The Gospels John

Jesus Washes the Disciples' Feet

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 191 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በአንድ አካባቢ ሁሉም ነበር ሲቀየር ያለተቀየረዉን ነገር ለመያዝ የሆነ ነገር ያስፈልገናል - ያም የእግዚአብሄር ቃል ነው ፡፡ ዮሐንስ 12 መጨረሻ ላይ ኢየሱስ አባቱ የተናገረዉን እና ሲያደርግ ያየዉን እንደ ሚያደርግ እና እንደሚናገር ጠቅሷል ፡፡ ዮሐንስ 13 ለደቀ መዛሙርቱ የሽኝቱ ማድረስ ጅማሬ ነበር ፤ እየመጣ ስለነበረው ያዘጋጃቸዉ ጀመር ፡፡

ትምህርት

ዮሐንስ (13፡ 3)፡ ኢየሱስ ጊዜዉ እንደ መጣ ያውቃል ፤ ማን እንደ ነበር፣ ከየት እንደ መጣ፣ ምንድን ለማድረግ እንደ መጣ እና ወዴት እንደ ሚሄድ ማንነቱን ያውቃል ፡፡ በማቴ (3፡ 17) አብ በልጁ ዉስጥ ማንነቱን ተናገረ ፤ እግዚአብሄር ኢየሱስን በእርሱ ደስ የሚለዉ እና እንደ ሚወደዉ ልጁ በሚሰማ አወጀ ፤ ይህ ንግግር ከኢየሱስ መልክ መቀየር በኋላ በእግዚአብሄር ተጨማሪ ትዕዛዝ “ እርሱን ስሙት “ በማለት (ማቴ 17፡ 5) ተደግሟል ፡፡ ክርስቶስን መከተል ኃጢዓታችንን ይቅር ስለ መባላችን እንደሆነ ምን ያክል ጊዜ እናስባለን በዚህስ በሌላ በብዙ ነገሮች አስፈላጊነታችንን በቀረዉ ህይወታችን እንፈልጋለን ? ነገር ግን የሚያስፈልገንን ሁሉ ሰጥቶናል - በክርስቶስ ማንነታችን የተገኘ ነው ፡፡

ጴጥሮስ አማኞችን እግዚአብሄር “ለሕይወትና እግዚአብሄርን ለመምሰል ሁሉን ነገር “ (2ጴጥ 1፡ 2-4) እንደ ሰጠ አስታውሷል ፤ ከዚህ በኋላ የሚጠቀምብን ለመሆን አንቀጥልም አሁን እንደ አንድ ልጆ እንጓዛለን ፡፡ በትክክል ይህን በተረዳን ጊዜ በተለዬ እንጓዛለን ፤ በስልጣን እንጓዛለን ፡፡ 1ተሰ (4፡ 16-18) ጳዉሎስ ያለው “ ጌታ ራሱ በትዕዛዝ በመለዓክትም አለቃ ድምፅ ….በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመዉ ይነሳሉ ፤ ከዚያም በኋላ እኛ ህያዋን ሆነን ….ጌታን በአየር ለመቀበል …..እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን “ ፡፡ በክርስቶስ ከየት እንደ መጣን፣ ማን እንደ ሆንን እና ወዴት እንደ ምንሄድ እናውቃለን ፡፡ ሮሜ (8፡ 14) እንደ እግዚአብሄር ልጆች በእግዚአብሄር መንፈስ እንደ ምንመራ አብራቷል ፡፡ በፍራት እና በባርነት ስር የምትኖሩ ከሆነ የመጣዉ ከዱሮ ህይወታችሁ ነው ፤ ማንነታችሁ በክርስቶስ ከተገኘ በሌላ ቦታ ልትፈልጉት አይገባችሁም ፡፡ ኤፌ (3፡ 20) እግዚአብሄር “ በእኛ እንደሚሰራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበዉ ሁሉ ይልቅ ሊያደርግ ይችላል “ ፤ በእርሱ ኃይል እንዴት እንደ ምንሄድ ልንማር ያስፈልገናል ፡፡

