Historical Books Joshua

The Wall Fell

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Commander Joshua 5-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 202 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ብዙ ምድር እንደ ሸፈንን ያክል ይሰማኛል ! አሁንም ብዙ ስጋ አለ ! አስታዉስ በትክክል እስራኤላዊያን በተስፋዪቱ ምድር ነበሩ ፡፡ ዛሬ ስለ እስራኤል ጦር እናወራለን ፡፡ ዳራዉን እስኪ እንመልከት፡ ኢያሱ ኢያሪኮን ለማጥቃት እየተዘጋጀ ነበር ፤ ኢያሪኮ በዮርዳኖስ ወንዝ በምዕራብ ዳርቻ ላይ ነው ፡፡

ትምህርት

ኢያሱ (5፡ 13-14)፡ የእግዚአብሄር መልዓክ (ሰይፍ የያዘ አንድ ሰዉ ) በኢያሱ ፊት ተገለጠ ፤ የኢያሱ የመጀመሪያ ጥያቄ የነበረው ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን ? የሚል ነበር ይህ የተፈጥሮ ጥያቄ ነዉ ብዬ አስባለሁ ነገር ግን አንዱ የምጠይቀዉ አይደለም ! መልዓኩም “ አይደለሁም … እኔ የእግዚአብሄር ሰራዊት አለቃ ሆኜ መጥቻለሁ አለ “ (ቁጥር 14) ፤ ኢያሱም ወዲያዉኑ በጉልበቱ ወደ ታች ተንበረከከ ፡፡

እዉነተኛዉ ጥያቄ የእግዚአብሄር ጦር አዛዥ ማነዉ የሚል ነው ? የእግዚአብሄር ጦር አዛዥ ማን እንደ ሆነ ስዕሉን መሳል እፈልጋለሁ ፡፡ እንደ አዛዥ የኢየሱስ መምጣት ለኢያሱ ተመሳሳይ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር ለሌሎች ታይቷል ፤ ለአብርሃም ጌታ ከእርሱ ጋር እራት በላ (ዘፍ 18፡ 1-8) በተጨማሪም ለሰዎስት ዕብራዊያን ሰዎች ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር በእሳት ዉስጥ በመቆም (ዳን 3፡ 25-26) ፤ አብዛኞቹ የክርስቶስ ቅድመ መልክ መገለጥን ይጣራሉ ፡፡ በብሉይ ኪዳን ዉስጥ ክርስቶስ በተጨባጭነት ይታይ ነበር (ዘኁ 22፡ 23, 1ነገ 22፡ 19, 1ዜና 21፡ 15, ኢዮ 32፡ 5-6, መዝ 148፡ 2) ፡፡

ኢያሱ (5፡ 15)፡ ኢያሱ በተቀደስ ስፍራ ስለ ቆመ ጫማዎቹን እንዲያወልቅ ታዘዘ ፤ በዘጸ (15፡ 3) ይህ ስለ ሙሴ ያስታዉሰናል በሚነድድ ቁጥቋጦ ዉስጥ መገናኘቱን ፡፡ ኢያሱ ለመዋጋት ለመሄድ እየተዘጋጀ ስለ ነበር ኢየሱስ እንደ አዛዥ ተገለጠለት ፡፡ ሁል ጊዜ እግዚአብሄር ከጌታ ምን ያክል ለመስማት ባስፈለገን መጠን ይገለጥልናል !

ኢያሱ (6፡ 1-2)፡ በእስራኤላዊያን ምክንያት ኢያሪኮ በጣም የጠነከረ ምሽግ ነበረች ፤ ማንም አይገባም ወይም አይወጣም ነበር ፡፡ እግዚአብሄርም ቀድሞ አሸናፊነትን ለኢያሱ ሰጥቶት ነበር ፡፡ የሚያስጨንቅ ምንም ነገር የለም ! እግዚአብሄር ዊጊያችንን ይዋጋል ፡፡ ቀድሞዉኑ ያለቀ ስምምነት ነው ( ዘጸ 15፡ 3, መዝ 46፡ 7-11) ! ለእኛ ይህ እንዴት የሚተገበር ነው ? ቀድሞዉኑ ድል አሸናፊ እንደሆንን ማስታወስ አስፈላጊ እንደ ሆነ አስባለሁ ፡፡ አለም፣ ስጋ እና ሰይጣን በመስቀል ላይ ተሸንፈዋል ፡፡

