The Gospels John

Jesus' Prayer For Our Unity

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 17 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 195 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዮሐንስ 14-15 እንደ መሸኛ ንግግር የተጠቀሰ ነው ምክንያቱም ለደቀ መዛሙርቱ የኢየሱስን የመጨረሻ ትምህርቶች ይይዛል ፡፡ በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ኢየሱስ ለመጸለይ እንደሄደ የሚናገሩ ብዙ ማጣቀሻዎች አሉ ነገር ግን ብዙዎቹ የኢየሱስ ትክክለኛ ቃላቶችን አልመዘገቡም ፤ ኢየሱስ የታሰረ፣ የደከመ እና የተሰቀለ ከመሆኑ በፊት ያለዉ የልብ ምቱ እዚህ ያለን ያ ነው ፤ ይህ ፀሎት የኢየሱስ የክህነት ፀሎት በመባል ይጠራል ፡፡ ዕብ (4፡ 14-15) ኢየሱስን፡ እንደ ታላቅ ሊቀ ካህናችን …. በእኛና በእግዚአብሄር መካከል እንደ አስታራቂ …..ስለ እኛ በድካማችን እንደ ሚቆም ይገልፀዋል ፡፡ በዮሐንስ 17 ትክክለኛ ፀላይ ኢየሱስ አለን በተጨማሪም ዕብ (7፡ 23-25) የሚለው ስለ እኛ ለዘላለም እየማለደ ይኖራል ለዘላለምም ወደ እግዚአብሄር ስለ እኛ ይሄዳል በዚህም በዮሐንስ 17 የኢየሱስ ፀሎት ለእኛ አንድ ጊዜ ብቻ አልፀለየም ፡፡ አሁንም ይህ የኢየሱስ ፀሎት እንደ ሆነ አምናለሁ ! የኢየሱስ ፀሎት በዘሌዋዉያን 16 የታላቁ ካህን የአሮንን ፍሬ ነገር(ቅደም ተከተልን) የተከተለ ነው ፤ ስለ ህይወቱ እና ተልዕኮዉ ፀለየ (ቁጥር 1-5) ፤ ስለ ሰዎቹ ፀለዬ (ቁጥር 6-19) ፤ በተጨማሪም ለወደፊት አማኞች ፀለየ ( ቁጥር 20-29) ፡፡

ትምህርት

ዮሐንስ (17፡ 1-5)፡ እነዚህ ቁጥሮች የኢየሱስን ፀሎት መጀመሪያ ያካትታል ፤ ኢየሱስ ለራሱ በመፀለዩ ለራሱ መፈለግ አልነበረም ፤ ልቡ ለአባቱ ክብር ነበር ፡፡ ኢየሱስ የሚገጥመዉን ስለ ሚያዉቅ ከፍ የሚያደርገዉ እንዲሆን ፀለየ በዚህም አባቱ ያነሳዋል ፤ በቁጥር (2-3) እግዚአብሄር በላከዉ በአንዱ በኩል በድነት በኩል ዘላለማዊ ህይወት እንደ ሚገኝ ኢየሱስ ገለፀ ፡፡ ኢየሱስ ተጠይቆ የነበረዉን ተልዕኮዉን ለመጨረስ ተዘጋጅቶ እንደ ነበር እና እንደ ፈፀመ ተናገረ (ቁጥር 4-5) ፤ እነዚህ ቁጥሮች ወደ ኋላ ዮሐ (1፡ 1) ያገናኘናል፡ “ በመጀመሪያዉ ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሄር ዘንድ ነበረ ቃልም እግዚአብሄር ነበረ “ ፡፡

