The Gospels John

I Am the Light of the Word

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 186 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዮሐንስ ዉስጥ ሰባት “ እኔ “ የሚሉ ንግግሮች አሉ ፤ እስካሁን አንዱን ብቻ ሸፍነናል፡ “ እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ “ (ዮሐ 6፡ 35) ፡፡ የዛሬዉ ፅሁፍ ሁለተኛዉን “ እኔ “ የሚለዉን ንግግር ያቀርባል ፤ ይህን ከማግኘታችን በፊት በዮሐ (8፡ 1-11) ላይ ኢየሱስ ለምን “ እኔ “ እንዳለ ጉዳይ ለመመስረት ያለን አንድ ታሪክ ላይ እንመለከታለን ፡፡

ትምህርት

ዮሐንስ (8፡ 1-3)፡ ኢየሱስ ከኢየሩሳሌም ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ኬብሮምን ሸለቆ አቋርጦ በመሄድ ምሽቱን በዚያ አሳለፈ (ቁጥር1) ፤ በማለዳም ኢየሱስ ወደ መቅደስ ተመለሰ “ ሁሉም ህዝቦች ወደ እርሱ እየመጡ ነበር “ (ቁጥር 2) ፤ ሁሉም ህዝብ ፡፡ ኢየሱስም ሊያስተምራቸዉ ተቀመጠ ፤ “ ከዚያም “ እየሆነ ለነበረዉ ነገር በምላሹ “ ፃፎች እና ፈሪሳዉያን “ ወደ ኢየሱስ መጡ (ቁጥር 3) ፤ ዮሐንስ ፃፎች እና ፈሪሳዉያንን በአንድ ላይ ከመዘገበባቸዉ ጥቂት ጊዜዎች ዉስጥ ይህ አንዱ ነው ፡፡ የዘሞተች ሴትን በኢየሱስ ፊት አመጡ (ቁጥር 3) ፤ የኔልሰን ማብራሪ የኢየሱስን ትምህርት ለመረበሽ እየሞከሩ እንደ ነበር ይናገራል ፡፡ ፃፎች እና ፈሪሳዉያና ስለ ኢየሱስ እየተከታተሉ ነበር፣ ለችግርም(ለአደጋ) እየተከታተሉ ነበር (ዮሐ 7፡ 45) ፤ ሴትየዋን በኢየሱስ ፊት በማምጣት በከካከል እንድትቆም አደረጓት ፡፡

ዮሐንስ (8፡ 4-5)፡ ፃፎች እና ፈሪሳዉያን ስለ ሴቲቱ ኃጢዓት በማብራራት የሙሴ ህግ በድንጋይ ተወግራ እንድትሞት እንደ ሚል ኢየሱስን አሳሰቡት (ቁጥር 4-5) ፤ ከዚያም ኢየሱስን ሴቲቱ ላይ ምንድን መደረግ እንዳለበት ምን እንደ ሚያስብ ጠየቁት (ቁጥር 5) ፡፡ ዮሐንስ ሁሉም አጋጣሚ (ክስተት) ወጥመድ እንደ ነበር ፅፏል (ቁጥር 6) ፡፡ በእዉነቱ ወጥመድ ብዙ ንብብሮች ነበሩት፡ ዘዳ (22፡ 23-24) አንዲት ወጣት የታጨች ድንግል ሴት ከአንድ ሰዉ ጋር ወሲብ ብታደርግ ሁለቱም ከከተማዋ በር በማዉጣት ተወግረዉ ይገደላሉ - እርሷ ስላልተጣራች እና እሱ የጎረቤቱነ እጮኛ ስለ ወሰደ ፡፡ ዘሌ (20፡ 10) የሚለው አንድ ሰዉ ከአገባች ሴት ጋር ዝሙት ቢፈፅም ሁለቱም እሱ እና ሴቲቱ በድንጋይ የሚወገሩ ይሆናሉ ፡፡ የዝሙት ድርጊት ሁለት ሰዎችን ይወስዳል ፡፡