ዮሐንስ (13፡ 4-5)፡ ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ ፡፡ በስርዓቱ ለእንግዶች አንድ አገልጋይ ይህን ተግባር ያደርጋል ፤ ኢየሱስ ለቀጣይ ኑሮአቸዉ ደቀ መዛሙርቱን ማዘጋጀት ለመጀመር ይህን ተግባር አደረገ - እየመጣ ስለ ነበረው መሪነትን ለመዉሰድ ፡፡ በሉቃ (22፡ 24) ኢየሩሳሌም እንደ ቀረቡ ደቀ መዛሙርቱ ከእነርሱ ማን ይበልጥ እንደ ነበር ተከራከሩ ፤ አሁን ኢየሱስ በጥሞና ከመቀመጫዉ ላይ በመነሳት በመንግስቱ ታላቅነት ምንድን እንደ ሚመስል ሞደል መሆን ጀመረ ፡፡ በማቴ (20፡ 25-28) ኢየሱስ እንዴት በመንግስቱ ታላቅነት እንደ ሚገኝ ገለፀ ፤ በዚህ ድርጊት ኢየሱስ የማንነቱን እና የልጅነቱን መረዳት አሳየ ፡፡ በትህትና አስፈላጊነትንም ተግባባበት ፤ በድርጊቱ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዴት ራሳቸዉን ፀባይተኛ እንደ ሚያደርጉ እና እንዴት ለሌላ ሰው ዋጋ እንደ ሚሰጥ አሳያቸው ፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ማን እንደ ነበር፣ ሌሎችን ማገልገል እንደ ሚችል እና ዋጋ እንዲሰጡ እንደ ሚያሳያቸዉ ስለ ሚያውቅ ፡፡ ጴጥሮስ አማኞችን “ ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እዉቅት እደጉ “ (2ጴጥ3፡ 18) በማለት ሞገታቸው ፡፡ ዋይርስቤ “ በእዉቀት እያደግን ነዉ ግን በፀጋ አይደለም “ ብሏል ፤ በአጋዥነትም ዋይርስቤአንድሪዉ ሙራይ “ የፀጋ ስር የሚሆነዉ ትህትና ብቸኛው ነው “ ብሎ የፃፈዉን ጠቅሷል ፡፡

1ጴጥ (5፡ 5-6) “ እግዚአብሄር ትቢተኞችን ይቃወማልና ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ፤ እንግዲህ በጊዜዉ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛዉ ከእግዚአብሄር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ ፤ የእግዚአብሄር ፀጋ በትህትናችን ዉስጥ እና በኩል ይፈስሳል ፡፡ ኢየሱስ ሁሉም ነገር ቢኖረዉም ራሱን በማዋረድ የአገልጋይ ስፍራን ወሰደ ፡፡

