Transferring Leadership
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Commander Joshua 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የኦሪትን (የህግን) አምስት መፅሀፍት እና የወንጌላትን አራት መፅሀፍ ካጠናን በኋላ አሁን በታሪክ መፅሀፍት ዉስጥ አዲስ ትምህርት እንጀምራለን ፡፡ እስካሁን 200 ክፍል ጨርሰናል ፡፡ በኢያሱ መፅሀፍ የሚጀምረዉን 12 ታሪካዊ መፅሀፍትን እናያለን ፤ ከኢያሱ እስከ ነህምያ (1405 -424 ከክርስቶስ ዉልደት በፊት ) ለ1000 አመታት የቆየዉን እናጠናለን ፡፡ እስራኤላዊያን ከ430 አመት በግብፅ እንደ ባሪያ ከሆኑበት (ዘጸ 12፡ 40-41) እና ከ40 አመት በምድረበዳ ከመንከራተት በኋላ ወደ ተስፋይቱ ምድር ባለቤትነት እየመጡ ነበር ፡፡
የታሪክ መፅሀፍት በሰዎስት ምድብ ሊከፋፈሉ ይችላሉ፡
ቅድመ ግዞት (ከምርኮ በፊት) | በግዞት (በምርኮ ጊዜ) | ከግዞት በኋላ (ከምርኮ በኋላ) |
ኢያሱ, መሳፍንት, ሩት | አስቴር | ዕዝራ |
1, 2 ሳሙኤል | ነህምያ | |
1, 2 ነገስት | ||
1, 2 ዜና |
እንዲሁም ታሪካዊ መፅሀፍት ከታች እንዳለዉ ሊከፈሉ ይችላሉ፡
ከንጉስነት ስልጣን የቀደመ | የንጉስነት ስልጣን | ከንጉስነት ስልጣን በኋላ |
ኢያሱ | 1, 2 ሳሙኤል | ዕዝራ |
መሳፍንት | 1, 2 ነገስት | ነህምያ |
ሩት | 1, 2 ዜና | አስቴር |
ኢያሱ (ትርጉሙ “ እግዚአብሄር ያድናል ወይም ጌታ አዳኝ ነው “ ማለት ነው) በሙሴ ስር ያጠና እና ስለ ክርስቶስ መምጣት ጥላ ነበር ፡፡ ለኢያሱ መፅሀፍ ያለዉ አንድ ቃል አዛዥ ነው ፤ የመፅሀፉ ፀሀፊ ኢያሱ ነበር ይሁንና አናዳንዶች ታላቁ ካህን አልዓዛር ወይም ልጁ ፊንሀስ እንደ ነበር ያስባሉ ፡፡ ኢያሱ 90 አመቱ ላይ የእስራኤል መሪ ሆነ ፤ 110 አመቱ ላይም ሞተ (ኢያ 24፡ 29) ፡፡ በኢያሱ መፅሀፍት ዉስጥ የእግዚአብሄርን መታመን እና የተስፋይቱን ምድር መዉረስ ስለ እስራኤል የእግዚአብሄርን ተስፋ መፈፀም እናያለን ፡፡
ትምህርት
ኢያሱ (1፡ 1)፡ ከሙሴ መሪነት ወደ ኢያሱ ግልፅ የሆነ ሽግግር እናያለን ፤ ቻርለስ ዌስልይ “ እግዚአብሄር ሰራተኛዉን ይቀብራል ነገር ግን በስራዉ ቀጠለ “ ብሎ ገልጧል ፤ ጄ. ኦስዋልድ ሳንድረስ “ በእግዚአብሄር የመነጨ(የተጀመረ) ስራ እና በመንፈሳዊ መርህ ላይ መፈፀም የመሪ መቀየር ነዉጥን ያሸንፋል በዚህም በእዉነት የተሸለ እንደ ሚሆን “ ተናግሯል ፡፡
ማክአርቱር እግዚአብሄር ኢያሱን በእርሱ ልምምድ በሙሴ ስር ለመሪነት እንዳዘጋጀዉ ይገልፃል፡
- በአገልግሎት ዉስጥ (ዘጸ 17፡ 10, 33፡ 11)
- በዉትድርና ዉስጥ (ዘጸ 17፡ 9-13)
- በስለላ ዉስጥ (ዘኁ 13-14)
በሙሴ ልመናን እና ተግባርን (ዘኁ 27፡ 15-17)
በእግዚአብሄር ሉዓላዊነት ዉስጥ (ዘኁ 27፡ 18)
በመንፈስ መገኘት ዉስጥ (ዘኁ 27፡ 18, ዘዳ 34፡ 9)