ፃፎች እና ፈሪሳዊያን በዝሙት ድርጊት የያዟትን አንዲት ሴት ወደ ኢየሱስ አመጡዓት ነገር ግን ተሳትፎ የነበረዉን ወንድ ተዉት ፤ በሴቲቱ ላይ ብቻ ኢየሱስ ምን እንደ ሚያደርግ ጠየቁት ፡፡ ኢየሱስ አትዉገሯት ካለ ከህጉ ጋር ይፃረራል ነገር ግን ዉገሯት ካለ አይሁዶች ግድያ ማድረግ አልተፈቀደላቸዉም ከሚለዉ ከሮማዉያን ህግ በተቃራኒ ይሄዳል ፤ ኢየሱስ በማሸነፊያ ሁኔታ ዉስጥ አልነበረም ፡፡

ዮሐንስ (8፡ 6)፡ ይህን ጥያቄ ኢየሱስን ለማጥመድ እና በእርሱ ላይ ማስረጃ ለማግኘት ጠየቁት (ቁጥር 6) ፤ በምላሹ “ ኢየሱስ ግን ጎንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ፃፈ “ (ቁጥር 6) ፡፡ በቆሻሻዉ ላይ ኢየሱስ ምን እንደ ፃፈ አናዉቅም ነገር ግን አንዱ ጥርጣሬ አስዕርቱን ትዕዛዝ ዘጸ (20፡ 1-17) እየፃፈ እንደ ነበር ነው ፡፡ ዘጸ (31፡ 18) የሚለው “ እግዚአብሄርም ከሙሴ ጋር በሲና ተራራ የተናገረዉን በፈፀመ ጊዜ በእግዚአብሄር ጣት የተፃፈባቸውን ከድንጋይ የሆኑ ሁለቱን የምስክር ፅላቶች ሰጠው “ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ምናልባትም ህጉን በመፃፍ ኢየሱስ በምልክት የህጉ መምህር ሳይሆን የህጉ ሰጪ እንደ ሆነ እያለ እንደ ሆነ “ ያመለክታል ፡፡

ኤር (17፡ 13) ሌላ ሊሆን የሚችል ስዕል ይሰጣል፡ “ አቤቱ የእስራኤል ተስፋ ሆይ የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ ፤ ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ዉሃ ምንጭ እግዚአብሄርን ትተዋልና በምድር ላይ ይፃፋሉ “ ፤ ዮሐንስ 7 የህይወት ዉሃ ከእግዚአብሄር እንደ ሚመጣ የኢየሱስን ትምህርት የመዘገበዉን ፡፡ በቆሻሻዉ ላይ ኢየሱስ ስማቸዉን መፃፍ በመጀመሩ ምንድን ሆነ ? ዘጸ (23፡ 1) ሌላ ሊሆን የሚችል ነገር ያሳያል፡ “ ሐሰተኛ ወሬ አትቀበል ሐሰተኛ ምስክርም ትሆን ዘንድ ከኃጢዓተኛ ጋር እጅህን አታንሳ “ ፡፡

ዮሐንስ (8፡ 7)፡ ኢየሱስን መጠየቃቸዉን ቀጠሉ በዚህን ጊዜ ተነስቶ “ ከእናንተ ኃጢዓት የሌለበት አስቀድሞ ይወገራት አላቸው “ ፡፡ ኢየሱስ ህጉን ሰለ ሚያዉቅ ወደ እነርሱ በመመለስ ተጠቀመበት ፤ ጥፋተኛዋን በድንጋይ የሚወግሯት ከሳሾቹ አንዶቹ ይሆናሉ (ዘሌ 24፡ 14; ዘዳ 13፡ 9; 17፡ 7) ፡፡

የኔልሰን ማብራሪያ ኢየሱስ “ የሙሴን ህግ አላጠፋም ይልቁንስ ሴቲቱን ከሰዋት በነበሩት ኑሮ ላይ ህጉን ተገበረው “ ፤ ኢየሱስ ቃሉን ያዉቀዋል ምክንያቱም ቃል ስለሆነ ፡፡

