The Gospels John

Peter's Denials; Jesus' Trials

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 196 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዮሐንስ 18 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለሞቱ እና ለትንሳኤዉ እያዘጋጀ የነበረበትን ክፍል ወደ መጨረሻዉ መጥተናል ፡፡ በላፉት ጥቂት ምዕራፎች ዉስጥ ይመጣ ስለ ነበረው፣ ደቀ መዛሙርቱ ይጠብቁት ስለ ነበረው እና እንዴት እንደ ሚመሩ የኢየሱስን ትምህርት ተመልክተናል ፡፡ በዛሬዉ ጥናታችን ያንን ወደ ጎን እናስቀምጠዋለን ምክንያቱም ኢየሱስ የነገራቸዉ ሁሉም ነገር ለመሆን እየጀመረ ስለ ሆነ ፡፡ ምዕራፍ 18 ላይ በኢየሱስ ፍርድ በኩል የሚወስዱንን አምስት ምልክቶች እንመለከታለን ፡፡

ትምህርት

ዮሐንስ (18፡ 1)፡ የቄድሮን ወንዝ በጌተሰማኔይ አትክልት ስፍራ እና በከተማዋ መካከል ከኢየሩሳሌም ምስራቅ በር ዉጪ ነው ፡፡ አንዳንዶች ይህ አትክልት ስፍራ የታጠረ(የተጠበቀ) እና የግል እንደ ነበር ይጠቁማሉ ፡፡ ዳዊትም ከራሱ ህዝብ ሲሸሽ የቄድሮን ሸለቆ አቋርጧል ፡፡

የመጀመሪያዉ ምልክት የአትክልት ስፍራው ሲሆን መታዘዝን ይወክላል (ቁጥር 1) ፤ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ወደ አትክልት ስፍራዉ ይሄዳል ፡፡ ሸሽቶ እየሮጠ አልነበረም ነገር ግን ያደርገዉ ወደ ነበረዉ ተጓዘ ፡፡ የሰዉ ታሪክ በኤደን ገነት ይጀምራል ነገር ግን አለመታዘዝ ወደ ገነቱ እና ወደ ሰዉ ልጅ ሁሉ ኃጢዓት አመጣ (ዘፍ 2፡ 8) ፡፡ ኢየሱስ በመታዘዝ ወደ አትክልት ስፍራዉ ሄደ በመጨረሻም በእርሱ ለሚታመሁ ሁሉ ፅድቅን እና ህይወትን አመጣ ፡፡ ታሪክ በመንግስተ ሰማይ ከተማ አንድ ቀን በሌላ አትክልት ስፍራ ያበቃል (ራዕይ 21-22) ፤ በዚያ ሞት፣ ሀዘን ወይም ህመም የሚኖር አይሆንም (ራዕ 22፡ 1-3) ፡፡ ዋይርስቤ የኤደን ገነትን እንደ አለመታዘዝ እና እንደ ኃጢዓት የአትክልት ስፍራ፣ ጌተሰማኔን እንደ የመታዘዝ እና የመገዝት አትክልት ስፍራ እና ሰማይን ደግሞ ለእግዚአብሄር ክብር እንደ ደስታ እና እርካታ ዘላለማዊ ስፍራ ገልጧል ፡፡

