The Gospels John

Born Blind and Then Healed

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 187 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

አሁን ስለ ሁለት “ እኔ “ ስለ ሚሉ ንግግሮች አዉርተናል፡ “ እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ “ (ዮሐ 6፡ 35, 48) እና “ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ “ (ዮሐ 8፡ 12) ፡፡ በዘጸ (3፡ 14) እግዚአብሄር “ እኔ እኔ ነኝ “ ባለዉ መሰረት ኢየሱስ እያብራራ ነበር ፤ ኢየሱስም “ እኔ “ እያለ ነበር ፡፡ በዮሐ (8፡ 12) ኢየሱስ አመንዝራይቱን ሴት በኃጢዓት እና በጨለማ ከዚህ በኋላ መቀጠል እንደ ማትችል ነገራት ፤ ምክንያቱም የሕይወት ብርሃን ስለ ሆነ ወደ ብርሃን መንገድ ስለ ወሰዳት ፡፡ በዮሐንስ 9 አራት የተለያዩ መግለጫዎች ወይም የኢየሱስ ጭብጦች(ቁም ነገሮች) ብዙ የፈዉስ ቁም ነገሮች ናቸው፡፡

ትምህርት

ዮሐንስ (9፡ 1-5)፡ በቁጥር 11 ዋይርስቤ “ አንድ ሰዉ ኢየሱስን ጠራው “ የሚለዉን የሹመቱን ጥቅም አመልክቷል፡፡ ኢየሱስ በአጠገቡ ሲጓዝ አንድ እዉር ሰዉ አየ (ቁጥር 1) ፤ በየቀኑ በሰዎች አጠገብ ስናልፍ በርህራሄ ልናያቸዉ ያስፈልጋል ፡፡ ኢየሱስ ለሰዉዬዉ ርህራሄ ነበረው እኛም ተመሳሳይ እንድናደርግ ተጠርተናል (ፊል 2፡ 4) ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ለእዉርነቱ መንስኤዉ የእርሱ ወይስ ቤተሰቦቹ ኃጢዓት ሰርተዉ ነበር በማለት ኢየሱስን ጠየቁት (ቁጥር 2) ፤ ደቀ መዛሙርቱ ሰዉዬዉን እንደ ተቸገረ ሰዉ አላዩትም ነገር ግን እንደ ስነ መለኮታዊ እዳ እንጂ ፡፡ አንዱ ዋና ቁም ነገር ሁለቱም ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስም ሰዉዬዉን ማየታቸዉ ነው ነገር ግን የኢየሱስ ምላሽ ለአይነ ስዉሩ ሰዉዬ ሙሉ ለሙሉ ከደቀ መዛሙርቱ የተለየ ነበር (ኢዮ 4፡ 7-8) ፤ በቁጥር 3 ኢየሱስ እሱም ሆነ ቤተሰቦቹ ጥፋተኞች እንዳልነበሩ ነገር ግን ችግሩ የእግዚአብሄር ስራ በእርሱ የሚታይ እንዲሆን መጣ ብሎ መለሰ (ዮሐ 5፡ 36)፡፡ ቁጥር 4 “ ስለ ጨለማ መምጣትን “ ሀሳብ ያወራል ይህን በተሻለ በምዕራፍ (10-11) አገኘዋለሁ ፡፡ ኢየሱስ “ የዓለም ብርሃን እንደ ሆነ “ እንደ ገና ገለፀ (ቁጥር 5) ፡፡

ዮሐንስ (9፡ 6-7)፡ ኢየሱስ ጭቃ ለመስራት መሬት ላይ በመትፋት ጭቃዉን በሰዉዬዉ አይኖች ላይ አደረገው (ቁጥር 6) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ አፈር እና ምራቅ መቀላቀል ለአይን በሽታ ለመጠቀም የተለመደ ተግባር እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ ኢየሱስ እያደረገዉ የነበረው በሙሉነት እንደ ፍፁም አልታዬም ፤ ዋይርስቤ የሚያመለክተው ተጠቅሞ የነበረዉን አፈር “ እንደ ስጋ መልበስ ስእል ፤ እግዚአብሄር የመጀመሪያዉን ሰዉ ከአፈር አበጀው እንደ ትክክለኛም ሰዉ እግዚአብሄር ልን እንደ ላከው “ ፡፡ ዋይርስቤ አፈሩ ( ሰብዓዊነታችን) በምንፃት ወደ መለየት ለሚመራው መስኖ (ሕያዉ ዉሃ) ለሚያስፈልገው የቁጣ (የኃጢዓተኝነት) መንስኤ እንደ ሆነ ያመለክታል ፤ ይህ ለእኔ ትርጉም አለዉ (ይሰጣል) ምክንያቱም እንደ እግዚአብሄር ልጅ እኔ ማን እንደ ሆንኩ ማየት እችላለሁ ፡፡ በቁጥር 7 ኢየሱስ ሰዉየዉን “ ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው “ ፤ የሰሊሆም መጠመቂያ ማለት “ መላክ “ ማለት ነው ፤ ሰዉዬዉም በመታዘዝ ለመታጠብ ሄደ (አይኑን ሊያለማ) ከዚያም ማየት በመቻል ተመለሰ ፡፡

