The Spirit of Truth
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዮሐ (15፡ 26-27) የሚለው “ ዳሩ ግን ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእዉነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል ፤ እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋር ኖራችኋልና ትመሰክራላችሁ “ ፤ ኢየሱስ እዉነት ነው ፤ ከአብ የመጣ እና “ የእዉነትን መንፈስ “ ወደ እኛ ይልክልናል ፤ በዚህም የዚህን ምስክርነትን እንሸከማለን ፡፡ ለሆነ ነገር ዝግጁ የሚያደርገን መንፈስ ቅዱስ አለን ፡፡
ትምህርት
ዮሐንስ (16፡ 1-3)፡ “ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችኋለሁ “ (ቁጥር 1) ወደ ሁሉም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቶቹ ትምህርቶች ስንጠቅስ ስለ መንፈስ ቅዱስ መምጣት ነው ፡፡ “ እንዳትሰናከሉ “ የሚለዉ ነገሮች ያለማቋረጥ ከእግዚአብሄር ሊያርቁን መምጣታቸዉን ይሚገልፅ ነው ፡፡ እግዚአብሄር በእርሱ መገኘት በምንጓዝ ጊዜ ምንም ወደ እኛ ሊሆን እንደ ማይችል ቃል ገብቷል (መዝ 91፡ 3-12) ፡፡ በዮሐ (16፡ 2) ኢየሱስ የገለፃቸው “ እነሱ “ ኃይማኖተኞቹ ክርስቶስን የሚከተሉትን እንደ ሚቀጡዓቸዉ ነው (ዮሐ 9፡ 22) ፡፡
በመንፈሳዊ ዉጊያ እንኖራለን በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ጠላትን እንኳን አታዉቅም ፡፡ የመነቃቂያ ጊዜ የተገኘው የምናደርገዉን ለማስቆም የሚሞክሩ በኑሮአችን መንፈስ ቅዱስ እያደረገ ያለዉን መቆጣጠር ስለ ማይችሉ በማይወዱን ኅይማኖተኞች ነው ፡፡ በክርስቶስ ወንጌል ወደፊት ስንጓዝ ሰዎች የተናደዱ እንደሚሆኑ እና በእኛ እንደ ሚፈሩ መጠበቅ አለብን ፤ ካልሆኑ በእግዚአብሄር ፈቃድ እያደርግን እንደ ሆነ መጠየቅ ያስፈልገናል ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከማይወዱን ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለብን እንድንማር ይረዳናል ፤ ኢየሱስ “ በከንቱ ጠሉኝ “ አለ (ዮሐ 15፡ 25) ፡፡ ጊዜዉ ወደ ኢየሱስ መመለስ ሲቀርብ ተቃርኖዉ በይበልጥ ይጨምራል ፡፡ በአሜሪካ ስለ እምነት ዋጋ መክፈል አናይም ምናልባትም ምክንያቱ ክርስቶስ እንድናደርገዉ በጠራን ለማድረግ እየሄድን ስላልሆነ ፡፡ መዝ (35፡ 19) የሚለው “ በግፍ የሚጠሉኝ በላዬ ደስ አይበላቸው በከንቱ የሚጠሉኝም በአይናቸዉም አይጣቀሱብኝ “ ፤ መዝ (69፡ 4) የሚለው “ በከንቱ የሚጠሉኝ ከራስ ጠጉር በዙ ፤ በዓመፅ የሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ በረቱ ፤ በዚያን ጊዜ ያልቀማሁትን መለስሁ “ ፡፡
ቁጥር 2 “ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሄርን እንደ ሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል “ በሚል ይቀጥላል ምክንያቱም “ አብን እና እኔን አያዉቁኝምና “ (ቁጥር 3) ፡፡ ፊል (1፡ 28-30) “ ሁሉም መከራ ስለ እርሱ ኢየሱስ እንደ ነበረዉ ተመሳሳይ ፈተና “ እንደ ሚያገኘን አመልክቷል ፡፡ ለመከራ መጠብቅ እንችላለን እስከ ሞት ድረስ እንኳን ፤ አስቡት - ወደ ማህበረሰቡ በምንሄድ ጊዜ የጠፉት ከእኛ ጋር በፍፁም ጉዳይ አይኖራቸዉም ነገር ግን ኃይማኖተኝነት ነው ! ሁልጊዜ በቤት ነው ፡፡ ያየነው ሰዎች ልምዳቸዉን በብዙ ከፍማድረግ በሚፈልጉ ጊዜ እዉነትን ከፍ ለማድረግ አስቸጋሪ ንደ ሆነ ነው ፡፡