ዮሐንስ (18፡ 2-9)፡ ሁለተኛው ምልክት መሳሙ ነው ፤ ይህ በትንሹ የሚዘረጋ(የሚሰፋ) ነዉ ምክንያቱም በዮሐንስ የለም ነገር ግን ይሁዳ ኢየሱስን በመሳም አሳልፎ እንደ ሰጠው እናውቃለን (ማቴ 26፡ 48-49) ፡፡ መሳም የፍቅር እና የመሰጠት ምልክት ነበር ፤ የቤተሰብ አባላት መገናኘት እና መለያየት ላይ ይሳሳማሉ ደቀ መዛሙርቱም መምህሮችን እንደ መሰጠት እና እንደ መታዘዛ ምልክት በመሳም ሰላም ብለዋል ፤ ነገር ግን የይሁዳ መሳም የመታዘዝ ምልክት ከመሆን ይልቅ የክህደት ምልክት ነበር (ቁጥር 2) ፡፡ ይሁዳ ከገለልተኛ ጭፍሮች (ሮማዉያን አስር አለቃ ጓዶች) ከ500 ወታደሮች ጋር ወደ ኢየሱስ መጣ ፡፡ ከኢየሱስ ምን እንደ ሚገጥማቸዉ ምንም ሀሳብ አልነበራቸውም ፡፡

ኢየሱስ ወታደሮቹ ሊያገኙዓቸዉ ወደ እነርሱ በመጡ ጊዜ ከይሁዳ አልሸሸም ፤ ኢየሱስ ጊዜዉ እንደ መጣ ያውቃል በሙሉም ቁጥጥር ስር ነበር ፡፡ ቀደም ብሎ (በፊት) ኢየሱስ ከአይሁድ ሰዎች ግጭት ጋር ሲወጣ(ሲደበቅ) ነበር ምክንያቱም ስዕቱ ገና ስላልደረሰ ፡፡ ወታደሮቹ ኢየሱስን የሚያስሩት ማንን እንደ ነበር ነገሩት ኢየሱስም “ እኔ ነኝ “ አላቸው (ቁጥር 5) ፤ “ እኔ “ በሚለዉ በኢየሱስ ንግግር ላይ እየተመለከትን ነው ፤ ምናልባትም በዚህ ክስተት ኢየሱስ “ እኔ ነኝ “ ብሎ መመለሱ ንግግሮቹ ሁሉ ወደ እርሱ ጠቅላላ ማንነት ያመጣሉ ፡፡ ጠባቂዎች በዚያ መለኮታዊ ስልጣን ፊት መቆም ባለመቻላቸዉ በእርሱ ፊት ወደ መሬት ወደቁ (ቁጥር 6-7) ኢየሱስ ራሱን በመለየት እንደ ገና ደቀ መዛሙርቶቹ በነፃ እንዲሄዱ የተፈቀደላቸዉ እንዲሆኑ ጠየቀ (ቁጥር 8-9) ፡፡

ዮሐንስ (18፡ 10)፡ ሰዎስተኛዉ ምልክት ሰይፉ ነው ፤ ስምዖን ጴጥሮስ አደጋ በሚፈጥር ሰይፍ በመሳብ የካህናት አለቃ አገልጋዩን የማልኮስን ጆሮ ቆረጠው ፤ የዮሐንስ መግለጫ ብቻ የአገልጋዩን ስም ይሰጣል ፡፡ ሰይፉ በእግዚአብሄር ፈቃድ ላይ ያለ አመፅን ይወክላል(ያመለክታል) ፡፡ ዋይርስቤ ጴጥሮስ “ የተሳሳተ ጠላት ተጣላ፣ የተሳሳተ መሳሪያ ተጠቀመ፣ የተሳሰተ ፍላጎት እንደ ነበረው እና የተሳሳተ ዉጤት እንዳሳካ !“ ይገልፃል ፤ ማቴ (16፡ 21-23) እንደ ሚታሰር፣ እንደ ሚገላታ እና እንደ ሚሰቀል ደቀ መዛሙርቱን በነገራቸዉ ጊዜ የጴጥሮስን መልስ አስታውሱ ፤ በእዉነቱ ጴጥሮስ ኢየሱስ ሊፈፅመዉ የመጣዉን ስራ አሰናከለ ፡፡ የጴጥሮስን ጀግንነት እና ቅንነት ብናደንቅም ከፍተኛ ጉጉት(ቅናት) ያልእዉቀት አደገኛ እንደ ሆነ እንገነዘባለን ፡፡ በመጨረሻም ጴጥሮስ “ የመንፈስ ሰይፍን “ አገኘ (ኤፌ 6፡ 17; ዕብ 4፡ 12) ፤ ኢየሱስ ጴጥሮስን በመዋጀት በሚገባ ተጠቀመበት - በጴንቴኮስታ ከ3,000 በላይ ነፍሳት ወደ ጌታ መጡ (ሐዋ 2፡ 38; 40-42) ፡፡

