Blatant Sin Against God
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Commander Joshua 7-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
አንድን ፊልም ለመመልከት እንዴት ትመርጣላችሁ ? የድብድብ ? የድራማ ? የኢያሱ መፅሀፍ እነዚህ ሁሉ አሉት ፡፡ ትናትና እስራኤላዊያን ኢያሪኮን ሲይዙ ኢያሱ 6 ላይ ተመልክተናል ምክንያቱም የእግዚአብሄር እቅድ ስለ ነበር ፤ በታሪኩ የተደረጉ ብዙ ድርጊቶች ነበሩ ፡፡ የዛሬዉ ፅሁፍ ድራማ ያመጣል ፤ እስራኤላዊያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲሄዱ በእግዚአብሄር እጅ እንደ ነበሩ ያውቃሉ ፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ሁል ጊዜ በዚያ እዉቀት በመታመን አልቀጠሉም ፡፡
ትምህርት
ኢያሱ (7፡ 1)፡ ቁጥር 1 ያን አለመታመን ያመለክታል ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን በኢያሪኮ ያለዉን ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሄር ከተገባዉ እና ለረዓብ እና ለቤተሰቦቿ ከሆነ ነገር በስተቀር እንዲያጠፉ አዞአቸዉ ነበር (ኢያ 6፡ 17-19) ፤ ይሁን እንጂ አንድ እስራኤላዊ እነዚህን ነገሮች አልተከተለም ይልቁንስ ከእግዚአብሄር ንብረት ጥቂት ብር፣ ወርቅ፣ ንሐስ እና ብረት መዉሰድ መረጠ ፤ ጥፋተኛዉ ሰዉ አካን ከይሁዳ ነገድ ነበር ስለዚህም ከክርስቶስ የዘር ግንድ ተጋርቷል ፡፡ የእግዚአብሄር “ ቁጣ “ በአካን ላይ ብቻ ሳይሆን በእስራኤላዊያን ሁሉ ላይ ነደደ ፤ የእግዚአብሄር ቁጣ ለምን በሁሉም ላይ ነደደ ?ዋይርስቤ “ እስራኤል በእግዚአብሄር አንድ ሰዉ እንደ ነበር እንጂ የተለያየ ነገድ፣ ጎሳ፣ ቤተሰብ እና ግለሰቦች ስብስብ እንዳልሆነ ይገልፃሉ “ ፡፡ የአካን ስም ትርጉሙ “ ችግር(አስጨናቂ) “ ማለት ሲሆን በቁጥር 25 መሰረት እስራኤልን ያስጨነቀ ሰዉ በመባል ታወቀ ፤ የኔልስን ማብራሪያ “ የንብረት መስረቅ “ (NKJV) የሚለዉን ሀረግ “ አሳልፎ እንደ መስጠት ተቃዉሞ “ መረዳት እንደ ሚቻል ይገልፃል ፡፡
ኢያሱ (7፡ 2-5)፡ ከኢያሪኮ ድል ማድረግ በኋላ ኢያሱ ሰዎችን እንደ ሰላዮች ወደ ጋይ ላከ ፡፡ “ ጋይ “ የሚለዉ ስም “ ጥፋት/ኪሳራ “ ማለት ሲሆን ትንሽ ከተማ ነበረች (12,000 ህዝብ ያለባት ኢያ (8፡ 25) ፡፡ በዕብራዉያን “ ሰላይ “ የሚለዉ ቃል በትርጉሙ የእግሮችን ትርጉም ይይዛል እኛንም እንደ ገና ወደ ፊት የሚጓዝ እግር ወደ ሚለዉ ሀሳብ ያመጣናል ፡፡ ሰላዮቹም ሰዎቹ በጣም ጥቂት እንደ ነበሩ ኢያሱም ብዙ ቁጥር ወታደሮች መያዝ እንደ ማያስፈልገዉ ከ 2,000 እስከ 3,000 ብቻ እንደ ሚበቃ ሪፖርት አደረጉለት ፤ የኢያሪኮን ከተማ ለመዉሰድ ወደ ከተማዋ የሄዱትን 40,000 ወታደሮችን አስታዉሱ (ኢያ 4፡ 13 ተመልከቱ) ፤ ይህ ይሁን እንጂ ትንሹ 3,000 ጦር ከጋይ ሸሹ ፡፡ ከእግዚአብሄር እቅድ ይልቅ የሰዉ እቅድ ማስረጃ ነው (ምሳ 16፡ 18) ፡፡ ሲሸሹ 36 እስራኤላዊ ወታደሮች ተገደሉ ሁሉም የእስራኤልም ህዝብ “ ልብ ቀለጠ እንደ ዉሃም ሆነ “ (ቁጥር 5) ፡፡ አስታዉሉ በእስራኤላዊያን አምላክ ኃይል ምክንያት የኢያሪኮያዊያን ልብ እንዴት እንደ ጠፋ (እንደ ቀለጠ) (ኢያ 2፡ 11) ፤ አሁን ደግሞ ካደረጉአቸዉ ሁለተኛ ዉጊያዎች የመጀመሪያ ሽንፈት ሲገጥማቸዉ ተመሳሳይ ነገር ተፈጠረ ፡፡
