Historical Books Joshua

Believing in God and Believing God

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Commander Joshua 9-10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 204 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በኢያሱ መፅሀፍት በእያንዳንዷ ቀን የምንመለከታቸዉ ሁለት ምዕራፎች አሉን ፤ ያም ለእኔ ዉስጣዉ ብጥብጥ ይፈጥርብኛል ማለትም እያንዷንዷን ቀን የትኛዉን ምዕራፍ ማስተማር እንዳለብኝ መወሰን ስለ ሚያስፈልገኝ ፡፡ ታሪካዊ መፅሀፍት የሚቀጥል ቋሚ ድርጊትን የሚመስል እንዲሰማ ያደርጋል ፡፡ ምዕራፍ 9 በኢያሱ እና በእስራኤላዊያን ላይ ህብረት በፈጠሩ ስድስት የሰዎች ቡድን ይከፍታል ፤ ይሁን እንጂ ገባኦናዊያን የተጎዱ እና ድሃ ስደተኞች በመምሰል እስራኤላዊያንን ለማታለል ሞከሩ ፡፡ እስራኤል ወደዚህ መታለል ገባ ሰላምም አደረገ (ቁጥር 1-15) ፤ ከሰዎስት ቀንም በኋላ እስራኤላዊያን ገባዖናዊያንን እንግዶች ሳይሆን ጎረቤቶቻቸዉ ሆነዉ አገኙአቸውገባዖናዊያንም አታለዋቸዉ እንደ ነበር አወቁ ፤ እስራኤላዊያንም እንደ ጠላቶቻቸዉ ገባዖናዊያንን መግደል እንደ ማይችሉ ተሰማቸዉ ምክያቱም በመካከላቸዉ ባለዉ ሰላም ስምምነት ስለዚህምእንዲኖሩ ፈቀዱላቸው ፡፡ ገባዖናዊያንምለእስራኤላዊያን ማህበር እንጨት ቆራጮች እና ዉሃ ተሸካሚዎች ሆኑ (ቁጥር 16- 27) ፡፡

ትምህርት

ኢያሱ (10፡ 1-5)፡ ይህ በመፅሀፍት የመጀመሪያዉ የኢየሩሳሌም መጠቀስ ነው (ቁጥር 1) ፡፡ ኮንስታብልበ1406 እና በ1340 ከክርስቶስ ልደት በፊት በተመዘገበዉ በአረማይን ቃላት መረጃ መሰረት “ ኢየሩሳሌም በ14 ክፍለ ዘመን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ዋና (እምብርት) እንደ ነበረች ፤ እንዲሁም ደግሞ ስለ ራሷ ደህንነት ሁልጊዜ የተጨነቀች እንደ ነበረች ይገልፃል “ ፡፡ በዚህም ምክንያት የኢየሩሳሌም ንጉስ የከተማዋን ደህንነት እንዴት እንደ ሚጠብቅ ለማሳየት ይሞክር ስለ ነበር የገባኦንን ከተማ ከእስራኤላዊያን በደህንነት የተመለከተች ስለ ነበረች የተበሳጨ ሆነ በእስራኤልም ላይ መስርተዉት የነበረዉ ትብበር ሳበ(ጠራ) (ቁጥር 2) ፤ ጥሩ ሰዉ ያልነበረዉ ንጉስ አዶኒጼዴቅ ገባዖናዊያንን ለመዋጋት እንዲረዱት ለአንድነቱ ላከ (ቁጥር 3-4) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ እነዚህ አምስት ንጉሶች በብዙ የቶር ቁጥራቸዉ የገባኦንን ትልቅ ከተማ እንዴት መያዝ እንደ ሚችሉ ለመወሰን “ የፖለቲካና የጦር ሂሳብ እንዳደረጉ “ ይናገራል ፡፡ ይህ ከከነዓናዊያን(አሞራዊያን) የንጉሶች ህብረት የገባዖንን ከተማ ከበቧት (ቁጥር 5) ፡፡

በአሁኑ ጊዜ በመካከለኛዉ ምስራቅምን እየተካሄደ እንደሚቀጥል ብትጠብቁ እያንዳንዳቸዉ አገራት የሌለኛዉን አገር እርዳታ ለማግኘት የሚሞክሩትን ይህን ተመሳሳይ ሂደት ሲያስቀጥሉ ታያላችሁ በዚህም ብዙ ኃይል እና ተፅኖ አድራጊነት ይኖራቸዋል ፤ በዚያ የሚሆነው የተለመደ ነገር ነው ፡፡ እንዲሁም የክርስቶስ ተቃዋሚዉ ወደ ጨዋታ በመጣ ጊዜ እስራኤል ሙሉ ለሙሉ የተሸደች ትሆናለች ፤ ነገር ግን ያ ማለት መሲሁ ይመጣል ! በአሁኑ ጊዜ የምናየው ይህ የሚያስደንቅ ጥላ አለ ፡፡

