Breaking Camp
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Commander Joshua 3-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በኢያሱ 2 ኢያሱ ወደ ኢያሪኮ ከተማ ሁለት ሰላዮች ላከ ፡፡ ኢያ (1፡ 11) በሰዎስት ቀናት ዉስጥ ለመጓዝ እንዲዘጋጁ ያዘዛቸዉን ታስታዉሳላችሁ ? ይህ ለእስራኤላዊያን ታላቅ ሳምንት የሚሆን ነበር ምክንያቱም ወደ ተስፋዪቱ ምድር እየሄዱ ስለ ነበር ፡፡ ሰላዮቹ ደብቃ የረዳቻቸዉን ረአብን አገኙ ፤ በእርዳታዋ ምክንያት እሷ እና ቤተሰቦቿ እስራኤላዊያን ከተማዋን በያዙ ጊዜ ይድናሉ ፡፡ በምዕራፍ 3 ለሆነ ይህ መነሻ ሀሳብ ነው ፡፡
ትምህርት
ኢያሱ (3፡ 1-2)፡ ኢያሱ በጥዋት በማለዳ ጀመረ ፤ በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ የእግዚአብሄር ሰዉ በጥዋት በማለዳ እንደ ሚነቁ ይመስላል (ዘጸ 24፡ 4, 2ዜና 29፡ 20, መዝ 57፡ 8, ማር 1፡ 35) ፡፡ ኢያሱ ከሁሉም እስራኤላዊያን ጋር ሰጢምን ለቀቀ ፤ ወደ ዮርዳኖስም ወንዝ በመሄድ ሰፈሩ ፡፡ ከሰዎስት ቀን በኋላ ሰራተኞቹ ህዝቡን ለማዘዘዝ በጠቅላላ በሰፈሩ ዉስጥ ሄዱ ፤ የኪዳኑን ታቦት በያዩ ጊዜ ሰፈራቸዉን በመስበር እንዲከተሉት ፡፡
ኢያሱ (3፡ 3)፡ ይህን ቁጥር እወደዋለሁ ምክንያቱም የእግዚአብሄርን መንቀሳቀስ ለማየት በምፈልግ ጊዜ ወደ እነዚህ ቁጥሮች ይመራኛል ፡፡ የእግዚአብሄርን ስራ ለመስራት መኖሪያችንን(የሰፈርንበትን) መስበር ያስፈልገናል ፡፡ ብዙ ሰዎች መስፈሪያቸዉን ለመስበር ፍላጎቱ እንዳላቸዉ አስባለሁ ነገር ግን ለማድረግ ይፈራሉ ፡፡
ኢያሱ (3፡ 4)፡ እስራኤላዊያን ከታቦቱ 1,000 ያርድ(ግማሽ ማይል) ርቀት ይጠብቃሉ ፤ መስፈሪያችሁን በሰበራችሁ ጊዜ ለመመልከት የምትፈልጉት በመንገዱ ላይ ለመመልከት ሙሉነት አትጠብቁትም ፡፡ ካምፓችሁን በመስበር ወደ ማታዉቁት ለመሄድ እምነት ሊኖራችሁ ያስፈልጋል ፤ ከአንዳንድ ነገር አንፃር በካምፕ ዉስጥ ጥቂት ድስታ ይኖራል ፡፡ በመጨረሻም እስራኤላዊያን መጀመሪያዉ መስመር ላይ ነበሩ ! እስካሁን አይተዉት ከነበረው እንደ ማይመስል ይጠብቃሉ ፡፡
ኢያሱ (3፡ 5)፡ ኢያሱ ህዝቡን ራሳቸዉን እንዲቀዱስ ነገራቸዉ ምክንያቱም በቀጣዮቹ ቀናት እግዚአብሄር በመካከላቸዉ ስለ ሚሆን ፤ እርኩስ ከሆነ ከማንኛዉም ነገር ጋር ያልተገናኙ እንደ ነበሩ እርግጠኞች መሆን አለባቸዉ፡፡ ይህ እግዚአብሄር ለህዝቡ ያመሰረተዉ የመቀደስ ስርዕት ነው ፤ ዋረን ዋይርስቤ የፃፈው ይህ ማለት “ ሁሉም ሰዉ በመታጠብ ልብሳቸዉን ይቀይራሉ በተጨማሪም የተጋቡ ጥንዶች ለእግዚአብሄር በሙሉ ራሳቸዉን ለእግዚአብሄር የተሰጡ ይሆናሉ “ ማለት ነው ፡፡ እራሳቸዉን ንፁህ አድርገዉ ይጠብቃሉ ፡፡
