The Gospels John

Belief and Unbelief

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 190 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዮሐንስ (12፡ 1-8) በቢታኒያ ማሪያም የኢየሱስን ራስ እና እግር ለመቀባት በግልፅ ሁሉንም ነገር በሰጠች ጊዜ ያለዉን ቅባት ይገልፃል ፤ ዮሐ (12፡ 9-11) በትንሳኤዉ ምክንያት ብዙ አይሁዶች በኢየሱስ በማመናቸው የኃይማኖት መሪዎች አለዓዛርን ለመግደል ወሰኑ ፡፡ ዮሐ (12፡ 12-19) በሌሎቹ ወንጌላት ጥናታችን የሸፈነዉን የኢየሱስን ወደ ኢየሩሳሌም በመለከት (በጩኸት) መግባትን ይገልፃል ፤ ዮሐ (12፡ 20-36) ኢየሱስ ሞቱን ያመለከተዉን አንዱን ጊዜ እንደ ገና አዉርቷል ፡፡

ዛሬ እንዴት አዲስ ኪዳን ወደ ኋላ ወደ ብሉይ ኪዳን እንደ ሚመለከት እንመልከት ፤ አሁን ያ ክርስቶስ ማን እንደ ነበር እያወራ ነበር ስለ ሚፈፀሙትም ብሉይ ኪዳን ትንቢቶች አመልክቷል ፡፡

ትምህርት

ዮሐንስ (12፡ 37-40)፡ኮንስታብል ዮሐንስ በአይሁድ ማህበረሰብ ዉስጥ የእምነት ሁለት ችግሮችን እንደ ገለፀ ተናግሯል ፤ የመጀመሪያው ችግር በዮሐ (6፡ 66) ተከስቷል፡ “ ከዚህም የተነሳ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም “ ፡፡ የኢየሱስን አንዳንድ ጠንካራ ትምህርቶች ከሰሙ በኋላ (ዮሐ 6፡ 60) ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ቀጥለዉ እርሱን ለመከተል አልፈለጉም ፡፡ ሁለተኛው ችግር በዮሐ (12፡ 27) ተከስቷል፡ “ ነገር ግን ይህን ያህል ምልክት በፊታቸው ምንም ቢያደርግ አለመኑበትም “ ፤ የኃይማኖት መሪዎች በእርሱ አለማመን ብቻ አላደረጉም ነገር ግን ሊገድሉት እየሞከሩ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ ለኢየሱስ የአይሁዶችን መልስ ሰዎስት ሁኔታ ገልፃአል ፤ መጀመሪያ አይሁዶች አላመኑበትም (ቁጥር 37) ፤ ሁለተኛ ማመን አይችሉም ምክንያቱም አለማመናቸዉ የነቢዩ ኢሳያስ ቃል መፈፀም ስለሆነ (ቁጥር 38) ፡፡ ቁጥር 38 ከኢሳ (53፡ 1) አወዳድሩ “ የሰማነዉን ነገር ማን አምኗል ? የእግዚአብሄርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል ? ሰዎስት አያምኑም ምክንያቱም እግዚአብሄር አይናቸዉን አሳዉሯል ልባቸዉንም አደንድኗል (ቁጥር 39-40) ፡፡ ማክአርቱር እነዚህ ምላሾች “ በእስራኤል የማደንደን የእግዚአብሄር ሉዓላዊ እቅድ ዉስጥ “ ተጫኑ ብሏል ፤ ይሁን እንጂ ይህ ማደንደን “ ከሰዉ ኃላፊነት እና ተወቃሽነት የተለዩ አልነበሩም “ ፤ ምክንያቱም መጀመሪያ አለማመንን ስለ መረጡ እግዚአብሄር ልባቸዉን አደነደነ ስለዚህ አያምኑም ፡፡