ዮሐንስ (8፡ 8-10)፡ ከዚያም ኢየሱስ መሬት ላይ መፃፉን ቀጠለ (ቁጥር 8) ፤ ኢየሱስ እየፃፈ ፃፎች እና ፈሪሳዉያን አንድ በአንድ መሄድ ጀመሩ “ ከትልቁ ሰዉዬ በመጀመር “ (ቁጥር 9) ፡፡ “ ትልቅ(ሽማግሌዎች) “ የሚበልጥ የወቀሳ ዝንባሌ አላቸው - ወደ መንገድም ወረዱ ብዙም በመቅመስ ተማሩበት ፡፡ በመጨረሻም ኢየሱስ በመካከለ ቆማ ከነበረችዉ ሴት ጋር ቀረ (ቁጥር 9) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ ይህ ጠቅላላ መገናኘት “ በጥቁት ደቂቃ መሆን እንደ ቻለ “ አመለከተ ፡፡ አሁንም ቀድሞ በማለዳ ነበር ፤ ኢየሱስ በመነሳት የተከሰሰችዉን ሴት ጠየቃት “ የፈረደብሽ የለምን ?” (ቁጥር 10) “ ማንም የለም ጌታ ሆይ “ ብላ መለሰችለት ፤ ኢየሱስም “ እኔም አልፈርድብሽም …..ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢዓት አትስሪ አላት “ (ቁጥር 11) ፡፡ “ ኢየሱስ ይቅር አላት ፤ አልፈረደባትምም ነገር ግን ኃጢዓቷንም አልፈቀደላትም “ ፤ ይህ ማለት ኃጢዓት በሚኖር ጊዜ ይቅር ልንባል እንችላለን ነገር ግን ኃጠጊዓቱ ሊፈቀድልን አይችልም ፡፡

ዮሐንስ (8፡ 12)፡ ኢየሱስ ከረብሻዉ(ከመቋረጡ) በፊት ሲያስተምራቸዉ ለነበረው “ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ “ አላቸው ፡፡ “ የእኔ “ ጥቅም አባቱ ሙሴን “ እኔ እኔ ነኝ “ (ዘጸ 3፡ 14) ባለዉ ጊዜ ወደ ኋላ ኢየሱስን ያስተሳስራል ፡፡ ኢየሱስን የሚከተሉ በፍፁም በጨለማ አይሆኑም ነገር ግን “ የህይወት ብርሃን “ ይኖራቸዋል ፤ ቁጥር 12 በቁጥር 11 ምክንያት ትርጉም ይሰጣል ፡፡ “ ሂጂ ደግመሽ ኃጢዓት አትስሪ “ ማለት ከብርሃን ኋላ መጋዝ ማለት ነው ፤ ይህ ወዲያዉን ከመመለስ በኃላ እንደ ተካሄደ እናስታዉሳለን ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ፀሀይ በአካል የአለም ብርሃን እንደ ሆነች እንደዚሁም ኢየሱስ የአለም መንፈሳዊ ብርሃን ነው “ ፤ በዮሐ (8፡ 1-11) ኢየሱስ ኃጢዓትን ገለጠ ፡፡ በዮሐ (9፡ 1-9) አንድ አይነ ስዉር ሰዉ ተፈወሰ ምክንያቱም ኢየሱስ እይታ ስለ ሰጠው ፡፡ ኢየሱስ በእዉነት ኃጢዓትን ገለጠ ህይወትንም ሰጠ ፡፡

እስካሁን ሁለት “ እኔ “ የሚሉ ንግግሮች አይተናል፡ “ እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ “ እና “ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ “ ፤

ኮንስታብ በብሉይ ኪዳን ሁል ጊዜ ብርሃን ከእግዚአብሄር መገኘት ጋር የተገናኘ እንደ ነበር ይገልፃል፡

  • እግዚአብሄር ብርሃንን ፈጠረ (ዘፍ 1፡3; 14-19) ፡፡
  • እግዚአብሄር ራሱን ለሙሴ እንደ ነበልባል አሳየው (ዘጸ 3፡ 2) ፡፡

እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን በምድረበዳ በደመና እሳት መራቸው (ዘጸ 13፡ 21-22) ፡፡

እግዚአብሄር ለእስራኤላዊያን በሲና ተራራ ላይ በእሳት ተገለጠ (ዘጸ 19፡ 11) ፡፡

ኢሳ (49፡ 6) የሚለው “ የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሳ ከእስራኤልም የዳኑትን እንድትመልስ ባሪያዬ ትሆን ዘንድ እጅግ ቀላል ነገር ነውና እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼኃለሁ ይላል “ ፡፡ ኢየሱስ የኢሳ (49፡ 6) የሚያስተምረዉን በመቅደስ ያሉት ሁሉ ይሰማሉ ፤ በዳስ በዓል ጊዜ ካህናቱ ሰዎስት ትላልቅ መብራቶች በሴቲቱ ፍርድ ላይ የእግዚአብሄርን መገኘት ለማመልከት ያበራሉ ፡፡