ዮሐንስ (17፡ 6-19)፡ ከዚያም ኢየሱስ ስለ ደቀ መዛሙርቱ ፀለየ ፤ ስለ ጥበቃቸዉ እና ስለ ሚቀጥለው ተልዕኮ ፀለየ፡፡

ዮሐንስ (17፡ 20-23)፡ ስለ ሰዎስት ምክንያቶች ለእኛ ይህ አስፈላጊ ንባብ ነው፡ የተመዘገበዉን የኢየሱስን ፀሎት ያካትታል፣ ኢየሱስ ከመታሰሩ በፊት የሚሆነዉን ይመዘግባል እንዲሁም ፀሎቱ ስለ እኛ ነው ፡፡ አንድንተን በመምረጥ ኢየሱስ ስለ ሁሉም ነገር ፀለየ (ቁጥር 21) ኢየሱስ አብ እና እርሱ አንድ እንደ ሆኑ ጠንካራ አንድነት እንደ ሆነው አንድ እንዲሆኑ ለእነርሱ ፀለየ ፤ በተመሳሳይ መንገድ አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ግለሰብ ቢሆኑም አንድ እግዚአብሄር እንደ ሆኑ አንድ ቤተ ክርስቲያን በመሆን የተለያየ አባላት እንድንሆን ተጠርተናል (ኤፌ 4፡ 4-5) ፡፡ አንድነታችን እግዚአብሄር እራሱ ምንድን እንደ ሚመስል ለአለም መስታወት እንዲሆን የተሰየመ ነው ፤ ይህን አካል ቀደን በምናስወግደዉ ጊዜ በግልፅ ለአለም የምናቀርበዉን የኢየሱስን መልክ እያሰናከልን ነው ፡፡ ስለ ኢየሱስ ትክክለኛ መልክ አስቡ ያንን ስዕል ብቻ በግልፅ ቀዳችሁ በምታስወግዱ ጊዜ ምን እንደ ሚሆን በአይምሯችሁ ሳሉ ፤ ኬቪን ድዮንግ የፃፈው፡ “ በሌሎች ሰዎች እና በሌሎች ቤተ ክርስቲያኖች ዉስጥ ሲሆን በማየት ደስተኛ በሆናችሁ ጊዜ በከተማችሁ በእዉነት መነቃቃት እንደ ምትፈልጉ ታውቃላችሁ “ ፡፡

አንድነት ማለት እንዳልሆነ በሆኑት ላይ እስኪ ግልፅ እናድርገው፡

አንድነት መመሳሰል አይደለም ፤ ለሆነ የሚያንስ የጋራ አካፋይ ሁሉንም ነገር ወደ ታች ማከፋፈል አይደለም ስለዚህም ሁሉንም በተመሳሳይ እንመለከታለን ፡፡ ሁሉም ሰዉ ተመሳሳይ ከሆነ አንድነት አያስፈልግም ፤ የአንድነት በጣም ትክክለኛዉ ሀሳብ በተለያዩ አካላት መካከል ግንኙነት ሲኖር ትርጉም ይሰጣል ፡፡ አላማው ሀሉም ሰዉ አምልኮ በተመሳሳይ ስታይል ተመሳሳይ ድርጊት ኖሮ በተመሳሳይ መንገድ ሲጀምሩ ማየት አይደለም ፤ ያ መመሳሰል ነው ፡፡

አንድነት በወንጌል መሰረት ልዩነቶቻችን እያሉ መንፈስ ቅዱስ አንድ ሲያደርገን ነው ….፤ አንድነት ማለት በሁለተኛ(በተጨማሪ) ጉዳዮች እንኳን የማንስማማ ብንሆንም አንድ ቤተሰብ ነን ማለት ነው ፡፡ በልዩነቶቻችን ምክንያት አንድነት ይሆናል ልዩነታችን ሳይከለክለን ፤ በብዙ አካል ስለ አንድ አካል የጳዉሎስን ትምህርት ወደ መዉሰድ በማዘንበል በአካባቢ አንድ ጉባኤ ላይ እንተገብራለን ፤ ነገር ግን እነዚህ አካሎች ጋላዊ ሰዎች ናቸው ፤ አንድነት ከዚያ ይበልጣል ፡፡ የክርስትና ጠቅላላ ጉባኤዎች እና ታሪካዊ መስመሮች(ወንዞች) ወደ አካሉ አስፈላጊ አካላትን ለመጨመር ይረዳሉ ፡፡

