The Door of the Sheep — The Good Shepherd
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዮሐንስ 7 ኢየሱስ ስለ እግዚአብሄር መንፈስ ማዉራት ጀምሯል ፤ በትክክል ይህ ትምህርት ሴረዉን ማነሳሳት ጀምሯል ፡፡ ኢየሱስ “ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ ፤ …. የሕይወት ዉሃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል አለ “ (ዮሐ 7፡ 37-38) ፤ እዚህ ላይ ኢየሱስ ኃይማኖትን ሳይሆን ግንኙነታቸዉን ማብራራት ጀመረ ፡፡ ፈሪሳዉያን እና ሰዱቃዉያን ኢየሱስ በሚናገር ጊዜ ያጠኑት ሁሉም ነገር ወደ እርሱ ማመልከቱን አልወደዱትም ፡፡ ኢየሱስ ሰዎችን በኃይማኖት መሪዎች በስህተት የተመሩ እንዳይሆኑ ነገር ግን እርሱን እንዲከተሉት ጠራቸው ፤ ከዚያም ኢየሱስ ሁለት ተጨማሪ “ እኔ “ የሚሉ ንግግሮች አደረገ ፡፡
ትምህርት
ዮሐንስ (10፡ 1)፡ “ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ ሁሉ …እርሱ ሌባም ወንበዴም ነው “ ፡፡ ስለ በጎችን እና ስለ እረኛን ይህን መልክ(ስዕል) እናውራ ፤ ኢሳ (56፡ 9-12)የእስራኤል መሪዎችን ይኮንናል(ያወግዛል)፡ “ የእስራኤል እረኞች እዉሮች ናቸው… ማንቀላፋትም ይወድዷሉ ፤ ኃይለኛ ፍላጎት አላቸው …..ያስተዉሉ ዘንድ የማይችሉእረኞች ናቸው ፤ ሁሉ ወደ መንገዳቸው… እያንዳንዳቸዉ ወደ ጥቅማቸዉዘወር ብለዋል “ ፡፡ ስለ በጎቹ የማታስቡ እረኞች ከሆናችሁ ወደ በረት የሚገባዉን አትጠብቁትም ፤ ስለ ራሳችሁ ብቻ የምታስቡ ናችሁ ፡፡ ሕዝቅኤል 34 ለሁሉም ለዮሐንስ 10 እንደ መነሻ ያገለግላል ፤ ከመንጎቻቸዉ ይልቅ ለራሳቸዉ የሚጠነቀቁትን እረኞች እግዚአብሄር አዉግዞአቸዋል፡ “ ጮማዉን ትበላላችሁ ጠጉሩንም ትለብሳላችሁ የወፈሩትን ታርዳላችሁ ፤ በጎቹን ግን አታሰማሩም ፡፡ የደከመዉን አላጸናችሁትም የታመመዉንም አላከማችሁትም የተሰበረዉንም አልጠገናችሁትም የባዘነዉንም አልመለሳችሁትም የጠፋዉንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቆናም ገዛችኋቸው ፡፡ እረኛም በማጣት ተበተኑ ….በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ተቅበዝብዘዋል…..የሚሻም የሚፈልግም አልነበረም “ (ሕዝ 34፡ 3-6) ፡፡ የማይጠነቀቅ አንድ እረኛ በጎቹን ከሌባ ወይም ከዘራፊ አያድንም ፤ በተቃራኒዉ መዝሙር እግዚአብሄር ህዝቡን እንዴት እንደ ሚጠብቅ ይገልፃል “ እግዚአብሄር እረኛዬ ነዉ ማንም የሚያሳጣኝ የለም “ (መዝ 23፡ 1) ፡፡ ኢሳ (40፡ 11) የሚለው “ መንጋዉን እንደ እረኛ ያሰማራል ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል “ ፤ እነዚህ ጥቅሶች በኃይማኖት ሳይሆን በእግዚአብሄር ያለን ግንኙነት ይገልፃሉ ፡፡ በኤር (3፡ 15) እግዚአብሄር “ እንደ ልቤም በግ ጠባቆችን እሰጣችኋለሁ በእዉቀትና በማስተዋልም ይጠብቁአችኋል “ ፡፡ ለእናንተ የሚጠነቀቅ ምን አይነት እረኛ ትፈልጋላችሁ ?የኔልሰን ማብራሪያ ሌባ ፀጥ እና ዝግ ያለ እንደሆነ እና ወንበዴ(ዘራፊ) ደግሞ በጣም በመጮኽ እና በመረበሽ የሚቀርብ እንደ ሚሆን አመልክቷል ፡፡ በአንዱ መንገድ እረኛዉ ኃላችሁ(ጀርባችሁ) ነው ፡፡