ይህ አድስ ጅማሬ እንደ ነበር የሚል የሚመስል ነው ፡፡ ኃጢዓት እንደ ቆሻሻ ስለሆን መታጠብ ያለበት ነው ( 2ሳሙ 12፡ 20, መዝ 51፡ 2) ፡፡ በመንፈሳዊ ንግግር እግዚአብሄር እስራኤላዊያን እንዲዘጋጁ አስፈለገው ፤ በሮሜ 6 ከምናየዉ ጥምቀት ጋር ተመሳሳይ ስዕል ያለዉ ነው ፡፡
ኢያሱ (3፡ 6-7)፡ ካህናቱ ታቦቱን በመሸከም በህዝቡ ፊት ይሄዳሉ ፤ አንዴ ካምፕ ስትሰብሩ እግራችሁን እርጥብ ዉስጥ ማስገባት ያስፈልጋችኋል ! በሌላ ቋንቋ ወደ ፊት መጓዝ ያስፈልጋችኋል ፡፡ እግዚአብሄር ኢያሱን በእስራኤል እይታ አከበረው (ከሙሴ ጋር እንዳደረገው) ስለሆነም መሪያቸዉ እንደ ነበር ያውቃሉ ፡፡ በእዉነቱ እግዚአብሄር ኢያሱን እና ካህናቱን ከእስራኤል ጋር እንደ ነበር ለማሳየት ተጠቀመባቸው ፡፡
ኢያሱ (3፡ 8-9)፡ ኢያሱ ካህናቱን ያዛቸዋል ፤ በዮርዳኖስ አጠገብ በደረሱ ጊዜ በዉሃዉ ጋር ይቆማሉ ፡፡ በህይወታችሁ የእግዚአብሄርን እንቅስቃሴ ለማየት ስትፈልጉ ለፍቃዱ ታዛዥ መሆን ያስፈልጋችኋል ! ሁሉም እንደ ገና ልክ እንደ ቀይ ባህር ድርጊት ይመስላል ? ለኔ ይሄ ይህ የተለዬ ታሪክ ነው ፡፡ እዉነታዉ በእምነት መጓዝ ያስፈልጋችኋል ነው (2ቆሮ 5፡ 7) ፤ ማንም ሰዉ ስለ ሚሆነዉ ምንም ፍንጭ አልነበረዉም ፡፡ በእምነት ብቻ ካህናቱ ወደ ዉሃዉ ይገባሉ ፡፡ በእምነት መጓዝ ትርጉም ባይሰጥም እንኳን (ያዕ 1፡ 22) እግራችሁ እንዲረጥብ በእምነት መጓዝ ያስፈልጋችኋል (ዕብ 11፡ 6) ፡፡
ኢያሱ (3፡ 10)፡ ኢያሱ “ እግዚአብሄር የሚያደርገዉን ታያላችሁ አለ “ ፤ እግዚአብሄር በምድሪቱ ሰባት ቡድኖችን ያስወግዳል ፡፡ እስራኤላዊያን እንደ ተሻገሩ እግዚአብሄር በምድሪቱ ጠላቶቻቸዉን እንደሚያስወግድ ተናግሯል ፡፡ ወንጌልን የምናጋራ አይመስለኝም ምክንያቱም እግዚአብሄር በነገሮች ጥንቃቄ እንደ ማይወስድ ጠላቶቻቸዉን እንፈራለን ፡፡
ኢያሱ (3፡ 11-13)፡ ኢያሱ ከእያንዳንዱ እስራኤል ነገድ አንድ 12 ሰዎች መረጠ ፡፡ በምዕራፍ 4 እነዚህ ሰዎችወደ ጨዋታ ይመጣሉ ፤ ኢያሱ እስራኤላዊያንን ካህናቱ በባህሩ ዉስጥ በቆሙ ጊዜ ዉሃዉ የተቆረጠ በመሆን “ እንደ ክምርም ይቆማል “ (ቁጥር 13) (ልክ እንደ ግድግዳ) ነገራቸዉ ፡፡
ኢያሱ (3፡ 14-17)፡ ህዝቡ ዮርዳኖስ ለመሻገር ካምፓቸዉን ሰበሩ ፡፡ ካህናቱ በወንዙ ዉስጥ ወዲያዉኑ እንደ ቆሙ ዉሃዉ በመቆም እንደ ክምር በመነሳት 18 ማይል ተዘረጋ ፤ አስታዉሉ 2 ሚሊዮን ሰዎች ወንዙን መሻገር ያስፈልጋቸቸዋል ፡፡ ካህናቱህዝቡ በደረቅ መሬት መሻገር ጀምረዉ ሁሉም እስራኤላዊ በተቃራኒ ዳርቻ እስከ ሚደርሱ ድረስ በዮርዳኖስ መካከል ላይ ይቆማሉ ፤ ካምፓችንን በምንሰብር እና እግራችን ሲረጥብ ተዓምራት መጠበቅ እንችላለን ፡፡
