Let Not Your Hearts Be Troubled
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዮሐንስ 13 መጨረሻ ላይ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን አንድ ሰዉ አሳልፎ እንደ ሚሰጣቸዉ ነገራቸው ፤ በዚያዉ ጫፍ(በዚያዉ ላይ) ላይ ኢየሱስ የጴጥሮስን ክህደት አመለከተ ፤ ነገር ግን ያ ጠቅላላ አልነበረም ! ደግሞም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን አሁኑ የተዋቸዉ እንደ ሚሆን ነገራቸው ፡፡ ሁሉም መጥፎ ዜናዎች ልባቸዉን አስደነገጣቸው ፡፡
ትምህርት
ዮሐንስ (14፡ 1)፡ በኢየሱስ በማመን ልባችንን የደነገጠ ከመሆን መከላከልን መርዳት እንችላለን ፤ በኢየሱስ ማመን ማለት ድነት አለን እንዲሁም ወደ ሰማይ እንሄዳለን ማለት ነው ፡፡ ይህ ልባችንን የደነገጠ ከመሆን ይረዳዋል ፡፡
ዮሐንስ (14፡ 2)፡ ዋይርስቤ “ ሰማይ የኃይማኖት አሳብ ዉጤት አይደለችም “ ይላል ፤ ሰማይ(መንግስተ ሰማይ) አባታችን የሚኖርበት ነው ፤ መንግሰተ ሰማይ ኢየሱስ የሚኖርበት እና ስለኛ የሚማልድበት ነው ፤ ይህ እዉነት ብቻዉን ልባችሁን ከድንጋጤ ይጠብቀዋል ፡፡ ማንኛዉም ሰዉ ወደ መንግስተ ሰማይ አይሄድም ፤ ክርስቶስ በሰማይ ዉስጥ የሚገኘዉ መሲሁ እንደ ሆነ የሚያምኑ ብቻ ናቸው (ሐዋ 4፡ 12) ፡፡ በክርስቶስ ይህ ድነት በሚኖረን ጊዜ በመንግስተ ሰማይ ቦታ አለን ፤ በተጨማሪም መንግስተ ሰማይ፡
- መንግስት ናት - “ እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግስት መግባት በሙላት ይሰጣችኋል “ (2ጴጥ 1፡ 11) ፡፡
- ርስት ናት - “ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ እድፈትም ለሌለበት ለማያልፍ ርስት ….ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል “ (1ጴጥ 1፡ 4) ፡፡
- ሀገር እና ከተማ ንት - “ አሁን ግን የሚበልጠዉን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና “ (ዕብ 11፡ 16) ፡፡
- ሰማይ ቤት ናት - “ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር ፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና “ (ዮሐ 14፡ 2) ፡፡
ሮበርት ፍሮስት “ ቤት በሄዳችሁበት ጊዜ በዉስጡ የምትቀመጡበት ቦታ(ስፍራ) ነዉ “ ብሏል ፤ በልባችሁ በጊዜያት ዉስጥ ችግር ሲያገኛችሁ ዘላለማዊዉ ላይ አትኩሩ ፡፡
ዮሐንስ (14፡ 3)፡ በሪቫይቭ ት/ቤት ስራችን ለክርስቶስ መመለስ እናንተን ማዘጋጀት ነው ፡፡ ሐዋ (1፡ 11) ኢየሱስ ልክ እንደ ሄደ ተመልሶ እንደ ሚመጣ ይነግረናል ፤ ዳን (7፡ 13) ኢየሱስ በሰማይ ደመናት ላይ ተመልሶ እንደ ሚመጣ ይናገራል ፡፡ ኢየሱስ ተመልሶ የሚመጣ ነው !
ዮሐንስ (14፡ 4-5)፡ ደቀ መዛሙርቱ የት እንደ ሚሄድ አላወቁም ስለዚህ የቶማስ ጥያቄ ምክንያታዊ ነበር ፤ ወደ ቢታኒያ ወይም ወደ ኢየሩሳሌም በጣም ባነሰ ደግሞ ወደ ሰማይ ይሂድ አያውቁም ፡፡
ዮሐንስ (14፡ 6)፡ ኢየሱስ ለቶማስ ጥያቄ በመልሱ ሌላ “ እኔ “ የሚል ንግግር ተናገረ “ እኔ መንገድና እዉነት ህይወትም ነኝ “ (ቁጥር 6) በማለት ፡፡ ቶማስ ኢየሱስ ወደ ሚሄድበት መንገዱን አያውቅም ፤ ልቡ የተቸገረ እንዳይሆን እንዴት መጠበቅ እንዳለበት አያዉቅም ፡፡ ኢየሱስ ቶማስን እና ደቀ መዛሙርቱን መንገዱን ነገራቸው ፤ መንገዱ ኢየሱስ ነበር !
