"Do You Love Me?"
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of God John 21 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ከወንጌል ይህ የመጨረሻዉ (89) ክፍል ነው ፡፡ በንጉስ፣ በአገልጋይ፣ በሰዉ ልጅ እና በእግዚአብሄር ልጅ ፍሬ ነገር (ጭብጥ) ላይ ተመልክተናል ፡፡ በዮሐንስ ወንጌል ኢየሱስ ሜንዲ በስዕሏ ያሳየችዉን ሰባት “ እኔ “ የሚለዉን ንግግር አድርጓል፡ 1) እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ፣ 2) እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፣ 3) እኔ የበጎች በር ነኝ፣ 4) እኔ መልካም እረኛ ነኝ፣ 5) እኔ ትንሳኤና ህይወት ነኝ፣ 6) እኔ መንገድም እዉነትም ህይወትም ነኝ እና 7) እኔ እዉነተኛ የወይን ግንድ ነኝ ፡፡ ሁልጊዜ ኢየሱስ “ እኔ “ ሲል አምላክ እንደሆነ እየገለፀ ነበር ፡፡ በዚህ በዮሐንስ ወንጌል ኢየሱስ ሰባት ምልክቶች ወይም ተዓምራቶች አሳይቷል ፤ ዮሐ (20፡ 30-31) ስለ እነዚህ ምልክቶች ምክንያት ይሰጣል፡ “ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ ክርስቶስ እንደ ሆነ እንድታምኑ “ ፡፡
ትምህርት
ዮሐንስ (21፡ 1-3)፡ “ ከዚህ በኋላ “ ባዶዉን መቃብር፣ ከትንሳኤ በኋላ የመጀመሪያ መልክን፣ የደቀ መዛሙርቱን ተልዕኮ እና የኢየሱስን መልክ ለቶማስ ይጠቅሳል ፡፡ እንደ ገና ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የገሊላ ባህር ተብሎ በሚታወቀዉ በጥብርያዶስ ባህር ተገለጠላቸዉ ፡፡ ሰዎቹ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ገሊላ ስለ መመለስ አስቸጋሪ ጊዜ ይሰጧቸዋል ነገር ግን ኢየሱስ ከትንሳኤ በኋላ ወደ ገሊላ እንደሚሄድ ሰዎስት ጊዜ ነግሯቸዋል፡ “ ከተነሳሁ በኋላ ግን ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ አላቸው “ (ማቴ 26፡ 32፣ ማቴ 28፡ 7፣ ማር 16፡ 7) ፤ ወደ ገሊላ ሄደዉ እርሱን በመጠበቅ ላይ እንዲሆኑ ብሏቸዉ የነበረዉን ደቀ መዛሙርቱ ሰምተዋል ፡፡ ቁጥር 3 አሳ አጥማጅ የነበሩትን ሁሉንም ደቀ መዛሙርት ይዘረዝራል፡ ስምዖን ጴጥሮስ፣ ዲድሞስ የሚባለዉ ቶማስ፣ ከቃና የሆነዉ ናትናኤል፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ እና ያልተጠቀሱት ሁለቱ ናቸው ፤ ሁሉም አሳ ለማጥመድ ሄዱ ነገር ግን ምንም አልያዙም ፡፡ አንዳንድ ምሁራን ደቀ መዛሙርቶቹ እንዳልታዘዙ እና ወደ ቀድሞዉ ህይወታቸዉ ተመልሰዉ እንደ ሄዱ ይናገራሉ ፡፡ በመጠበቅ ላይ እያሉ ኢየሱስን ለመጠበቅ እና አሳ ለማጥመድ ወደ ገሊላ እንደ ሄዱ አምናለሁ ፡፡
