ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዮሐንስ 14-17 የኢየሱስ የመጨረሻ ቃላቶች ለደቀ መዛሙርቱ ወደ መስቀል ከመሄዱ በፊት የሽኝት ሰፊ ንግግርን ይይዛል ፡፡ ዮሐንስ በማሰብ ስለ ኢየሱስ መለኮታዊነት እያሳየ ነበር ፤ በወንጌሉ ይህን ያደረገበት አንዱ መንገድ በሰባቱ “ እኔ “ በሚሉት ንግግር ነበር ፡፡ እስካሁን ከሰባቱ “ እኔ “ ከሚሉት ንግግሮች ስድስቱን ተመልክተናል፡ 1) እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ ፤ 2) እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ፤ 3) እኔ የበጎች በር ነኝ ፤ 4) እኔ መልካም እረኛ ነኝ ፤ 5) እኔ ትንሳኤ እን ህይወት ነኝ እና 6) እኔ መንገድም እዉነትም ህይወትም ነኝ ፡፡ ዛሬ የመጨረሻዉን “ እኔ “ የሚለዉን ንግግር እንመለከታለን ፡ “ እኔ እዉነተኛ የወይን ግንድ ነኝ “ ፡፡
ትምህርት
ዮሐንስ (15፡ 1)፡ አንዳንድ ትርጉሞች እንደ አትክልተኛ ወይም እንደ ወይን አሳዳጊ አባት አላቸዉ ፤ ኢየሱስ እዉነተኛ የወይን ግንድ እንደ ሆነ አጥብቆ ተናገረ ፤ ማን እንደ ሆነ ስለ እርሱ የሆነ ነገር ለመናገር እየሞከረ ነበር ፡፡ እርሱን ከሌሎች የወይን ግንዶች የተለዬ የሚያደርግ የተለየ ንግግር ነው ፡፡ በብሉይ ኪዳን እስራኤል በእግዚአብሄር እንደ ተተከለ የወይን ግንድ ተጠቅሳለች፡
- እስራኤል እንደ ወይን ተክከል፡ “ ከግብፅ የወይን ግንድ አመጣህ ፤ አሕዛብን አባረርህ እርስዋንም ተከልህ ፡፡ በፊትዋም ስፍራን አዘጋጀህ ስሮችዋንም ተከልህ ምድርንም ሞላች ፡፡ ጥላዋ ተራሮችን ከደነ ጫፎችዋም እንደ እግዚአብሄር ዝግባ ሆኑ ቅርንጫፎችዋንም እስከ ባህር ቡቃያዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች ፡፡ አጥርዋን ለምን አፈረስህ ? መንገድ አላፊም ሁሉ ይቀጥፉታል ፡፡ የዱር እሪያ አረከሳት የአገር አዉሬም ተሰማራባት “ (መዝ 80፡ 8-13) ፡፡
- እስራኤል እንደ ተመረጠ የወይን ተክል፡ “ እኔ የተመረጠች ወይን ፍጹምም እዉነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር ፤ አንቺ ግን ክፉ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ ? “ (ኤር 2፡ 21) ፡፡
በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄርን እስራኤልን እንደ ራሱ የወይን አትክልት ተከላት ነገር ግን እስራኤል እግዚአብሄር ወደ ማይፈልገዉ ነገር አደገች ፡፡ እስራኤል ከንፁህ ዘር ተለየች ፤ የኢየሱስ ንግግር አባቱ እግዚአብሄር በእስራኤል ተክሎት በነበረው ከንፁሁ ዘር በትክክል ያደገ እንደ ነበር ነበር ፡፡ ኢየሱስ እግዚአብሄር የፈለገዉ ትክክለኛዉ የወይን ግንድ እንጂ በምድረበዳ የተበተነዉ አይደለም ፡፡ ኢየሱስ እና እስራኤል አባታቸዉ ተመሳሳይ አትክልተኛ ነበራቸው ፤ የኢየሱስ የወይን ግንድ እግዚአብሄር በአብርሃም ከተከለዉ ንፁህ ዘር ጋር ተመሳሳይ የወይን አትክልት ነው ፤ በሙሉ ጤንነት ባደገ ጊዜ እንዲመስል የነበረዉ የእግዚአብሄር እቅድ መልክ ነው ፡፡