ከሙሴ በመለየት (ዘኁ 27፡ 18-23, ዘዳ 31፡ 7-8, 13፡ 15)
ፈፅሞ እግዚአብሄርን በመከተል ዉስጥ (ዘኁ 32፡ 12)
ኢያሱ (1፡ 2-3)፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያን ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደ ሚገቡ ሰጥቷቸዉ የነበረውን ተስፋ በኢያሱም መሪነት ስርም ደገመው (ዘፍ 12፡ 7, 13፡ 14-15, 15፡ 18-21) ፡፡ ማንኛዉም የሚረግጡት ቦታ የእግዚአብሄር ይሆናል ፤ ወደ ምድሪቱ በመጓዝ ደረጃ በደረጃ መብት ያገኛሉ ፡፡
ሮሜ (10፡ 15) ይህን ትዕዛዝ እና መፈፀም የሚያግዝ ይመስላል፡ “ መልካሙን የምስራች የሚያወሩ እግሮቻቸዉ እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ ? “ ፤ ወንጌልን የሚያወሩ ሁሉም ወደ ሚሄዱበት ሁሉም ቦታ ይህን ክስተት መሳል እንዲችሉ እግዚአብሄር መንገዱን እንዳዘጋጀላቸዉ ታስባላችሁ ?
ኢያሱ (1፡ 4-5)፡ ቁጥር 4 እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን የሰጣቸዉን ምድር ሁሉንም ዳርቻዎች ያስቀምጣል ፤ የብሉይ ኪዳንን ካርታ በመጠቀም ዳርቻዎቹን ከአሁኑ ከእስራኤል ድንበሮች ጋር ብታወዳድሩት ግልፅ ነው አይገናኝም ፡፡ የሊባኖስ፣ የሶሪያ፣ የጋዛ እና የጆርዳን ምድር ሁሉም እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን በሰጣቸዉ ምድር ዉስጥ የተካተቱ ነበር ፤ በአሁኑ ጊዜ የማይከሉ የሚሆኑበት አስፈላጊነቱ ይህ ነዉ ምክንያቱም አሁንም በእግዚአብሄር እና በህዝቡ ስር ስለሆኑ ፡፡ በሚያናድድ ሁኔታ በመካከለኛዉ ምስራቅ ምድሪቱን በመክፈል እና ጥቂቱን በመስጠት ሰላምን ማሳካት እንደ ምንችል እናስባለን ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚሄደዉ ከእግዚአብሄር ተስፋ በተቃራኒ ነው ፤ የዘረኝነት አስተያየት አይደለም የእግዚአብሄር ቃል ጥናት እንጂ ፡፡
በቁጥር 5 እግዚአብሄር ኢያሱን በህይወት እስካለ ድረስ ከእርሱ ጋር እንደ ሚሆን ቃል ገባለት ፤ እግዚአብሄር ይህ ተስፋ እንዲሁ ለሌሎችም አድርጓል፡ ያዕቆብ (ዘፍ 28፡ 15)፣ ጌዲዎን (መሳ 6፡ 16) እና አይሁዶች ከባቢሎን ግዞት ሲመለሱ (ኢሳ 41፡ 10, 43፡ 5) ፡፡ እግዚአብሄር በልጁ በአማኑኤል በኩል ሁልጊዜ ከእኛ ጋር እንደ ሚሆን ተስፋ ይሰጣል (ማቴ 1፡ 23) ፤ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ነው (ማቴ 28፡ 20) ደግሞም በፍፁም አይተወንም (ዕብ 13፡ 5) ፡፡ በታሪክ መፅሀፍት ዉስጥ ያለዉ ቋንቋ ከአዲስ ኪዳን ጋር ተመሳሳይ ፤ እግዚአብሄር ትናትናም፣ ዛሬም፣ ነገም…..ሁልጊዜም ተመሳሳይ ነው ፡፡