ዮሐንስ (21፡ 4-8)፡ ሲነጋም ኢየሱስበዳርቻዉ ላይ ቆመ ነገር ግን ልክ እንደ መግደላዊት ማሪያም እና በኤማሆስ መንገድ ላይ ኢየሱስን አዉቀዉት እንዳልነበረ ደቀ መዛሙርቱ አላወቁትም ( ቁጥር 4) ፤ ከዚያም ኢየሱስ ጠራቸዉና አሳ እንዳላቸዉ ጠየቃቸው (ቁጥር 5) ፡፡ በግሪክ ቃል ኢየሱስ ከእነርሱ አሳ ለመግዛትእንደ ጠየቃቸዉ ያመለክታል ፤ ኢየሱስ አሳ ለማግኘት ከጀልባዉ በቀኝ በኩል እንዲጥሉት ነገራቸው ፤ እንደ ነገራቸዉ አደረጉ ወደ ጀልባዉ መጎተት ከማይችሉት በላይ አሳ ያዙ (ቁጥር 6) ፤ በሉቃ (5፡ 1-7) ላይ ከዚህ በፊት ተፈጥሮአል ፡፡ በፊት ሆኖ የነበረውን ነገር ድግግሞች ለእነርሱ ራሱን ሊገልጥላቸዉ ተጠቀመበት ፤ ዮሐንስም እንደ ገናራሱን “ ኢየሱስን የሚወደዉ ደቀ መዝሙር “ በመጥቀስ ኢየሱስን እንዳወቀዉ አዉርቷል (ቁጥር 7) ፡፡ ( ዮሐንስ ራሱን በዚህ መንገድ አምስት ጊዜ ገለፀ፡ ዮሐ 13፡ 23፣ 19፡ 26, 20፡ 2፣ 21፡ 7 እና 21፡ 20) ይህ የሚያቃጥል ፍላጎት እና ፍቅር ለኢየሱስ አለን ? ወዲያዉኑ ስምዖን ጴጥሮስ ወደ ዉሃዉ በመዝለል ወደ ኢየሱስ ዋኘ (ቁጥር 7) ፡፡ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ከዳርቻ 100 ያክል ያርድ ጀልባዋን እና አሳዎቹን አመጡ (ቁጥር 8) ፡፡ የጴጥሮስን ድርጊት እንደ ችኩልና በማሰብ እናዘነብላለን ነገር ግን ምናልባትም ኢየሱስን ለማግኘት ወደ ባዶ መቃብሩ መሮጡ እና ወደ ዳርቻዉ መዋኘቱ ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በይበልጥ እዉቅና መስጠት ነው ፤ ወደ ኢየሱስ ለመመለስ እና ከካደዉ በኋላ ከእርሱ ጋር ያለዉን ግንኙነት ለማስተካከል ፈለገ ፡፡ በሱስ ወይም በከፍተኛ ኃጢዓት የተቸገሩ ከብዙዎቻችን በሚበልጥ መዋጀትን እንደ ሚረዱት የሚመስል ነው ፤ ጴጥሮስ ወደ ኢየሱስ መቅረብ ፈለገ ነገር ግን በእዉነት ቆሽሾ እንደ ነበር ስለ ሚያውቅ ፡፡
ዮሐንስ (21፡ 9-14)፡ ኢየሱስ ምናልባትም በአሳና እና በእንጀራ ብዙ ህዝብ እንደ መገበዉ ስዕል ቁርሳቸዉን በፍም እሳት ላይ ሰራላቸው (ቁጥር 9) ፤ የጴጥሮስ የመጨረሻ ጊዜ ኢየሱስን ሰዎስት ጊዜ ክዶበት በነበረው በፍም እሳት ጋር ነበር (ዮሐ 18፡ 18, 25-27) ፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለእርሱ ከያዙት አሳ እንዲያመጡ ነገራቸዉ ጴጥሮስም በመነሳት ከባዱን መረብ አንቀሳቀሰው (ቁጥር 