ዮሐንስ (15፡ 2)፡ “ ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለዉን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል ፤ ፍሬ የሚያፈራዉንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል “ ፤ በቁጥር 2 “ እሱ “ እግዚአብሄር ነው ፤ እግዚአብሄር ፍሬ የማያፈሩትን ቅርንጫፎች ያስወግዳቸዋል(ይቆርጣቸዋል) ፡፡ ኢየሱስ ይህን እዉነት በጣፋጭ ነገር አልሸፈነዉም ፡፡ እግዚአብሄር ፍሬ የሚያፈሩትን እንዲያፈሩ ይከረክማቸዋል ፤ ኢየሱስ በሁለቱም ምድብ አይነት ሰዎች የሚያፈሩ እንዲሆኑ ሁሉንም ሰዎች ደረሳቸው ፡፡ ፍሬ የማያፈሩት የማያምኑ ናቸው ፤ ከወይን ግንዱ ጋር ስላልተገናኙ ማፍራት አይችሉም ፤ ጠዉልገዉ ይሞታሉ ምክንያቱም ከወይኑ ግንድ ጋር ስላልተገናኙ ፡፡ ኢየሱስ በቁጥር 6 “ በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ዉጭ ይጣላል ይደርቅማል ፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉዓቸዋል ያቃጥሉአቸዉማል “ ባለ ጊዜ ይህን ስዕል በደንብ ግልፅ ያደረገዉ ነው ፡፡
ይህ ከባድ ነገር ይናገራል ነገር ግን ኢየሱስ እዉነተኛ የህይወት ምንጭ ከሆነ እና ከህይወት ምንጭ ጋር የማትገኛኙ ከሆነ ሞትን የመረጣችሁ ናችሁ ፤ ምርጫችሁ ህይወት መስጠት ከሚችለዉ ብቸኛዉ ምንጭ ተቆርጣችኋል ፡፡ ቅርንጫፍ ከምንጩ የተቆረጠ ከሆነ ይሞታል ፤ ከወይን ግንዱ ጋር ያለዉ ግንኙነት በህይወት መኖሩን የሚጠብቅለት ነው ፤ ከዚያ ግንኙነት ዉጪ ቅርንጫፉ አይኖርም ፡፡
ኢየሱስ የደረሳቸዉ ሁለተኛዉ ቡድኖች ፍሬ የሚያፈሩት ሰዎች ነበሩ ፡፡ ቅርንጫፎች ከወይን ግንዱ ጋር የተገናኙ ከሆኑ ፍሬ ያፈራሉ ምክንያቱም ከምንጩ ጋር ስለ ተገናኙ ፡፡ ፍሬ ከወይኑ ግንድ የሚፈስ ምግብ ማስረጃ ነው ፤ ነገር ግን ፍሬ ለሚያፈሩትም ክርከማ ይከናወንባቸዋል ፤ የተከረከመ መሆን እንደ ቀልድ ማለት አይደለም ፤ ነገር ግን ኢየሱስ ከእርሱ ጋር በምንገናኝ ጊዜ ፍሬ እንደ ምናፈራ እና እግዚአብሄር እንደ ሚከረክም በዚህም ብዙ ማፍራት እንደ ምንችል ምናፈራ ተናግሯል ፡፡ ከክርስቶስ ጋር የተገናኛችሁ ከሆናችሁ መከርከምን ጠብቁ እግዚአብሄር ብዙ እንድታፈሩ ይፈልጋልም መልካም አትክልተኛም ሊከረክም(ሊኮተኩት) ይገባዋል ፡፡ መከርከም አድስ ለሆነ ነገር እንዲያበቅል በዳ ቦታ(እድል) ለመስራት የሞቱትን በመቁረጥ የሚከናወን ነው ፤ ጤንነትን የመጨመር እና ወደ ሆነ ቅርፅ የመቀየር ሂደት ነው ፤ እግዚአብሄር በኑሮአችን ላይ በትክክል የሚያደርገዉ ይህን ነው ፡፡ ለአድስ ነገር እና ለእኛ በማጠራቀሚያ ላለዉ ሙሉነት ስፍራ ለመስራት በእኛ ዉስጥ በሙሉነት የማይኖሩ ነገሮችን ይከረክማል ፤ ክርከማ ይጎዳል ነገር ግን ለጥቅም ነው ፤ ክርከማ እግዚአብሄር ሊቀጣን የሚያደርገዉ ነገር አይደለም ፡፡ እግዚአብሄር ሊያሻስለን እና ሊባርከን ይከረክመናል ፡፡
በቁጥር 4 ኢየሱስ በቁጥር (1-17) ሰባት ጊዜ የተጠቀመበትን “ በእኔ ኑሩ “ የሚለዉን ሀሳብ አስተዋወቀ ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን የነገራቸዉ በጣም መሰረታዊ ነገር ፍሬ ማፍራት ከፈለጉ በእርሱ መኖር እንደ ሚያስፈልጋቸዉ ነበር ፡፡ ከኢየሱስ ተለይተዉ ምንም ማድረግ አይችሉም ፡፡ ጥቅሱን “ ከእኔ ተለይታችሁ የሆነ ነገር ማነድረግ ትችላላችሁ “ እንደ ሚል ለማንበብ ዝንባሌ አለን ፤ ነገር ግን ኢየሱስ ከእርሱ ተለይተን ምንም ማድረግ እንደ ማንችል ነዉ የተናገረው ፤ ስለዚህ ራሳችንን “ እንድናፈራ የተሰየምንነዉ ለምንድን ፍሬ ነው ? “ በተጨማሪም ያንን ለማድረግ በእርሱ እንዴት ታማኝ እንደምንሆን ? “ መጠየቅ ያስፈልገናል ፡፡
