I Am the Resurrection and the Life
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ወደ ህይወት ተመልሰዉ ስለ መጡት ሰዎች አዉርተናል፡ በሉቃስ 7 የመበለቲቱ ወንድ ልጅ እና በሉቃስ 8 የኢያኢሬስ ሴት ልጅ ወዲያዉኑ ወደ ህይወት ተመለሱ ፤ ነገር ግን በዮሐንስ 11 በአልዓዛር ሞት እና ወደ ህይወት ተመልሶ በመጣበት ጊዜ መካከል ትንሽ የሚበልጥ ጊዜ ነበር ፡፡ በዮሐንስ ኢየሱስ በሆኑ ሰዎች ህይወት ላይ በፍፁም ያሳያቸዉ ሰባት ተዓምራቶች ነበሩ ፤ ኢየሱስ አልዓዛርን ወደ ህይወት ማስነሳቱ ከእነዚህ ተዓምራቶች ሰባተኛዉ ነበር ፡፡
ትምህርት
ማክአርቱር የአልዓዛር ትንሳኤ የኢየሱስን አምላክነት እንደ ሚያመለክት ተናግሯል ፤ ኢየሱስ ይህን በማድረግ አምላክ እንደ ነበር አሳዬ ፡፡ የደቀ መዛሙርቱን እምነት አጠነከረ ፤ በቀጥታ ወደ መስቀሉ መራቸዉ ምክንያቱም አንዳንድ ኃይማኖተኞች በትንሳኤዉ ስላላመኑ ፡፡
ዮሐንስ (11፡ 1-16) ደቀ መዛሙርቶቹ
ዮሐንስ (11፡ 1-3)፡ የቢታኒያዉ አልዓዛር ታሞ ነበር ፤ ( በሉቃስ 16 በአብርሃም ስፍራ ላይ የተቀመጠው ድሃዉ አልዓዛር አልነበረም) እህቱ ማሪያም በዘይት የኢየሱስን እግር በመቀባት በፀጉሯ የጠረገችዉ ነች ፤ በቢታኒያ ይህ ታዋቂ ቤተሰብ ነበር ፡፡ ማሪያም እና ማርታ አልዓዛር ታሞ እንደ ነበር ለኢየሱስ ቃል ላኩለት ፡፡ አስታዉሉ፡ በዚህ ጊዜ አልዓዛር አልሞተም ነበር ፡፡
ዮሐንስ (11፡ 4-7)፡ ኢየሱስም “ ይህ ህመም በሞት አያበቃም ነገር ግን ለእግዚአብሄር ክብር ነው “ ፤ ይህ ወደ ኢየሱስ አምላክነት አመልክቷል ፡፡ እነዚህ ክስተቶች እግዚአብሄርን ለማክበር ይካሄዳል ፡፡ ይህ ምዕራፍ 11 ቁልፍ ጥቅስ ነው እንጂ ለሁሉም የዮሐንስ መፅሀፍ አይደለም ፡፡ “ ኢየሱስም ማርታንና እህትዋን አልዓዛርንም ይወድ ነበር “ (ቁጥር 5) ፤ ይህ የኢየሱስን ርህራሄ እና ፍቅር ያሳያል ፡፡ አልሰማቸዉም ነበር ፤ ኢየሱስ ይመጣ ለነበረው በደረጃዉ ላይ ተቀምጦ ነበር ፤ “ በነበረበት ስፍራ ሁለት ቀን ዋለ “ (ቁጥር 6) ፤ ሁሉም ስለ እግዚአብሄር ጊዜ ነበር ፡፡ ቀን 1፡ መልዕክተኛዉ በአልዓዛር መታመም ዜና መጣ ፤ ቀን 2፡ መልዕክተኛዉ ወደ ቢታኒያ ተመለሰ ፤ ቀን 3፡ ኢየሱስ ቆዬ ፤ ቀን 4፡ ኢየሱስ በቢታኒያ ደረሰ ፤ ከዚያም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ይሁዳ መልሶ መራቸዉ ወደ አደጋ ተመለሱ ምክንያቱም በአይሁዶች ይጠላ ስለ ነበር ፡፡
ዮሐንስ (11፡ 8)፡ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ይሁዳ መመለስ ተቃወሙ ምክንያቱም አይሁዶች በዚያ ኢየሱስን ሊወግሩት ሞክረዉ ስለ ነበር ፡፡ ዮሐ( 8፡ 59) ላይ ተመልሰን ስንመለከት “ ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሱ “ ፤ ዮሐ (10፡ 31) ላይ ተመልሰን ስንመለከት “ አይሁድ ሊወግሩት ደግመዉ ድንጋይ አነሱ “ ፡፡ ደግሞ ደግሞ እንደ ገና ኢየሱስ በኃይማኖተኛ ሰዎች ጠቅልሎ በመግፋቱ ሊገድሉት ፈለጉ ፡፡