ዮሐንስ (12፡ 40-41)፡ በቁጥር 40 ዮሐንስ ኢሳ (6፡ 9-10) ጠቀሰ ፤ ኢሳያስ በግልፅ የእግዚአብሄርን ክብር አይቶ ነበር (ቁጥር 41) ፤ አሁን ዮሐንስ አይሁዶች የእግዚአብሄርን ክብር አይተዉ እንደ ነበር ነገር ግን እንዳላመኑ አመለከተ ፡፡ ማክአርቱር እምነት ማጣታቸዉ ኢየሱስን “ የእስራኤል ድንዳኔ ፈራጅነት አድራጊ አደረገው “ ብሏል ፤ በሌላ ቋንቋ ኢየሱስ በዳኝነት ተግባር አገለገለ ፡፡ ዮሐንስ በሌላ ቦታ ይህን እዉነት ጠቅሷል ፡፡ ዮሐ (5፡ 22-23) የሚለው እግዚአብሄር ሁሉንም ፍርድ ለልጁ ሰጥቷል ነው ፤ ዮሐ (5፡ 27) እግዚአብሄር ኢየሱስን ፍርድ እንዲያስተላልፍ መብት ሰጥቶታል ይላል ፤ በዮሐ (5፡ 30) ኢየሱስ “ እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝ ፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና “ አለ ፤ በኢሳያስ እንደ ተገለፀው ኢየሱስ የህዝቡ ፈራጅ ነበር ፡፡ ባለማመናቸዉ እግዚአብሄር የአይሁዶችን ልብ በማደንደን ከእግዚአብሄር በመለየት ወደ ሲኦል አስቀመጣቸዉ በዚህም አህዛብ ወደ ድነት መጓዝ ቻሉ ፡፡ በዮሐ (5፡ 42) ኢየሱስ አይሁዶች ለእግዚአብሄር ፍቅር እንዳልነበራቸዉ አሳውቋል ፡፡

ዮሐንስ (12፡ 42)፡ ብዙ አይሁዶች መሪዎችም እንኳን በኢየሱስ አምነዋል ነገር ግን ፈሪሳዉያን ከምኩራብ እንዳይቀጡዓቸው ስለ ፈሩ አልገለፁትም ፤ ይሁን እንጂ በአይሁዶች መካከል ደንዳኖችም ቢኖሩ አሁንም ተስፋ ነበር ምክንያቱም ብዙዎች በኢየሱስ ስላመኑ ፡፡ ልባቸዉን አደነደኑ ወይስ እግዚአብሄር አደነደናቸው ? ለሁለቱም ጥያቀቄ መልሱ አዎ ነው ፤ 100 ፐርሰንት የእግዚአብሄር እና 100ፐርሰንት የሰዉ ነው ፡፡ ዮሐንስ እነዚህን ሁለቱን ፅሁፎች አላነሳም አልመረጠም ፤ ዮሐንስ በወንጌሉ ዉስጥ ከብሉይ ኪዳን እና ከአዲስ ኪዳን እዉነቶችንአገናኝቶ ፃፈ ፡፡ እነዚህ ደቀ መዛሙርቶች የእግዚአብሄርን ቃል ያዉቃሉ ስለሆነም ኢየሱስ ብሉይ ኪዳንን መናገር በጀመረ ጊዜ አወቁት ፤ እነዚህን ምሳሌዎች ተመልከቱ፡