ዮሐንስ (10፡ 2-3)፡ የበሩ ጠባቂ ለእርሱ ስለ ሚከፍትለት እረኛዉ በበረቱ በር ይገባል ፤ በጎቹን በስማቸዉ በመጥራት ይመራቸዋል ፤ ጥሪዉ ግላዊ (በግል) ነው ፡፡ እረኛዉ ሁልጊዜ በጎቹን በስማቸዉ ይጠራቸዋል ፤ መዝ (147፡ 4) የሚለው “ የከዋክብትንም ብዛት ይቆጥራል ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል “ ፡፡ በተጨማሪ ኢሳ (40፡ 26) እግዚአብሄር ሁሉንም ከዋክብት በስማቸዉ ይጠራቸዋል ይላል ፤ ይህ እረኛ ሁሉንም በጎች በስማቸዉ ይጠራቸዋል ፡፡
ዮሐንስ (10፡ 4-5)፡ “ ከበጎቹ ፊት ይሄዳል “ ፤ በምዕራብያዊያን ባህል እረኛዉ ከበጎቹ ኋላ ይሄዳል ብዙ ጊዜ ደግሞ በጎቹን ለመመለስ ዉሻ ይጠቀማሉ ፤ በምስራቃዊያን ባህል እረኛዉ ከፊት በመሄድ በጎቹን ይመራል ፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ እና ኢየሱስ ይህንን አደረጉ - እንድንከተላቸዉ ለእኛ መንገድን አዘጋጁ ፡፡ “ በጎቹ ይከተሉታል ምክንያቱም ድምፁን ስለሚያዉቁት “ ፤ በጎቹ በፍፁም እንግዶችን አይከተሉም ፤ ይልቁንስ ከእነርሱ ይሸሻሉ ምክንያቱም ድምፃቸዉን ስለማያዉቁት ፡፡ በመንፈስ ድምፁን እንዴት እናዉቀዋለን ? በእግዚአብሄር ቃል ስትሆኑ ፤ በእናንተ ዉስጥ ያለዉ የእግዚአብሄር መንፈስ መፅሀፍ ቅዱስን እንዳነበባችሁት ለእርሱ ይመልስለታል ፡፡
ዮሐንስ (10፡ 6)፡ ኢየሱስ ይህን የበግ እና የእረኛ ማሳያ(ገለፃ) ሰጣቸዉ ነገር ግን አልተረዱትም ፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ለመስማት እንዴት መማር ትችላላችሁ ? ለመከተል ሁልጊዜ ጡሩ ሞደል አላችሁ - እንደ ሰሙት እና እግዚአብሄርን እንደ ተከተሉት እንደትመለከቱ የፈቀደላችሁ ተቆጣጣሪ እንዴት ከእግዚአብሄር እንደምትሰሙ ለእናንተ ሞደላችሁ ነው ፡፡
ዮሐንስ (10፡ 7-8)፡ ኢየሱስ “ እኔ የበጎች በር ነኝ አለ “ (ቁጥር 7) ፤ ይህ የኢየሱስ “ እኔ “ የሚለዉ ሰዎስተኛዉ ንግግር ነበር (በዮሐንስ 10 ደግሞ የመጀመሪያው) ፡፡ “ ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው ፤ ዳሩ ግን በጎቼ አልሰሙአቸውም “ (ቁጥር 8) ፡፡ ምሽት ላይ እረኞች በጎቻቸዉን ለመከላከል ሰዉነታቸዉን ከበረቱ በር ፊት አለዉ ክፍት ቦታ ላይ ያስቀምጣሉ ፤ በጎቹን ምንም ሊያገኛቸዉ አይችልም ምክንያቱም እረኛዉ በበጎቹ እና በአደጋዉ መካከል ስለነበር ፡፡
ዮሐንስ (10፡ 9)፡ ኢየሱስ ንግግሩን ደገመ፡ “ እኔ በር ነኝ “ ፤ በጎቹን ያድናቸዋል ፡፡ መዳኛ የሚሆን ብቸኛዉ መንገድ ኢየሱስ ነው ፤ ኢየሱስ ይህን በዮሐ (14፡ 6) “ እኔ መንገድም፣ እዉነትም፣ ህይወትም ነኝ “በማለት ደገመው ፡፡ ኢየሱስ ብቸኛዉ ምርጫ ነው ፡፡
ዮሐንስ (10፡ 10)፡ “ሌባዉ ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም “ ፡፡ ሌባዉ ጣላት ነው፡ ሰይጣን እና ማናኛውም በጎቹን ለመጉዳት የሚፈልግ ሁሉ ፤ ጠላት ያለማቋረጥ ለመስረቅ፣ ለመግደል እና ለማጥፋት ይፈልጋል ፤ ነገር ግን ኢየሱስ በጎችን የተትረፈረፈ ህይወት ይሰጣቸዋል ፡፡ ቃል የገባዉን መትረፍረፍ እንድንቀምስ ይፈልጋል ፡፡
ዮሐንስ (10፡ 11)፡ “ እኔ መልካም እረኛ ነኝ “ ፤ ይህ የኢየሱስ አራተኛዉ “ እኔ “ ያለዉ ንግግር ነው (በዮሐንስ 10 ደግሞ ሁለተኛው) ፡፡ “ መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል “ ፤ ኢየሱስ ራሱን ሊሰጠን መጣ በዚህም ህይወት ሊኖረን ቻለ ፡፡ ይህን በጥልቀት እንቆፍረዉ እስኪ ፤ በ 1ዮሐ (3፡ 16) ዮሐንስ፡ “ እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አዉቀናል “ ፤ ለሌላ ሰዉ ኑሮአችንን ልንሰጥ ይገባናል ፡፡