ኢያሱ (7፡ 6-9)፡ ኢያሱና ሽማግሌዎቹ ልብሳቸዉን ቀደዱ፣ በራሳቸዉ ላይ ትቢያ አደረጉ በማዘንም መሬት ላይ በግንባራቸዉ ተደፉ (ዘፍ 37፡ 34፣ መሳ 20፡ 26፣ መዝ 6፡ 6፣ ኢሳ 32፡ 12፣ ሰቆ ኤር 2፡ 10፣ ዕዝ 9፡ 5) ፡፡ ጦርነቱን ለምን እንደ ተሸነፉ ኢያሱ አልገባዉም ነበር (ቁጥር 7) ፡፡ እስራኤላዉያን በምድረበዳ እንደ ነበሩ ምን እያደረጉ እንደ ነበር ጠይቀዉ ነበር (ዘጸ 16፡ 3፣ ዘኁ 20፡ 3-5) ፤ አሁን ደግሞ ኢያሱ በተመሳሳይ ስለ እግዚአብሄር ዝና እንኳ ሲል እንዴት ይህ ይሆናል በማለት አጉረመረመ (ቁጥር 8-9) ፡፡ በፀሎትና በፆም ጊዜ እንዲያዳምጠዉ እና ፈጣን ምላሽ እንዲወስድ ወደ እግዚአብሄር በተጣራ ጊዜ ዳንኤል ይህ ተመሳሳይ አሳብ ነበረው (ዳን 9፡ 16-19) ፡፡
ኢያሱ (7፡ 10-12)፡ በምላሹም እግዚአብሄር ኢያሱን ለምን መሬት ላይ እንደ ተደፋ ጠየቀው (ቁጥር 10) ፤ እግዚአብሄር “ እስራኤል ኃጢዓት እንደ ሰራ “ እና “ ኪዳኑን እንደ ጠሳ “ ገለፀለት ፡፡ ለእርሱ ከተለየዉ ነገር ከእግዚአብሄር ሰርቀዉ ነበር (ቁጥር 11) ፤ እግዚአብሄር ወቀሳ የሚያቀርብበት እያንዳንዱ ኃጢዓት “በእነርሱ “ ላይ - በሁሉም እስራኤላዊ ላይ ነበር ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ እግዚአብሄር ለእስራኤል እና ለከነዓናዊያን ለሁለቱም የፀና ስርዓት ነበረው….አንድ ሰዉ እንኳን ቢሆን እስራኤል ብልሹ አሰራር እንዲለምድ አልፈቀደም በተለይም ትዕዛዙን በተመለከተ ጥሰቱ በጣም ግልፅ በነበር ጊዜ “ በማለት ይገልፃል ፡፡ እስራኤላዊያን በጋይ ላይ መቆም ያልቻሉበት ምክንያት ይህ እንደ ነበር እግዚአብሄር ገለፀ (ቁጥር 12) ፤ ጥፋታቸዉን ካላስወገዱ በቀር እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር አይሆንም ፡፡
ኢያሱ (7፡ 13-15)፡ እግዚአብሄር ኢያሱን እስራኤልን ከእርሱ የለያቸዉን ኃጢዓታቸዉን እንዲያስወግዱ እና በእርሱ ፊት ለመምጣት እንዲዘጋጁ ህዝቡን እንዲቀድስ ነገረው (ቁጥር 13) ፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ራሳቸዉን በየነገዳቸው፣ በየቤተሰባቸዉ ከዚያም አንዱ እግዚአብሄር በተጣራው መሰረት በየሰዉ ይቀርባሉ (ቁጥር 14) ፤ ጥፋተኛዉም በሚገባ ቅጣት የሚቃጠል ይሆናል (ቁጥር 15) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ጥፋተኛዉ ሰዉ “ ስለ እግዚአብሄር ፍቃድ ትርጉም የሌለዉ እና ለፍላፊ እንደ ነበር “ ይናገራል ፡፡ ይህንን በአዲስ ኪዳን አዉድ ብምናስቀምጠዉ ጊዜ ወደ ኃጢዓት በምንመርጥ ጊዜ ትርጉሙ በእርሱ ለመኖር መስቀሉ ለእኛ በቂ አይደለም እያልን ነዉ ማለት ነው ፡፡ አካን አታላይ በመሆን ተያዘ !