ዮሐንስ (11፡ 9-10)፡ እነዚህ ጥቅሶች ሁሉም ስለ ጊዜ ናቸው ፡፡ ዋይርስቤ፡ “ ኢየሱስ በመለኮታዊ የጊዜ ሰንጠረዥ ኖረ “ ብሏል ፡፡ በዮሐ (2፡ 4) ኢየሱስ “ ጊዜዬ ገና አልደረሰም አለ “ ፤ በዮሐ (7፡ 6-8) ኢየሱስ “ ጊዜ ገና አልደረሰም ….እኔስ ጊዜዬ ገና ስላልተፈፀመ “ አለ ፤ መቼ ጊዜዉ እንደ ሚመጣ ያውቃል ፡፡ ዮሐ (8፡ 20) የሚለው “ ጊዜዉ ገና አልደረሰምና ማንም አልያዘዉ “ ፤ ቆይቶም በዮሐ (17፡ 1) ኢየሱስ “ አባት ሆይ ሰዓቱ ደርሶአልና ፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ “ አለ ፡፡ በምሽት ስለ መደናቀፍ ለኢየሱስ ንግግር አስፈላጊ ነገር ነበር (ቁጥር 10) ? በማቴ (26፡ 47-49) ይሁዳ ኢየሱስን በምሽት ጨለማ አሳልፎ ሰጠው ፤ በማቴ (26፡ 57) ኢየሱስ በታላቁ ካህን፣ በፃፎች እና በሽማግሌዎች ፊት በምሽት ተመርቶ(ተወስዶ) ነበር ፡፡ እነዚህ ሁሉ ምሽት ላይ መካሄዳቸዉን እንዴት አወቃችሁ ? በማቴ (26፡ 74-75) ጴጥሮስ ኢየሱስን ሲክድ አዉራ ዶሮ ጮኸ ፤ ሁል ጊዜ አዉራ ዶሮዎች ፀሀይ መዉጫ ላይ ይጮኋሉ ፡፡ በመጨረሻም ማቴ (27፡ 1) የሚገልፀው “ ሲነጋም የካህናት አለቆች እና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ “ ፡፡
ዮሐንስ (11፡ 11-13)፡ “ ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቶአል ፤ ነገር ግን ከእንቅልፍ ላስነሳው እሄዳለሁ አላቸው “ ፤ ኢየሱስ ስለ ተፈጥሮአዊዉ እንቅልፍ እያወራ እንደ ነበር ደቀ መዛሙርቱ አሰቡ ፤ አለ አልዓዛር ትክክለኛ ሞት ኢየሱስ ያወራ ስለነበረው ፍንጭ አልነበራቸውም ፡፡ አዲስ ኪዳን እንደ ሚያሳዉቀው ሞት በኃይለኛነት ከእንቅልፍ ጋር ተወዳድሯል፡፡ በሐዋ 97፡ 60) እስጢፋኖስ ተወግሮ በሞተ ጊዜ ሉቃስ “ እንደ አንቀላፋ “ ብሏል ፡፡ በ 1ቆሮ (15፡ 51) ጳዉሎስ የፃፈው “ ሁላችን አናንቀላፋም ….ነገር ግን ….እኛም እንለወጣለን “ ፤ በ 1ተሰ (4፡ 13-17) ጳዉሎስ ያለው “ ያንቀላፉት….ቀድመዉ ይነሳሉ….. በአየር ላይ ጌታን ለመገናኘት “ ፡፡ ያንቀላፉ ወይም የሞቱ በጌታ ለመሆን ወደ ህይወት የሚነሱ ይሆናሉ ፡፡
ዮሐንስ (11፡ 14-16)፡ ኢየሱስ “ አልዓዛር ሞተ ፤ እንድታምኑ…” ብሎ ነገራቸው ፤ ኢየሱስ አልዓዛር እንዲሞት በፈቀደ ጊዜ የሚፈፅመዉ የተለየ አላማ ነበረው ፤ “ ከዚያም ቶማስ እንሂድ ከእርሱ ጋር እንሞታለን አለ “ ፡፡ ዋይርስቤ የቶማስን መንትያ ስም አናዉቅም ነገር ግን ምናልባትም ሁላችንም የእርሱ መንትዮች ነን ብሏል ፤ አንዳንድ ጊዜ ቶማስ ክርስቶስን ከማመኑ በፊት ማረጋገጫ ፈልጓል ነገር ግን ሌላ ጊዜ ላይ በአደጋ ዉስጥ ኢየሱስን ለመከተል ፈጣን ነበር ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ እንዴት ክርስቶስን እንደ ሚከተሉት ለመሳል እየሞከሩ ነበር ፡፡