ዮሐንስ (18፡ 11-14)፡ አራተኛዉ ምልክት መታዘዘን የሚወክለዉ ፅዋ ነው ፤ ኢየሱስ ስለ መታዘዝ ፅዋ እና የእግዚአብሄርን ፍቃድ ስለ መቀበል አወራ (ማቴ 26፡ 39, 42) ፡፡ በመፅሀፍ ቅዱሳዊ ብዙ ጊዜ ፅዋዉ መከራን እና ሀዘንን ያሳያል ፤ ለምሳሌ ባቢሎን ኢየሩሳሌምን ከያዘች በኋላ ኢሳ (51፡ 17) “ ከእግዚአብሄር እጅ የቁጣን ፅዋ ጠጥተሸል “ ይላል ፡፡ ኤርሚያስ በህዝቦች ላይ የእግዚአብሄርን ቁጣ ሞልቶ እንደ ፈሰሰ ፅዋ አቅርቦታል (ኤር 25፡ 15-28) ፤ ቢሆንም እንደ ክርስቶስ ተከታዮች በእግዚአብሄር እጅ ያለን ፅዋ መፍራት አያስፈልገንም ፤ ኢየሱስ ከእኛ በፊት ከፅዋዉ ጠጥቷል ፡፡ ህመም እና መከራ ይገጥመናል ነገር ግን ክርስቶስ ያን በመጨረሻ ወደ ክብር ይቀይረዋል ፡፡

ዮሐንስ (18፡ 15-27)፡ አምስተኛዉ ምልክት ክህደትን የሚወክለዉ እሳት ነው ፤ ኢየሱስ ጴጥሮስን ዶሮ ከመጮሁ በፊት ሰዎስት ጊዜ እንደ ሚክደዉ ነገረው ነገር ግን ጴጥሮስ ያን ማድረግ እንደ ሚችል ካደ ፡፡ ሁሉም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ከጴጥሮስ እና ምናልባትም ከዮሐንስ ዉጪ ሁኔታዉን ሸሽተዋል ፤ ጴጥሮስ ከሌሎች ደቀ መዛሙርት ጋር ሳይሸሽ ህዝቡን በመከተሉ ለፈተና ራሱን በማሳቀመጡ ኢየሱስን ሰዎስት ጊዜ ካደ፡ እርሱን ባወቀችዉ አገልቻይ ሴት (ቁጥር 17)፣ ቆይቶም በሌሎች አገልጋይ እና ሰራተኞች በቀረቡት ጊዜ እና በማልኮስ ዘመድ (ቁጥር 26) ፡፡ ጴጥሮስ ተለይቶ ባለመሄዱ ምክንያት በፍፁም ሊያደርገዉ የማይችለዉን ነገር አደረገ ፤ የጴጥሮስ ድርጊት መዝ (1፡ 1) በዚህ ተመሳሳይ፡ ጴጥሮስ “ የእግዚአብሄር ምክር ባልሆነ “ ተጓዘ ( በታላቅ ካህናት አደባባይ)፣ በእሳት አጠገብ ከጠላቶቹ ጋር ቆመ እንዲሁም ከጠላቶቹ ጋር ተቀመጠ (ሉቃ 22፡ 55) ፡፡ ፈተና በምናስብ ጊዜ 2ጢሞ (2፡ 22) የሚለው መሸሽ ነው ፡፡