ዮሐንስ (9፡ 8-12)፡ እዉሩን ሰዉዬ እንደ ለማኝ ያዉቁት የነበሩት ሰዎች ባዩት ተገረሙ (ተደነቁ) ፤ ራሱ እንደ ነበር መጠየቃቸዉን ቀጠሉ እርሱም እራሱ እንደ ነበር መናገሩን ቀጠለ (ቁጥር 8-9) ፡፡ እንዴት አይኖቹ እንደ ተከፈቱ ጠየቁት (ቁጥር 10) እይታዉን ስለ መለሰለት “ ኢየሱስ ተብሎ ስለ ሚጠራዉ ሰዉዬ “ ነገራቸው (ቁጥር 11) ፤ ሰዎቹም ኢየሱስ የት እንደ ነበር ጠየቁት ሰዉዬዉም አላዉቅም አለ (ቁጥር 12) ፡፡

ዮሐንስ (9፡ 13-23)፡ በእነዚህ ጥቅሶች ኢየሱስ እንደ “ አንድ ነቢይ “ የሚታወቅ ሆነ ፤ ኢየሱስ በሰንበት ሰዉዬዉን ስለ ፈወሰው (ቁጥር 14) የሰዉዬዉ ወዳጆች ወደ ፈሪሳዉያን አመጡት (ቁጥር 13) ፡፡ ፈሪሳዉያን ተፈጥሮ የነበረውን ጠየቁት (ቁጥር 15) በተለይም በሰንበት ላይ ስለ ነበር ፤ ነገር ግን “ ኢየሱስ ከሰንበት የበለጠ ነገር ለሰዎቹ እያቀረበ እንደ ነበር አላወቁም - እዉነተኛ መንፈሳዊ እረፍት ከእግዚአብሄር ይመጣል (ማቴ 11፡ 28-30) “ ፡፡ ሰዉዬዉ ኢየሱስ አድርጎለት የነበረውን ነገራቸው ነገር ግን አንዳንድ ፈሪሳዉያን ሰንበትን ካልጠበቀ ኢየሱስ ከእግዚአብሄር ሊሆን እንደ ማይችል ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ አንድ ኃጢዓተኛ ሰዉ እንዴት እንዚህን ምልክቶች ወይም ተዓምራቶች ሊያደርግ ይችላል በማለት ይጠይቃሉ (ቁጥር 16) ፤ ይህ በኃይማኖት መሪዎች መካከል መለያየት ፈጠረ ፡፡ ፈሪሳዉያን ሰዉዬዉን ስለ ኢየሱስ ምን እንደ ሚያስብ ጠየቁት ኢየሱስ “ አንድ ነቢይ “ እንደ ነበር መለሰላቸው (ቁጥር 17) ፡፡

