The Gospels John

The Day of Jesus' Passion

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 19 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 197 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዮሐንስ 19 በምድር ላይ የኢየሱስ ህይወት አካላዊ መጨረሻ ነው ፤ በዚህ ምዕራፍ በጣም ብዙ ጥቅል ፡፡ ታሪኩ ከዚህ በፊት መጥፎ እንደ ሚሆን ከዚያም እንደ ሚሻል ዮሐንስ 19 ያ ነው ፡፡ ዛሬ ኢየሱስ ያለፈበትን - ድብደባዉን፣ መገረፉን እና መሰቀሉን እንመለከታለን ፡፡

ትምህርት

ዮሐንስ (19፡ 1)፡ ኢየሱስ “ የብረት እና የአጥንት ስለታም ቁርጥራጮች ተጣብቀዉበት በነበረው በረጅም ጠፍር “ ተገረፈ ፤ በዚህ መንገድ ተገረፈ ማለት ስጋዉ እና ኦርጋኑም እንኳን የተጎዳ ወይም ከሰዉነቱ የተቦጫጫቀ ሆነ ማለት ነው ፡፡ ደ. ኤ. ካርሰን ከትንሹ እስከ ትልቁ ስሜት ድረስ ሰዎስት አይነት ግርፋቶችን ይዘረዝራል፡ 1) በቆመጥ መግረፍ - ዱርዬዎችን(አጭበርባሪዎች) ብቻ የሚገረፉበት ቀላል ቅጣት፣ 2) በልምጭ መግረፍ - ከባድ ወንጀል ጥፋተኞች የነበሩ ወንጀለኞች የሚቀበሉት ከባድ ቅጣት እና 3) በመቀጥቀጥ መቅጣት (ኃይለኛ ቅጣት) - ለከባድ ወንጀሎች የሚሰጥ በጣም አደገኛ ቅጣት ሲሆን የሚሰቀሉትንም ያካትት ነበር ፤ ከፍርዱ በፊት ኢየሱስ የመጀመሪያዎቹን ሁለቱን ቅጣጦች ይቀበላል ከተፈረደበት በኃላ ደግሞ ሰዎስተኛዉን ቅጣት ተቀበለ ፡፡

ዮሐንስ (19፡ 2-6)፡ ከግርፋት በኋላ ወታደሮቹ የእሾክ ዘዉድ ምናልባት ከተምዕረ ዘንባባ ዛፍ በመስራት “ በቀልድ የንጉስ ዘዉድ “ ኢየሱስ ራስ ላይ አስቀመጡት እንዲሁም “ በአስቂኝ የድል አድራጊ ንጉሳዊ “ ቀይ ካባ አለበሱት ፡፡ ወታደሮቹም አጃጃሉትም በእጆቻቸዉም በመምታት በቃልም በአካልም አጠቁት (ቁጥር 4) ፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በብሉይ ኪዳን ፃሀፊዎች ተተንብየዋል፡

  • መዝ (22፡ 7)፡ ቀለዱበት(አፌዙበት) (ዮሐ 19፡ 3) ፡፡
  • ኢሳ (53፡ 9)፡ ንፁህ ነበር (ዮሐ 19፡ 4) ፤ ሌንሲክ የፃፈው “ ኢየሱስ ከመሰቀለ የሚለቀቅ እንጂ የተሰቀለ ለመሆን የሚሰጥ አልነበረም “ ፡፡
  • ኢሳ (53፡ 5)፡ የተሸነፈ እና የሚያሳዝን ነበር (ዮሐ 19፡ 5) ፡፡
  • ኢሳ (53፡ 9)፡ ንፁህ እንደ ነበር ጮኾ ተናገረ (ዮሐ 18፡ 38; 19፡ 4, 6) ፡፡
  • ኢሳ (53፡ 3)፡ የተጠላ ነበር (ዮሐ 19፡ 6) ፡፡
  • ኢሳ (53፡ 7)፡ የተጨቆነ እና የተጎሳቆለ ነበር ነገር ግን አልተናገረም (ዮሐ 19፡ 9) ፡፡
  • ኢሳ (53፡ 10)፡ ከእግዚአብሄር ስልጣን ነበረው (ዮሐ 19፡ 11) ፡፡

