The Coming of the Holy Spirit to Dwell in Us
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትናትና ወደ ሰባቱ “ እኔ “ ወደ ሚሉት ንግግሮች መፈለግ ጀምረናል ፤ የመጀመሪያዉ “ እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ “ ነበር (በአለም ዉስጥ እንጀራ ዋና ምግብ ነው ) ስለዚህም ኢየሱስ የሚያስፈልገን ዋና እንደሆነ እያመለከተ ነበር ፡፡ በዮሐንስ 7 በመንፈስ ቅዱስ ላይ ትኩረት ለማድረግ በትንሹ ዞር እንላለን ፤ ዮሐ (7፡ 1-9) ወንድሞቹ ለኢየሱስ ሊነግሩት መሞከራቸዉ የቤተሰብ ኅይል ምንድን ማድረግ እንደ ሚያስፈልገው ያቀርባል ፡፡ በዮሐ (7፡ 10-24) ኢየሱስ በድብቅ ወጣ በዮሐ (7፡ 25-36) ደግሞ ሰዎች እንደ መሲህ የኢየሱስን ማንነት መጠየቅ ጀመሩ ፡፡ ለዳስ በዓል በኢየሩሳሌም 20 ማይል ዉስጥ ያለ አይሁዳዊ ቤተሰብ ሁሉ መገኘት ይጠበቅበታል(ያስፈልገዋል) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ በዓሉ ለሰባት ቀን እንደ ሚቆይ እና ሰዎቹም ከቅጠል እና ከቅርንጫፍ መጠለያ እንደ ሚሰሩ ይናገራል ፤ “ድግሱ እስራኤላዊያን በምድረበዳ የተንከራተቱዓቸዉን እና በድንኳን የኖሩዓቸዉን ቀናቶች ያስታዉሳል “ (ዘሌ 23፡ 40-43) ፤ ይህ እግዚአብሄር በምድረበዳ እስራኤላዊያንን እንደ ተንከባከባቸዉ እና ያ እግዚአብሄር ጥንቃቄ ማድረጉን እንደ ቀጠለ አይሁዶችን ለማስታወስ ነበር ፡፡
ትምህርት
ዮሐንስ (7፡ 37)፡ በቁጥር 37 አገላለፅ “ ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛዉ ቀን “ ምሁራን ሰባተኛዉ ቀን ወይም ስምንተኛዉ ቀን ላይ ነበር በማለት አልተስማሙም ፤ ኢየሱስ በመቆም ( ያስተምር እንደ ነበረው የተለመደ አልነበረም) “ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ !” ብሎ በታላቅ ድምፅ ተናገረ በበዓሉ በእያንዳንዷ ቀን ታላቁ ካህን እና ሰዎቹ በዘንባባ ቅርንጫፎች በመሰዊያዉ ዙሪያ በመሰብሰብ እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረዉን እዉቅና ለመስጠት ይመጣሉ ፡፡ ሌላዉ ካህን ከሲሎም ገንዳ በመጣ ዉሃ የወርቅ ማንቆርቆሪያዉን በመሙላት እንደ ቁርባን በመሰዊያዉ ላይ ከላይ ያፈስሰዋል ፤ ምናልባትም በዚያ ክስተት ላይ ኢየሱስ ለመናገር ቆመ ፡፡ ኮንስታብል የማንቆርቆሪያዉ ዉሃ በዉሃዉ በር በኩል የሚሸከም እንደ ነበር ይናገራል ፡፡ ካህኑ ዉሃዉን እያፈሰሰ ሌለኛዉ ካህን ደግሞ በመሰዊያዉ ላይ የወይን ቁርባን ያፈስሳል ፡፡ ዉሃው እግዚአብሄር በምድረበዳ የሰጣቸዉ ዉሃ መወከያ ነበር ወይኑ ደግሞ በመጨረሻዉ ቀን እግዚአብሄር መንፈሱን እንደ ሚልክላቸዉ ሰዎቹን ያሳስባቸዋል ፡፡ ህዝቡ መዝ (18፡ 1 እና 118፡ 5) በመጠቀም ምስጋናቸዉን ዘመሩ ፡፡
በዘጸ (17፡ 1-7) እግዚአብሄር ዉሃ ከአለቱ አፈሰሰ ፤ ቀይ ባህር ላይ በመገኘቱ እግዚአብሄር ከፈለው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ በድግሱ መጨረሻ ቀን ላይ የእስራኤላዊያንን በኢያሪኮ ዙሪያ መዞራቸዉን ለማስታወስ ህዝቡ በመሰዊያዉ ዙሪያ ሰባት ጊዜ እንደ ሚዞሩ ይገልፃል ፡፡ ብዙ ነገሮች እየተደረጉ ነበር…… ሰዎች ይዘምራሉ ቅርንጫፎችን ያወዛዉዟሉ፣ ካህናቱ ዉሃዉን እና ወይኑን ያፈስሳሉ በተመሳሳይ ጊዜም ይጓዛሉ ፤ ምናልባትም ካህኑ ዉሃዉን እያፈሰሰ ኢየሱስ የተጠሙትን ወደ እርሱ ጠራ ፡፡
ዮሐንስ (7፡ 38)፡ ኢየሱስ በእርሱ የሚያምን መፅሀፍ እንደ ሚል ከዉስጡ የህይወት ዉሃ ወንዝ እንደ ሚፈስ ገለፀ ፤ በመፅሀፍ ይህ የት ላይ ይናገራል ?