ዮሐንስ (11፡ 17-40)፡ እህትማማቾቹ
ዮሐንስ (11፡ 17-23)፡ ኢየሱስ በቢታኒያ(ኢየሩሳሌም አጠገብ) በደረሰ ጊዜ ለአራት ቀን አልዓዛር መቃብር ዉስጥ ነበር ፡፡ ብዙዎች ማርታን እና ማሪያምን ሊያፅናኑ መጥተው ነበር ፤ ሉቃ (10፡ 38-42) ማሪያም በኢየሱስ እግር ላይ በተቀመጠችበት ጊዜ ማርታ ስራ ላይ እንደ ነበረች ገልጣል ፡፡ ማርታ ኢየሱስን ለማግኘት ተጣደፈች ፤ “ ጌታ ሆይ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር “ (ቁጥር 21) ፤ ንግግሯ ይመስለዉ በነበረው ተደንቃችኋል ? እየከሰሰችዉ ነበር ? ምናልባትም ኢየሱስ ብቻ ሊረዳት እንደ ሚችል ታውቃለች “ አሁንም ከእግዚአብሄር የምትለምነዉን ሁሉ እግዚአብሄር እንዲሰጥህ አዉቃለሁ አለችዉ “ (ቁጥር 22) ፡፡ ኢየሱስ ማርታን “ ወንድምሽ ይነሳል አላት “ ፤ ይህ መለዋወጥ ለኢየሱስ ሁሉንም ስሜታችንን ለመግለፅ ለማዘን እና ለደህንነት ጤነኝነትን ያሳያል፡፡ “ አልገባኝም ነገር ግን በቁጥጥር እንደ ሆናችሁ እዉቃለሁ ማለት “ እንችላለን ፤ የሚያደርገዉን ለሚያዉቀዉ ለኢየሱስ ሁሉንም ነገር መስጠት እንችላለን ፡፡
ዮሐንስ (11፡ 24-27)፡ ማርታ ኢየሱስ እያወራ የነበረው ስለ መጫረሻዉ ዘመን እንደ ሆነ በግልፅ አስባለች ፡፡ ዳን (12፡ 2) የሚለው “ በምድርም ትቢያ ዉስጥ ካንቀላፉት ብዙዎች ይነቃሉ ፤ …..እኩሌቶቹ ወደ ዘላለም ህይወት “ ፤ ከዚያም ኢየሱስ አምስተኛዉን “ እኔ “ የሚለዉን ንግግር አደረገ፡ “ እኔ ትንሳኤ እና ሕይወት ነኝ ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳን ህያዉ ይሆናል “ ፤ በዚህ እንደ ምታምን በጠየቃት ጊዜ ማርታ “ አዎን ጌታ ሆይ ፤ አንተ ወደ የሚመጣዉ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ አለችዉ “ ፡፡ ይህ ንግግር የዮሐንስን መፅሀፍ አላማ ይደግፋል “ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደ ሆነ እንድታምኑ “ (ዮሐ 20፡ 31) ፡፡
ዮሐንስ (11፡ 28-34)፡ ማርታ ተመልሳ በመሄድ ለማሪያም “ መምህሩ እዚህ ነዉ “ አለቻት ፤ ማሪያም ከአካባቢዉ በሄደች ጊዜ አይሁዶች ለማልቀስ ወደ መቃብር እየሄደች እንደ ነበር በማሰብ ከእርሷ ጋር ሄዱ ፡፡ ልክ እንደ ማርታ ማሪያምም “ ጌታ ሆይ በዚህ ኖረህ ቢሆን…..” አለች ፤ እያንዳንዱ ቀብር ስነ ስርዓት ላይ እንደ ቃል ልምዳቸዉ መሰረት ቤተሰቦች ለሞተዉ ለማዘን ቢያንስ ሁለት ዋሽንት ተጨዋቾች እና አንድ ጎበዝ አልቃሽ ሴት ይቀጥራሉ ፡፡ ማሪያም እና ማርታ እንደ ቀረቡ እነዚህ ሰዎች ተከተሉዓቸው ፤ ኢየሱስ ይህን ባዬ ጊዜ ባለማመናቸው ምክንያት ተበሳጨ ፤ “ ወዴት አኖራችሁት ? ብሎ ጠየቃቸው ፡፡