ኢየሱስ ከመፅሀፍ ዉጪ ሊያደርግ ሳይሆን መፅሀፍን ሊፈፅም እንደ መጣ ተናግሯል (ማቴ 5፡ 17) ፡፡

ዮሐንስ (19፡ 7-10)፡ አይሁዶች ኢየሱስን የእግዚአብሄር ልጅ ነኝ ብሏል በሚል ስም ማጥፋት ከሰሱት (ዘሌ 24፡ 16) በዚህም ተፈረደበት (ዮሐ 5፡ 18; 8፡ 58-59; 10፡ 33-36) ፡፡ ጲላጦስ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ ነኝ ብሎ መናገሩ ጉዳዩ አይደለም ነገር ግን ለአይሁዶች የኢየሱስ ንግግርን አስፈላጊነት በተረዳ ጊዜ በጣም የፈራ ሆነ ፤ በቁጥር (9-10) ጲላጦስ ኢየሱስ ከየት እንደ ነበር ጠየቀዉ ነገር ግን ኢየሱስ አልመለሰለትም (ማቴ 26፡ 23; 27፡ 14) ፡፡

አሁንም እንኳን ብዙ አይሁዶች ኢሳ (53፡ 1-12) እንደ ሆነ አያዉቁም ምክንያቱም ይህን ለመቀበል ስለ ኢየሱስ የእነዚህን ትንቢቶች መፈፀም መረዳት ይጠበቅባቸዋል ፡፡

ዮሐንስ (19፡ 11-16)፡ በቁጥር 11 ኢየሱስ ለጲላጦስ እጅ ተላልፎ እንደ ሚሰጠ ተናግሯል ፤ በማን ? ምናልባትም በቀያፋ ወይም በይሁዳ ፡፡ እዚህ ላይ ኮንስታብል አይሁዶች ኢየሱስ ከነበረዉ በይበልጥ ለእስራኤል አስፈሪ እየሆኑ እንደ ነበር ይገልፃል ጲላጦስ ኢየሱስን ለመልቀቅ የሚያስችለዉን ጥረት ሁሉ አደረገ ነገር ግን በመጨረሻ ከኢየሱስ በኩል ወይም ከአይሁዶች በኩል ፈቃደኛ ለነበረው ይወስናል ፤ ጲላጦስ ከአይሁዶች በኩል ለመወገን ወሰነ በዚህም በአንቶኒ ምሽግ ዉስጥ ባለ ትልቅ ስፍራ ኢየሱስን ዉጪ ድንጋይ ላይ አዉጥቶ ሰጠው (ቁጥር 14) ፡፡ ጲላጦስ “ ንጉሳቸዉን “ ኢየሱስን ለአይሁዶች ሰጣቸው ነገር ግን ኢየሱስ የተሰቀለ እንዲሆን ጮኹ ፡፡ ለፋሲካ ዝግጅት የሚደረግበት ማለዳ ስድስት ሰዓት አካባቢ አርብ ነበር ፤ አይሁዶች ለቄሳር እንደ ብቸኛ ንጉሳቸዉ ሙሉ ታማኝነትን ተናገሩ (ቁጥር 15 ፤ እምነታቸዉን የስጋቸዉን ፍላጎት ለሚያሟሉላቸዉ ማመቻመች ጀመሩ ፤ በዚህም ጲላጦስ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው (ቁጥር 16) ፡፡

ዮሐንስ (19፡ 17-22)፡ በቁጥር 17 የሚፃረር ሀረግ አለ ጎልጎልታ (የራስ ቅል ቦታ ) ተብሎ ወደ ሚጣራዉ ቦታ ሲሄድ “ የራሱን መስቀል ተሸከመ “ ፤ በአገልግሎቱ ጊዜ ኢየሱስ ተከታዮቹ መስቀላቸዉን በመሸከም እርሱን እንዲከተሉት ተናግሯል (ማቴ 16፡ 24) ፤ ኢየሱስ ከተካታዮቹ የሚፈልገዉን አደረገ ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ በሁለት ሌሎች መካከል ተሰቀለ - ሰዎስት መስቀሎች (ቁጥር 18) ፤ ጲላጦስ በኢየሱስ መስቀል ላይ ኢየሱስን እንደ አይሁድ ንጉስ የሚገልፅ ምልክት አንጠልጥሎበት ነበር ፡፡ መስቀሎቹ ከከተማዋ ግንብ ዉጪ ተተክለዉ ነበር ነገር ግን በብዙ የአይሁድ ሰዎች በመጠጋት ኢየሱስን በመስቀል ላይ አዩት እንዲሁም ከራሱ በላይ ያለዉም ምልክት አነበቡ ፤ ምልክቱ በአረማይክ፣ በላቲን እና በግሪክ የተፃፈ ነበር ፤ በአሁኑ ጊዜ በኢየሩሳሌም ምልክቶቹ በዕብራይስጥ፣ በአረማይ እና በእንግሊዘኛ ናቸዉ ምክንያቱም ሰዎች ከመላዉ አለም በዚያ ስለ ሚጎርፉ ፡፡ አይሁዶች ጲላጦስ ስለ ፃፈዉ ምልክት ቅር ተሰኙ(አጉረመረሙ) ምክንያቱም ኢየሱስን የአይሁዶች ንጉስ “ መባል “ ማለት ስለሌለበት ነገር ግን ጲላጦስ ለመቀየር አልተቀበላቸውም (ቁጥር 21-22) ፡፡