ዮሐንስ (10፡ 12-13)፡ የኃይማኖተኝነት ስዕል ነው፡ “ …..ሞያተኛ ግን ተኩላ ሲመጣ ባዬ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል “ ፤ የኃይማኖት መሪዎች እነርሱን ከሚጠቅምበት ዉጪ አለምን ለማቅረብ እና ሰዎችን ለመዉደድ የሚፈሩ ያልጠኑ (ጫጮቶች) ነበር ፤ ስለ በጎቹ አይጨነቁም(አይጠነቀቁም) ፡፡
ዮሐንስ (10፡ 14-15)፡ እንደ ገና ኢየሱስ “ እኔ መልካም እረኛ ነኝ “ በማለት ንግግሩን ደገመው ፤ ሁለት ጊዜ ኢየሱስ በተመሳሳይ ምዕራፍ ሁለቱንም ንግግር አደረገ፡ እኔ በር ነኝ እና እኔ መልካም እረኛ ነኝ የሚለውን ፡፡ “ አብም እንደ ሚያዉቀኝ እኔም አብን እንደ ማዉቀው የራሴን በጎች አዉቃለሁ የራሴም በጎች ያዉቁኛል ነፍሴንም ስለ በጎቼ አኖራለሁ “ ፤ ኢየሱስ ራሱን ለእኛ እንዲታወቅ ያደርጋል ፡፡ ዋይርስቤ ያመለከተው፡ ኢየሱስ ስማችንን እንደ ሚያውቀው ፤ ጴጥሮስ ችኩል እንደ ነበር፣ ቶማስ ተጠራጣሪ እንደ ነበር እና ይሁዳ አሳልፎ እንደ ሚሰጠዉ እንዳወቀ ተፈጥሮአችንንም ያውቀዋል ፡፡ የሚያስፈልገንን ያዉቃል ምክንያቱም ስለ በጎቹ ሁሉንም ነገር ስለ ሚያውቅ ፡፡ ራሱን ለእኛ የሚታወቅ ያደርጋል በዚህም እርሱን መውደድ እና ድምፁን ማመን እንማራለን ፡፡
ዮሐንስ (10፡ 16)፡ “ ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ “ ፤ ሁሉንም በጎች በመቀበል በአንድ ላይ ያመጣቸዋል ፤ ይህ ለወንጌል እና ለድምፁ ምላሽ ለመስጠት እድል የነበራቸዉን አህዛብን ይገልፃል (ይጠቅሳል) ፡፡ በሮሜ (1፡ 16) ጳዉሎስ የፃፈው፡ “ በወንጌል አላፍርምና አስቀድሞ ለአይሁድ ደግሞም ለግሪክ ሰው ለማያምኑ ሁሉ የእግዚአብሄር ሃይል ለማዳን ነውና “ ፡፡ በኤፌ (2፡ 16) በአንድ እረኛ አንድ መንጋ ይሆናሉ፡ “ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸዉን በአንድ አካል ከእግዚአብሄር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው “ ፤ ክርስቶስ ይህን ስላደረገ አንድ እንሆናለን ፡፡ ገላ (3፡ 28) የሚለው “ አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰዉ የለም ባሪያ ወይም ጨዋ ሰዉ የለም ወንድም ሴትም የለም ፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰዉ ናችሁና “ ፤ ኢየሱስ ስለ ሁሉ ሞተ ፡፡ ይህ መንጋ ለአይሁዶች እና ለአሕዛቦች ማለት ነው ፤ 1ቆሮ (12፡ 13)፡ “ እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናል “ ፤ በኢየሱስ ያመኑት የክርስቶስ አካል ክፍል ናቸው ፡፡
ዮሐንስ (10፡ 17-18)፡ “ ነፍሴን ደግሞ አነሳት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል ፤ እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም “ ፤ እንደ ገና መደገሙን ተመልከቱ ? ኢየሱስ ህይዎቱን ለማኖር መርጧል በዚህም የተትረፈረፈ ህይወት ይሰጠናል ፡፡
መዝጊያ
ኢየሱስ ስለ በጎቹ በር በመሆን ህይወቱን ለመስጠት ፈቃደኛ የነበረ መልካም እረኛ ነው ስለሆነም ህይወት ይኖረናል ፤ ይህ የሚሰራው በዚያ ነው ፡፡ ይህን ኢየሱስ ለኃይማኖት መሪዎች ከገለጠ በኋላ መከፋፈል በአይሁዶች መካከል ሆነ ፤ ዉጥረቱ በኃይማኖተኞቹ እና ከእርሱ ጋር መገናኘት በሚፈልጉት መካከል ጨመረ ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1338.