  • ዮሐ (1፡ 23)፡ “ መጥምቁ ዮሐንስም ነቢዩ ኢሳያስ እንዳለ -የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰዉ ድምፅ እኔ ነኝ አለ “ ፤ ዮሐንስ መጥምቁ ዮሐንስን ነቢዩ ኢሳያስ እንዳለው በምድረበዳ እንደ ሚጮኽ ድምፅ ገልፆታል (ኢሳ 40፡ 3) ፤ ዮሐንስ በብሉይ ኪዳን ላይ በመመስረት በእግዚአብሄር ቃል ላይ እምነትን መሰረተ(አደረገ) ፡፡ በወንጌሉ ዉስጥ የራሱን ጉዳይ ገነባ ፤ መጥምቁ ዮሐነስ እዉነትን እንዳወራ እያተናገረ ነበር ፡፡
  • ዮሐ (2፡ 17)፡ “ ደቀ መዛሙርቱም የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደ ተፃፈ አሰቡ “ ፤ ይህ ከመዝ (69፡ 9) የተሳበ ንግግር ነበር ፡፡
  • ዮሐ (6፡ 31)፡ “ ኢየሱስ “ እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ “ (ዮሐ 6፡ 35) ከማለቱ በፊት እግዚአብሄር ለአባቶቻቸው “ እንዲበሉት ከሰማይ እንጀራ “ እንደ ሰጣቸው አስታወሳቸው ፤ ኢየሱስ ከመዝ (78፡ 24) እየጠቀሰ ነበር ፡፡
  • ዮሐ (6፡ 45)፡ “ ሁሉም ከእግዚአብሄር የተማሩ ይሆናሉ ተብሎ በነቢያት ተፅፏል “ ፤ ይህ ከኢሳ (54፡ 13) የተጠቀሰ ነበር ፡፡ ስለ አድስ ኪዳን ከአይሁድ ሰዎች ጋር መስተጋብር ብታደርጉ ፅሁፎቹን ከህጉ እና ከነቢያት ያስተዋዉቋቸዋል(ያገናኙአቸዋል) ፡፡
  • ዮሐ (10፡ 34)፡ ኢየሱስ “ እኔ አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተፃፈ አይደለምን ? ብሎ ጠየቃቸው (መዝ 82፡ 6) ፡፡
  • ወደ ዮሐንስ 12 ፅሁፍ ስንገባ ብዙ ግንኙነቶችን እናያለን ፡፡ ዮሐ (12፡ 13) ከመዝ (118፡ 26) ጠቅሷል ፤ ዮሐ (12፡ 15) ከዘካ (9፡ 9) ጠቅሷል ፤ ዮሐ (12፡ 38) ከኢሳያስ የተሳበ ነበር ፡፡ ዮሐንስ ይህን ለምን አደረገ ? ማቴ (5፡ 17) ላይ ተመልከቱ ፤ ኢየሱስ ህግን እና ነቢያትን ሊፈፅም እንጂ ሊያጠፋ አልመጣም ፡፡ ኢየሱስ በእነዚህ ትንቢቶች መፈፀም ተጓዘ ፡፡

የአይሁዶችን ልብ ለማደንደን እግዚአብሄር ምንድን አላማ ነበረው ?

መጀመሪያም ከፊል ድንዛዜ ነበር (ዮሐ 12፡ 42) ፤ አንዳንድ አይሁዳዊ ሰዎች መሪዎችም እንኳን በኢየሱስ አምነዋል ነገር ግን ፈሪሳዊያን ከሙክራብ እንዳይቀጡዓቸዉ ስለ ፈሩ በአደባባይ አልገለፁትም(አልተቀበሉትም) ፡፡

ዮሐንስ (12፡ 43)፡ በኢየሱስ ቢያምኑም ሰዉን ይፈሩ ነበር ፤ ( ወደፊት አሆነ ጊዛ ላይ ኒቆዲሞስ እና አርማቲዮስ ዮሴፍ በመጨረሻ መናገር ጀመሩ) ፤ ማክአርቱር የመሪዎች እምነት “ በምኩራብ ከሚታዩበትን ስፍራ ወደ ማንኛዉም ስፍራ መወሰዳቸዉን ለመቃወም በጣም ደካማ እንደ ነበር “ ተናግሯል ፤ ፍላጎታቸዉ ለሰዉ ክብር መስጠት ለእግዚአብሄር ክብር ከመስጠት ቅድሚያዉን ስለ ወሰደባቸው በክርስቶስ እምነታቸዉን በአደባባይ ለማሳወቅ አልፈለጉም ፡፡ 1ዮሐ (2፡ 28) “ አሁንም ልጆች ሆይ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ “ ፤ በአማኞች መካከልም እምነታቸዉ ደካማ ነበር ፡፡ ማክአርቱር “ ያልበቃ መረዳትን፣ ወላዋይነትን እና የተጥበረበረ እምነትን “ እነዚህን ህጎች አጥብቋቸዋል ፤ በሌላ አባባል “ በእርሱ ነኝ ነገር ግን የእርሱ አይነት ነኝ “ እያሉ ነበር ፡፡ በተለዬ በዮሐ (12፡ 42) ላለዉ “ ማመን “ ለሚለው የግሪኩ ቃል ከጥርጣሬ ጥላ ዉጪ የእምነትን መያዝ ያመለክታል ፡፡ ዮሐ (8፡ 30) ተመሳሳይ ቋንቋ ተጠቅሟል “ ብዙዎች በእርሱ አመኑ “ ፤ አዎ አምነዋል ነገር ግን ለመወሰን ፈርተዉ ነበር ፡፡