ዮሐንስ (19፡ 23-24)፡ ኢየሱስ ተሰቀለ ወታደሮቹም በመካከላቸዉ ልብሶቹን በመከፋፈል ስለ ካባዉ(እጀ ጠባቡም) እጣ ተጣጣሉ (ቁጥር 23) ፤ ዮሐንስ በመዝ(22፡ 18) እና በኢሳያስ 53 ሁለቱንም ትንቢቶች እንዴት ኢየሱስ እንደ ፈፀማቸዉ ገለፀ ፡፡

ዮሐንስ (19፡ 25-27)፡ ኢየሱስ ስለ እናቱ ጥንቃቄ(እንክብካቤ) ስጦታ አደረገ ፤ ከዚያች ክስተት አንስቶ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ዮሐንስ ማሪያምን ወደ ቤቱ በመዉሰድ እንደ እናቱ ተንከባከባት ፡፡

ዮሐንስ (19፡ 28-30)፡ መንፈሱን በመስጠት በምድር ላይ ይህ የክርስቶስ ያለቀ ስራ ነው ፡፡

ዮሐንስ (19፡ 31-37)፡ የኢየሱስ ጎን ተወጋ (ዘካ 12፡ 10) ፤ የፋሲካ በግ የሚለው መስፈርት ለማሟላት ቁጥር 36 የኢየሱስ አጥንት እንዳልተሰበረ ይጠቅሳል (ዘጸ 12፡ 46) ፡፡

2 D. A. Carson, The Gospel According to John (Leicester, England: Inter-Varsity Press, and Grand Rapids: Wm. B. Eerdmans Publishing Co., 1991), p. 595; quoted in Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: John, p. 341; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/john.pdf.

ዮሐንስ (19፡ 38-42)፡ የኢየሱስ አካል ሀብታም እና የኢየሱስ ሚስጥራዊ ተከታይ በነበረው በአርማቲዮስ ዮሴፍ ተጠየቀ ፤ ዮሴፍ እና ኒቆዲሞስ የኢየሱስን አካል በተልባ እግር ልብስ በመሸፈን እና በሽቶ ለመቃብር በማዘጋጀት በአድስ መቃብር አስቀመጡት ፡፡ የመቃብሩ መሰጠት(መገኘት) ሌላ የመፅሀፍ መፈፀም ነበር ፡፡

መዝጊያ

ይህ ሁሉ እርሱን በገፉት በዚህ አለም የተጠላን እንደ ምንሆን ይነግሩናል ፤ በእያንዳንዱ ቀን መስቀላችንን ስናነሳና ስንከተለው መዝሙር 22 እና ኢሳያስ 53 እንይዛለን ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1355.

  2. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: John, p. 341; available online at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/john.pdf.

  3. Nelson’s, p. 1355.

  4. Richard C. H. Lenski, The Interpretation of St. John’s Gospel (Minneapolis: Augsburg Publishing House, 1961), pp. 1243; quoted in Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: John, p. 340; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/john.pdf.