- ኢሳ (55፡ 1)፡ “ እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ ወደ ዉኃ ኑ ፡፡ “
- ኢሳ (12፡ 3)፡ “ ዉኃዉንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ ፡፡ “
- ዘኁ (24፡ 7)፡ “ ከማድጋዎቹ ዉኃ ይፈስሳል ዘሩም በብዙ ዉኖች ይሆናል ፡፡ “
ኢሳ (58፡ 11)፡ “ እግዚአብሄርም ሁልጊዜ ይመራሃል ፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል ፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት ዉኃዉም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ ፡፡ “
ኢየሱስ በመፅሀፍ ይህን መልክ - የእግዚአብሄር ዉሃ በፍፁም አይጠፋም ፡፡
ዘካ (14፡ 8)፡ “ በዚያም ቀን የሕይወት ዉሃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል ፤ እኩሌታው ወደ ምስራቁ ባሕር እኩሌታዉ ወደ ምዕራብ ባሕር ይሄዳል ፤ ይህ በበጋና በክረምት ይሆናል ፡፡ “
ይህ የሚጠበቀዉ ድግስ ተስፋ መፈፀም ጅማሬ ነው ፤ ዮሐ (4፡ 14) በፍፁም ስለ ማይጠፈዉ ከኢየሱስ የሆነዉን ዉሃ “ እንደ ምንጭ ዉሃ “ ይገልፀዋል ፡፡
ዮሐንስ (7፡ 39)፡ በቁጥር 39 ዮሐንስ ዉሃዉ መንፈስ ቅዱስ እንደ ሆነ ተናግሯል ፡፡ እግዚአብሄር በእነርሱ ዉስጥ እንደ ሚሆን ፤ ነገር ግን እስካሁን “ ኢየሱስ አልከበረም ነበር “ ማለትም ኢየሱስ አልተሰቀለም ወይም አልተነሳም ነበር ፡፡ እስከዚህ ጊዜ ለሆነ ጊዜእና ለሆነ ተግባር መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ላይ ይመጣል ነገር ግን በእነርሱ ዉስጥ አልኖረም (አላደረም) ፡፡ ለሆነ ወቅት ብቻ ነበር (ዘኁ 37፡ 15; ሕዝ 2፡ 2) ፤ ይሁን እንጂ በኢየሱስ የምታምኑ መንፈስ ቅዱስ በፍፁም አይተዋችሁም ! ትልቅ ማዕረግ ነው ፡፡ የማይደርቀዉ ወይም ሁል ጊዜ ስለ ሚወርደዉ የወንዝ ዉሃ የጉድጓዱ ስዕል መንፈስ ቅዱስ በዉሳጣችን የሚያድርብንም በፍፁም እንደ ማይተወን ያሳያል(ያጎላል) ፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ በፍፁም አማኞችን አይተዉም ፡፡ በ 1ቆሮ (12፡ 13) ከአንዱ መንፈስ እንድንጠጣ ተጠይቀናል፡፡ ኤፌ (1፡ 13-14) አማኞች “ በመንፈስ ቅዱስ እንደ ታተሙ “ እና መንፈስ ቅዱስ በዉስጣችን እንደ ሚሰራ ይገልፃል ፡፡
ይህ የዉሃ ስዕል በጣም አስፈላጊ ነው ፤ በሞቃት ቀን ላይ ከአንድ ብርጭቆ ዉሃ በላይ በጣም የሚያረካ ምንም የለም ፤ ዉሃ መቅዳት አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ጠቃሚ ነው ፤ ይህም ለእኛ በመንፋሳዊነት ጥሩ ስዕል ነው ፡፡
መዝጊያ
ኬንት ሁግስ እንዴት ከዚህ የህይወት ዉሃ እንደ ምንቀዳ ይገልፃል፡
መጠማታችንን እና ባዶነታችንን ልናዉቅ ይገባናል ፡፡
በእኛ ዉስጥ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ምንም እንደሌለን ማመን ያስፈልገናል ፡፡
ኃጢዓተኞች እንደ ሆንን ማመን ያስፈልገናል ፡፡
በየቀኑ የተሞላን እንድንሆን መጠየቅ ያስፈልገናል ፡፡
በዮሐ (7፡ 37) ኢየሱስ ማንም የተጠማ ቢኖር ለመጠጣት ወደ እርሱ መምጣት እንዳለበት ተናግሯል ፤ ይህ በዮሐንስ መፅሀፍ ገበታዉን ከእኛ በማዞር ሙሉ ለሙሉ ለክርስቶስ የሚያደርግ ዋና ጥቅስ ነው ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል በፍጥነት ህይወታችሁን ይቀይራል !