ሁለተኛ የአይሁዶች ልብ በመደንደኑ ምክንያት ወንጌል ለአህዛብ ህዝቦች ተለቀቀ(ደረሰ) (ሮሜ 11፡ 11-12) ፤ እነርሱን ያስቀናቸዉ ዘንድ በእነርሱ በደል መዳን ለአሕዛብ ሆነ “ (ቁጥር 11) ፤ ይህ የአይሁዶችን ልብ በማደንደን የእግዚአብሄር የጨዋታ እቅድ እና አላማ ነበር ፡፡ የአይሁዶች መሰናከል ለአለም ለአሕዛቦች ባለጠግነትን አመጣ “ ይልቁንስ መሙላታቸዉ እንዴት ይሆን ! “ (ቁጥር 12) ፤ ጳዉሎስ “ ወንድሞች ሆይ ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ…..የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው “ በማለት ቀጠለ (ሮሜ 11፡ 25) ፡፡

ዮሐንስ ኢሳያስ የአይሁዶች ልብ የደነደነ እንደሚሆን ያለዉን አስታወሰ ፤ በዚያ ደህና መሆን እንችላለን ምክንያቱም ለአሕዛብ “ ሙሉ ቁጥራቸዉ እስኪያምኑ ድረስ “ መዳንን ስላመጣ ፡፡ መቼ እንደሚሆን እንዴት እናዉቃለን ? አናውቅም ኃላፊነታችን ወንጌል መጋራት ነዉ ምክንያቱም ይህ ቁጥር መቼ እንደሚሞላ እዉቀቱ ስሌለለን ፤ “ በዚህ መንገድ ሁሉም እስራኤል ይድናል “ (ሮሜ 11፡ 27) ፡፡

ሰዎስተኛ በአሕዛብ ሙላት ምክንያት ሁሉም እስራኤል ይድናል ፡፡ በዮሐንስ 12 ስለ አይሁድ መደንዘዝ ያነበብነው ወደ ሮሜ 11 እንድንሄድ ያበረታታናል ምክንያቱም በመጨረሻ ሁሉም እስራኤል ስለሚድን ፡፡

መዝጊያ

በመሄድ ወንጌልን ከአይሁዶች ጋር የምንጋራ(የምናጋራ) ከሆነ አይሁዶች የበረቱ ይሆናሉ ፤ ለምን ? ድነት በአህዛብ ሙላት ምክንያት በሚመጣዉ መሲኀቸዉ በኩል ስለሚመጣላቸዉ ነው ፡፡

  1. Dr. Thomas Constable. Dr. Constable’s Bible Study Notes: John, p. 124; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/john.pdf.

  2. Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), pp. 274–275.