ዮሐንስ (13፡ 6-10)፡ ጴጥሮስ የኢየሱስን ታላቅነት እዉቅና ሰጠ ምክንያቱም “ ታላቅ “ ሰዎች ይህን ድርጊት ስለማያደርጉት ኢየሱስ እግሩን እንዳያጥበዉ ተቃወመ (ቁጥር 8) ፡፡ ኢየሱስ “ ካለጠበሁህ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም “ ባለዉ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን “ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም “ ብሎ በመጠየቅ መለሰለት (ቁጥር 9) ፤ ጴጥሮስ ሁሉንም ነገር ኢየሱስ ለእርሱ እንዲያቀርብለት ፈለገ ፡፡ በቁጥር 10 የኢየሱስ ምላሽ ወደ ክርስቶስ በመጣን ጊዜ ኃጢዓታችን ይቅር እንደተባለ እና በክርስቶስ የእግዚአብሄር ፅድቅ እንደ ምንሆን አረጋግጧል ፤ ያም ማንፃት ሁሉንም ኃጢዓታችንን ያጥበዋል ፡፡ በ 1ቆሮ (6፡ 9-11) ጳዉሎስ ሁሉም ኃጢዓተኞች በክርስቶስ ስም እና በእግዚአብሄር መንፈስ እንደ ታጠብን፣ እንደ ተቀደስን እና እንደ ፀደቅን ገልጾአል ፡፡ ቲቶ (3፡ 3-5) “ እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተዉል ነበርንና….ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሄር ቸርነት ….በተገለጠ ጊዜ …..አዳነን እንጂ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ስራ እንዳይደል “ አመልክተዋል ፤ ይህ ኢየሱስ ጴጥሮስን እግሩን ብቻ እንጂ በሙሉ እንደ ገና መታጠብ እንደ ማያስፈልገዉ ለምን እንደ ነገረዉ ይገልፃል ፡፡ የኢየሱስ ንግግር በህይወት ስንኖን (ስንጓዝ) እንደተፈጠረ ያለሟቃረጥ ኃጢዓታችንን ንስሀ እንድንገባ እንጂ ድነታችንን እንደማናጣዉ አመልክቷል ፡፡ ይህ እዉነት መጀመሪያ በአሮን እና በልጆቹ እንደ ካህን በመለየት የታየ ነበር ፤ በዘጸ (29፡ 4) አሮን እና ልጆቹ ለአገልግሎት በተለዩ ጊዜ በዉሃ ታጠቡ ነገር ግን በዚያ የማንፃት ተግባር ያ የመጀመሪያ ጊዜ ነበር ፡፡ በዘጸ (30፡ 17-18) እግዚአብሄር ሙሴን በመገናኛዉ ድንኳን እና በመሰዊያዉ መካከል የነሀስ መታጠቢያዉን እንዲያስቀምጥ አዘዘዉ ፤ መቼም ቢሆን ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ “ አሮንና ልጆቹም እጆቻቸዉንና እግሮቻቸዉን ይታጠቡበታል “ (ዘጸ 30፡ 19-21) ፡፡ በኑሮአችን ንስኃ ያልገባንባቸዉ ኃጢዓቶች በሚኖሩ ጊዜ ከእግዚአብሄር አንሰማም ፤ ኃጢዓታችንን በመናዘዝ ግንኙነታችንን ይጠነክራል ፡፡

ዮሐንስ (13፡ 12-16)፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለሚከተሉት ሌሎችን የማገልገል ምሳሌ ሰጣቸው ፤ ኢየሱስ ሌሎችን ለማገልገል የትህትና ልብ እንዲኖራቸዉ ፈለገ ፡፡ ኢየሱስ ከልብ መቀየር ዉጪ የዉጪ ገለፃ አልነበረም ፤ በማቴዎስ 23 በዚያ ነዉ ፈሪሳዊያንን የጠራቸው ፤ ኢየሱስ ሁሉንም እንደ ምናደርገዉ ተቀብለን በትህትና ላይ እንድንመሰረት ተጠርተናል ፡፡ ክርስቶስ እንድንሆን ለጠራን ሁሉም ነገር መሆን ስንፈልግ ምን እንደ ሆንን እና በትህትና እንደ ምንጓዝ እናውቃለን ፡፡

ዮሐንስ (13፡ 17)፡ “ ይህን ብታዉቁ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ “ ፤ እነዚህን ነገሮች ስናደርግ በረከት ይመጣል ፡፡ ዶናልድ ካርሶን ያለው፡ “ስለ እነርሱ አንዳንድ ጊዜ ማንኛዉንም ነገር የሚያደርጉ በጣም አጥባቂ ለሆኑት ደቀ መዛሙርቶች ፍላጎት ልባዊ አሜን የሚያሰሙ አይነት አጥባቂ ኃይማኖተኞች አሉ ! “ ፤ ያዕ (1፡ 22) አማኞች “ ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ሰሚዎች ብቻ አትሁኑ “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ኢየሱስ ቃሉን የሚያደርግ እንደ ሚባረክ ተናግሯል ፡፡

መዝጊያ

ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጆች እንደ ሆናችሁ እንድታዉቁ ይፈልጋል እንዲሁም እንደ እርሱ ልጆች በትህትና እንድትጓዙ ይፈልጋል ፡፡

3 D. A. Carson, The Gospel According to John (Leicester, England: Inter-Varsity Press, and Grand Rapids: Wm. B. Eerdmans Publishing Co., 1991), p. 496; quoted in Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: John, p. 253; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/john.pdf.

  1. Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 276.