ኃይማኖተኞች በኢየሱስ እና በወንጌሉ ላይ የተቃረኑት(የተነሱት) ለምን ነበር ? ዳን ስቴዋርት (blueletterbible. Org) ስድስት ምክንያቶችን ያመለክታል (ይጠቁማል)፡
- የኢየሱስ ንግግሮች ከኃይማኖተኞች ስልጣን በለጠ (ዮሐ 7፡ 48-49) ፤ ኢየሱስ ስለ ኃይማኖት መሪዎች ስልጣን አይጨነቅም ምክንያቱም ሊያደርገዉ ከመጣዉ በላይ ልምድ እንዲበልጥ ስላልፈቀደ ፡፡
የኢየሱስ ተግባራት የኃይማኖት መሪዎችን በጣም አበሳጩዓቸው (ማቴ 12፡ 23-29) ፤ ስራዎቹ የእግዚአብሄር ልጅ እንደ ነበር መሰከሩ በዚህም የአይሁድ መሪዎች ተበሳጩ ፡፡
ኢየሱስ ለአይሁድ የኃይማኖት ስርዓት(ዘዴ) አስፈሪ ነበር ፤ ዮሐ (2፡ 13-15) ኢየሱስ መቅደሱን እንዳነፃዉ ይገልፃል ፤ ሁልጊዜ እዉነት በእምነት በማይጓዙ የተፈጠረን ዘዴ ያስፈራራል ፡፡
ኢየሱስ ለአይሁድ መሪዎች የህይወት መንገድ አስፈሪ ነበር ፤ በክርስቶስ አካል በፍፁም ግዛታዊነትን አልተረዳሁም ፤ በእዉነት ሁሉም በአንድ ላይ እንደ ክርስቶስ አካል ሲመጣ አድርገን እንደ ሆን አስቡት !
ኢየሱስ በተግባባቸዉ ሰዎች የኃይማኖት መሪዎች ተበሳጩ (ማቴ 11፡ 19; ሉቃ 7፡ 39) ፤ የኃይማኖት መሪዎች ከኃጢዓተኞች ጋር ማህበራዊ ህይወት አያደርጉም ምክንያቱም በሀሰት ኩራት ስለ ተሞሉ ፡፡
ብዙ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኖቻችን ማህበረሰባቸዉን አያንፀባርቁም ነገር ግን በተሰቀሉባቸዉ ያንፀባርቃሉ ፤ ክርስቶስ በእኛ ተሰቀለ (ሮሜ 5፡ 8) ፡፡ በጣም የተለያዬ የሆነች አንድ ቤተ ክርስቲያን ለመስራት ጊዜ የሚፈጁ የሚያድጉ ህመሞች እና ባህላዉ ጉዳዮች ይገጥሟታል ፡፡ ኢየሱስ እነዚህን ጉዳዮች እና የሚያሰናክሉ አጥሮች ለመቋቋም በማህበረሰባቸዉ ዉስጥ በመሰቀል (በመጠበቅ0 እንደ ሆነ ያስተዋዉቃል ፡፡
ኢየሱስ ለልምዳቸዉ ክብር አልነበረውም ፤ ቆላ (2፡ 6-8) የሚለው “ እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ ፤ ስር ሰዳችሁ በእርሱ ታነፁ እንደ ተማራችሁትም በሃይማኖት ጽኑ ምስጋናም ይብዛላችሁ ፡፡ እንደ ክርስቶስ ትምህርት እንደ ሰው ወግና እንደ አለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ “ ፡፡ ልማዶች በእግዚአብሄር ባላችሁ ጉዞአችሁ ዉስጥ የሚናገር ህይወት በማይሆኑ ጊዜ እንዲሄዱ የምትፈቅዱበት ጊዜ ነው (ማር 3፡ 4-6; ሐዋ 5፡ 29; ዕብ 5፡ 11 – 6፡ 3) ፡፡
ዮሐንስ (16፡ 4)፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እነዚህን ሁሉ ነገሮች ነግሯቸዉ እንደ ነበር ነገራቸዉ ስለዚህም የችግር ጊዜአቸዉ በመጣ ጊዜ አስጠንቅቋቸዉ እንደ ነበር እና በእነርሱ ዉስጥ የሚኖረዉ መንፈስ ቅዱስ እንደ ሚረዳቸዉ ተስፋም እንደ ገባላቸዉ ያስታውሳሉ ፡፡
መዝጊያ
ሁላችንም ይህን ጥያቄ ልንመልስ ይገባናል፡ እምነታችንን በእዉነት ላይ ወይስ በልምዶች ላይ ማስቀመጥ እንፈልጋለን ? ልምዶች አስፈላጊዎች ናቸው ፤ ቤተሰባዊ ልምዶች አስቂኝ ናቸው ፤ ነገር ግን እባካችሁ እነዚህን ልምዶች ከኢየሱስ ክርስቶስ በላይ እንዳታስበልጧቸው ፡፡ ካልተጠነቀቅን እንዲሆኑ መፈቀድ ቀላል ነው ፡፡
ማር (3፡ 26-27) የሚለው “ ሰይጣንም ራሱን ተቃዉሞ ከተለያየ መጨረሻ ይሆንበታል እንጂ ሊቆም አይችልም ፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ ኃይለኛዉን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃዉን ሊበዘብዝ የሚችል የለም ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል “ ፡፡