ኢያሱ (6፡ 3-5)፡ ኢያሱ የጨዋታው እቅድ ተሰጠው ፡፡ የእስራኤል ጦር ለስድስት ቀን ከተማዋን ይዞራሉ ፤ በሰባተኛዉ ቀን በከተማዋ ዙሪያ ሰባት ጊዜ ዞሩ ፤ ከዚያም ካህናቱ መለከቶቻቸዉን ይነፋሉ ከዚያም ኢያሱ ለጦሩ እንዲጪኹ ትዕዛዝ ሰጠ ፡፡

ይህ ለእኔ ቀልደ ነው፡ ኢያሪኮ ሁሉም ዙሪያዊያን ከግማሽ ማይል እንደ ሚያንስ እንደ ነበር ይናገራሉ ፤ ምናልባትም በዙሪያ ለመሄድ ረጅም ርቀት አልወሰደም ፡፡ በከተማችሁ ዙሪያ ሰዎች ምንም ሳይሉ ሲዞሩ ብትመለከቱ አስባችሁታል ? በእኛ እይታ የእግዚአብሄር እቅድ ሙሉ ለሙሉ ሞኝነት ስለሆነ ነዉ የምወደው ፤ ይህን እቅድ እወደዋለሁ ምክንያቱም ማድረግ የሚችለዉ እግዚአብሄር ብቻ ስለሆነ (2ዜና 16፡ 9) ! ለእርሱ በሙሉነት የተሰጠን ነን ?

እነዚህ ተጠቅመዉባቸዉ የነበሩት መለከቶች አስፈላጊ ጊዜዎችን የሚያመለክቱ የተለመዱ የብር መለከቶች አልነበሩም ፤ አድስ ነገር በመጣ ጊዜ በኢዩቤኤል ክብረ በዓል ላይ ይነፉ የነበሩ ከቀንድ የተሰሩ መለከቶች ነበሩ (ዕብ 11፡ 30) ፡፡ ህዝቡ በእምነት መጓዝ አስፈለጋቸው በእምነት ደግሞ የኢያሪኮ ግን ወደቀ ፡፡

ኢያሱ (6፡ 6-9)፡ ኢያሱ ካህናቱን በመሰብሰብ እቅዱን ነገራቸው ፡፡ መለከት የያዙት ካህናት ከጦሩ ኋላ እና የኋለኛ ጠባቂ ከታቦቱ ኋላ ሄዱ (ኢሳ 52፡ 12) ፤ የእግዚአብሄር እቅድ ይህ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄርን ስለ ማገልገል ሰዎስት የተለያዩ መንገዶችን የጆ. ሁድሶን ቴይለር ቃላቶች እጠቅሳለሁ በማለት፡ 1) ማድረግ የምንችለዉን ምርጡን እቅድ በማድረግ ማሳካት ፤ 2) የራሳችን እቅድ በማድረግ እግዚአብሄር እንዲባርከዉ መጠየቅ ፤ ወይም ደግሞ ስለ እርሱ በመጠየቅ የሚነግረንን ማድረግ “ ፅፏል ፡፡

ለእናንተ የምሞግታችሁ በህይወታችሁ እቅድ ላይ የት ላይ እንዳላችሁ እንድትመለከቱ ነው ? አቅዳችኋል ወይስ የእግዚአብሄርን ምሪት ትፈልጋላችሁ ?

ኢያሱ (6፡ 10)፡ ኢያሱ ሰዎቹን ድምፃቸዉ እንዲሰማ እንዳይፈቅዱ አዘዛቸው ፤ በከተማዋ ግንብ ዙሪያ በፀጥታ ይዞራሉ ፤ ሞኝነት ይመስላል ! ምላሳችንን እና አካላታችንን መቆጣጠር መቻል ያስፈልገናል (ያዕ 3፡ 1-2) ፡፡ ይህ አስቸጋሪ የሆነ ይመስላል ፤ ዝም የሚባልበት ጊዜ አለው (መክ 3፡ 7, ሉቃ 23፡ 9) ፡፡ ኢየሱስ የዝምተኝነት ተግባርን ደግሞ ደግሞ እንደ ገና ምሳሌ ሆኗል ፡፡

ኢያሱ (6፡ 11-18)፡ እስራኤላዊያን የእግዚአብሄርን የጨዋታ እቅድ ለመፈፀም ተዘጋጁ ፤ በዝምታም ለስድስት ቀናት በከተማዋ ዙሪያ ተጓዙ ፤ ሰባተኛዉ ቀን ማለዳ ላይ በከተማዋ ዙሪያ ሰባት ጊዜ ዞሩ ፤ ካህናቱም መለከቶቹን ነፉ ህዝቦቹም ጪኹ ፡፡