  5. Nelson’s, p. 1355.

ጥያቄዎች

  1. በማጃጃል የሮማዉያን ወታደሮች ኢየሱስ “ ንጉስ “ እንደ ነበር ለማመልከት ምንድን አደረጉ ? (ዮሐ 19፡ 2-3) ፤ ይህን ለምንድን አደረጉ ? (መዝ 22፡ 7, ዮሐ 18፡ 37)
  2. ጲላጦስ በኢየሱስ ጥፋት እንዳላገኘበት ስንት ጊዜ ተናገረ ? (ዮሐ 18፡ 38, 19፡ 4, 6) ፤ ዮሐ (19፡ 12) ጲላጦስ ለመልቀቅ ጥረት እንዳደረገ ይናገራል ፡፡ ይህን ከመሆን ምንድን አገደዉ(ጠበቀው) ? (ዮሐ 19፡ 12, ኢሳ 53፡ 9)
  3. “ ከቄሳር በቀር ሌላ ንጉስ የለንም “ ባሉ ጊዜ የካህናት አለቆች ከልባቸዉ(በእዉነት) ነበሩ ? (ዮሐ 19፡ 15) ፤ በግልፅና ሙሉ በሙሉ ኢየሱስን እንደ ንጉስ አልተቀበሉትም ፡፡ በበላፈዉ ጊዜ እስራኤላዊያን እግዚአብሄርን እንደ ንጉስ ያልተቀበሉት መቼ ነበር ? (1ሳሙ 8፡ 7)
  4. በዘፍ (22፡ 6) ይስሐቅ በምን መንገድ የክርስቶስ ጥላ ሆነ ? (ዮሐ 19፡ 17) አብርሃም ልጁን ይስሐቅን እንደ መስዋዕት ያቀረበበትን ቦታ “ እግዚአብሄር ይሰጣል “ በማለት ጠራው ፤ ዮሐንስ 19 የዚህ ትንቢታዊ ስም መፈፀም ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  5. በዮሐንስ 19 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin John 19:9

“He went back into the headquarters and asked Jesus, ‘Where are You from?’ But Jesus did not give him an answer.”

ጲላጦስ ኢየሱስ እንዲገረፍ አዘዘ፡፡ ወታደሮቹም ራሱ ላይ የእሾህ አክሊል ደፍተው ቀይ ልብስም አልብሰው ተሳለቁበት፡፡ ከዚያም ጲላጦስ ኢየሱስን ለመስቀል በቂ ምክንያት ስላላገኘ፥ ምን እንደሚያደርገው መጠየቁን ቀጠለ፡፡ ኢየሱስ ለዓለም ኃጢያት በህመም እና በስቃይ መካከል እንኳን ሆኖ፥ በምሳሌነት መኖርን ቀጠለ፡፡ ጲላጦስ ይህንን ጠየቀው፥ " ከወዴት ነህ?" ኢየሱስ አቆመ፡፡ በመጨረሻም ምላሽ ሲሰጥ፥ በእርጋታ እና በጥሪው በመተማመን ነበር፡፡

ክርስቶስን ለመከተል እና ለእርሱ ለመኖር ባደረጋችሁት ውሳኔ ተጠይቃችሁ ታውቃላችሁ? አንዳንድ ጊዜ ሰዎች የሚጠይቁበት መንገድ ፥ ማሳየት ያለባችሁ ነገር እንዳለ አይነት ፥ በንዴት ምላሽ እንድትሰጡ እንድትፈልጉ ሊያደርጋችሁ ይችላል፡፡ ነገር ግን በዚያን ጊዜ፥ ለእምነታችሁ መቆም እንደሚገባችሁ ሲሰማችሁ፥ አትናደዱ፥ አትታበዩ ደግሞም አታወላውሉ፡፡ ክርስቶስ በመከራ ውስጥ በነበረበት ጊዜም ለእኛ ያለውን ምሳሌ አስታውሱ፡፡ ቆም በሉ፥ ተንፍሱ፥ ለመመለስ ዘግዩ፡፡ መንፈስ እንዲመራችሁ እና ምላሻችሁን እንድታውቁ እንዲረዳችሁ ፍቀዱ፡፡ ለሚጠይቃችሁ ሰው መንፈስ ራሱ ይናገር፡፡ ከዚያም ጊዜው ሲደርስ፥ በኢየሱስ ፍቅር እና ስልጣን ተናገሩ፡፡

“ተመልሶም ወደ ገዡ ግቢ ገባና ኢየሱስን፦ አንተ ከወዴት ነህ? አለው። ኢየሱስ ግን አንድ እንኳ አልመለሰለትም።”

— ዮሐንስ 19:9

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ኦሪት ዘጸአት 14:14 – “እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ አላቸው። ”
  • መጽሐፈ መክብብ 5:1–2 –ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤ ለመስማት መቅረብ ከሰነፎች መሥዋዕት ይበልጣልና፤ እነርሱም ክፉ እንዲያደርጉ አያውቁምና። እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኵል፤ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን።
  • የያዕቆብ መልእክት 1:19–20 –ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤ የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና።

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 87