ኢያሱ (7፡ 16-19)፡ ነገዶች ወደ ፊት መጡ የይሁዳም ነገድ ተመረጠ ( ምናልባትም በካህናት ስር በኩል ተለየ ( 1ሳሙ 23፡ 6, 9፣ 30፡ 7-8) ፤ ከዚያም የይሁዳ ወገን ወደ ፊት መጣ የዛራንም ወገን ተለየ (ቁጥር 17) ከዚያም ዘንበሪም ተለየ ፤ ከዚያም የዘንበሪም ቤተሰብ ሰዉ በሰዉ ወደ ፊት መጡ ፤ አካንም ተለየ (ቁጥር 18) ፡፡ አካን አድርጎት የነበረውን ተናዘዘ (ቁጥር 19-21) ፤ ኢያሱም ሰርቆት የነበረዉን ነገር እንዲያገኙት አካን ድንኳን ዉስጥ ሰዎችን ላከ በእግዚአብሄር ፊትም አቀረባቸው ፡፡ ከዚያም አካንን እና ቤተሰቦቹን ወደ አኮር ሸለቆ በመዉሰድ እስኮሞቱ በድንጋይ በመዉገር አካላቸዉን አቃጠሉት (ቁጥር 22-26) ፡፡ አካን የተናገረው አያዉ፣ ፈለገው(ተመኘው)፣ በመስረቅ ደበቀው ፤ ሁል ጊዜኃጢዓትን ለመደበቅ እንሞክራለን ፡፡
መዝጊያ
ሁል ጊዜ እግዚአብሄር ኃጢዓታችንን ያውቃል ፤ ከእርሱ ልንደብቀዉ አንችልም፡
- መዝ (139፡ 7)፡ “ ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ ? ከፊትህስ ወዴት እሽሻለሁ ? “
ኤር (16፡ 17)፡ “ ዓይኔ በመንገዳቸው ሁሉ ላይ ነው ፤ ከፊቴም አልተሰወሩም ኃጢዓታቸዉም ከዓይኔ አልተሸሸጉም “ ፡፡
ግን አዲስ ዜና አለን ፤ በአዲስ ኪዳን ምክንያት ለኃጢዓታችን የእግዚአብሄር ይቅር ባይነት ዋስትና አለን ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Joshua (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2003), p. 49.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 284.
Nelson’s Commentary, p. 284.
Nelson’s Commentary, p. 284.
Nelson’s Commentary, p. 285.
Nelson’s Commentary, p. 285.
ጥያቄዎች
-
እስራኤል ኢያሪኮን ካሸነፈች በኋላ ለምን ነበር ጋይ ላይ የተሸነፈችው ? የበኩራት ፍሬ የእግዚአብሄር ንብረት መሆኑን ታዩታላችሁ ? (ዘዳ 26፡ 1-10)
-
የአካን ኃጢዓት ምን ነበር ? እግዚአብሄር የአካንን ሙሉ ቤተሰብ በእርሱ ኃጢዓት እየቀጣ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? መልሶ በመታደስ ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት ለማድግ ምንድን መደረግ ነበረበት ?
-
የእስራኤል ጦር ከማሸነፍ ወደ መሸነፍ ከዚያ ወደ ማሸነፍ ሄዶ ነበር ፤ ጋይን ለሁለተኛ ጊዜ ሲገጥሟቸዉ እንዴት አሸነፉዓቸው ?