ሁሉም ነገር የሚጠፍ ይሆናል ቀድመዉ ወደ ኢያሪኮ ሄደዉ የነበሩትን ሰላዮች በመርዷቷ ከርአብ እና ከቤተሰቦቿ በስተቀር ፡፡ በጦሩ ዉስጥ ያሉ ሰዎች ምንም ነገር አይጠብቁም ፤ በእርግጥ አንድ ሰዉ ማንኛዉንም ነገር ቢጠብቅ ጥፋት በሁሉም አካል ላይ የሚመጣ ይሆናል ፡፡

ኢያሱ (6፡ 19-21)፡ ሁሉም ብረቶች ለእግዚአብሄር የተለዩ በማድረግ እርሱ ንብረት ዉስጥ ይቀመጣል ፤ ሰዎቹ አንዴ ሲጮሁ ግንቦቹ ይፈርሳሉ ፤ ግንቦቹ ከወደቁ በኋላ ጦሩ ወደ ፊት በመሄድ ከተማዋን ይይዛል ፡፡

ኢያሱ (6፡ 22-26)፡ ኢያሱ የእስራኤል ሰላዮች ለረዓብ የገቡላትን ተስፋ ማክበር ስለ ፈለገ ረዓብ ዳነች ፤ ጦሩም ረዓብን እና ቤተሰቦቿን ከከተማዋ አወጡዓት ፤ ከሰፈሩም ዉጪ ተቀመጡ ፤ ከዚያም ጦሩ እስከ ምድር ከተማዋን አቃጠሉዓት ፡፡ ከተማዋ ከፈረሰች በኋላ ኢያሱ እርግማን አስቀመጠ ፤ ኢያሱም ማንም ኢያሪኮን እንደ ገና ለመገንባት የሚሞክር የዚያ ሰዉ ሁለት ልጆች እንደ ሚሞቱ ተነበዬ (1ነገ 16፡ 34) ፡፡

1 Dr. and Mrs. Howard Taylor, Biography of James Hudson Taylor (London: China Inland Mission, 1965), p. 271; quoted in Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Jacob (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2003), p. 43.

መዝጊያ

የኢያሱም ዝና በምድሪቱ ተሰራጨ ፤ እዚህ ልንሄድባቸዉ የምንችላቸዉ ብዙ አይነት ስዕሎች አሉ ፡፡ በጦርነት በምናልፍበት ስራ በእግዚአብሄር ላይ በምንደገፍበት ጊዜ ጦርነታችንን ለማሸነፍ ክርስቶስ መንፈሳዊ መሳሪያ ይሰጠናል ፡፡

  • 2ቆሮ (10፡ 2-6)፡ “ በዓለማዊ ልማድ እንደምንመላለስ በሚቆጥሩን በአንዳንዶች ላይ አምኜ ልደፍር አስባለሁ በዚያ እምነት ግን ከእናንተ ጋር ሆኜ እንዳልደፍር እለምናችኋለሁ ፡፡ በሰዉ ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን እንደ ሰዉ ልማድ አንዋጋም ፤ የጦር እቃችን ስጋዊ አይደለምና ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሄር ፊት ብርቱ ነው ፤ የሰዉንም አሳብ በእግዚአብሄር እዉቀት ላይ የሚነሳዉን ከፍ ያለዉን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን መታዘዛችሁም በተፈፀመች ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉ ልንቀበል ተዘጋጅተናል “ ፡፡

ኤፌ (6፡ 10-12)፡ “ በቀረዉስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ ፡፡ የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሄርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ ፡፡ መጋደላችን ከደምና ከስጋ ጋር አይደለምና ከአለቆችና ከስልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊት ጋር ነዉ እንጂ “ ፡፡