ዮሐንስ (15፡ 7-17)፡ ኢየሱስ ያወራዉ ስለ ምንድን ፍሬ ነው ? ለመጠቅለል ቀላሉ መንገድ ኢየሱስን የምንመስል እንድንሆን ማለት ነው ፡፡ ፍሬ ማፍራት የእርሱ ደቀ መዛሙርት እነማን እንደሆኑ ያረጋግጣል ፤ ኢየሱስ “ እርስ በእርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ “ አለ (ዮሐ 13፡ 35) እንዲሁም “ አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ ፤ በፍቅሬ ኑሩ ፡፡ እኔ የአባቴን ትዕዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር ትዕዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ “ (ዮሐ 15፡ 9-10) ፡፡ አብ ኢየሱስን ወደደዉ ፤ ኢየሱስ አብን ታዘዘዉ ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ስለ ወደዳቸው በእርሱ በመኖር ኢየሱስን ይታዘዙታል ፤ በእርሱ ሲኖሩ ወደ እግዚአብሄር ሙሉ መታዘዝ የሚወስደዉን ፍቅሩን ያውቃሉ ፡፡ ኢየሱስ “ እዉነት እዉነት እላችኋለሁ አብ ሲያደርግ ያየዉን ነዉ እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም ፤ ያ የሚያደርገዉን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና “ አለ (ዮሐ 5፡ 19) ፡፡ ኢየሱስ ሲያደርግ ያየነዉን በምናደርግ ጊዜ ፍሬ እናፈራለን ፤ የምናፈራዉ ያ ፍሬ የኢየሱስ መግለጫ ነው - ፍሬው ክርስቶስን መሳይ(ክርስቶስን መምሰል) ነው፡ “ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የዋህነት፣ ራስን መግዛት ነው “ (ገላ 5፡ 22-23) ፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ጉልበት በዉስጣችሁ በሚፈስ ጊዜ ከህይወት ምንጩ ከኢየሱስ ጋር ተመሳሳይ ማፍራት ትጀምራላችሁ ፡፡
በኢየሱስ መታመን ኢየሱስን ወደ መዉደድ ይመራል ፤ ኢየሱስን መዉደድ ወደ መታዘዝ ይመራል ፤ መታዘዝ ወደ ፍሬ ይመራል ፤ ፍሬ ክርስቶስን መምሰል ነው ፡፡ ይህ ሂደት የሚሽከረከር ነው ፤ ደግሞ ደግሞ እንደ ገና ይደገማል ፤ ኢየሱስን የመከተል የህይወት ኡደት ነው ፡፡ ልክ እንደ ኢየሱስ ማድረግ ልክ ኢየሱስ እንዳደረገው የምታገኙአችዉን ሁሉ ወንጌልን(መልካሙን ዜና) ማካፈልን ያካትታል ፡፡
ከወይኑ ግንድ ጋር ተገናኝታችሁ እንዴት ትቆያላችሁ ?
በቃሉ መቆየት ፤ በሪቫይቭ ት/ቤት እያደረጋችሁት ያለዉ ያንን ነው ፤ በቃሉ ቆይታችኋል (ትቆያላችሁ) ምክንያቱም ኢየሱስን እዚያ ስለ ምታገኙት ፡፡
ፀሎት ፤ ከማንኛዉም ጓደኛችሁ ጋር ወይም ከቤተሰብ አባላችሁ ጋር እንዴት ተገናኝታችሁ ትቆያላችሁ ? ከእነርሱ ጋር በማዉራት ጊዜ ታሳልፋላችሁ ፤ ፀሎት ከእግዚአብሄር ጋር ያላችሁ ግንኙነታችሁ ነው ፤ ከእርሱ ጋር ለማዉራት የምታሳልፉት ጊዜአችሁ ነው ፡፡
በኢየሱስ የምትኖሩ ከሆነ እርሱ በእናንተ ይኖራል ፀሎታችሁ እንደ ሚመለስ ትጠብቃላችሁ ምክንያቱም ከልቡ ስለ ምትጠይቁት ፤ ፍሬ የመጨረሻዉ ጎል አይደለም ፡፡ የእግዚአብሄር ክብር የመጨረሻዉ ጎል ነው ፡፡ ፍሬ ሰዎችን በትክክል እግዚአብሄር ማን እንደ ሆነ ሰዎችን ያመለክታል ፡፡
መዝጊያ
ኢየሱስን የምትወዱ ከሆነ ትታዘዙታላችሁ ፤ ክብር ወደ ሚቀበለዉ ወደ አብ ብዙ ሰዎችን የሚያመለክት ብዙ ፍሬ ማፍራት ትጀምራላችሁ ፡፡
ጥያቄዎች
-
በዮሐ (15፡ 2) ስለ ቅርንጫፎቹ “ የተከረከሙ “ መሆን ማለት ምን ማለት ነው ? እግዚአብሄር የከረከመባችሁን ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ ? በምን መንገድ ?