ዮሐንስ (11፡ 35-42)፡ ኢየሱስ አለቀሰ ፤ ቃሉ ከሙያተኛ አልቃሾች ለቅሶ ይልቅ ዝም ያለን ለቅሶን አመልክቷል ፡፡ ኢየሱስ “ የሕመም ሰው ደዌንም የሚያዉቅ ሰዉ ነበር “ (ኢሳ 53፡ 3) ፤ አይሁዶች እንኳን ለአልዓዛር የኢየሱስን ፍቅር ተረዱ በመጀመሪያዉ ቦታ ከሞት ባለመታደጉ ቀለዱበት ፡፡ ወደኋላ ያላለዉ ኢየሱስ ድንጋዩን እንዲያስወግዱት ነገራቸው “ ብታምኚስ የእግዚአብሄርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን ? አላት ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ ፀለየ በዚህም ህዝቡ እግዚአብሄር እንደ ላከዉ ያምናሉ ፡፡
ዮሐንስ (11፡ 43-45)፡ ኢየሱስ “ አልዓዛር ወደ ዉጭ ና ! “ ብሎ ጮኸ ኢየሱስ በጎቹ ድምፁን እንደሚሰሙ እና እንደ ሚከተሉት ወደ አስተማራቸዉ ወደ ዮሐ (10፡ 1-5) ስንሄድ ፤ አልዓዛር በወጣ ጊዜ ኢየሱስ ሰዎቹን “ ፍቱትና ይሂድ ተዉት አላቸው ! “ ከአይሁዶች ብዙዎቹ በዚያ ክስተት በእርሱ አመኑ ፡፡
መዝጊያ
ኢየሱስ በግልፅ “ እኔ ትንሳኤና ህይወት ነኝ “ አለ ፤ ህይወት መስጠት የሚችል ኢየሱስ ብቻ ነው ! የትኛዉም ህይወት ላይ ብትሆኑ ሀዘን ላይ ወይም ደስታን በመፈለግ ላይ ብትሆኑም፡ በእግዚአብሄርን ልብ ታመኑ፣ ለእናንተ ምርጥ የሆነዉን እንደ ሚፈልግ ታመኑት፣ በጊዜዉ ታመኑ፣ ሁል ጊዜ ለእናንት እንደሚሰራ እመኑት (ሮሜ 8፡ 28) ፡፡ አሁንም ሁኔታው ትርጉም በማይሰጥበት ጊዜ የእግዚአብሄር ጊዜ ከእናንተ እንደ ሚበልጥ ታመኑ ፤ የእግዚአብሄርን እጅ ለማስገደድ አትሞክሩ - አፈግፍጋችሁ ጠብቁ ፡፡ ኤር (17፡ 7-8) የሚለው “ በእግዚአብሄር የታመነ እምነቱም እግዚአብሄር የሆነ ሰው ብሩክ ነው ፡፡ በዉኃ አጠገብ እንደ ተተከለ በወንዝም ዳር ስሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ …..ፍሬዉንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል “ ፤ ሁኔታችሁን ሳታስቡ በእግዚአብሄር ጊዜ ታመኑ፡፡
John F. MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 1394.
Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 267.
Wiersbe, p. 268.
Wiersbe, p. 268.
Wiersbe, p. 269.
ጥያቄዎች
-
የአልዓዛርን መታመም ቃል ይዞ ለመጣዉ መልዕክተኛ የኢየሱስ የመጀመሪያ መልስ ምን ነበር ? (ዮሐ 11፡ 4) ፤ ቀጣዩስ መልሱ ምን ነበር ? ኢየሱስ ወደ ቢታኒያ ለመሄድ ለምን ሁለት ቀን እንደ ጠበቀ ምን ታስባላችሁ ?