በመጠኑ የተቃዋሚ/አርሜኒያኒዝም ደጋፊ ወንዝን በልምድ እቅድ መስራት አድጌአለሁ ፤ ነገር ግን ለመፅሀፍ ጥልቅ ፍቅር እንዲኖረኝ ያስተማሩኝ በስነ መለኮታዊ ዶግማ/በተሸሻለ ወንዝ(ጠብታ) ዉድ ጓደኞች አሉኝ ፤ ስለ መንፈስ ቅዱስ ያስተማሩኝ በካሪስማቲክ/በጴንጤኮስታል ወንዝ (ጠብታን) ዉድ ጓደኞች አሉኝ ፡፡ መሄድ እችላለሁ ነገር ግን ሀሳቤን ሀሳቤን ታገኙታላችሁ - አንድኛችን ለአንድኛችን እናስፈልጋለን ! ሀሳቡ ይህ ነው ፤ በቤተ ክርስቲያን ዝቅ በማለት ልክ እንደ ወንድሞቻችሁ ማምለክ አይጠበቅባችሁም ነገር ግን በእዉነት ዝቅ በማለት ወንድሞቻችሁን ለማወቅ ዝቅ ማለት ያስፈልጋችኋል በተጨማሪም ስለ እግዚአብሄር ፍቅር በተመሳሳይ ቡድን እንደ ራሳችሁ ተግብሩ!

አንድነት መቻቻል አይደለም ፤ ኢየሱስ “ እርስ በእርሳችሁ በመቻቻላችሁ የኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ ያዉቃችኋል “ አላለም ፤ ይህ ለሌላ ቤተ ክርስቲያን በጣም አስፈላጊ ለመሆን ቀላል አይሆንም ፡፡ (ዮሐ 13፡ 35) ፡፡

መዝሙር 133 የአንድነትን መልክ ይሰጣል ፤ ይህ በኢየሩሳሌም ወደ መቅደሱ መንገድ ላይ በምስጋና ተዘምሮ የነበር ወደ ላይ የሚወጣ መዝሙር ነው ፡፡ እነዚህ ቃላቶች በእግዚአብሄር መሰዊያ ላይ እንደ እስራኤል ነገድ በአንድ ላይ በመምጣት በአንድነት ተዘመሩ ፤ በቁጥር 1 (ዳዊት) ፀሀፊዉ “እነሆ “ በማለት ጀምሯል - የእስራኤል ነገዶች ተሰብስበዉ በአንድነት ሲመጡ የሚያምር እና የሚደነቅ ነገር ነበር ፤ ያ አንድነት በእግዚአብሄር ሰዎች “ መልካም እና ያማረ “ ሁለቱንም ነው ፡፡ ዳዊት አንድነት ምንድን እንደ ሚመስል ብዙ ስዕሎችን ሰጥቷል ፡፡

መጀመሪያ በራስ በጢም ላይ እና እስከ ክህነት ልብስ ላይ እንደ ሚወርድ ዘይት ገልፆታል (ቁጥር 2) ፤ ዘይቱ የእግዚአብሄር መገኘትን ይወክላል ፡፡ የእግዚአብሄር ሰዎች በአንድነት በሚኖሩ ጊዜ የእግዚአብሄር መንፈስ ይገለጣል፡፡ ከወንድሞቻችን ጋር አንድነትን በምንፈልግ ጊዜ በዚያ ስፍራ እግዚአብሄር በረከትን አዟል ፤ እንዲሁም አሮን የተቀባዉ ዘይት ስለ ሌሎች ለየው ፡፡ አሮን ለእግዚአብሄር መሀከለኛ በመሆን እንደ ታላቅ ካህን እንዲያገለግል የተለየ ነበር ፤ የእስራኤል ሰዎች በአሮን በኩል እግዚአብሄርን ማግኘት ነበራቸው ፡፡ እንደ ክርስቲያን የዚህ ተመሳሳይ የካህናት ቤተሰቦች እና በዚህ አለም የእግዚአብሄርን መገኘት እና ይቅርታ የምናስፋፋ ነን (1ጴጥ 2፡ 9) ፡፡

የተመሳሳይ መቅደስ ካህናቶች እርስ በእርስ ጦርነት ላይ ከሆኑ አለም በእኛ እንዴት እግዚአብሄርን ያወቀዋል ?