John F. MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 1391.
Nelson’s Commentary, p. 1338.
Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 265.
ጥያቄዎች
-
ኢየሱስ ስለ ራሱ ያደረጋቸዉ ሰዎስት አዋጆች ምንድን ናቸው ?
-
አንድ እረኛ እንደ እዉነተኛ እረኛ እንዲታይ ማድረግ ያለበትን ኢየሱስ ምን አለ ? ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገቡት ሰዎች ምን እንደ ሚመስሉ ተናገረ ?
-
በዮሐ (10፡ 16) አየሱስ ተናግሮ የነበረው ስለ የትኛዉን “ መንጋ/ በረት “ ነበር ? ሌሎቹ በግች እነማን ነበሩ? (ኢሳ 42፡ 6, 56፡ 8, ኤፌ 2፡ 11-18)
-
መልካም እረኛ ስለ መሆን ኢየሱስ አብራርቷቸዉ የነበረዉ ብዙ ነገሮች ምንድን ነበሩ ? (ዮሐ 10፡ 11, 14-16, 17-18, 27-28)
-
በዮሐ (10፡ 31) አይሁዶች እንደ ገና ኢየሱስን ለመዉገር ለምን ድንጋይ አነሱ ? (ዘሌ 24፡ 16)
-
በዮሐንስ 10 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin John 10:7, 14–15
“Jesus said again, ‘I assure you: I am the door of the sheep . . . I am the good shepherd. I know My own sheep, and they know Me, as the Father knows Me, and I know the Father. I lay down My life for the sheep.’”
በዚህ ክፍል፥ በዮሐንስ መጽሐፍ ውስጥ ከሚገኙት ከሰባቱ የ"እኔ ነኝ" መግለጫዎች ኢየሱስ ሦስተኛውን እና አራተኛውን ተናገረ፦ "እኔ የበጎች በር ነኝ፣" እና "እኔ መልካም እረኛ ነኝ፡፡"
ኢየሱስ የመጣው ለሚያምኑት እና በእርሱ በኩል በመዳን በር ለሚገቡት የዘላለምን ሕይወት ሊሰጣቸው ነው፡፡ ሌላ ቦታ ማየት አያስፈልጋችሁም፡፡ በኢየሱስ ደጅ በኩል ኑ፡፡በበሩ ውስጥ፥ ስትመጡ እና ስትሄዱ ይጠብቃችኋል፡፡
ኢየሱስ መልካም እረኛ ነው፥ እንደ እረኛም ነፍሱን ስለእናንተ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ እረኛ እያንዳንዱን በጎች እንደሚያውቅ እና ወደ መሰማሪያው በረት እንደሚያመጣቸው ኢየሱስም ይወዳችኋል እናም ይንከባከባችኋል፡፡ እረኛ የጠፋውን በግ ፍለጋ እንደሚሄድ፥ ኢየሱስ እናንተን ፍለጋ ይሄዳል፡፡ ልባችሁን ክፈቱ፥ ማንኛውንም የተቃውሞ ወይም ያለመብቃት ስሜት አውጡ እና ፥ ዛሬ ፍቅሩን ተቀበሉ፡፡ ልክ እንደሆናችሁት እንደዚያው ይወዳችኋል፡፡ ፈጥሯችኋል፥ ያውቃችኋል፥ በስማችሁ ይጠራችኋል፡፡ ኢየሱስ እረኛችሁ እንዲሆን ፍቀዱለት እና በፍቅሩ እና በጥበቃው ዛሬ እረፉ፡፡ ምንም አይጎድላችሁም፡፡
“ ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ። . . . መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።”
— ዮሐንስ 10:7, 14–15
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 23:1 – “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። ”
- ትንቢተ ኢሳይያስ 43:1 – “አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ። ”
- የሐዋርያት ሥራ 4:12 – “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 78
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።