ኢያሱ (10፡ 6-8)፡ ገባዖናዊያን ለእርዳታ ኢያሱን ጠሩት (ቁጥር 6) ፤ ኢያሱና የእስራኤላዊያን ጠቅላላ ተዋጊ ኃይል ከጌልጌላ መጡ (ቁጥር 7) ፡፡ ዋይርስቤ በዚህ ፅሁፍ ለእርዳታ ሰዎስት “ ጥሪዎች “ እንዳሉ ያስቀምጣል፡ 1) አዶኒጼዴቅ በገባዖናዊያን ላይ ለእርዳታ ሌሎቹን ንጉሶች መጣራቱን፣ 2) በዚህ ህብረት ላይ ገባዖናዊያን ለእርዳታ ኢያሱን መጥራታቸዉ እና 3) ኢያሱ ወደ እግዚአብሄር መጣራቱን ፡፡ እግዚአብሄርበእነርሱ ላይማንም ሊቆም እንደ ማይችል ቃል ገባላቸው ኢያሱም እግዚአብሄርን አመነ (ሮሜ 14፡ 23፣ 10፡ 17) ፤ በብዙ ከመንፈስ ቅዱስ ስንሰማ በእምነት መጓዝ እንችላለን ፡፡

ዋይርስቤ ያመለከተው “ የእግዚአብሄርን ተስፋ ስላመኑ አሸናፊነታቸዉን እንደ ሚያረጋግጡ ስለ ሚያዉቁ “ በህብረቱ ላይ ለአስደናቂ ማጥቃት ምሽት ላይ ደረሱ ፤ የእስራኤላዊያን ጉዞ 20 ማይል የሚርቅ ተራራማ ስፍራ ነበር ነገር ግን በእግዚአብሄር ተስፋ ባላቸዉ እምነት ምክንያት በፍጥነት ተጓዙ (ቁጥር 9) ከእስራኤል ጠቅላይ ሚንስተር አንዱ “ በታዓምራቶች አንታመንም በእነርሱ ላይ እንደገፋለን እንጂ “ ብሏል ፡፡ ኢያሱ በሚያስደንቅ ህብረቱን ያዘ እግዚአብሄርም ጣላቶቻቸዉን ወደ ዉዝግብ ዉስጥ በመጣል አሸነፉዓቸው፣ አሳደዱዓቸው በእነርሱም ላይ በረዶ አወረደባቸው ፤ ብዙዎች ከሰይፍ ይልቅ በእግዚአብሄር የመዓት ድንጋይ ሞቱ (ቁጥር 10-11) ፡፡ ከእስራኤላዊያን መካከል ለምን አንድም በእግዚአብሄር መዓት እንዳልሞቱ ሁልጊዜ አደንቃለሁ ፡፡

ኢያሱ (10፡ 12-15)፡ ኢያሱ በጦርነቱ የእስራኤል ህዝብ አምላክ በሆነዉ ፊት ፀለየ ፀሀይ ብርሃኗን እንድትሰጥ እና ጨረቃ እንድትቆም ጠየቀ (ቁጥር 12-13) ፡፡ በሌለዉ እና በ 2ሳሙ (1፡ 18) በተጠቀሰው በያሻር መፅሀፍ ፀሎቱ የተረጋገጠ ነበር (ቁጥር 13) ፤ እነዚህ ተዓምራቶች እንዴት ሆኑ ?የኔልሰን ማብራሪያ ሰዎስት ሊሆኑ የሚችሉ ሀሳቦችን ያቀርባል፡ 1) በእዉነቱ ፀሀይ ካልተንቀሳቀሰች አንዳንዶች እግዙአብሄር የምድርን ዙሪት እንዳቆመ ያመለክታሉ፣ 2) አንዳንዶች ከተለመደዉ ጊዜ ይልቅ ለረጅም ጊዜ ቆይታ “ እግዚአብሄር ፀሀይ የምትታይ ሆና እንድትቀር በምድር አካባቢ ላይ ላልተለመደ ለብርሃን ነፀብራቅ ምክንያት እንደሆነ “ ያመለክታሉ፣ እና 3) አንዳንዶች ደግሞ በትክክል የኢያሱ ፀሎት የደከሙትን ወታደሮቹን ለመጠበቅ ጥፍታ ከምትቆም ይልቅ እንድትቆም እንደ ነበር ፀሎቱ ያመለክታሉ ፤ ይህን እንዴትም ብታዩት ባስፈለገበት ትክክለኛ ክስተት የተፈጥሮን ክስተት በመቀየር እግዚአብሄር ኃይሉን በመጠቀም የሰዉ ፀሎት መለሰ ፡፡ ቁጥር 14 የሚለው “ እግዚአብሄር ለእስራኤል ይዋጋ ነበርና እግዚአብሄር የሰዉን ድምፅ ሰማ “ ፡፡ ኢያሱና ሰዎቹ ከእግዚአብሄር ጋር ወደ ጌልጌላ ተመለሱ (ቁጥር 15) ፡፡