ኢያሱ (1፡ 6-9)፡ ቁጥር 6 በምዕራፍ 1 እግዚአብሄር ኢያሱን “ ጽና አይዞህ “ ካለዉ ከብዙ ምሳሌዎች የመጀመሪያ ነው ፤ እግዚአብሄር የምድሪቱን የተለያ ክፍል ለተለያየ ነገዶች ሰጥቶ ነበር ነገር ግን መጀመሪያ እስራኤላዊያን ምድሪቱን መያዝ አለባቸው ፡፡ እግዚአብሄር እንደ ገና ኢያሱን ለሙሴ የተሰጠዉን ሁሉንም ትዕዛዝ በመከተል (ወይም በእነርሱ ዉስጥ ቃሉን በመሳላሰል) “ ጽና አይዞህ “ አለው ፡፡
በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንን የገጠማት ጉዳይ ሁል ጊዜ በእርሷ ዉስጥ የእግዚአብሄር መንፈስ የለም በዚህም ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ ትስታለች ፡፡ በእግዚአብሄር ቃል በምንሆን ጊዜ እና ወደ ምንሄድበት ሁሉ እርምጃችንን እንዲቆጣጠር ስንፈቅድለት ስኬትን እናገኛለን ፡፡
ኢያሱ (1፡ 10- 18)፡ ኢያሱ ከህዝቡ መካከል በሰዎስት ቀናት ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመሻገር እንዲዘጋጁ እንዲነግሩአቸው ሰራተኞችን ላከ ፤ በዮርዳኖስ ወንዝ በምስራቅ በኩል ተቀምጠዉ ለነበሩት (ቁጥር 12-15) ለሮባዊያን፣ ለጋዲያዊያን እና ለምናሴ ግማሽ ነገዶች ነገር ግን ለተስፋይቱ ምድር መዋጋት ስለ ነበረባቸዉ ነገራቸው፡፡ ኢያሱ የእስራኤላዊያን ጉዞ መጨረሻዉ እንደ መጣ እና የመነጫነጭ ጊዜ እንዳበቃ እያሳወቃቸዉ ነበር ምክንያቱም እግዚአብሄር ለእነርሱ ወደ ተስፋይቱ ምድር መንገዱን አዘጋጅቶላቸዉ ስለ ነበር ፡፡ ሁሉም ሰዉ የኢያሱን መሪነት ለመከተል ተስማሙ (ቁጥር 16) ፤ እስከ መጨረሻዉ ድረስ የታዘዙ ነበሩ ፡፡
መዝጊያ
በሚመጡት ቀናት በህዝቡ መካከል አንዳንድ አስደናቂ በእግዚአብሄር የጉዞ ታሪክ ዉስጥ እንሄዳለን ፤ እንኳን ወደ ኢያሱ ጥናት መጣችሁ ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 255.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Joshua, p. 2; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/joshua.pdf.
Charles Wesley; quoted in Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Joshua (Nashville: Thomas Nelson Publications, 2003), p. 16.
J. Oswald Sanders, Spiritual Leadership (Chicago: Moody Press, 1967), p. 132; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Joshua, pp. 12-13.
John MacArthur, p. 257.
ጥያቄዎች
-
በቁጥር 8 እግዚአብሄር የሚለው “ የዚህ ህግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ “ ይህ ማለት ምን ማለት ? በቀንና በማታ ማሳላሰል ማለት ምን ማለት ነው ?