10) ፤ በመረቡ ዉስጥ 153 አሳዎች ነበሩ (ቁጥር 11) ፡፡ ዮሐንስ ያን ያውቃል ምክንያቱም እንደ አይን ምስክር በዚያ ነበር ፤ 1ዮሐ (1፡ 1-4) ፡፡ ዋይርስቤ ኢየሱስ ሰዎስት ጊዜ ሰዎችን ወደ እርሱ እንደ ጋበዛቸዉ አመልክቷል፡ “ መጥታችሁ እዩ (ዮሐ 1፡ 40)፣ መጥታችሁ ጠጡ (ዮሐ 7፡ 37) እና መጥታችሁ ብሉ (ዮሐ 21፡ 12) “ ፡፡ በዮሐንስ ወንጌል ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥ ይህ ሰዎስተኛው ነበር (ዮሐ 20፡ 19-23, 20፡ 26-29 እና 21፡ 7-14) ፡፡
ዮሐንስ (21፡ 15-19)፡ ዋይርስቤ “ ጴጥሮስ እና ጌታው በግል የተገናኙ ቢሆንም እንዲሁም የጴጥሮስን ኃጢዓት ጥንቃቄ ስለ መወሰዱ ጥርጣሬ አይኖርም ነገር ግን ጴጥሮስ ጌታን በአደባባይ ስለ ካደው(ሉቃ 24፡ 31, 1ቆሮ 15፡ 5) የአደባባይ መመለስ መኖር አስፈላጊ እንደ ነበር “ ይናገራል ፡፡ ቁጥር 15-19 ይህን የሚታወቅ መታደስ ይመዘግቧሉ ፤ ሰዎስት ጊዜ ኢየሱስ ጴጥሮስ እርሱን ይወደዉ እንደ ሆነ ጠየቀው (ዮሐ 21፡ 15-17) ፤ በእነዚህ ጥቅሶች “ ፍቅር “ ለሚለዉ ቃል ሁለት ተመሳሳይ ተጠቅሟል ፡፡ ማክአርቱር “ በአዉድ ሁለት ተመሳሳዮች በተቀራረበ ቅርበት በተቀመጡ ጊዜ በትርጉም የሚለያዩትን በትንሽ የተብራራ እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢየሱስ “ ሙሉ መሰጠትን በሚያጎላው “ ቃል አጋፔን በመጠቀም ጠየቀው ጴጥሮስም በወንድማማችነት ፍቅር በሆነ ወይም በስሜታዊነት ጓደኝነት ፊሊያ የሚለዉን ቃል በመጠቀም መለሰ ፡፡ እነዚህ ቃሎች በአዲስ ኪዳን ዉስጥ በመቀያየር ጥቅም ላይ የዋሉ ናቸው ስለሆነም በመካከላቸዉ የተጋነነ ልዩነት የለም ፡፡ ይሁን እንጂ ኢየሱስ የጴጥሮስን ሙሉ መታዘዝ(ተግባር) እንደ ሰዉ አጥማጅ ፈለገ ፤ በራሱ ተግባር ዙሪያ ላይ እና ሙሉዉን በመያዝ መጫዎቱን እንዲያቆም ለጴጥሮስ እድል ለመስጠት ፈለገ ፡፡ ኢየሱስም “ በጎቼን መግብ(አሰማራ) አለው “ ፤ ኢየሱስ “ እኔ መልካም እረኛ ነኝ “ ብሎ ነበር ስለዚህም የጴጥሮስ ጥሪ የኢየሱስን በጎች እንዲጠብቅ ነበር ፡፡ “ ማሳማራት የሚለዉ ቃል ለበጎቹ ከሚጠነቀቀዉ ከእረኛዉ ስር በመሆን እግዚአብሄርን ለማገልገል የተሰጠ የመሆን ሀሳብ ያሳያል “ (1ጴጥ 5፡ 1-4) ፡፡ ማክአርቱር ማሳማራት የሚለዉ ቃል ለመንጋዉ የማያቋርጥ ምግብን መስጠትን ያሳያል ምክንያቱም “ የኢየሱስ ክርስቶስ መልዕክተኛ የመጀመሪያ ተግባር የእግዚአብሄርን ቃል ማስተማር እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡
ሁለተኛ ጊዜ ኢየሱስ ጴጥሮስን በመጠየቅ ጴጥሮስን በጎቹን እንዲጠብቅ ወይም “ እንዲከባከብ “ ነገረው (ቁጥር 16) በተጨማሪም ሰዎስተኛ ጊዜ ኢየሱስ በመጠየቅ ጴጥሮስን በጎችን “ እንዲያሰማራ “ ነገረው (ቁጥር 17) ፤ ኢየሱስ ጴጥሮስን ሰዎስት ጊዜ ጠየቀዉ ምክንያቱም ጴጥሮስ ሰዎስት ጊዜ ክዶት ስለ ነበር ፡፡ ኢየሱስ ጴጥሮስ መልሶ በደቀ መዛሙርቱ ፊት ሙሉ በሙሉ መለሰው (አደሰው) ፡፡ የጴጥሮስ ኢየሱስን እንደ ክርስቶስ መካድ በጣም ስላስጨነቀዉ ምርር ብሎ አስለቅሶት ነበር ፡፡
በአሁኑ ጊዜ በአገልግሎት በእዉነት የቆሸሹ ሰዎች አሉ ቤተ ክርስቲያንም ፈልጎ ለአገልግሎት ከመመለስ ይልቅ ስቦ ላማስወጣት አዘንባላለች ፡፡
እርሱን በመመለስ ኢየሱስ ለወደፊት በጴጥሮስ ላይ ስለ ሚሆነው ተነበየ - በኢየሱስ ባለዉ እምነት እንደ ሚሞት (ቁጥር 18-19) ፤ ጴጥሮስ ከክርስቶስ ሞት (67-68) በነበረዉ ንጉስ ኔሮ ተሰቀለ በልምድ መሰረት ስቅላት በመስቀል ላይ ከታች ወደ ላይ አልተሰቀለም ምክንያቱም ልክ እንደ መሲሁ መሰቀል አልፈለገም ፡፡ ምንም እንኳን ጴጥሮስ ሰዎስት ጊዜ ቢቆሽሽም ( እኛም ሁላሽንም ቢያንስ አንድ ጊዜ ቆሽሸናል) ለአገልግሎት የታደሰ መሆን ቻለ ምክንያቱም ለኢየሱስባለዉ ፍቅር ፡፡
መዝጊያ
ከጴጥሮስ የተማርነዉ ለእርሱ መከራን ለመቀበል እና ለመሞት የተዘጋጀን ለመሆን ለሚያስፈልገን ሀሳብ ለክርስቶስ የታደስን መሆን እንደ ምንችል ነው ፤ በፊት ያደረግነዉ ምንም ቢሆን ሁላችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ተፅዕኖ ማምጣት እንችላለን ምክንያቱም ኢየሱስ የተትረፈረፈ ህይወት ሊሰጥ የመጣ የእግዚአብሄር ልጅ ስለ ሆነ ፡፡ ያም ህይወት አያበቃም ምክንያቱም ስለ ቆሸሽን ፤ መቼም ቢሆን በክርስቶስ ተስፋ እንዳትቆርጡ ምክንያቱም እርሱ በእኛ ተስፋ ስለ ማይቆርጥ ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 397.
Wiersbe, pp. 397-398.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1426.
MacArthur, p. 1426.
MacArthur, p. 1427.
MacArthur, p. 1427.
ጥያቄዎች
-
በምዕራፍ 21 መክፈቻ ጥቅሶች ላይ ደቀ መዛሙርቱ ያለ ስኬት እንደ ገና አሳ አጠመዱ ፤ የኢየሱስን ወንጌል ከማካፈል ይልቅ ለምን አሳ ያጠምዱ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ?
-
በዮሐ (21፡ 9) ደቀ መዛሙርቱ ወደ ዳርቻ በተገኙ ጊዜ ኢየሱስ አሳ እና በእሳት ላይ እንጀራ ነበረው ፤ አሳዉን እና እንጀራዉን ከየት አገኘው ? ኢየሱስ ከምግብ ያለፈ “ መገባቸው “ ?