አንዳንድ ጊዜ የአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ቁጥር 6 ለይቶ በማንሳት የምንወደዉን ምርጡን እንመርጣለን ፤ ኢየሱስ እዉነት እንደ ሆነ እንመርጣለን ፤ ኢየሱስ ትንሳኤና ሕይወት እንደ ሆነ እንመርጣለን ፤ ነገር ግን በጠባቡ መንገድ መከተልን አንፈልግም ፡፡ ኢየሱስ የእምነትን ትንሽ አስቀያሚ መንገድን እንድንቀበል በሚጠይቀን ጊዜ አንፈልገዉም ፤ ነገር ግን በኢየሱስ ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ አይመጣም ፡፡ የሰማይ ብቸኛ መንገድ ስለሆነዉ ስለ ኢየሱስ ለጠፉት ሰዎች በፍፁም ስላልነገርናቸዉ ፖለቲካሊይ ትክክል በመሆን በጣም የምናተኩር መሆን እንችላለን ፤ የቅርብ ጊዜ የኢየሱስ ተከታዮች “የመንገዱ(የሁኔታዉ) “ተከታዮች በመባል ይታወቃሉ ፡፡
ዮሐንስ (14፡ 7-11)፡ በአሁን ሰዓት አብን ማወቅ ልባችን የተቸገረ እንዳይሆን ይረዳዋል ፤ ኢየሱስን የምታዉቁ ከሆነ አባቱን (አብን) ታዉቃላችሁ ፤ አሁኑ አባቱን(አብን) ማግኘት(መልመድ) ትችላላችሁ ፡፡ እርሱን ለማግኘት(ለመቅመስ) በዘላለማዊ ሁኔታ መጠብቅ አይጠበቅባችሁም ፡፡
ዮሐንስ (14፡ 12-15)፡ ልባችሁን የተቸገረ(የደነገጠ) ከመሆን መጠበቅ ትችላላችሁ ምክንያቱም የፀሎት እድለኞች ናችሁ (የመፀለይ መብት አላችሁ) ፡፡ ክርስቶስ ስለ እኛ ባደረገልን በሁሉን ቻዩ እግዚአብሄር ፊት የመምጣት መብት አለን ፡፡
ዮሐንስ (14፡ 16-17)፡ ግራ የተጋባ ከመሆን ልባችሁን መጠብቅ ትችላላችሁ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ስላላችሁ ፤ ህይወትን በሚገባ እንድንጋፈጥ እንደ ሚያስችለን መንፈስ ቅዱስን እናስባለን ፡፡ እርሱ የእዉነት መንፈስ ነው በፍፁም እዉነት ያልሆነ ማንኛዉንም ነገር አያሳስበንም ያጠነክረናል እንጂ ፡፡
ዮሐንስ (14፡ 18-24)፡ በአብ ፍቅር እየተደሰታችሁ ልባችሁን ግራ የተጋባ ከመሆን መጠበቅ ትችላላችሁ ፡፡
ዮሐንስ (14፡ 25-31)፡ የእግዚአብሄር ስጦታ የሆነ ሰላም ስላላችሁ ልባችሁን የተቸገረ ከመሆን መጠበቅ ትችላላችሁ ፤ በክርስቶስ ከሆናችሁ ይህ ሰላም አላችሁ ፡፡
መዝጊያ
ለማስታወስ ዋረን ዋይርስቤ ልባችንን የተቸገረ (ግራ የተጋባ) ከመሆን መጠበቅ የምንችልበትን አምስት መንገዶች ሰጥቶናል ፡
ወደ ሰማይ ትሄዳላችሁ (ዮሐ 13፡ 36 – 14፡ 6) ፡፡
በአሁኑ ሰዓት(አሁኑኑ) አብን ታዉቁታላችሁ (ዮሐ 14፡ 7-11) ፡፡
የመፀለይ መብት አላችሁ (ዮሐ 14፡ 12-15) ፡፡
መንፈስ ቅዱስ አላችሁ (ዮሐ 14፡ 16-18) ፡፡
የአብን ፍቅር ታጣጥማላችሁ (ዮሐ 14፡ 19-24) ፡፡
Warren W. Wiersbe, Wiersbe Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2007), p. 272.