  3. John MacArthur, NASB MacArthur Study Bible, updated edition (Nashville: Thomas Nelson, 2006), p. 1576.

  4. MacArthur, p. 1576.

  5. MacArthur, p. 1576.

  6. MacArthur, p. 1576.

  7. MacArthur, p. 1576.

ጥያቄዎች

  1. ለኢየሱስ ማሪያም እንዴት አድርጋ ፍቅሯን አሳየች ? (ማቴ 26፡ 6-13, ማር 14፡ 3-9) ፤ እነዚህን ነገሮች ለምን አደረገች ? በኢየሱስ ይሆን ስለ ነበረዉ ተረድታለች እና አዉቃለች ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  2. በዉድ ስጦታዋ ማሪያም በብዙ እንዴት ንጉስ ዳዊትን ትመስል ነበር ? (2ሳሙ 24፡ 24)
  3. የካህናት አለቆች ኢየሱስን ብቻ ሳይሆን አልዓዛርንም ለመግደል ያሴሩ የነበረው ለምን ነበር ?
  4. በቁጥር 28 እግዚአብሄር ለሰዎስተኛ ጊዜ በወንጌል በኃይል ተናገረ ፤ በሚሰማ የተናገራቸዉን ሌሎቹን ሁለቱን ጊዜዎች መጥቀስ ትችላላችሁ ? (ማቴ 3፡ 17, ሉቃ 9፡ 35)
  5. አንዳንድ ገዢዎች(መሪዎች) በግልፅ ለማወጅ ሳይፈልጉ በኢየሱስ ማመንን ለምን አደረጉ ? እምነታቸዉ እንደ ሚያድን እምነት ታዩታላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላያችሁትም ? (ማቴ 10፡ 32-33, ሮሜ 10፡ 9-10)
  6. በዮሐንስ 12 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin John 12:24–26a

“I assure you: Unless a grain of wheat falls to the ground and dies, it remains by itself. But if it dies, it produces a large crop. The one who loves his life will lose it, and the one who hates his life in this world will keep it for eternal life. If anyone serves Me, he must follow Me.”

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ለማስተማር የእርሻ ምሳሌ ተጠቀመ፥ "የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች፥ ብቻዋን ትቀራለች፥ ብትሞት ግን፥ ብዙ ፍሬ ታፈራለች፡፡" ኢየሱስ ሊመጣ ስላለው ስቅለቱ እና ሞቱ ደቀመዘሙርቱን አዘጋጃቸው፡፡ የሰው ልጅ ፥ኢየሱስ፥ ይከብር ዘንድ ሰአቱ ደርሷል፡፡ ነገር ግን በኢየሱስ ሞት ታላቅ የመዳን መከር ይመጣል!

በተመሳሳይ መንገድ፥ ኢየሱስ አማኞች ለራሳቸው መሞትን የዕለት ተዕለት ተግባራቸው እንዲያደርጉ አዟል፡፡ ለራሳችሁ ስትሞቱ፥ ስንዴ ወደ ምድር በመውደቅ ብዙ ፍሬ እንደሚያፈራ ኢየሱስ በይበልጥ በሕይወታችሁ እንዲከብር ሥፍራን ታዘጋጃላችሁ፡፡ ዛሬ፥ ጌታን እንዲህ በሉት፥ " አንተ፥ ኢየሱስ፥ በእኔ እንድትከብር ፥ እንዴት ለራሴ መሞት እንደምችል ዛሬ አሳየኝ!" ጌታ ወደ አዕምሮአችሁ የሚያመጣቸውን ነገሮች ስትለቁ፥ በፀጋ ላይ ፀጋ ይጨመርላችሁ እና ከምታስቡት በላይ አዲስ ሕይወት ያድጋል፡፡ በሕይወታችሁ ልትቆጣጠሩት ወይም ልትይዙት የሚያሰፈልግ ቦታ እንዳለ ልታስቡ ትችላላችሁ፥ ነገር ግን ኢየሱስ ሕይወታችሁን ሰታጡ ፥ ብዙ እንደምታገኙ ተናግሯል፡፡ ተከተሉት፥ ፍቅሩ ለዘወትር አይወድቅም፡፡

“እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች። ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም በዚህ ዓለም የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል። የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፥ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይሆናል”

— ዮሐንስ 12:24–26ሀ

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ሉቃስ 9:23–24 – “ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፤ ስለ እኔ ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን እርሱ ያድናታል። ”
  • ሮሜ 8:12–13 – “እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ዕዳ አለብን፥ እንደ ሥጋ ፈቃድ ግን እንኖር ዘንድ ለሥጋ አይደለም። እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ። ”
  • ገላቲያ 2:20 – “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው። ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 80