በየቀኑ የእግዚአብሄርን እቃ ጦር የምንለብስ ከሆነ በመንገዳችን የሚገጥመንን ማንኛዉንም ጦርነት ለመግጠም የተዘጋጀን እንሆናለን ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች እግዚአብሄር ለእስራኤላዊያን አድርጎት የነበረዉን በሰሙ ጊዜ ምላሻቸዉ ምን ነበር ? ለምን ያክል ጊዜ ፈርተዉ ነበር ? (ኢያ 2፡ 9-11)
  2. የእስራኤል ወንዶች ለሁለተኛ ጊዜ መገረዝ ለምን አስፈለጋቸዉ ? ይህ ለማድረግ ለምን አደገኛ ነገር ሊሆን አልቻለም (ዘፍ 34፡ 25፣ ኢያ 5፡ 8) ? እግዚአብሄር እምነታቸዉን እየፈተነ ነበር ብላችሁ ታምናላችሁ ? ለምን ?
  3. ለእስራኤላዊያን መቼ ነበር መና ያቋረጠው ? አሁን እየበሉት የነበረዉ ምንድን ነበር ?
  4. በቁጥር 14 የእግዚአብሄር ጦር አዛዥ ማን ነበር ? (አስታዉሉ ለእርሱ ዝቅ እንዲል ኢያሱን አላዘዘዉም)
  5. በኢያሱ 6 የኢያሪኮ መሸነፍ ዝርዝሩ ምንድን ነበሩ ? እነዚህን የተለዩ ምሪቶች እግዚአብሄር ይሰጥ የነበረበት ግቡ ምን ነበር ? (ዘዳ 7፡ 24፣ ኢያ 6፡ 2)
  6. በኢያ (6፡ 2) እግዚአብሄር ቀድሞ ኢያሪኮ የተሸነፈች እንደ ነበረች ተናገረ ፤ እንደ ክርስቲያን ለእኛ የጦርነት አሸናፊነት ቀድሞ እንዴት ሆኗል ? (2ዜና 20፡ 15፣ ዮሐ 12፡ 31፣ 16፡ 33፣ 1ቆሮ 15፡ 57፣ ቆላ 2፡ 13-15)
  7. በኢያ (5-6) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Joshua 6:2-4

“The Lord said to Joshua, ‘Look, I have handed Jericho, its king, and its fighting men over to you. March around the city with all the men of war, circling the city one time. Do this for six days…on the seventh day, march around the city seven times, while the priests blow the trumpets.’”
b

ጌታ ለኢያሱ ኢያሪኮን የሚቆጣጠርበት፥ ከጥፋት ድል የሚያመጣበትን እቅድ ሰጠው፡፡ ኢያሱ ጌታን በማዳመጥ፥ እንደ አዛዥ፥ መመሪያውን ለእስራኤላውያን ሰጣቸው፡፡ ምንም እንኳን መመሪያዎቹ እንግዳ ቢመስሉም እና ከተማን ለመቆጣጠር የተለመደ አይነት ትእዛዝ ባይሆኑም፥ የጌታን መመሪያ ተከትለዋል፡፡ ኢያሱ ጌታን በማመን በመታዘዝ መልስ ሰጠ፡፡

በዕየለቱ የምትጋፈጧቸውን ውጊያዎች ጌታ ያውቃል፡፡ በከተማ ዙሪያ እየዞራችሁ ባይሆንም እንኳን፥ ለአመታት በነበራችሁ ግንኙነት ወስጥ ተመሳሳይ ጦርነት እያጋጠማችሁ እንደሆነ ሊሰማችሁ ይችላል፡፡ ደጋግማችሁ ኃጢያት ለመስራት ካለው ፈተና ጋር ተመሳሳይ ትግል እያደረጋችሁ እንደሆነ ሊሰማችሁ ይችላል፡፡ ጌታ ጦርነቶችን እንደምትጋፈጡ ይናገራል፡፡ ዛሬ፥ ቁጣ እና ቅናትን ለማስወገድ ተዘጋጅታችኋል? የአደንዛዥ ዕፅን ወይም የአልኮልን ኃይል በህይወታችሁ ለማሸነፍ ዝግጁ ናችሁ? ቁጥጥሩን ትታችሁ ለጌታ ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ? ለጨዋታው እቅድ ጌታን የምንፈልግበት ጊዜ ነው፡፡ የምትጋፈጧቸውን ትግሎች እንዲያሸንፍ ጠይቁት፡፡ ሊዋጋላችሁ ቃል ገብቷል፡፡ በስሙ ድልን ቃል ገብቷል፡፡ ዛሬ፥ ቆም ብላችሁ ፊቱን ፈልጉ፥ የሚሰጣችሁን እቅድ ታመኑ እና በመታዘዝ ምላሽ ስጡ፡፡

“እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፦ ተመልከት፥ ኢያሪኮንና ንጉሥዋን ጽኑዓን ኃያላንዋንም በእጅህ ሰጥቼአለሁ። ሰልፈኞቻችሁ ሁሉ ከተማይቱን አንድ ጊዜ ይዙሩአት፤ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ። ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ።”

—መጽሐፈ ኢያሱ 6:2-4

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ኦሪት ዘጸአት 15:2 — “ጕልበቴ ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፥ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነውማለሁ፥ የአባቴ አምላክ ነው ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ፡፡ ”
  • መዝሙረ ዳዊት 46:10 — “ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ። ”
  • ወደ ዕብራውያን 11:30 — “የኢያሪኮ ቅጥር ሰባት ቀን ከዞሩበት በኋላ በእምነት ወደቀ። ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበታሪክ መፅሀፍት፡ ክፍል 3