The Gospels John

"I Have Seen The Lord"

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 198 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና ሁሉም ኢየሱስ የሄደበትን በመመልከት እና በምን ዉስጥ መጓዝ እንዳለብን ስንጨርስ ዮሐንስ ምዕራፍ 19 ጠንካራ ፅሁፍ ነበር ፤ በመልካም ዜና አልጨረስንም ምክንያቱም ዮሐንስ በመልካም ዜና ስላልጨረሰ ፡፡ ዮሐንስ 20 ወደ ህይወት በመለወጥ እና በተስፋ ይጀምራል ፡፡

ትምህርት

ዮሐንስ (20፡ 1-10)፡ መግደላዊት ማሪያም በጥዋት ወደ መቃብር መጣች ከመግቢያዉ ላይ ድንጋዩ ተንከባሎም ባገኘችዉ ጊዜ ጴጥሮስን እና ዮሐንስን ለማግኘት ሮጠች (ቁጥር 1) ፡፡ አስተዉሉ ዮሐንስ በፍፁም ራሱን በስሙ አልጠቀሰም ነገር ግን “ በኢየሱስ የሚወደደዉ አንዱ “ በማለት እንጂ ይህ በዮሐንስ በኩል ትህትና ነበር ፡፡ ማሪያም ደቀ መዛሙርቶቹን የኢየሱስ መቃብር ባዶ እንደ ሆነ እና አካሉን እንዳጣችዉ (ቁጥር 2) ፤ ስምዖን ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ወደ መቃብሩ ሮጡ ፤ ዮሐንስ መጀመሪያ ደረሰ ነገር ግን አልገባም (ቁጥር 3-5) ፡፡ ስምዖን ጴጥሮስ ወደ መቃብሩ በመግባት የተልባ እግሩን ልብስ ተጣጥፎ አየው (ቁጥር 6-7) ፤ ዮሐንስ አይቶ አመነ ነገር ግን መፅሀፍ ኢየሱስ ከሞት እንደ ሚነሳ ያሉትን አልተረዱም ( ቁጥር 8-9) ፤ ከዚያም ሁለቱ ትተዉ ወደ ቤታቸዉ ተመለሱ ፡፡

ዮሐንስ (20፡ 11-18)፡ መግደላዊት ማሪያም ደግሞ ወደ መቃብሩ በመመለስ እያለቀሰች ነበር ነገር ግን በዚያ እንዴት እንደ ምታገኘው ወይም ደቀ መዛሙርቱን እንደምታይ መረጃ የተሰጣት መረጃ የለም ፤ ምሳ (8፡ 17) የሚለው “ እኔ የሚወዱኝን እወድዳለሁ ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል “ ወደ መቃብሩ ተመልሳ መምጣቷ የመግደላዊት ማሪያም ይህ የሚያምር መልክ ነው ፡፡ (መዝ 30፡ 5) ወደ መቃብሩ በተመለከተች ጊዜ ሁለት መለዓክቶችን አየች (ቁጥር 12) ፤ ሉቃ (24፡ 4) አስታዉስ ሁለት መለዓክት ብሎ ሲመዘግብ ማር (16፡ 5) እና ማቴ (28፡ 2-3) እያንዳንዳቸዉ አንድ መለዓክት መዝግበዋል ፡፡ መለዓኩ ማሪያም ለምን እያለቀሰች እንደ ነበር ጠየቃት (ነገር ግን ለምን እንደ ነበር ያውቃሉ !) ፤ ስትዞር ኢየሱስን አየችው ነገር ግን አላወቀችዉም ፤ ማክአርቱር ማሪያም ኢየሱስን ያላወቀችበትን ብዙ ምክንያቶችን ያቀርባል፡ 1) ምናልባትም በእንባዋ ዉስጥ ልታየዉ አልቻለችም፣ 2) አሁንም በሀሳቧ የኢየሱስ መቀበር እይታ እና የተጎዳዎ አካሉ ስለ ነበራት፣ 3) ምናልባትም ከትንሳኤ በኋላ በጣም የተለየ ስለ ሚመስል እና 4) ምናልባትም “ በመለኮት እንድታዉቀዉ እስኪ መርጥ ድረስ ከማወቅ የተከለከለች ስለ ነበር ፡፡ እንዲሁም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በኤማሆስ መንገድ ላይ ከትንሳኤዉ በኋላ ኢየሱስን አላወቁትም (ሉቃ 24፡ 16-31) በገሊላ ወንዝ ዳርቻ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ባላወቁት ጊዜ ዮሐንስ ኢየሱስን አወቀዉ (ዮሐ 21፡ 7) ፡፡