Robert Frost, “The Robert Frost Reader: Poetry and Prose,” (New York: Henry Holt and Co., 1972) p. 24.
Warren W. Wiersbe, “Be Transformed: Christ’s Triumph Means Your Transformation” (Colorado Springs: David C. Cook, 1986), pp. 34–46.
ጥያቄዎች
-
በዮሐ (14፡ 5) ቶማስ ኢየሱስን የሚሄድበትን መንገድ እንዴት እንደ ሚያዉቁ ጠየቀዉ ፤ ኢየሱስ “ እኔ መንገድና እዉነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም “ ብሎ ለምን መለሰለት ? (ቁጥር 6)
-
በዮሐ (14፡ 14) ኢየሱስ “ ማናቸዉንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ “ አለ ፤ በኢየሱስ ስም ጠይቃችሁ እንኳን እግዚአብሄር ፀሎታችሁን ላለመመለስ የመረጠበት ጊዜ ኖሯችሁ ያውቃል አዋ ከሆነ ለምን ? (ሮሜ 14፡ 23, ያዕ 4፡ 3)
-
የእግዚአብሄር ትዕዛዛትን መጠበቅ እንዴት እርሱን እንደምትወዱት ያሳያል ? (አሞ 3፡ 3, ዕብ 11፡ 5)
-
በዮሐ (14፡ 8-9) ከሰዎስት አመት ከግማሽ በኋላ ፍልጶስ ኢየሱስ በአብ አብ ደግሞ በእርሱ እንዳለ ያልገባዉ እንዴት ነበር የሚቀለው ?
-
በዮሐንስ 14 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin John 14:1, 6
“Your heart must not be troubled. Believe in God; believe also in Me . . . Jesus told him, “I am the way, the truth, and the life. No one comes to the Father except through Me.”
ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ በቀጥታ ተናገረ፥" ልባችሁ አይታወክ፡፡ በእግዚያብሔር እመኑ በእኔም ደግሞ እመኑ፡፡ " ከዚያም ኢየሱስ በሰማይ ሄዶ ሰለሚያዘጋጀው ስፍራ ከነገራቸው በኋላ፥ ኢየሱስ ሌላ የ"እኔ ነኝ" መግለጫ ሰጣቸው፡ " እኔ መንገድ እና እውነት ሕይወትም ነኝ፡፡" ኢየሱስ በምድር ላይ የነበረው ጊዜ ለመፈፀም እየቀረበ መሆኑን ስለተረዳ፥ ብዙ ቃላትን ከመጠቀም ይልቅ ወደ ዋናው ነጥብ ወዲያው ይሄድ ነበር፡፡
ለዛሬም ተመሳሳይ ነው አትሉም? የሰዎች ልብ ታውኳል፡፡ በእያንዳንዱ አቅጣጫ መንገዱን፣እውነቱን እና ሕይወቱ ይፈልጋሉ፡፡ሰኬትን ይፈልጋሉ፡፡ እያንዳንዱን ሁኔታ በቁጥጥር ስር አውሎ ለመቆየት ይሞክራሉ፡፡ ብዙ ሀይማኖቶችን እና ፍልስፍናዎችን ይመረምራሉ፡፡ ነገር ግን የእግዚያብሔር ቃል እንዲህ ይላል፥ " ኢየሱስ መንገድም፥ እውነትም፥ ሕይወትም ነው፡፡" በኢየሱስ እመኑ እና ትድናላችሁ፡፡ ልቡ የታወከ እና መንገዱን የሚፈልግ አንደ ሰውን ታውቃላችሁ? ለእርሱ ወይም ለእርሷ ፀልዩ፡፡ ጌታ እንደሚመራችሁ፥ በክርስቶስ የሆነውን የመዳንን መንገድ አካፍሏቸው እና በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር እና ፀጋ አማካኝነት የምትፈልጉትን ነገር እንዴት እንዳገኛችሁ አካፍሏቸው፡፡ ጌታ ብዙዎችን ወደ አዳኙ ፀጋው ይምራ፡፡ መንገዱን ስላገኙ ልባቸው ከእንግዲህ ወዲህ አይታወክ፡፡ አዎን፥ ጌታ ሆይ፥ በአንተ መገኘት የሚያስፈልጋቸው የጠፉ ሰዎችን አድን፡፡ አሜን!
“ ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።. . . ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”
—ዮሐንስ 14:1, 6
ተጨማሪ ጥቅሶች
- የሐዋርያት ሥራ 4:12 – “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። ”
- ሮሜ 10:9 – “ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና ”
- 1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5 – “አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡”
የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 82
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።