መዝጊያ

ዮሐንስ ፈሪሳዉያን በኢየሱስ ላይ በተቃርኖ የቀጠሉትን አንድ ንግግር መዝግቧል ፤ ኢየሱስ “ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ “ (ቁጥር 12) ላለው ንግግር አላረጋገጠም ነበር በዚህም ምስክርነቱ እዉነት ነው ምክንያቱም ከየት እንደ መጣ እና ወዴት እንደ ሚሄድ ያውቃል (ቁጥር 14) ፡፡ ከዚያም ተከታታይ ጥያቄዎችን ጠየቁት፡

አባትህ የት ነበር ? ኢየሱስም በእዉነት አባቴን የምታዉቁት ቢሆን እርሱንም ደግሞ እንደ ሚያዉቁት መለሰላቸው (ዮሐ 8፡ 19-20) ፡፡

ኢየሱስ ራሱን ሊገል ነበር ? ኢየሱስ “ እኔ ከላይ ነኝ “ ከዚህ አለም አይደለሁም አለ (ዮሐ 8፡ 21-24) ፡፡

ኢየሱስ ማን ነበር ? ተናግሮት የነበረዉ ትክክል ነበር በተጨማሪም አባቱ እንዲናገር የነገረዉን ብቻ ይናገራል (ዮሐ 8፡ 25-29) ፡፡

እንዴት ነፃ ታደርጋለህ ? ሁሉም በእርሱ ነፃ መሆን እንደሚችሉ መለሰ (ዮሐ 8፡ 30-37) ፡፡

እነዚህ ሁሉ ኢየሱስን “ እኔ “ - እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ፣ እኔ የህይወት ዉሃ ነኝ የሚለዉን በማቅረብ - እኔ እግዚአብሄር ነኝ እንደ ማለት ነው ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1333.

  2. Nelson’s Commentary, p. 1333.

  3. Nelson’s Commentary, p. 1333.

  4. Nelson’s Commentary, p. 1333.

  5. Nelson’s Commentary, p. 1333.

  6. Nelson’s Commentary, p. 1333.

  7. Nelson’s Commentary, p. 1333.

  8. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes: John, p. 167; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/john.pdf.

