሶች የግል ድነት ሂደቶች ናቸው ፡፡ አብ ኢየሱስን ለሁሉም ሰጠ ወደ ክርስቶስ የሚመጣ በፍፁም አይጣል(አይወጣም) ፤ የመለኮት ልዓላዊነት እና ግላዊ ሀላፊነት መቀራረብ የተመጣጠነ አቀራረብ አለ ፤ ይህን ለ16 ሳምንታት ለማድረስ(ለመፍታት) ችለናል ነገር ግን ሰዎች ክርስቶስን እንደ ፈለጉት የህይወት እንጀራ እንደሆነ እንዲረዱት ስለ መፈለጉ ማብራሪያዬ አልሄድንም !
ዮሐንስ (6፡ 41-45)፡ ህዝቡ ማጉረምረም ጀመሩ ፤ አሁን ይህ ድምፅ በብሉይ ኪዳን የአይሁዶችን ድምፅ ይመስላል ! ህዝቡም “ ከናዝሬት የማሪያም እና የዮሴፍ ልጅ ነዉ ፤ የህይወት እንጀራ አይደለም ፤ ጎረቤታችን ነው ! “ ብለዉ ተናገሩ ምክንያቱም ልባቸዉ ደንድኖ ስለ ነበር ሊያዩት አልቻሉም ፡፡ ኢየሱስ ማጉረምረማቸዉን እንዲያቆሙ ነገራቸው ፤ ከዚያም ማንም በአብ ካልመጣ በስተቀር ማንም ወደ እርሱ መምጣት እንደ ማይችል ደጋግሞ ተናገረ ፡፡ ነቢያቶች ወደ ተናገሩት ወደ ኃላ ለማመልከት ብሉይ ኪዳንን በመጠቀም ኢየሱስ ኢሳ (54፡ 13) ደግሞ እየተናገረ ነበር ፡፡
ዮሐንስ (6፡ 46-50)፡ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት አለው ፡፡ ኢየሱስ አባቶቻቸዉ መና በልተዉ እንደ ሞቱ አመለከተ ፤ ኢየሱስ “ አባቶቻችሁ ከነበራቸዉ መና እበልጣለሁ ፤ ለመጠየቅ(ለማጉረምረም) ድፍረት ቢኖራችሁም ! ስራዬ ከዚያ ይበልጣል “ በማለት ተናገረ ፡፡
ዮሐንስ (6፡ 51-56)፡ እንደ ገና ኢየሱስ ከሰማይ የወረደ የህይወት እንጀራ እንደሆነ ተናገረ ፡፡ ዋይርስቤ የፃፈው “ መና ምሽት ላይ ከሰማይ መጣ ኢየሱስ ደግሞ ኃጢዓተኞች በሀሳብ እና በመንፈስ ጨለማ ዉስጥ በነበሩ ጊዜ ወደዚህ ምድር መጣ ፤ መናዉ ትንሽ ነበር (ሰብዓዊነቱ)፣ ክብ የሚመስል ነበር (ዘላለማዊነቱ) እና ነጭ ነበር (ንፁህነቱን) “ ፡፡ ኢየሱስ ደግሞ ደግሞ እንደ ገና “ መስዋዕት ነኝ ፤ አሰተሰሪይ ነኝ “ እያለ እየተናገረ ነበር ፡፡ በዮሐ (3፡ 16) ኢየሱስ ለአለም ሞተ ፤ በዮሐ (15፡ 13) ኢየሱስ ለወዳጆቹ ሞተ ፤ በገላ (2፡ 20) ኢየሱስ ስጋዉን ሰጠ ስለዚህ ህይወት ሊኖረን ችሏል ፤ ይህ ቋንቋ ስለ ስጋ ለመረዳት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል ፡፡ አይሁዶች በግልፅ ያለማቋረጥ የቃሉን ትክክለኛ ትርጉም ከመረዳት በሚጠብቃቸው ነገር ኢየሱስን እየወሰዱ ነበር (ዮሐ 2፡ 19-21) ፡፡
ዮሐንስ (6፡ 57-62)፡ ኢየሱስ አስቸጋሪዉን(ጠንካራዉን) እዉነት እየገለፀ ነበር ከእርሱም ወደ ኋላ አልተመለሰም ፤ ያለማቋረጥ በአባቱ እና በልጁ መካከል ትስስር እያብራራ ነበር ፤ ኢየሱስ መልስ ነው ፡፡ እንዲሰሙ ተስፋ በማድረግ ኢየሱስ በመደጋገም ተናገረው ፤ ምክንያቱም እዉነቱ በጣም ጠንካራ ስለ ነበር ብዙ ደቀ መዛሙርቱን ጨምሮ ህዝቡ ተለዩ ፡፡
ዮሐንስ (6፡ 63-65)፡ ዋይርስቤ የፃፈው “ ኢየሱስ ቋንቋዉ ምሳሌያዊ እና መንፈሳዊ እንጁ ፅሁፍ እንዳልሆነ ገለፀ ፤ በስጋ ድነት የለም ፤ በእርግጥ በአዲስ ኪዳን ስለ ስጋ የሚለዉ መልካም ነገር አልነበረውም (ሮሜ 7፡ 18; ፊል 3፡ 3)”፡፡ በስጋ በራስ መተማመን ምግየት አትችሉም ፤ በእግዚአብሄር መንፈስ የሚሰራ ሁሉም ነገር አለ ፡፡ ያላመኑ ጥቂቶች እና ለመሳተፍ የማይፈልጉ ሰዎች አሉ ፤ አሁንም እንደ ገና ኢየሱስ ስለ እግዚአብሄር ሉዓላዊነት እና ስለ ሰዉ ምላሽ አወራ ፡፡
መዝጊያ
ኢየሱስ ሰዎቹ ወደ እርሱ እንዲመለሱ አስፈለገው ፤ ህያዉ ህይወትን ለክርስቶስ ማዋል የማይመች የኑሮ ስርዓት ነው ፤ ራሳችንን በመካድ መስቀልን የምናነሳ(የምንሸከም) ነን ፡፡ ፀሎታችን ከእኛ ማንም እንዳይለይ ነው ፡፡
Warren Wiersbe. The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2008), p. 249.