ኢየሱስ መጀመሪያ ለሴቶች መገለጡ አስፈላጊ ማስታወሻ ነው ፤ ኮንስታብል “ በቀደመዉ አለም ማንም አይሁዳዊ ፀሀፊ ለዚህ በጣም ጠቃሚ(አስፈላጊ) ለሆነ ክስተት እንደ መጀመሪያ ምስክርነት ሴቶችን አያቀርቡም “ ብሎ ይጠቅሳል ፡፡ ማሪያምን ኢየሱስ መለዓኩ ጠይቋት የነበረዉን ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየቃት፡ “ ለምን ታለቅሻለሽ ? “ ስትመለከት ስለ ነበረው ጠየቃት (ቁጥር 15) ፤ የኢየሱስን አካል ወዴት ወስዶት እንደ ነበር የሚያዉቀዉ ዘበኛዉ እንደ ሚሆን አሰበች ፤ በግልፅ ኢየሱስ በህይወት ይኖራል ብላ አልጠበቀችም ፡፡ በቁጥር 16 ኢየሱስ “ ማሪያም “ ሲል ማን እንደ ነበር አወቀች ፤ ዮሐ (10፡ 27) የሚለው “ በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አዉቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል “ ፤ ማሪያም ድምፁን በመስማት ጌታን አወቀችዉ ፡፡

የማሪያም ኢየሱስን ማወቅ ወደ እርሱ ሰባቱ “ እኔ “ ወደ ሚሉት ንግግሮቹ መልሰዉ ይወስዱናል እነርሱም፡

  1. እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ (ዮሐ 6፡ 35) ፡፡
  2. እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ (ዮሐ 8፡ 12) ፡፡
  3. እኔ የበጎች በር ነኝ (ዮሐ 10፡ 11, 14) ፡፡
  4. እኔ መልካም እረኛ ነኝ (ዮሐ 10፡ 11, 14) ፡፡
  5. እኔ ትንሳኤና ህይወት ነኝ (ዮሐ 11፡ 25) ፡፡
  6. እኔ መንገድም እዉነት እና ህይወት ነኝ (ዮሐ 14፡ 6) ፡፡
  7. እኔ እዉነተኛ የወይን ግንድ ነኝ (ዮሐ 15፡ 1, 5) ፡፡

ኮንስታብል በኢየሱስ ከትንሳኤ በኋላ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሁሉንም ከትንሳኤ በኋላ መልኮቹን ለይቷቸዋል፡

በፋሲካ ጠዋት ላይ ኢየሱስ ለመግደላዊት ማሪያም (ማር16፡ 9-11፣ ዮሐ 20፡ 10-18)፣ ለሌሎች ሴቶች (ማቴ 29፡ 9-10) እና ለጴጥሮስ (ሉቃ 24፡ 34፣ 1ቆሮ 15፡ 5) ፡፡

በፋሲካ ከሰዓት ላይ ኢየሱስ በኤማሆስ መንገድ ላይ ለሁለቱ ደቀ መዛሙርት ተገለጠላቸው (ሉቃ 24፡ 13-32) ፡፡

ፋሲካ ምሽት ላይ ኢየሱስ ለ12ት ያክል ደቀ መዛሙርት ቶማስን ሳይጨምር ተገለጠ (ማር 16፡ 14, ዮሐ 20፡ 19-23) ፡፡

በቀጣዩም እሁድ ላይ ኢየሱስ ቶማስን ጨምሮ ለ 11 ደቀ መዛሙርት ተገለጠ ( ዮሐ 20፡ 26-26) ፡፡

በቀጣዮቹ 32 ቀናት ጊዜ ደግሞ ኢየሱስ በገሊላ ባህር አጠገብ ለ7 ደቀ መዛሙርት ( ዮሐ 21፡ 1-23), በገሊላ በተራራ ላይ ለ 500 ሰዎች (ማቴ 28፡ 16-20፣ 1ቆሮ 15፡ 6), በአንድ በኩል ወንድሙ ለሆነዉ ለያዕቆብ (1ቆሮ 15፡ 7), ለደቀ መዛሙርቱ በኢየሩሳሌም (ሉቃ 24፡ 44-49, ሐዋ 1፡ 3-8, 1ቆሮ 15፡ 7) እና በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ለደቀ መዛሙርቱ (ማር 16፡ 19-20, ሉቃ 24፡50-53, ሐዋ 1፡ 9-12) ፡፡