ጥያቄዎች

  1. ኢየሱስ ራሱ የአለም ብርሃን እንደ ሆነ ተናገረ ፤ ወደ ኋላ ንጉሱን አግኝተዉ ለማምለክ የብርሃን ኮኮቡን ስለ ተከተሉት “ ሰብዓ ሰገሎች “ አስቡ ፤ ማቴ (2፡ 2, 9-11) ፤ በኢየሱስ መተግበር የሚቻለዉ የብርሃን ባህሪያት ምንድን ናቸው ? (ዮሐ 1፡ 4-5, 9)
  2. ብርሃኑን መከተል (ዮሐ 8፡ 12) በብርሃኑ ከመጓዝ ጋር ተመሳሳይ ነው ? (1ዮሐ 1፡ 7) ፤ በጨለማ መጓዝ ምንድን ይመስላል ? (ማቴ 6፡ 23, 8፡ 12, ዮሐ 3፡ 19, ሮሜ 13፡ 12-13, ኤፌ 5፡ 11-12, 1ዮሐ 2፡ 11)
  3. ፈሪሳዉያን ኢየሱስን “ማነህ ?” ብለዉ ጠየቁት ኢየሱስም “ ከመጀመሪያ ምንድን አልኳችሁ ?” በሚል ጥያቄ መለሰላቸው ስለ ራሱ ብሏቸዉ የነበረዉ ነገሮች ምንድን ናቸው ? (ዮሐ 3፡ 13-15, 4፡ 26, 5፡ 18,39፣ 6፡ 35, 8፡ 12)
  4. ኢየሱስን አምነዉ የነበሩት አይሁዶች በፍፁም በማንም ባሪያ እንዳልነበሩ አቀረቡ ፤ (ዮሐ 8፡ 33) ፤ በዘጸዓት በባርነት የነበሩት እስራኤላዊያን እነማን ነበሩ ? (ዘጸ 2፡ 23) ፡፡ ይህ ንግግር በሚካሄድበት ጊዜ በማን ቁጥጥር ስር ነበሩ ? ( ሉቃ 2፡ 1, 3፡ 1) ፤ በእስራኤል ታሪክ በሌላ በባርነት ስር ሆነዉ ያውቃሉ ? (2ነገ 17፡ 6, 2ነገስት 25 ) ፡፡ ኢየሱስ በምንድን ባሪያ እንደ ነበሩ ነገራቸው ? (ዮሐ 8፡ 34)
  5. ዮሐ (8፡ 30) ብዙዎች ወደ እርሱ ሊያምኑ እንደ መጡ ቢናገርም ቃለ ምልልሱ እንደ ቀጠለ ኢየሱስ አባታቸዉ ዲያብሎስ እንደሆነ ነገራቸው ( ማቴ 13፡ 38, ዮሐ 8፡ 44) ፤ በእርሱ ካመኑ ለምን እንደዚህ አላቸው ?( ዮሐ 3፡ 36, 8፡ 31, ,45፣ ሮሜ 10፡ 9, ያዕ 2፡ 19)
  6. በዮሐ (8፡ 58) ኢየሱስ “ ከአብርሃም በፊት እኔ ነበርኩ “ ባለ ጊዜ በትክክል ምን እያለ ነበር ? (ዘጸ 3፡ 14)
  7. በዮሐንስ 8 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin John 8:12

“I am the light of the world. Anyone who follows Me will never walk in darkness but will have the light of life.”

ኢየሱስ ለጸሐፍት እና ለፈሪሳውያን በቤተመቅደስ ግቢ ውስጥ ተናገረ፡፡ ፈሪሳዊያን አንዲት አመንዝራ ሴትን ወደ እርሱ ካመጡ በኋላ፥ ኢየሱስ የሌሎችን ኃጢያት እንዳይኮንኑ ወይም እንዳይፈርዱ ነገራቸው፡፡ ኢየሱስ ይህችን ሴት ሄዳ ከእንግዲህ ኃጢያት እንዳትሠራ ነግሯታል፡፡ ብዙም ሳይቆይ፣ ኢየሱስ ሁለተኛውን የ"እኔ ነኝ" መግለጫ ቃል አውጇል፡ " እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፡፡"

ኢየሱስ የዓለም ብርሃን ነው፡፡ ብርሃኑ በዓለም ላይ ላለ ለእያንዳንዱ ሰው ነው—ማንንም አይተውም፡፡ ኢየሱስ እየኮነናችሁ ወይም እየፈረደባችሁ አይደለም፡፡ የህይወት ብርሃናችሁ ሊሆን መጥቷል፡፡ ከኢየሱስ ጋር ከተራመዳችሁ፥በፍጹም በጨለማ ውስጥ አትሆኑም፡፡ እንዴት ያለ አስደናቂ የጌታ ቃል ኪዳን ነው!

ዛሬ፥ እየተከተላችሁት እና ብርሃናችሁ እንዲሆን እየፈቀዳችሁለት፥ ከኢየሱስ ጋር ተራመዱ፡፡ ጨለማ እየከበባችሁ እንደሆነ ከተሰማችሁ፥ ወደ ኢየሱስ ብርሃን ተጠጉ፡፡ አስታውሱ፥ ይወዳችኋል፡፡ ስለዚህ ዝም ብላችሁ አትቀመጡ! ከእርሱ ጋር ተራመዱ፡፡ ከዚያም ወደ ዓለም ሁሉ በመሄድ የኢየሱስን ብርሃን አብሩ!

“ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።”

—ዮሐንስ 8:12

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ትንቢተ ኢሳይያስ 49:6 — “እርሱም፦ የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የዳኑትን እንድትመስል ባሪያዬ ትሆን ዘንድ እጅግ ቀላል ነገር ነውና እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ይላል።”
  • ዮሐንስ 8:58 — “ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ”
  • 1ኛ ዮሐንስ 1:5–6 — “ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 76