-
በዮሐ (21፡ 15-17) ኢየሱስ ጴጥሮስን እንደ ሚወደዉ ለምን ሰዎስት ጊዜ ጠየቀው ? ኢየሱስ “ በጎቼን አሰማራ “ ማለቱ ምን ማለቱ ነበር ? በጎቹ እነማን ናቸው ?
-
በዮሐ (21፡ 21) ዮሐንስ ስለ ሚያደርገው ጴጥሮስ ኢየሱስን ለምን እንደ ጠየቀዉ ምን ታስባላችሁ ? ኢየሱስ ለጴጥሮስ እንዴት መለሰለት ?
-
በዮሐንስ 21 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin John 21:17
“He asked him the third time, “Simon, son of John, do you love Me?” Peter was grieved that He asked him the third time, “Do you love Me?” He said, “Lord, You know everything! You know that I love You.” “Feed My sheep,” Jesus said.”
በዮሐንስ ወንጌል የመጨረሻ ምዕራፍ፥ ኢየሱስ ፀጋውን እና ፍቅሩን በጴጥሮስ ሕይወት በኩል አሳየ፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ከመሞቱ በፊት፥ ጴጥሮስ ሶስት ጊዜ ካደው፡፡ አሁን፥ ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ፥ የት ማጥመድ እንዳለበት በማሳየት፥ ካሰበው በላይ ብዙ አሳዎችን በማዘጋጀት፥ ቁርሱን በማብላት ፥ኢየሱስ ጴጥሮስን በአካል መጥቶ ረዳው፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ለጴጥሮስ ሁለተኛ እድል ሰጠው፡፡ ጴጥሮስ ኢየሱስን ከካደው በኋላም፥ በገሃድ ወደ አገልግሎት መለሰው፡፡
ወዳጆች፥ ልክ እንደ ጴጥሮስ፥ ኢየሱስ በጣም ይወዳችኋል፡፡ አዎን፥ ልባችሁን ያያል፡፡ አዎን፥ በኃጢያት ስትወድቁ፥ ከእርሱ ዘወር ስትሉ፥ እና ድካሞቻችሁ ምን እንደሆኑ ያውቃል፡፡ ግን ኢየሱስ ለእናንተ ነው፡፡ የራሴ ብሎ ይጠራችኋል፡፡ ስለዚህ፥ ልክ እንደ ጴጥሮስ ፥ በኃጢያት ከወደቃችሁ፥ ለፈተናዎቻችሁ እጅ ከሰጣችሁ፥ ወይም ቀላል መውጪያ መንገድን ከፈለጋችሁ፥ ከኢየሱስ ጋር ያላችሁ ሕይወት አላበቃም፡፡ ኢየሱስ በእናንተ ስራውን አልጨረሰም፡፡ ይወዳችኋል፥ ስለ እናንተ ወደ ምድር መጥቷል፡ ኢየሱስ ለጴጥሮስ አዲስ የስራ ድርሻ ሰጠው፡፡ አዎ፥ በጴጥሮስ ነገሮችን ማበላሸት ውስጥም እንኳን፥ ኢየሱስ ጴጥሮስን ለወንጌል አገልግሎት በመመለስ፥ የእርሱን ሕዝብ እንዲወድ እና እንዲንከባከብ ጠራው፡፡ ወዳጆች፥ ኢየሱስ ለእናንተም ተመሳሳይ ነገርን ያደርጋል፡፡ ምህረቱ ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፥ ርህራሄውም አያልቅም፡፡ ታሪካችሁ አላበቃም፡፡
“ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው። ሦስተኛ ጊዜ፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። ሦስተኛ፦ ትወደኛለህን? ስላለው ጴጥሮስ አዘነና፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ኢየሱስም፦ በጎቼን አሰማራ።”
—ዮሐንስ 21:17
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ሰቆቃው ኤርምያስ 3:21–23 – “ይህችን በልቤ አኖራለሁ፥ ስለዚህ እታገሣለሁ። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው። "
- ዮሐንስ 18:27 – “ጴጥሮስም እንደ ገና ካደ፥ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።”
2ኛ ጴጥሮስ 3:9 – “ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 89
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።