ዮሐንስ (18፡ 12-14, 28-40)፡ አሁን ወደ መከራዎቹ ወደ ራሳቸው እንመለስ ፤ ወታደሮቹ በማሰር ኢየሱስን ወደ ሐና ወሰዱት (ቁጥር 12-13) ፤ የማይታወቀዉን ታላቅ ካህና ሐናን ዮሐንስ ብቻ ጠቅሶታል ፡፡ ሁለት አይነት የፍርድ አቀራረቦች ነበሩ፡ የኃያማኖተኞች (የአይሁዶች) ፍርድ እና የከተማ (የሮማዉያን) ፍርድ ፤ የአይሁዶች ፍርድ ሰዎስት ደረጃ ነበረው፡

  1. በሐና ቤት በሐና ቤት ኢየሱስ ተመረመረ (ቁጥር 13) ፡፡
  2. በሊቀ ካህኑ በቀያፋ እና በአንዳንድ መማክርቶቹ ፊት (ቁጥር 24) ፡፡
  3. በማግስት በሮማዉያን ጉባኤ ፊት ኢየሱስ ሞት ተፈረደበት (ቁጥር 28) ፡፡

በአይሁዶች ስልጣን መሰረት አይሁዶች ብቻቸዉን ኢየሱስን እስኪሞት መዉገር ብቻ ይችላሉ ፡፡ ኢየሱስ በመስቀል እንዲሞት በመተንበዩ ምክንያት በዚያ መንገድ ለመፍረድ ሮማዉያን ብቻ ስልጣን ነበራቸው ፡፡

ከእነዚህ ሰዎስት ደረጃዎች በኋላ ኢየሱስ ሄሮድስ እነበረበት ድንኳን ተወሰደ ፤ አይሁዶች ከእርሱ ጋር አይገቡም ወይም የረከሱ ስለ ሚሆኑ በፋሲካ ላይ አብረዉ መዉሰድ አይችሉም ፡፡ ኮንስታብል “ በቆራጥነት እነዚህ አይሁዶች የኃያማኖታዊ ስርዓትን መርከስን ለማስወገድ በኃይል ተዘጋጁ የዓለምን ኃጢዓት የሚያስወግደዉን የእግዚአብሄርን በግን ለመግደል እየተዘጋጁ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፤ ኢየሱስ ነፃ ሊያደርገን መጣ ፡፡ ለእኛ እርግማን ሆነ በዚህም ምክንያት በነፃነት መጓዝ እንችላለን (ገላ 3፡ 13) ፡፡ ኢየሱስ በጲላጦስ ፊት ተወሰደ (ዮሐ 18፡ 28-38) ወደ ሄርዶስም ተላከ (ሉቃ 23፡ 6-12) ከዚያም እንደ ገና ተመልሶ ወደ ጲላጦስ ተላከ (ዮሐ 18፡ 39 -19፡ 16) ፡፡ ዮሐንስ በተለየ በሮማዉያን ፍርድ ላይ አትኩሯል ፤ ዮሐንስ ይህን ወንጌል በሚፅፍ ጊዜ የአይሁድ ህዝብ በሮማዉያን ተበትነዋል፣ የኢየሩሳሌም ከተማ ተፍታለች በተጨማሪም የሮማዉያን ኃይል ነገር ጉዳይ ነበር ፡፡