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1330.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes, p. 155; available at http://planobiblechapel.org/constable-notes/.
Radmacher, et al, pp. 1331–1332.
Constable, pp. 155-156.
Radmacher, p. 1332..
R. Kent Hughes, John: That We May Believe (Wheaton, IL: Crossway, 1999), n. p.
ጥያቄዎች
-
ስራዉ የታየ እንዲሆን ወንድሞቹ ኢየሱስን ወደ ይሁዳ እንዲሄድ ለምን ነገሩት ? (ዮሐ 7፡ 3)
-
በዮሐ (7፡ 34) እና በዘዳ (4፡ 29) መካከል ልዩነቶቹ ምንድን ናቸው ? በምንስ መንገድ ይለያያሉ ?
-
“ ከሆዱ የህይወት ዉሃ ወንዝ ይፈልቃል “ ባለ ጊዜ ምን ማለት ነው ? ይህን የህይወት ዉሃ እንዴት ታገኙታላችሁ ? (ዮሐ 7፡ 38)
-
በዮሐንስ 7 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin John 7:37–39a
“If anyone is thirsty, he should come to Me and drink! The one who believes in Me, as the Scripture has said, will have streams of living water flow from deep with him. He said this about the Spirit. Those who believed in Jesus were going to receive the Spirit.”
ሕዝቡ በዳስ በዓል መጨረሻ ቀን እንደተሰበሰቡ ሳለ፥ ኢየሱስ አላቸው፥ " ማንም የተጠማ ቢኖር፥ ወደ እኔ ይምጣ እና ይጠጣ! በእኔ ብታምኑ፥ የሕይወት ውሃ ወንዝ ከውስጣችሁ ይፈልቃል፡፡"
ኢየሱስ የጥማታችሁ መልስ ነው፡፡ ተክሎች ወሃ ሲፈልጉ ነገር ግን ምንም ካላገኙ ምን ይከሰታል? ይደርቃሉ እና በመጨረሻም ይሞታሉ፡፡ለአማኞችም መንፈሳዊ ሁኔታ ተመሳሳይ ነው፡፡ የሕይወት ውሃ ምንጭ የሆነውን ኢየሱስን ካልነካችሁት ትደርቃላችሁ፡፡ እየደረቃችሁ እንደሆነ እንዴት ታውቃላችሁ? ለጌታ ድምጽ ትደነዝዛላችሁ፡፡ ምናልባት የእናንተ ብልጭታ ዝንባሌዎች በፍጥነት ይገለጣሉ ወይም ዓይናችሁን በኢየሱስ ላይ ከማድረግ ይልቅ እርካታ ለማግኘት ወደዚህ ዓለም ነገሮች ዘወር ብላችሁ ራሳችሁን ታገኙታላችሁ፡፡ የሀዘን ስሜት ይሰማችሁ እና በደስታ ላትሞሉ ትችላላችሁ፡፡ አስታውሱ፥ በጌታ ፊት የደስታ ሙላት አለ፡፡ ወደ እርሱ ዘወር በሉ እና ጓደኛችሁ በኢየሱስ እንድትሞሉ እንዲፀልይላችሁ ጠይቁት፡፡ አሁን ጮክ ብላችሁ እንዲህ በሉ፥ "ኢየሱስ ከህያው ውሃህ በአዲስ መልኩ ሙላኝ! አሜን!"
“ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ። ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ”
—ዮሐንስ 7:37ለ–39ሀ
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘኍልቍ 24:7 — “ከማድጋዎቹ ውኃ ይፈስሳል፥ ዘሩም በብዙ ውኆች ይሆናል፥ ንጉሡም ከአጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል፥ መንግሥቱም ይከበራል። ”
- ትንቢተ ኢሳይያስ 58:11 — “እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ። ”
- 1ኛ ቆሮንቶስ 12:13 — “አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 75
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።