የትንሳኤዉ መልክ በዛሬዉ ምዕራፍ የመጀመሪያዉ ነበር ፤ ኢየሱስ ለብዙ ሰዎች፣ ቡድኖች እና ህዝቦች በተለያዩ ሁነቶች መታየቱ ለመረዳት ታሪካዊ ትርጉም ነው ፡፡

ብዙ ጊዜ ማሪያም ኢየሱስን ባየችዉ ጊዜ በኢየሱስ እግር ላይ በወመዉደቅ የተገለፀች ነች ፤ ስለዚህም ከትንሳኤ በኋላ ኢየሱስን ባገኘችዉ ጊዜ ወደ እርሱ እንዳትቀርብ(እንዳትጠመጠምበት) ነገራት (ዮሐ 20፡ 17) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ መጠምጠም “ የሚለዉን እንደ “ ራስን ማጣበቅ (ማያያዝ) “ ወይም እንደ “ መያዝ “ ይገልፀዋል ፡፡ ምናልባትም ማሪያም ኢየሱስ ላይ መጠምጠም ፈለገች ምክንያቱም ደግማ ልታጣዉ ስላልፈለገች ፡፡ ኢየሱስ እርሱን እንዳየችዉ ለደቀ መዛሙርቱ እንድትነግራቸዉ ላካት ፤ ሴቷ ማሪያም ለደቀ መዛሙርቱ ትንሳኤዉን እንድታሳዉቅ አሳይመንት ተሰጣት ፤ ወዲያዉኑ በመሄድ “ ጌታን አይቸዋለሁ “ በማለት ተናገረች ፡፡

2 Edwin A. Blum, “John,” in Bible Knowledge Commentary: New Testament, ed. John F. Walvoord and Roy B. Zuck, (Wheaton, IL: Scripture Press Publications, Victor Books, 1983) p. 342; quoted in Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: John, p. 371; available online at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/john.pdf.

ዮሐንስ (20፡ 19-23)፡ ደቀ መዛሙርቱ በአንድ ላይ ከተዘጋ በር ኋላ ነበር ምክንያቱም አይሁዶችን ፈርተዉ ስለ ነበር ፤ አይሁዶች ኢየሱስን ገለዉት ስለ ነበር ቀጣዮቹ እነርሱ እንዳይሆኑ ፈሩ ፡፡ ምንም እንኳን በሩ ቢዘጋም በተዓምራት በእነርሱ ፊት በመገለጥ “ ሰላም ለእናንተ ይሁን “ አላቸው - ምድር ላይ አገልግሎቱን ፈፅሞ ነበር ፡፡ በእጆቹ ላይ ጠባሳዉን በማሳየት “ ሰላም ለእናንተ ይሁን ፤ አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ አላቸው “ (ቁጥር 22) ፡፡ እንዲያደርገዉ ተልኮት የነበረዉን በትክክል እንዲያደርጉ ሾማቸዉ - የሰላምን ወንጌል እንዲያመጡ (ዮሐ 17 ፡ 18) ፤ በአለም ላይ ልክ እንደ ኢየሱስ መሆን አለብን ፡፡

“ ይህንም ብሎ እፍ አለባቸዉና መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ “ (ቁጥር 22) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ ይህ “ በጴንቴኮስታ የቤተ ክርስቲያን መሰረት እንዲሆኑ የሀዋሪያት የተለየ ዝግጅት ነበር “ ያብራራል በዚህም በዘፍጥረት ለአዳም ህይወት የሰጠዉን የእግዚአብሄርን ትንፋሽ ለማሳሰብ ኢየሱስ “ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መንፈስን እፍ አለባቸዉ “ ፡፡ ጥያቄዉ ደቀ መዛሙርቱ መንፈስን የተቀበሉት እዚህ ወይስ ጴንቴኮስታ ላይ ነው ፤ ለእኛም ቢሆን የምናዉቅበት መንገድ የለም በዚህ ክስተት በኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስን እንደ ተቀበሉ አምናለሁ እነርሱን ለጴንቴኮስታ በማዘጋጀት (ዮሐ 14፡ 25-29) በጴንቶኮስታ የእሳት ጥምቀትን ይቀበላሉ ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ብቻ ነዉ የሚመጣው ፡፡

መዝጊያ

ኢየሱስ ያለ ማቋረጥ ለደቀ መዛሙርቱ ይታይ ነበር እንዲሁም ለዕኛ ያለ ማቋረጥ የሚገለጥ ነው ፤ ኢየሱስን ባገኘነዉ ጊዜ ሁል ጊዜ የእርሱ ሰላም ይኖረናል ፡፡