-
ተመልሶ ወደ ቢታኒያ ለመሄድ ለምን ነበር አደገኛ የሆነበት ? ምንም ይሁን ለመሄድ ፍቃደኛ የነበረዉ ለምን ነበር ? (ዮሐ 15፡ 13)
-
ለማርታ ሲናገር ኢየሱስ ራሱን እንዴት ገለጠላት ? ይህ ንግግር ለእርሷ እና ለእናንተ እንዴት አድርጎ ተስፋ ይሰጣችኋል ? (ዮሐ 5፡ 21, 1ቆሮ 15፡ 22)
-
ዮሐ (11፡ 33, 35 እና 38) የኢየሱስን ሰብዓዊነት እንዴት ይናገራል ? ስለ እርሱ አምላክነት እንዴት አድርገው ይናገራል ? ይህ ለእናንተ እንዴት ምቾት(ደስታ) ያመጣል ? (ኢሳ 53፡ 3, ዕብ 2፡ 14-18)
-
የአልዓዛር ሞት እና ትንሳኤ ንስኃ ለገቡ እና ኢየሱስን ለታመኑት ኃጢዓተኞች እንዴት ጥሩ መግለጫ ይሰጣል ? (ዮሐ 5፡ 24, ኤፌ 2፡ 1-10)
-
በዮሐንስ 11 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin John 11:25–26
“Jesus said to her, ‘I am the resurrection and the life. The one who believes in Me, even if he dies, will live. Everyone who lives and believes in Me will never die—ever. Do you believe this?’”
ኢየሱስ ሙታንን ወደ ሕይወት የማምጣት ሥራ ላይ ነው፡፡ ወንድሟ አልዓዛር ለሞተባት ማርታ፥ እንዲህ አላት፥ "እኔ ትንሳኤ እና ሕይወት ነኝ፡፡" የኢየሱስ ንግግር ለራሱ ትንሳኤ ጥላ ነው ፥ ነገር ግን የወንጌልም ታሪክ ነው፡፡
የሞቱ የሚመስሉ ነገሮች በኢየሱስ ኃይል፣ ፀጋ እና ፍቅር ሕያዋን ይሆናሉ፡፡ ኢየሱስ ለአራት ቀናት ሞቶ የነበረውን አልዓዛርን ፥ በተአምር ከሞት አስነስቶታል፡፡ ኢየሱስ ተስፋ ቢስ በሆኑ ሁኔታዎችም ላይ ሕይወትን ሊያመጣ ይችላል፡፡ ያላችሁን ሁሉ ለጌታ አሳልፋችሁ በመስጠት፥ ለራሳችሁ እና በህይወታችሁ ላለው ኃጢያት ስትሞቱ፥ ፍቅሩ እና ፀጋው በክርስቶስ አዲስ ሕይወትን ይሰጣችኋል፡፡ ኢየሱስ ሁሉንም አሳልፋችሁ ስጡ ይላል፦ ሕይወታችሁን፥ ትዳራችሁን፥ ልጆቻችሁን፥ ገንዘባችሁን ከዚያም ጸልዩ ፥" ጌታ ሆይ፥ የእኔ (ባዶ ቦታውን ሙሉት) አሁን ላይ የሞተ ይመስላል፡፡ እንዴት እንደሚለወጥ እና ሕይወትን እንደሚያገኝ አላውቅም፥ ነገር ግን አምንሀለው፡፡" ኢየሱስ በዕየለቱ እንደዚህ እንድትኖሩ ይጠራችኋል፡፡ በዚህ እውነት በእምነት ለመራመድ በበቂ መንገድ ይህንን ታምናላችሁ? ዛሬ ጀምሩ!
“ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት።”
— ዮሐንስ 11:25–26
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ሉቃስ 9:24–25 – “ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፤ ስለ እኔ ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን እርሱ ያድናታል።ሰው ዓለሙን ሁሉ አትርፎ ራሱን ቢያጠፋ ወይም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ”
- ሮሜ 6:8 – “ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን”
- 1ኛ ቆሮንቶስ 15:31 – “በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለኝ በእናንተ ትምክህት እየማልሁ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ዕለት ዕለት እሞታለሁ። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 79
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።