ጲላጦስ ኢየሱስን የአይሁዶች ንጉስ እንደ ነበር ጠየቀዉ ፤ በምላሹ ኢየሱስ ጲላጦስንጥያቄ ጠየቀዉ በእዉነቱ ጲላጦስ በትህትና የእዉነት ፈላጊ እንደ ነበር ወይም ለፈለጉት ለአይሁዶች አሳልፎ ሊሰጠዉ እንደ ሚሞክር ጠየቀ (ቁጥር 34) ፡፡ ጲላጦስ ሁለቱንም ወገን ለማስደሰት “ ማምለጫ ቀዳዳ “ እየፈለገ ነበር - ህዝቡን ፈርቶ ነበር ነገር ግንበእስረኞቹ ከፍተኛ ፍራት አሳደገ ፡፡ ቢያንስ ሰዎስት ጊዜ (ሉቃ 23፡ 13-15, 22 እና ዮሐ 19፡ 4, 6) ጲላጦስ ኢየሱስ በምንም ወንጀል ጥፋተኛ እንዳልነበር ተናገረ ይሁንና እርሱን አለቀቀዉም (ቁጥር 39, ዮሐ 19፡ 16) ፡፡ ጲላጦስ ኢየሱስ ንጉስ እንደ ነበር ጠየቀ (ቁጥር 37) ኢየሱስም “ ከእዉነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው “ ፤ ጲላጦስ ስለ እዉነት እንደ ጠየቀዉ እንዴት ያውቃል ? በእዉነት መገኘት ዉስጥ ነበር ( እኔ መንገድም እዉነትም ህይወትም ነኝ” ዮሐ 14፡ 6) ፡፡ በኢየሱስ መገኘት የነበሩት በሀሳባቸዉ እዉነቱ ትክክል እንደ ነበር አላወቁም ምክንያቱም “ድምፁን አልሰሙትም “ ፡፡

መዝጊያ

ኢየሱስ ወደ ምድር ያለኃጢዓት እንከን የሌለበት የእግዚአብሄር ሆኖ ወደ ምድር የመጣበት ምክንያቱ ይህ ነው ፡፡ ምን እንደ ሚሆን ያውቃል - በኃሰት እንደ ሚከሰስ, በኃሰት እንደ ሚጠቃ, እንደ ሚሸነፍ, እንደ ሚዋረድ እና እንደ ሚተፉበት - ሁሉም ኃይል ቢኖረውም ፡፡ በመታዘዝ በመጓዝ ይህ ሁሉ እንዲሆን ፈቀደ ፤ ለእናንተና ለእኔ ያን አደረገ፡፡ ኢየሱስ ለእኛ በእርሱ ላይ ለዞሩበት እና ለሚጠሉትም እንኳን ለመሞት መጣ ፤ ስለዚህ በምላሹ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በድፍረት ወደፊት መሄድ አለብን ፡፡ ደፋር ሁኑ እንጂ ለብ ያላችሁ አትሁኑ (ራዕ 3፡ 15-16) ፡፡ የክርስቶስ እዉነት ነፃ አዉጥቶናል ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook. 1989), pp. 372–375.

  2. Wiersbe, p. 372.

  3. Wiersbe, p. 374.

  4. Thomas Constable, Dr. Constables Expository (Bible Study) Notes: John, p. 333; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/john.pdf.

ጥያቄዎች

  1. አዳም ተፈጥሮ በኤደን ገነት ተቀመጠ (ዘፍ 2፡ 8) ፤ የሰዉነት መጀመሪያ እና የሰዉ ልጅ ዉድቀት ሁለቱም በኤደን ገነት ተካሄዱ (ዘፍ 3፡ 1-8) እንዲሁም በተጨማሪ አንድ ጋርደን የኢየሱስ ተላልፎ መሰጠት እና መታሰር ሆነበት ይህ “ ለዳግም ዉልደታችን “ መንገድ መክፈቱ አስፈላጊ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ዮሐ 18፡ 1-2)
  2. የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን ለማሰር ለምን የሮማዉያንን የጦር ጓዶች(ምናልባትም 500 ወታደሮች) እንደ ላኩ ምን ታስባላችሁ ? “ እኔ ነኝ “ ብሎ በመመለስ ለሚፈልጉት ኢየሱስ ራሱን ከገለጠ በኋላ ምንድን ተፈጠረ ? (ዮሐ 18፡ 6)
  3. ኢየሱስ ለጲላጦስ ንጉስ እንደ ነበር አረጋገጠለት ነገር ግን መንግስቱ ከዚህ አለም እንዳልሆነ ገለፀ ፤ መንግስቱ ከዚህ አለም ሆና ቢሆን ነበር ኢየሱስ ምንድን እንደ ሚሆን ተናገረ ? (ማቴ 26፡ 53, ዮሐ 18፡ 36)
  4. በጋርደን በሚፀልይበት (ማቴ 26፡ 39) እና ተላልፎ በሚሰጥበት እና በሚታሰርበት በሁለቱም ጊዜ ኢየሱስ የመከራ ፅዋ እንደ ሚገጥመዉ ጠቀሰ ፤ ይህን ለመጠጣት ፍቃደኛ መሆኑ ምንድን ይገልፃል ? (ዮሐ 10፡ 11, 18፣ 18፡ 11) በሌላ መፅሀፍት ፅዋ ምንድን ይወክላል ? ( ኢሳ 51፡ 17, ኤር 25፡ 15, ሕዝ 23፡ 33, ራዕ 14፡ 10) ፤ በመፅሀፍ ፅዋ ሁል ጊዜ መጥፎ የሆነ ነገርን አይወክልም ፡፡
  5. በዮሐንስ 18 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin John 18:37b–38a