  2. Wiersbe, p. 276.

ጥያቄዎች

  1. ኢየሱስ ጴጥሮስን “ ካላጠብኩህ ከኔ ድርሻ የሌህም “ ለምን አለው ?
  2. በዮሐ (13፡ 14-15) ኢየሱስን የሌሎችን ሰዎች እግር እንድናጥብ ወይስ በቀላሉ ራሳችንን ዝቅ በማድረግ ሌሎችን እንድናስተምር እያዘዘን እንደ ሆነ ታስባላችሁ ?
  3. በዮሐ (13፡ 27) ኢየሱስ ለይሁዳ “ የምታደርገዉን ፈጥነህ አድርግ “ ለምን እንዳለዉ ምን ታስባላችሁ ?
  4. በዮሐ (13፡ 34) ኢየሱስ እርስ በእርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትዕዛዝ እሰጣችኋለሁ “ ይህን ለምን እንዳዘዘ ምን ታስባላችሁ ? (ዘሌ 19፡ 18)
  5. በዮሐንስ 13 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin John 13:3–5

“Jesus knew that the Father had given everything into His hands, that He had come from God, and that He was going back to God. So He got up from supper, laid aside His robe, took a towel, and tied it around Himself. Next, He poured water into a basin and began to wash His disciples’ feet and to dry them with the towel tied around Him.”

ኢየሱስ ይህን ዓለም ትቶ ወደ አባቱ የሚሄድበት ሰዓት እንደደረሰ አውቋል፡፡ ኢየሱስ በዙሪያው ያሉትን ይወድ ነበር፥ እስከመጨረሻው ትንፋሹ ድረስም ያለውን አፈሰሰባቸው፡፡ እንደ እግዚያብሔር ልጅ የነበረውን ማንነት ተረድቶ ነበር፡፡ በማንነቱ በመተማመን ከሚራመድበት ከዚህ ስፍራ ኢየሱስ ሌሎችን ያገለግል እና ይወድ ነበር፡፡ ከፋሲካ በፊት በእራት ሰአት፥ በትህትና እግራቸውን በማጠብ ደቀመዛሙርቱን አገለገላቸው፡፡ ኢየሱስ ትንሽ ቆይቶ እንደሚሸጠው የሚያውቀውን የአስቆሮቱን ይሁዳ እግር ሳይቀር አጠበ፡፡

ሌሎችን ስትወዱ እና በትህትና ስታገለግሉ፥ የእግዚያብሔር ልጅ እንደመሆናችሁ በክርስቶስ ካላችሁ ማንነት ከሆነ ስፍራ አድርጉት፡፡ ውብ እና ድንቅ ሆናችሁ ለአላማ እንደተፈጠራችሁ እና በኢየሱስ ፍፁም እንደተወደዳችሁ ተቀበሉ፡፡ በዚህ ማንነት ስትራመዱ፥ በኢየሱስ እንደነበረው፥ መውደድ እና ማገልገል ከዚያም ትህትና ተፈጥሮአዊ ይሆኑላችኋል፡፡ ምን እንደምታደርጉ ሳይሆን፥ በክርስቶስ ማን እንደሆናችሁ ነው፡፡ የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠብ ኢየሱስ ምሳሌውን ሰጥቷችኋል፡፡ ዋና መጋቢ፣ አስተማሪ፣ ሥራ አስኪያጅ፣ ርዕሰ መምህር፣ ወይም ልጆችን የሚያሳድጉ እናት እና አባት ትሆናላችሁ፥ ቢሆንም ግን ሌሎችን እንድታገለግሉ እና እንድትወዱ ተጠርታችኋል፡፡ ለአንድ ደቂቃ ቆም በሉ እና ጌታን ጠይቁት፥ ዛሬ አንድ ብርጭቆ ውሃ ለማን በፍቅር ላቅርብ? የማንን ቆሻሻ ልይዝ እችላለሁ? የማንን ቆሻሻ እግር ልጠብ? ዙሪያችሁን ተመልከቱ፡፡ ሌሎችን መውደድ እንድትችሉ ኢየሱስ ወዷችኋል፡፡

“ኢየሱስ አብ ሁሉን በልጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥ ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ። ”

—ዮሐንስ 13:3–5

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ዮሐንስ 1:12 — “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው”
  • ፊልጵስዩስ 2:3–5 — “ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ። በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። ”
  • 1ኛ ጴጥሮስ 5:5ለ–6 — “ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል። እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 81