ኢያሱ 4፡ ኢያሱ 12ቱን ሰዎች በመጥራት እያንዳንዳቸዉ ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል አንዳንድ ትልቅ ድንጋይ እንዲወስዱ አዘዛቸው (ቁጥር 8) ፤ እነዚህ ሰዎች እነዚህን ድንጋዮችእግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረዉን ለእስራኤላዊያን እንደ መታሰቢያ እንዲያገለግሉ በሰፈራቸዉ ጠርዝ ላይ ያቆሟቸዋል ፡፡
ኢያሱ እስራኤላዊያንን ድንጋዮቹን ያየ የምድር ሰዉ ሁሉ እግዚአብሄር ሁሉን ቻይ እንደ ሆነ እንደሚያዉቁ እና ሁል ጊዜ እንደ ሚፈሩት ነገራቸው (ቁጥር 24) ፡፡ ኢያሱም 12ቱን ድንጋዮች በማንሳት የኪዳን ታቦት በነበረበት በዮርዳኖስ መካከል ላይአስቀመጣቸው (ቁጥር 9) ፡፡ ሁሉም ሰዉ በተቃራኒዉ ዳርቻ ከደረሱ በኋላ ካህናቱ መሻገሩን ይጨረሳሉ ፤ ካህናቱ ደረቅ ምድር ላይ ወዲያዉኑ እንደ ቆሙ ወንዙ ወደ ቀደመ ፍሰቱ ተመለሰ (ቁጥር 18) ፡፡
መዝጊያ
ሁሉም ሰዉ እግዚአብሄር ሁሉን ቻይ እንደ ሆነ ያዉቃል ፡፡ እዉነታው እስራኤላዊያን ወደ አዲስ ወቅት እየተሻገሩ እንደ ነበር ነው ፤ ርስታቸዉን እየወረሱ ነበር ፤ ኢያሱም እንደ ክርስቶስ አይነት አገለገለ፡
1ቆሮ (2፡ 9-10)፡ “ አይን ያላየችዉ ጆሮም ያልሰማዉ በሰዉም ልብ ያልታሰበዉ እግዚአብሄር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንደ ተፃፈ እንዲህ እንናገራለን ፡፡ መንፈስ የእግዚአብሄርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሄር በመንፈሱ በኩል ገለጠው “ ፡፡
እግዚአብሄር በእርሱ ባለን ግንኙነት በኩል እነዚህን ጥልቅ ነገሮች እያዘጋጀ ነው ፤ እግዚአብሄር ለእኛ ያስቀመጠዉ(ያዘጋጀዉ) ርስት አለው ፤ ይህን ርስት ለመቀበል ብቸኛዉ መንገድ በእምነት መጓዝ ነው (መዝ 47፡ 4)፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Joshua (Colorado Springs, GA: David C. Cook, 2003), p. 30.
ጥያቄዎች
-
የእስራኤላዊያን ታቦቱን መከተላቸዉ አስፈላጊነቱ ምንድን ነው ? (ዘጸ 13፡ 21-22፣ ዮሐ 16፡ 7፣ 13)
-
በሁሉም እስራኤል ፊት እግዚአብሄር ኢያሱን ለምን ሞገስ እንደ ሰጠዉ ምን ታስባላችሁ ?
-
ካህናቶቹ ፀንተዎ ቆመዉበት ከነበረዉ ቦታ ስር ድንጋዮቹን እንዲወሰዱ እግዚአብሄር ለምን አዘዘ ? (ማቴ 7፡ 24)
-
እግዚአብሄር ዉሃዉን እንዲከፍለዉ ካህናቱ በወንዙ ዉስጥ ለምን እንደ ሚቆሙ ምን ታስባላችሁ ?