አይሆዶች አሁንም ሰዉዬዉን አላመኑትም ስለዚህም የሰዉዬዉን ቤተሰቦች ልጃቸዉ እዉር ሆኖ ተወልዶ እንደ ነበር እና እንዴት እንደ ተፈወሰ ጠየቁዓቸው (ቁጥር 19) ፤ ቤተሰቦቹም ሰዉዬዉን እንደ ልጃቸዉ ለዩ ነገር ግን እንዴት ተፈዉሶ እንደ ነበር እዉቀቱ አልነበራቸውም ፤ ፈሪሳዉያንን ሰዉዬዉ ስለ ራሱ እንደ ሚናገር ነገሯቸዉ ምክንያቱም ኢየሱስን እንደ መሲህ ከገለፁት ፈሪሳዉያን በምኩራብ እንዳይቀጡዓቸው ስለ ፈሩ (ቁጥር 20-23) ፡፡ በአሚሽ ማህበረሰብ ሁሉም መፅሀፍ ቅዱስ ለማንበብ ወይም በቡድን ለማጥናት ሲጀምሩ ኢየሱስን እንደ አዳኝ በማወጃቸው እሱ ወይም እሷ ከማህበረሰቡ ስለ መቀጣታቸው መስክሬአለሁ ፡፡ የዚህ የተፈወሰዉ ሰዉዬ ቤተሰቦቹ በምላሻቸዉ ሊቀጡ ስለ ሚችሉ በጣም ፈሩ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ በመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን ሰዎስት የዉግዘት ደረጃዎችን ዘርዝሯል፡ የ30 ቀን ዉግዘት ከሁሉም ሰዉ የተወገዘዉ ሰዉ ስድስት እርምጃ በመራቅ በሚቀመጥ ጊዜ ፤ የማያበቃ ጊዜ ዉግዘት የተወገዘው በአምለኮ ወይም ህብረት ላይ መገኘት አይችልም ፤ ወይም ደግሞ “ ለዘላለም ጨርሶ ማስወጣት “ ከእነርሱ ጋር ምንም ማድረግ ስራም እንኳን መስራት በማይችል ጊዜ ፡፡

ዮሐንስ (9፡ 24-34)፡ በእነዚህ ቁጥሮች ኢየሱስ እንደ “ እግዚአብሄር ልጅ “ የተጠቀሰ ነው ፡፡ ፈሪሳዉያን እንደ ገና ሰዉዬዉን ተፈጥሮ ስለ ነበረው በመጠየቅ ኢየሱስ ኃጢዓተኛ እንደ ነበር አቀረቡ (ቁጥር 24) ፤ ሰዉዬዉም “ እዉር ነበርኩ አሁን ማይት እችላለሁ “ በማለት መለሰ (ቁጥር 25) ፡፡ ስለ ዝርዝር ጠየቁት ሰዉዬዉም አላደመጣችሁኝምን በማለት መለሰላቸው (ቁጥር 26) ፤ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ለመሆን ፈለጋችሁን በማለት ጠየቃቸው (ቁጥር 27) ፤ እንደ አንድ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ሰዉዬዉን ቀለዱበት ነገር ግን የሙሴ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆኑ እና ኢየሱስ ከየት እንደ መጣ እንደ ማያዉቁ ተናገሩ (ቁጥር 28-29) ፡፡ ሰዉዬዉም ከየት እንደ መጣ የማያዉቁት ኢየሱስ አይኖቹን እንደ ፈወሰለት መለሰላቸው (ቁጥር 30) ፤ ሰዉዬዉ እዉር ሆኖ የተወለደ ማየት ሲችል ከዚህ በፊት ማንም አልነበረም ስለዚህም ኢየሱስ ከእግዚአብሄር መጥቷል (ቁጥር 31-33) በማለት ገለፀ ፤ ፈሪሳዉያን በምላሹ በጣም በመበሳጨት ወርዉረዉ አስወጡት (ቁጥር 34) ፡፡

ዮሐንስ (9፡ 35-41)፡ ዋይርስቤ በዮሐንስ 9 የመጨረሻዉ ርዕስ “ የእግዚአብሄር ልጅ “ እንደ ሆነ ያመለክታል ፤ ሰዉዬዉ ላይ ምን እንደ ተፈጠረ ኢየሱስ በሰማ ጊዜ “ ሲያገኘው አንተ በእግዚአብሄር ልጅ ታምናለህን ? “ (ቁጥር 35) ፤ ሰዉዬዉም የሰዉ ልጅ ማን እንደ ነበር ጠየቀዉ ፤ ኢየሱስም “ አይተኸዋል በእዉነትም ከአንተ ጋር እየተነጋገረ ነዉ አለው “ (ቁጥር 36-37) ፡፡ ስለዚህ አስቡ - ሰዉዬዉ ኢየሱስን ማየት የቻለበት ይህ የመጀመሪያ ጊዜዉ ነበር ፤ በሰዉዬዉ ህይወት ድነት ተካሄደ በአካላዊ ፈዉስም ጀመረ (ቁጥር 36) ፤ ኢየሱስም ለፍርድ ወደ አለም እንደ መጣ ተናገረ - በኃይማኖተኞች ላይ ያነጣጠረ ነበር (ቁጥር 37) - እዉሮች እንዲያዩ ለመፍቀድ እና የሚያዩ የማያዩ እንዲሆኑ ፡፡ አንዳንድ ፈሪሳዉያን ይህን በሰሙ ጊዜ የማያዩ እንደ ሆኑ ጠየቁ (ቁጥር 40) ፤ ኢየሱስም “ ዕዉሮችስ ብትሆኑ ኃጢዓት ባልሆነባችሁም ነበር ፤ አሁን ግን እናያለን ትላላችሁ ፤ ኃጢዓታችሁ ይኖራል “ አለ ፤ ያ ማለት አይኖቻቸዉ በኢየሱስ ላይ አልነበሩም ነገር ግን ኃይማኖተኝነትን ብቻ ያያሉ ማለት ነው ፡፡ ልባቸዉ ደንድኖ እንዲሁም አይኖቻቸው ተከድነዉ ነበር ፡፡