-
በዮሐ (5፡ 5) ኢየሱስ እርሱ የወይን ግንድ እኛ ደግሞ ቅርንጫፎች እንደ ሆንን ተናግሯል ፤ ኢየሱስ እያወራዉ ስላለዉ በህይወታችሁ ፍሬ አይታችሁ ታዉቃላችሁ ? በምን መንገድ ? ከእርሱ ተለይተን ምንም ማድረግ እንደ ማንችል ለምን አለ ?
-
ዮሐ (15፡ 13) ለእናንተ እንዴት ይናገራችኋል ? ይህን ቃል በቃል ትወስዱታላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አትወስዱትም ?
-
ኢየሱስ ተገደለ (ተሰቃየ) በብዙ እንደ ምንሰቃይ ነገረን ፤ ስለ ኢየሱስ ስትሉ የተሰቃያችሁ እንደ ሆነ ይሰማችኋል ? በምን መንገድ ?
-
በዮሐንስ 15 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin John 15:1-2
“I am the true vine, and My Father is the vineyard keeper. Every branch in Me that does not produce fruit He removes, and He prunes every branch that produces fruit so that it will produce more fruit.”
ኢየሱስ ሰባተኛውን የ"እኔ ነኝ" መግለጫ አሰተዋወቀ፡ " እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፡፡" በጥንቷ እስራኤል፥ ወይን ዋነኛ የግብርና ምርት ነበር፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ራሱን እንደ ወይን ግንድ፥ እግዚያብሔር አብን እንደ ገበሬ፥ እና በክርስቶስ የሚያምኑትን እንደ ቅርንጫፍ በምሳሌ መጠቀሙ አግባብ ነበር፡፡ የወይኑ ጠባቂ ተክሉ ምን እንዲመስል እንደሚፈልግ ያውቃል ስለዚህም ያጠራዋል፥ ጥሩ እንደሆነ በሚያውቅበት መንገድ ያድግ ዘንድ ፥ቅርንጫፎችን ይቆርጣል፡፡ በተመሳሳይ መንገድ፥ ብዙ ፍሬ ያድግ ዘንድ፥ እግዚያብሔር በሕይወታችሁ ውስጥ ፍሬ የማያፈሩ ቅርንጫፎችን ይቆርጣል፡፡
ኢየሱስ በእርሱ ካልኖራችሁ፥ ምንም ማድረግ እንደማትችሉ በግልፅ ተናግሯል፡፡ ምንም አይነት ፍሬ አታፈሩም፡፡ ምንም፡፡ አለቀ፡፡ ሕይወት የሚሰጥን ፍሬ ታፈሩ ዘንድ በእውነተኛው የወይን ግንድ በክርስቶስ ውስጥ መኖር አለባችሁ፡፡ በክርስቶስ መኖር ወይም መቆየት ማለት ከኢየሱስ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ማለት ነው፥ ይኸውም ቃሉን ማንበብ ወይም መፀለይ፡፡ ልክ ጓደኛችሁን እንደምታውቁት ፥ ከኢየሱስ ጋር ባላችሁ ሕብረት ጊዜ ማሳለፍን ቀጥሉ፡፡ በክርስቶስ ስትኖሩ፥ ፍሬያችሁ የክርስቶስን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት እና ራስን መግዛት ይመስላል፡፡በዙሪያችሁ ያሉት በእናንተ ወስጥ ይሄንን ፍሬ የሚያፈራው ምን እንደሆነ ለማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ ከዚያም እነርሱን ወደ ክርስቶስ በመጠቆም አብን ታከብራላችሁ፡፡
“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው። ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።”
—ዮሐንስ 15:1-2
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ዮሐንስ 15:5 — “እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። ”
- ዮሐንስ 15:8 — “ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል። ”
- ገላቲያ 5:22–25 — “የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 83
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።