Wiersbe, p. 249.
Wiersbe, p. 249.
Wiersbe, p. 250.
Wiersbe, p. 251.
ጥያቄዎች
-
በዮሐ (6፡ 16-21) ደቀ መዛሙርቱ በጀልባ ወደ ቅፍርናሆም ሄዱ ነገር ግን ንፋስ በመምጣት የትም እንዳይደርሱ አስቸገራቸዉ(ፈተናቸው) ፤ ኢየሱስ በዉሃዉ ላይ በመራመድ ወደ እነርሱ በመምጣት ንፋሱን አረጋጋው ፡፡ በህይወታችሁ ችግር ገጥሟችሁ በነበረበት ቦታ ኢየሱስ በመታየቱ ነገሩ ሲቀየር ገጥማችሁ ነበር? ምሳሌ መስጠት ትችላላችሁ ?
-
በዮሐ (6፡ 25) ህዝቡ ኢየሱስን ባህሩ ዳርቻ ላይ ባገኙት ጊዜ እንዴት እዚህ መጣህ ብለዉ ጠየቁት ፤ በዮሐ (6፡ 26) ኢየሱስም ሌሎች ሲመግባቸዉ ስላዩ እንጂ ምልክትን ስላዩ እንዳልነበር መለሰላቸው ፡፡ ሰሰዎቹ የፈለጉት ለእነርሱ ማድረግ ስለ ሚችልላቸዉ እንጂ ለእርሱ ማድረግ ስለ ሚችሉት እንዳልሆነ ታዉቃላችሁ ?
-
ዮሐ (6፡ 51-58) ላይ አሰላስሉ ፤ ኢየሱስ እንዴት የህይወት እንጀራ ነው በዚህስ ለዘላለም እንዴት መኖር እንችላለን ? (ዘዳ 8፡ 3, ማቴ 4፡ 4)
-
12ቱን ሳያካትት ብዙ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርቶች እርሱን ለመከተል ሳይቀጥሉ በኢየሱስ ላይ ወደ ኋላቸዉ ለምን ተመለሱ ? (ዮሐ 6፡ 66) ፤ ኢየሱስን ከመከተል የተመሳችሁበት ጊዜ ነበራችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አልገጠማችሁም ?
-
በዮሐንስ 6 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin John 6:35
“‘I am the bread of life,’ Jesus told them. ‘No one who comes to Me will ever be hungry, and no one who believes in Me will ever be thirsty again.’”
ኢየሱስ አምስቱን ሺህ እንጀራ እና ዓሣ ከመገበ በኋላ፥ ሄደ፡፡ በቀጣዩ ቀን፥ ሕዝቡ ኢየሱስን ፈልገው ሄደው ከባሕር ማዶ አገኙት፡፡ ኢየሱስ ተአምር ሲያደርግ አይተው ከእግዚያብሄር ብዙ ስራዎችን ለማየት ተራቡ፡፡ ኢየሱስ አላቸው፥ " የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፡፡" የኢየሱስ ፈቃድ በእግዚያብሔር ልጅ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እና በእርሱ እንዲረካ ነው፡፡
ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ ከሆነ፥ ይህ ዛሬ ለእናንተ ምን ማለት ነው? እንጀራ ለአካላችን አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ በእንጀራ እና በውሃ ብቻ ለረጅም ጊዜ መኖር ትችላላችሁ፡፡ ልክ እንደ እንጀራ፥ ለዕለታዊ ኑሮ ኢየሱስ ያስፈልጋል፡፡ በዕየለቱ በኢየሱስ መሞላት አለባችሁ፡፡ በኢየሱስ ካልተሞላችሁ ግን፥ በሕይወት ውስጥ እርካታ አይኖራችሁም፡፡ ትራባላችሁ እናም ሕይወታችሁን በሌሎች ነገሮች ለመሙላት ትፈልጋላችሁ፡፡ ስለዚህ ዛሬ፥ በኢየሱስ ተሞሉ፡፡ ወደ እርሱ ዘወር በሉ፥ እርካታችሁን በእርሱ ብቻ አግኙ፥ እና ቃሉን አሰላስሉ፡፡ ስለ መልካምነቱ፥ ስለ ውበቱ፥ ስለ አቅርቦቶቹ አመስግኑት፡፡ ቀናችሁን በምታሳልፉበት ጊዜ ወደፊት የሚያጋጥማችሁን ማንኛውንም ነገር ለመጋፈጥ ከጌታ ጉልበት እንድታገኙ እርሱ እንዲሞላችሁ ፍቀዱለት፡፡ የዕለት እንጀራችሁ እርሱ ነው፡፡
“ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።”
—ዮሐንስ 6:35
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 107:9 — “የተራበችን ነፍስ አጥግቦአልና፥ የተራቈተችንም ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና። ”
- ዮሐንስ 6:40 — “ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።”
- የዮሐንስ ራእይ 7:16–17 — “ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፥ ከእንግዲህም ወዲህ አይጠሙም፥ ፀሐይም ትኵሳትም ሁሉ ከቶ አይወርድባቸውም፤በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፥ ወደ ሕይወትም ውኃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 74
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።