መዝጊያ

ለመዝጋት ስለ ፈዉስ ማዉራት እፈልጋለሁ ፡፡ ኃይማኖተኛዉ ማህበረሰብ እዉር ሆኖ ለተወለደዉ ሰዉዬ ኢየሱስ የሰጠዉን እይታ የሚመስል ነገር በፍፁም አላዩም ፤ በዚህም በነገሩ ወደ ኃላ ተሳቡ ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን የምናደርገዉ ተመሳሳይ ነገር ነው - ምቹ ከማያደርጉን ነገሮች ወደ ኃላ እንሳባለን ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የኢየሱስ የፈዉስ ተዓምራቶችን እነዚህን ባህሪያት ያጋራል፡

  • የኢየሱስ የተዓምራት ፈዉሶች መለኮታዊ ኃይሉን ገልቷል ፡፡
  • ከሁሉም የህይወት እንቅስቃሴ ሰዎችን ፈዉሷል - ሀብታምን፣ ድሃን እና የማይነኩትን ፡፡
  • ሁሉንም ሰዉ አልፈወሰም ፡፡
  • በአዛኝ ምልክቶች እንዲሁም በመንፈሳዊ አዉስቷል (ተግባብቷል) ፡፡
  • ታመዉ በነበሩት ትዕግስት፣ ርህራሄ እና ጀግንነት አሳይቷል ፡፡
  • በሌላ በምን ሳይሆን የእግዚአብሄርን ኃይል በመጠቀም ፈዉሷል ፡፡
  • አንዳንድ ጊዜ በህመሞች እና በመንፋሳዊ ፍላጎቶች መካከል ተመሳሳይነት ነበር ፡፡
  • አንዳንድ ጊዜ ፈዉስን ከእምነት እና ከምህረት ጋር አያይዞታል ፡፡
  • ሁሉም ህመሞች የእግዚአብሄር ፍርድ ብቻ ሳይሆኑ የእግዚአብሄር ክብር እንዲመጣ የነበሩ እንደ ነበር ያውቃል ፡፡
  • በመንገዱ ላይ የኃይማኖት ልምዶች ለማግኘት አልፈቀደም ፡፡
  • በማንኛዉም ሁኔታ ለመፈወስ ኃይል ነበረው ፡፡
  • ለመፈወስ የነበረዉ ያ ኃይል ለተከታዮቹ ተሰጥቷል ፡፡
  • የኢየሱስ ተከታዮች ከህመም ነፃ አይደሉም ፡፡
  • በመጨረሻም ህመም እና ሞት አይሆንም (ራዕ 21፡ 4) ፡፡
  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 324.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1336.