በቁጥር 3 ዳዊት አንድነትን “ እንደ አርሞንዔም ጠል “ ገልፆታል ፤ አርሞንኤም ተራራ በእስራኤል ከፍተኛ ስፍራ እና አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ለእስራኤል ዉሃ የሚሰጥ በረዶ ይሰበስባል ፡፡ የቀለጠው በረዶ ወደ አለቱ ክፍል እና ቀዳዳዎች ዉስጥ በመስረግ ተራራው ስር ላይ ምንጮችን በመመገብ ትንንሽ ጠብታዎቹን እና ወንዞችን በመስራት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ይቀላቀላሉ ፡፡ መዝሙሩ ይህን ከእግዚአብሄር እንደ ሆነ በረከት ይገልፀዋል ፡፡ ዮርዳኖስ ወንዝ ኢየሱስ የተጠመቀበት ስፍራ ነበር ፤ እንዲሁም ፂዎንን (የእስራኤልን ምድር) ለሚመጣዉ ሰማይ እንደ ዘይቤዓዊ ነግግር የተጠቀመ ነው ፤ ስለሆነም ወንድሞች በአንድነት በሚኖሩ(በሚቀመጡ) ጊዜ የእግዚአብሄር በረከት ያዝዛል እንዲሁም በትክክል በሰማይ በብዙ ለዘላለም የሚጠብቀንን ክብር ስዕል ይሰጠናል ፡፡

መዝጊያ

በግልፅ ለሰማይ እየተለማመድን ነው ፤ ብዙ ጊዜ በትላላቅ ክስተቶች ጊዜ “ ከእናንተ ከሚለዩ ሰዎች በመቀጠል ለማምለክ የማትፈልጉ ከሆነ ሰማይን ማስወገድ ትፈልጋላችሁ “ እላለሁ ፡፡ በመሰባሰብ አይኖቻችንን ኢየሱስ ላይ በማድረግ የኢየሱስ ፀሎት መልስ እንሆናለን ፡፡

ጳዉሎስ ብዙ ጊዜ ለቤተ ክርስቲያን የሰዉን አካል ዘይቤአዊ አነጋገር ተጠቅሟል (ኤፌ 1፡ 22-23; ቆላ 1፡ 18) ፤ አንድ አካል ተመሳሳይ እራስ ያለዉ አንድ አካል ብቻ ይሆናል ፤ ራሱ ከተወገደ ህይወት አይኖረዉም ፤ አንድ ጭን በማስወገድ መኖር ትችላላችሁ ፡፡ ነገር ግን ራሱ ከተወገደ አካሉ ሙት ነው ፡፡

አ. ወ. ቶዘር የፃፈው “ ለእነንተ አንድ መቶ ፒያኖዎች ለተመሳሳይ መንታዎች ለእርስ በእርስ መተሳሰር በፍጥነት ሁሉም ተገናኝተዉ ያውቃሉ ? የተገናኙ በመሆን በመስማማት አንድ ናቸዉ እንጂ አንዱ ለአንዱ አይደለም ነገር ግን ለሌላዉ መለኪያ እያንዳንዳቸዉ በግላቸዉ ይነፋሉ(ይጮኻሉ) ፤ ስለሆነም አንድ መቶ አምላኪዎች በአንድ ላይ እያንዳንዳቸዉ ከክርስቶስ ዞረዉ የሚመለከቱት ምናልባትም በማሰብ አንድ መሆን እንደ ሚችሉ አይናቸዉን ከእግዚአብሄር በማዞር ስለ ተቀራረበ ህብረት ከመትጋት ይልቅ እርስ በእርስ በልባቸዉ የተቀራረቡ ናቸው “ ፡፡

ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን መዉደድ በመማር እና በአንድነት በመጓዝ በግልፅ ለሊቀ ካህናችን ለኢየሱስ ዘላለማዊ ፀሎት መልስ እንሆናለን ፡፡ ኢየሱስ በሚመለስ ጊዜ የሚመታዉ ለሙሽራዋ ነው….ለሙሽሮች አይደለም ፡፡