-
ሰላዮቹ ለመኖር ወደ ረዓብ ቤት ለምን እንደ ሄዱ ምን ታስባላችሁ ?
-
የእስራኤላዊያን ሰላዮች ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት ፈርተዉ ነበር (ዘኁ 13፡ 28-29) ፤ ከዚያስ ከነዓናዊያን እስራኤላዊያን ወደ ምድራቸዉ ሲገቡ ለምን እንደ ፈሩ ምን ታስባላችሁ ? (ኢያ 2፡ 9-11)
-
በመፅሀፍ ዉስጥ የእግዚአብሄር ሰዎች ከሞት እንዲያመልጡ በቤታቸዉ ላይ ምልክት እንዲያደርጉ የተነገረባቸዉን ሌላ ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ ? (ዘጸ 12፡ 23)
-
በኢያ (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Joshua 1:5, 7a
“No one will be able to stand against you as long as you live. I will be with you, just as I was with Moses. I will not leave you or forsake you . . . Above all, be strong and very courageous to carefully observe the whole instruction My servant Moses commanded you.”
ከሙሴ ሞት በኋላ፥ ኢያሱ የእስራኤላውያን መሪ ሆነ፡፡ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሮ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሕዝቡን እንዲመራ ጌታ ኢያሱን አዘዘው፡፡ ወደ አዲሱ ምድር ከመሻገሩ በፊት፥ ጌታ ለኢያሱ ስለታማኝነቱ ቃል ገባለት፥ "የእግራችሁ ጫማ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቻለሁ፡፡ ማንም ሊቋቋምህ አይችልም፡፡ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፡፡ አልተውህም፡፡ በምታደርገው ነገር ሁሉ ይከናወንልሃል፡፡ በምሄድበት ቦታ ሁሉ ከአንተ ጋር ነኝ፡፡"
በእምነት ከጌታ ጋር ስትራመዱ፥ የእግዚያብሔር ተስፋዎች ለእናንተም እንዲሁ እውነት ናቸው፡፡ ቃሉ ትላንትና፥ ዛሬ፥ ነገም፥ ያው ነው፡፡ ጌታ አንድ ነገር እንድታደርጉ ወይም ወደ አንድ ቦታ እንድትሔዱ ሲጠራችሁ፥ በፓርክ ውስጥ ከአንድ ሰው ጋር መጸለይ ወይም ስራችሁን ለቃችሁ ሌላ እንድትጀምሩ ቢሆን፥ በምትሄዱበት ሁሉ እግዚያብሔር ከእናንተ ጋር ነው፡፡ ነገርግን፥ እግዚያብሔር ኢያሱን " ከህጉ መጽሐፍ ፈቀቅ እንዳይል" አዘዘው፡፡ እግዚያብሔር በእምነት ሲመራችሁ፥ በእግዚያብሔር ቃል ተጠብቃችሁ መቆየትን አስታውሱ፡፡ በእምነት መራመድ ጀምራችሁ ከዚያም በራሳችሁ መንገድ እንድትሄዱ አይፈልግም፡፡ ይልቁንም፥ በእምነት ስትራመዱ በታማኝነት የገባውን ቃል በማስታወስ ቃሉን እንድታነቡ እና እንድትከተሉ ጌታ ይፈልጋል፡፡ በእግዚያብሔር ቃል እውነት ውስጥ ብርቱ እና ጽኑ ሆናችሁ ትቆያላችሁ፡፡ ዛሬ፥ ጌታ አምላካችሁ በምትሄዱበት ሁሉ ከእናንተ ጋር እንደሚሆን በማወቅ፥ በእምነት ተራመዱ፡፡
“በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም።. . . ነገር ግን ጽና፥ እጅግ በርታ፤ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም”
—መጽሐፈ ኢያሱ 1:5, 7ሀ
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘፍጥረት 28:15 — “እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።”
- የማቴዎስ ወንጌል 28:20 — “ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
- ወደ ዕብራውያን 13:5 — “አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕልበታሪክ መፅሀፍት፡ ክፍል 1
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።