  3. Wiersbe, pp. 324–325.

  4. Wiersbe, p. 325.

  5. Wiersbe, p. 325.

  6. Wiersbe, p. 325.

  7. Nelson’s Commentary, p. 1337.

  8. Wiersbe, p. 325.

  9. Wiersbe, p. 326.

ጥያቄዎች

  1. እዉሩ ሰዉዬ ተፈወሰ በዚህም የእግዚአብሄር ስራ በእርሱ ታዬ (ተገለጠ) ፤ (ዮሐ 9፡ 3) ፤ የእግዚአብሄርን ስራ መግለጥ(ማሳየት) አላማዉ ምን ነበር ? (ዮሐ 6፡ 29, 10፡ 25, 37-38) ፤ በእነዚህ “ ስራዎች “ ምክንያት በኢየሱስ ያመነ ነበር ? (ዮሐ 6፡ 14, 9፡ 16, 31-33, 10፡ 41-42)
  2. በዮሐ (9፡ 4) ኢየሱስ “ ማንም ሊሰራበት የማይችል ሌሊት ይመጣል “ በማለቱ ምንድን ማለቱ ነበር ?
  3. ቀድሞ አይነ ስዉር የሆነ ሰዉ እግዚአብሄር ኃጢዓተኞችን እንደ ማይሰማ ተጠቅሷል (ዮሐ 9፡ 31) ፤ በዚህ ላይ በምን የተመሰረተ ሆነ ? (መዝ 66፡ 18) ፤ በዮሐ (9፡ 24) ፈሪሳዉያን ኢየሱስ ኃጢዓተኛ እንደ ነበር ለማወቅ ጠየቁ ፤ ምንድን ኃጢዓት ፈፅሟል ብለዉ ነበር ያመኑት ? (ዮሐ 10፡ 33)
  4. ዮሐንስ 9 ኢየሱስ በፈወሰዉ አንድ እዉር ሰዉ ሲጀመር “ በማየቱ “ በጠየቁት በፈሪሳዉያን ይጨርሳል ፤ በዮሐ (9፡ 39) “ የሚያዩ እንዳያዩ “ የሚለዉን የኢየሱስን ንግገር እንዴት ትገልፁታላችሁ ?
  5. በዮሐንስ 9 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin John 9:1

“As He was passing by, He saw a man blind from birth.”

ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር እየተራመደ ሳለ በዓይነ ሰውር ሰው በኩል አለፈ፡፡ ኢየሱስ ሰውየውን በአካላዊውም በመንፈሳዊውም አይቶታል፡፡ ኢየሱስ ቆም ብሎ፥ ከሰውየው ጋር አወራ፥ እና ፈወሰው፡፡ አሁን ዓይነ ስውሩ ከተወለደ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል ማየት ችሏል፡፡ ይህ አካላዊ ፈውስም ሰውየው የኢየሱስን ኃይል እና ርህራሄ እንዲያይ አስችሎታል፡፡ ሰውየው ስለ ኢየሱስ መሰከረ፥ እንዲህ ብሎ ጠራው፥ " ኢየሱስ፥ነብይ፥ ጌታ እና የሰው ልጅ፡፡" ዓይነ ስውሩ ኢየሱስን እንደ ጌታው እንዲያይ መንፈሳዊ ዓይኖች ተሰጡት፥ እናም ሰገደለት፡፡

ኢየሱስ ዓይነ ስውሩን አይቶ እርምጃ ወሰደ፡፡ ራሳችሁን ጠይቁ፡ ሰዎችን አያለው ወይስ ሰዎችን እመለከታለው? መመልከት አንድ አፍታ ብቻ ሊወስድ ይችላል፡፡ እንደ ኢየሱስ ሰዎችን ማየት ሁኔታውን መገንዘብ፥ መራራት፥ እና እርምጃ መውሰድን ይጠይቃል፡፡ ይህ ዓለም ሥራ የበዛበት እና በፍጥነት የሚራመድ ነው፡፡ እንደ ኢየሱስ ሰዎችን ለማየት ጊዜ ያለው ማን ነው? የምትሰሯቸው ሥራዎች እና የምትሄዱባቸው ቦታዎች አሏችሁ! ዛሬ፥ መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን ለማየት ዓይኖቻችሁን እንዲከፍት እና መውሰድ ያለባችሁን እርምጃ እንድትገነዘቡ እንዲረዳችሁ ጠይቁት፡፡ እርምጃ በመውሰድ፥ በአካላዊ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ለእነርሱ ያለውን ፍቅር ለማየት ዓይኖቻቸውን በመክፈት በመንፈሳዊውም ልትረዷቸው ትችላላችሁ፡፡ በኢየሱስ በማመን የምታገኙትን ሰዎችን የማየት ፀጋ እና ጥንካሬ በእምነት ተቀበሉ፡፡

“ሲያልፍም ከመወለዱ ጀምሮ ዕውር የሆነውን ሰው አየ።”

—ዮሐንስ 9:1

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 119:18 — “ዓይኖቼን ክፈት፥ ከሕግህም ተኣምራትህን አያለሁ።”
  • መዝሙረ ዳዊት 146:8 — “እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሣል፤ እግዚአብሔር ዕውሮችን ጥበበኞች ያደርጋቸዋል፤ እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል”
  • ማቴዎስ 13:13–15 — “ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ እየሰሙም ስለማይሰሙ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ። መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም። በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።"

’”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 77