  1. John MacArthur, The John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1425.

  2. Constable, p. 369.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1358.

  4. Nelson’s Commentary, p. 1359.

ጥያቄዎች

  1. ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ወደ መቃብሩ ሮጡ ነገር ግን አካሉ ተሸፍኖበት የነበረዉን ልብስ ብቻ ቀርቶ መቃብሩን ባዶዉን አገኙት ፤ ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ልብሱን በእዚያ መሆኑ ነገር ግን ኢየሱስ አለመኖሩን ተረድተዉታል ብላችሁ ታስባላችሁ ? በራሱ ዙሪያ የነበረዉ ልብስ ተለይቶ ለምን ወድቆ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ?
  2. ማሪያም ኢየሱስን ለምን እንዳላወቀችዉ ምን ታስባላችሁ ? (ዮሐ 20፡ 14-16) ፤ ማሪያም ማን እንደ ነበር አሰበች ?
  3. ቶማስ ቁስሉን ካልነካ በስተቀር ኢየሱስ እንደ ነበር ለምን አላምንም አለ ? በምንድን ትዕዛዝ መተላለፍ ጥፋተኛ ነበር ? (ማር 9፡ 24, ማቴ 17፡ 17)
  4. በዮሐ (20፡ 29) ላይ አሰላስሉ ፤ አንዱን ሳያዩ የሚያምን የሚበልጥ እምነት እንደ ሚወስድ ታስባላችሁ ? ለምን ?
  5. በዮሐንስ 20 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin John 20:29

“Jesus said, “Because you have seen Me, you have believed. Those who believe without seeing are blessed.”

መግደላዊት ማሪያም፥ ስምኦን ጴጥሮስ፥ እና ሌሎቹ ደቀመዛሙርት ወደ መቃብሩ በማለዳ ሲሄዱ፥ መቃብሩ ባዶ ነበር፡፡ እንደተናገረው ኢየሱስ ከሙታን ተነስቷል! ከትንሳኤው በኋላ፥ ደቀመዛሙርቱ ከኢየሱስ ጋር ጊዜ አሳለፉ እና ለአገልግሎት ተላኩ፡፡ ይሁን እንጂ፥ ቶማስ ከኢየሱስ ጋር ስላልነበረ በእርግጥ ህያው መሆኑን አላመነም፡፡ በመጨረሻም፥ ከስምንት ቀን በኋላ፥ ለቶማስ በሚስማር የተወጉትን እጆቹን እና እግሮቹን በአካል ለማሳየት ኢየሱስ ለቶማስ እና ለሌሎቹ ደቀመዛሙርት ተገለጠ፡፡ ቶማስ ኢየሱስን እና ከሞት የተነሳውን አካሉን በአካል ካየ በኋላ ብቻ አመነ፡፡ ኢየሱስ ቶማስን አለው፥ " ስላየኸኝ፥ አምነሃል፥ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁአን ናቸው፡፡"

ኢየሱስን በአካል አይታችሁት ላታውቁ በብዙ ትችላላችሁ፡፡ ወደ ሰማይ ሲመለስ፥ በአባቱ ቀኝ እንደሚቀመጥ ተናግሯል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የምትቀበሉት በእምነት ነው፡፡ ኢየሱስ በተመለሰ ጊዜ ደቀመዛሙርቱ እንደነበራቸው እምነት— ኢየሱስ የእግዚያብሔር ልጅ እንደሆነ የምታምኑት በእምነት ነው፡፡ ይሁን እንጂ፥ እምነታችሁ በይበልጥ እንደ ቶማስ ሊሆን ይችላል፤ ኢየሱስን በአካል ለማየት ትፈልጉ ይሆናል፡፡ዛሬ፥ በአካል ባይሆንም፥ ፍቅሩን እና በዙሪያችሁ ያለውን ልዩ መንካቱን እንድታዩ አይኖቻችሁን እንዲከፍት በመፍቀድ ኢየሱስ በሕይወታችሁ እንዲገለጥ ጠይቁት፡፡ ስትጠይቁ፥ እንደሚመልስ እመኑ፡፡ ዛሬ ምን እንደሚያስፈልጋችሁ ያውቃል፡፡

“ኢየሱስም፦ ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው።”

—ዮሐንስ 20:29

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ትንቢተ ኤርምያስ 32:17 – “አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም። ”
  • ዕብራውያን 11:1 – “እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ”
  • ሮሜ 10:17 – “እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት፡ ክፍል 88