-
በኢያ (3-4) በትምህርት ወይም በትናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Joshua 3:14-15
“When the people broke camp to cross the Jordan, the priests carried the ark of the covenant ahead of the people. Now the Jordan overflows its banks throughout the harvest season. But as soon as the priests carrying the ark reached the Jordan, their feet touched the water at its edge and the water flowing downstream stood still, rising up in a mass that extended as far as Adam, a city next to Zarethan.”
እስራኤላውያን የተስፋውን ምድር ከፊታቸው ተመለከቱ እና የዮርዳኖስን ወንዝ በመንገዳቸው ውስጥ አዩ፡፡ ኢያሱ እንዴት መሻገር እንዳለባቸው ከጌታ ትእዛዝን ተቀብሏል፡፡ በመጀመሪያ እስራኤላውያን፥ የምቾት ቦታን በመተው፥ ድንኳናቸውን ለቀው መውጣት ነበረባቸው፡፡ ከዚያም ካህናቱ በሁለቱም እግሮቻቸው ውሃው ውስጥ መቆም ነበረባቸው፡፡ እነዚህን ትእዛዛት ሲከተሉ፥ የእግዚያብሔርን ተአምራዊ እጅ አዩ—በሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን በወንዙ ዳርቻ ላይ እንዲራመዱ በማስቻል፥ የዮርዳኖስ ወንዝ ደረቀ፡፡
ድንኳኖቻቸውን ለቀው ውሃው ላይ እንዲቆሙ . . . በእምነት ሲራመዱ እስራኤላውያን እንዲያደርጉ የታዘዙት ይህንን ነበር፡፡ ዛሬ ይህ ለእናንተ ምን ማለት ነው? በህይወታችሁ ከምቾት መለየት ያለባችሁ የቱ ጋር ነው? ለብዙ አሥርት አመታት ከያዛችሁት ሥራ እንድትርቁ ጌታ ጠይቋችኋል? ምናልባት ለወራት በልባቸሁ የከበደን ነገር ለአንድ ሰው መናገር ሊያስፈልጋችሁ ይችላል፡፡ ድንኳንን ለቆ የመውጪያው ጊዜው ነው፡፡ ከዚያም ሙሉ በሙሉ ግቡ፡፡ ለማድረግ ያህል አታድርጉ፡፡ በጌታ ጥሪ እርግጠኛ ሁኑ፡፡ በሁለቱም እግሮቻችሁ ውሃው ውስጥ ቁሙ፡፡ ወደ ሌላ ከተማ ተዘዋወሩ፡፡ አናግሯችሁ የማያውቀውን ወዳጃችሁን እራት ጋብዙ፡፡ ዝም ብላችሁ ሂዱ፡፡ ጌታ እንድታደርጉት እየመራችሁ ከሆነ፥ ከእናነተ ጋር ይሆናል፡፡ ለምሪቱ በመታዘዝ እና በመታመን ስትንቀሳቀሱ፥ የእግዚያብሔርን ሀያል እጅ፥ ታላቅ ሀይሉን፥ እና ታላቅ መግቦቱን በህይወታችሁ ታያላችሁ፡፡ በድፍረት በመታዘዝ ውጡ! እግዚያብሔር ከእናንተ ጋር ነው፡፡
“እንዲህም ሆነ፤ ሕዝቡ ዮርዳኖስን ሊሻገሩ ከየድንኳናቸው በወጡ ጊዜ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በሕዝቡ ፊት ይሄዱ ነበር። እንደ መከር ወራት ሁሉ ዮርዳኖስ እጅግ ሞልቶ ነበርና ታቦት ተሸካሚዎቹ ወደ ዮርዳኖስ ሲደርሱ፥ ታቦቱንም የተሸከሙት የካህናቱ እግሮች በውኃው ዳር ሲጠልቁ”
—መጽሐፈ ኢያሱ 3:14-15
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 16:8 — “እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ስሙን ጥሩ፤ ለአሕዛብ ሥራውን አውሩ።”
- መጽሐፈ ምሳሌ 3:5-6 — “በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። ”
- ትንቢተ ኢሳይያስ 42:16 — “ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፥ በማያውቋትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፥ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውምም።”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በታሪክ መፅሀፍት፡ ክፍል 2
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።