በኃይማኖተኝነት መንፈስ እያወራችሁ ከሆነ ሌሎች አማኞችን በአንድ ላይ በመሰብሰብ የክርስቶስ መንፈስ የኃይማኖተኝነትን መንፈስ እንዲያጣብቁዉ(እንዲይዘዉ) ፀልዩ ፡፡
ጥያቄዎች
-
በዮሐ (16፡ 2) ኢየሱስ “ ጊዜዉ እንደ መጣ “ ተናገረ በዮሐ (16፡ 1-3) በተነገረበት በእነዚያ ጊዜያት እንዳላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላሰባችሁም ?
-
ለኢየሱስ ወጥቶ መሄዱ እና አማካሪዉ መምጣቱ ለምን ነበር አስፈላጊነቱ ? (ዮሐ 14፡ 16, 15፡ 26)
-
በዮሐ (16፡ 33) ኢየሱስ ልብን እንደ ሚይዝ (“ መልካም ደስታ እንዲሆን “ NKJV) ተናገረ ምክንያቱም አለምን ስላሸነፈ ፤ ይህ ምን ማለት ነው ? እንዴት እንዲሰማችሁ ያደርጋችኋል ?
-
በዮሐንስ 16 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin John 16:13–14
“When the Spirit of truth comes, He will guide you into all the truth. For He will not speak on His own, but He will speak whatever He hears. He will also declare to you what is to come. He will glorify Me, because He will take from what is Mine and declare it to you.”
ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ከመሰናከል ለመጠበቅ ብዙ ነገር ነገራቸው ምክንያቱም ኃይማኖተኞች ወይም የማያምኑት ደቀመዛሙርቱን ለመጣል እና እግሮቻቸው እንዲሰናከሉ ለማድረግ እንደሚሞክሩ ያውቅ ነበር፡፡ነገር ግን ኢየሱስ የእርሱ የሆኑትን ሰዎች ወደ እውነት ሁሉ እንዲመራቸው በእውነት መንፈስ አስታጥቋቸዋል፡፡
በኢየሱስ እውነት በመራመዳችሁ በጥያቄ ውስጥ እንደሆናችሁ ተሰምቷችሁ ያውቃል? አስታውሱ፥ በክርስቶስ ውስጥ ስትኖሩ፥ ሥር እየሰደዳችሁ፥ በእርሱ እያደጋችሁ ፥ እና በእምነታችሁ እየፀናችሁ ነው፡፡ ከኃይማኖታዊ አስተሳሰብ እና ከባህል ባለፈ፥ ወደ እውነት ሁሉ እንዲመራችሁ እየፈቀዳችሁ በእውነት መንፈስ ተራመዱ፡፡ ይህ እውነት ለጌታ ክብርን ያመጣል ምክንያቱም የምትራመዱት የእውነት መንፈስ እንደሚነግራችሁ ነው፡፡ ዛሬ፥ የኃይማኖተኝነት መንፈስን በማሰር ፥ነፃነት በሕይወታችሁ እንዲነግስ በመፍቀድ፥ በእውነት መንፈስ ውስጥ ስሩ፡፡
“ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና።”
—ዮሐንስ 16:13–14
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 69:4 – “በከንቱ የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጕር በዙ፤ በዓመፅ ያሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ በረቱ፤ በዚያን ጊዜ ያልቀማሁትን መለስሁ። ”
- ዮሐንስ 16:1 – “እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። "
- ቆላስይስ 2:6–8 – “እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ፤ ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ። እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 84
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።