-
ጋይን ካሸነፉ በኋላ እንዲያደርጉት እግዚአብሄር ስለ ነገራቸዉ ምንድን ታስታዉላላችሁ (ኢያ 8፡ 1-2) ? አካን ጠብቆ በነበር የፈለገዉ ሁሉም ኃብት ሊኖረዉ ይችል ነበር ፤ ለሆነ ነገር ትግስት ያጣችሁበት ጊዜ አለ ? የእግዚአብሄርን ጊዜ ስለመጠበቅ እንዴት ልትማሩ ትችላላችሁ ? (መዝ 27፡ 11-14፣ ኢሳ 64፡ 4)
-
በጌባል ተራራ ላይ መሰዊያ መገንባት እንዴት የዘዳግም 27 መፈፀም ይሆናል ? ጋይን ከማሸነፍ በኋላ ብዙ የመታዘዝ ድርጊቶችን እንዴት ታዩአቸዋላችሁ ?
-
በኢያሱ (7-8) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Joshua 8:1
“The LORD said to Joshua, ‘Do not be afraid or discouraged. Take the whole military force with you and go attack Ai. Look, I have handed over to you the king of Ai, his people, city, and land.’”
እስራኤላውያን ከጋይ ከተማ ጋር በተደረገው ጦርነት ከተመቱ በኋላ፥ ኢያሪኮ በጠፋበት ወቅት " የዛራ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የከርሚ ልጅ አካን" እግዚያብሔር ለእስራኤላውያን ለሰጣቸው ዕቅድ ታማኝ እንዳልሆነ ኢያሱ አየ፡፡ አካን ትእዛዙን በመጣስ ተለይቶ የነበረውን ነገር ወሰደ፡፡ ስለዚህ፥ እስራኤላውያን ከጋይ ጋር ውጊያ ሲገጥሙ፥ በጌታ ስላልተጠበቁ ፥ ሰዎች ሞቱ፡፡ እስራኤላውያን ተስፋ ቆረጡ፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም፥ እግዚያብሔር ኢያሱን አዘዘው፥ " አትፍራ ወይም አትጨነቅ"፡፡ እግዚያብሔር ጋይን ለማሸነፍ አዲስ እቅድ ነበረው፡፡
እንደ አለመታደል ሆኖ፥ ኃጢያት እና አለመታዘዝ በአለም ውስጥ አለ፡፡ ምርጫ ታደርጋላችሁ፥ እንዲሁም የዕለትተዕለት ህይወት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ምርጫዎችን በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ያደርጋሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ነገሮች በጣም ተስፋ የሚያስቆርጡ ስለሆኑ በፎጣው ውስጥ መጣል ትፈልጋላችሁ፡፡ ነገርግን ፥ የእግዚያብሔር ፀጋ በድካማችሁ ውስጥ ብርቱ ነው፡፡ የእግዚያብሔር ኃይል በእናንተ ውስጥ በስራ ላይ ነው፡፡ የእግዚያብሔር እቅድ ለመልካም እንጂ ለጥፋት አይደለም፡፡ በፊቱ ስትመጡ እና ስታምኑት፥ ሁሉም ነገር ተያይዞ ለበጎ እንደሚሰራ ቃል ገብቷል፡፡ ስለዚህም አትፍሩ ወይም ደግሞ ተስፋ አትቁረጡ፡፡ ጌታን ፈልጉት፥ ቀጣዩን እርምጃ ይመራችኋል፡፡ ወዳጆች፥ አንገታችሁን ቀና አድርጉ፥ ተስፋ አትቁረጡ! እግዚያብሔር ይወዳችኋል ስለዚህ ምንጊዜም ቢሆን አይተዋችሁም ወይም አይጥላችሁም!
“’ እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ አትፍራ፥ አትደንግጥ፤ ሰልፈኞችን ሁሉ ከአንተ ጋር ውሰድ፥ ተነሥተህም ወደ ጋይ ውጣ፤ እይ፥ የጋይን ንጉሥ ሕዝቡንም ከተማውንም ምድሩንም በእጅህ ሰጥቼሃለሁ።”
—መጸሐፈ ኢያሱ 8:1
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 37:24 — “ቢወድቅም ለድንጋፄ አይጣልም፥ እግዚአብሔር እጁን ይዞ ይደግፈዋልና። ”
- ትንቢተ ኢሳይያስ 41:10 — “እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ። ”
- ትንቢተ ኤርምያስ 29:11 — “ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕልበወንጌላት ክፍል፡ 4
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።