“‘You say that I’m a king,’ Jesus replied. ‘I was born for this, and I have come into the world for this: to testify to the truth. Everyone who is of the truth listens to My voice.’ ‘What is truth?’ said Pilate.”

ከደቀመዛሙርቱ አንዱ፥ አሰቆሮቱ ይሁዳ፥ የኢየሱስን እስር በመምራት፥ ኢየሱስን ለኃይማኖት መሪዎች አሳልፎ ሰጠ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ ጴጥሮስ፥ ሌላ ደቀመዝሙር ፥ ኢየሱስን ሶስት ጊዜ ካደ፡፡ በመጨረሻም፥ ሊቀ ካህናቱ እና አማቹ፥ ቀያፋ እና ሐና፥ ኢየሱስ ሞት እንዲፈረድበት በመፈለግ፥ ኢየሱስን ወደ ገዢው ዋና መስሪያ ቤት፥ ወደ ጲላጦስ ለመላክ ወሰኑ፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ፥ ጲላጦስ በኢየሱስ ላይ ምን ማድረግ እንዳለበት ለመወሰን ተቸግሮ ነበር፡፡ ኢየሱስን ይህንን ጥያቄ ጠየቀው፥ "እውነት ምንድን ነው?"

ልክ እንደ ጲላጦስ፥ በዓለም ላይ ያሉ ብዙዎች እውነትን ለማወቅ ይሞክራሉ፡፡እውነት ምን እንደሆነ ለማወቅ፥ ወደ ማህበራዊ ድህረ ገፆች፥ ምግብ፥ ስፖርቶች፥ ትምህርቶች፥ ወይም ወደ መዝናኛ ይመለከታሉ፡፡ እንደ ክርስቶስ ተከታይ፥ ኢየሱስ እውነት እንደሆነ ታውቃላችሁ፡፡ ኢየሱስ ዓለሙ ይድን ዘንድ መጥቷል፡፡ ከዚህ በላይ አትመልከቱ፡፡ ኢየሱስ እውነት ነው፡፡ ዛሬ፥ እውነትን በመፈለግ ላይ ላሉት ፀልዩ፡፡ "እውነት ምንድን ነው?" ፥ ብሎ አንድ ሰው ቢጠይቃችሁ—እውነትን አካፍሏቸው!

“ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው።ጲላጦስ፦ እውነት ምንድር ነው? አለው።”

— ዮሐንስ 18:37ለ–38ሀ

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ዮሐንስ 1:17 — “ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ። ”
  • ዮሐንስ 17:17 — “በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። ”
  • 1ኛ ዮሐንስ 4:6 — “እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም። የእውነትን መንፈስና የስሕተትን መንፈስ በዚህ እናውቃለን። ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 86