  1. A. W. Tozer, The Pursuit of God (Harrisburg, PA: Christian Publications, 2015), pp. 79–80.

ጥያቄዎች

  1. በዮሐ (17፡ 3) ኢየሱስ እንዴት ዘላለማዊ ህይወትን ገልፆታል ?
  2. በዮሐ ( 17፡ 4) በኢየሱስ ፀሎት ኢየሱስ “ እንዲያደርገዉ የሰጠዉን ስራ እንደ ፈፀመ “ ተናግሮ ነበር ፤ እግዚአብሄር እንዲያደርገዉ ሰጥቶት የነበረው ስራ ምን ነበር ? (ዮሐ 3፡ 16-17, 4፡ 34, 5፡ 20-21, 36፣ 14፡ 6)
  3. በዮሐ (17፡ 17) ኢየሱስ በምንድን እንደ ሚቀድሰን ተናገረ ? (ዮሐ 1፡ 1, 17፡ 19, ኤፌ 5፡ 25-26) ፤ የተቀደሰ መሆን ማለት ምን ማለት ነው ?
  4. በዮሐ (17፡ 20) ኢየሱስ ስለ ማን ፀለየ ? በደቀ መዛሙርቱ ቃል በኩል በእርሱ የሚያምኑ እነማን ናቸው ? እንዴት እንዲሰማችሁስ ያደርጋችኋል ?
  5. በዮሐ (17፡ 21) መሰረት አማኞች በአንድነት አንድ መሆን እንዲሁም በአብ እና በወልድ አንድ መሆን አላማዉ ወይም ጎሉ ምንድን ነው ? (ዮሐ 17፡ 23)
  6. በዮሐንስ 17 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin John 17:20, 23

“I pray not only for these, but also for those who believe in Me through their message . . . I am in them and You are in Me. May they be made completely one, so the world may know You have sent Me and have loved them as You have loved Me

ኢየሱስ ከመታሰሩ በፊት እና ከመሞቱ በፊት በነበረው ጊዜ፥ ሁሉንም አማኞች በመወከል በፀሎት ወደ አብ ሄደ፡፡ ለአንድነት ፀለየ፡፡ አብ እና ኢየሱስ አንድ እንደሆኑት ፥ ሁሉም አማኞች አንድ ይሆኑ ዘንድ ፀለየ፡፡ አማኞች በሰላም እና በአንድነት ሲኖሩ ፥ ዓለም እግዚያብሔር አብ እግዚያብሔር ወልድን እና የሚያምኑትን ሁሉ ምን ያህል እንደሚወድ እንዲያይ ፀለየ፡፡ እግዚያብሔር ሁሉንም ሰው ያለገደብ ይወዳል፥ ስለዚህም ዓለሙ ይህንን ፍቅር በተከታዮቹ እና በእርሱ በሚያምኑት እንዲያይ ይፈልጋል፡፡

ዓለም የክርስቶስን አካል የሚያየው እንዴት ነው? አማኞች በአንድነት ሲሰሩ ወይስ አማኖች የራሳቸውን ነገር ሲሰሩ ያያሉ? ኢየሱስ በምድር በቀረው በመጨረሻ ሰአት ስለ አንድነት ስለፀለየ ፥ በእርግጥ አንድነት ለኢየሱስ ልብ ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ለዚህ ነገር ምን ታደርጋላችሁ? ለአካሉ አንድነት እና መንፈስ ቅዱስ አካሉን በልዕለ ተፈጥሮአዊ መንገድ አንድ እንዲያደርግ ፀልዩ፡፡ ዓይኖቻችሁን በኢየሱስ ላይ ጣሉ እንጂ በማናቸውም ትናንሽ ነገሮች ላይ አይደለም፡፡ ዛሬ ደግሞ፥ ሂዱ እና ከሌላ ቤተክርስቲያን የሆነን አንድ ሰው የአንድነት ጊዜ እንድታደርጉ እና ስለ ኢየሱስ እንድታወሩ ጠይቁ፡፡ ወይም አንድ እርምጃ በመሄድ፥ እንደ አንድ አካል በአንድነት ሄዳችሁ ለጠፉት ኢየሱስን አካፍሉ፡፡ ከቤተክርስቲያናችሁ ግድግዳ ስትወጡ ምን እንደሚፈጠር ብቻ እዩ፡፡ ዓለም የአብን ታላቅ ፍቅር ያውቅ ዘንድ ኢየሱስ አካሉ አንድ እንዲሆን ካለው ልብ የተነሳ ነው!

“ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም . . .እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል። ”

— ዮሐንስ 17:20, 23

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 133:1 – “ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው። ”
  • ኤፌሶን 4:3–5 – “በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት”
  • ዕብራውያን 12:2 – “የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 85