ኢያሱ (10፡ 16-21)፡ የተሸነፉት ነገስታት በመሸስ በዋሻ ዉስጥ ተደበቁ ፤ ኢያሱም የነበረበትን ባገኙት ጊዜ በፊቱ ትልቅ ድንጋይ በማንከባለል በዉጪ ጠባቂ እንዲያስቀምጡ ለሰዎቹ ነገራቸው ፤ የቀሩት ሰዎቹ ደግሞ መዋጋታቸዉን እንዲቀጥሉ እና ጠላቶቻቸዉ እስኪጠፉ ድረስ በመከታተል እንዲያጠቁዓቸዉ ተነገራቸው ፤ ይሁን እንጂ ከሞት የተረፉት ጥቂቶቹ በአንዳንድ የተመሸጉ ከተሞች ዉስጥ ተደበቁ ፡፡ ይህ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም እንዲያደርጉ ተነግረዉ የነበረውን ስላልጨረሱት ይህም ቆይቶ በኢያሱ መፅሀፍ በሚመጡ ነገሮች ላይ ተፅዕኖ ያመጣል ፡፡

ኢያሱ (10፡ 22-28)፡ ኢያሱም ንጉሶቹን ከዋሻዉ ዉስጥ አመጣቸው ኢያሱም በንጉሶቹ አንገት ላይ እግሮቻቸዉን ያስቀመጡ አዛዦች ነበሩት ( መዝ 8፡ 6፣ 110፡ 1፣ 1ቆሮ 10፡ 15 ) ፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ስራ ስለ ነበር ኢያሱ አዛዦቹን አበረታታቸው ፡፡ ነገስታቶቹም ተገደሉ በዛፎችም ላይ ተሰቀሉ ፤ ምሽትም ላይ አካላቸዉ እንደ ገና በዋሻዉ ዉስጥ ተወረወረ ፡፡ በዚያም ቀን ኢያሱ መቄዳን ያዘ እንዲሁ ንጉሷንም ገደለ ፡፡

ስለ ድንጋዮቹ ማዉራታችንን እንጠብቃለን(እንቀጥላለን) ምክንያቱም በጉዞአቸው ሆኖ የነበረዉን መታሰቢያ ስለ ሚሰጡ ፡፡

መዝጊያ

ኢያሱ እግዚአብሄር ያምን ብቻ አልነበረም እግዚአብሄርን በማመን ባመነበት ይተገብር(ያደርግም) ነበር እንጂ ፡፡

  1. Davis Dale Ralph Davis, No Falling Word (Grand Rapids: Baker Book House, 1988), p. 95; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Joshua, p. 59.

  2. TThomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Joshua, p. 59; available online at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/joshua.pdf.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 289.

  4. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2003), pp. 63–64.

  5. Wiersbe, p. 65.

  6. Nelson’s Commentary, p. 290.

  7. Nelson’s Commentary, p. 290.

  8. Nelson’s Commentary, p. 290.

  9. Nelson’s Commentary, p. 290.

ጥያቄዎች

  1. የገባዖን ሰዎች ለምን ወደ ማታለል ተመለሱ ? እንዴት አድርገዉ እስራኤላዊያዋንን አታለሏቸው ?
  2. ገባዖናዊያንን ኢያሱ እና እስራኤላዊያን ለምን አላጠፏቸውም ? መጀመሪያ ምንድን አደረጉ (ኢያ 9፡ 14) ? እግዚአብሄርን ሳታማክሩ መጥፎ ዉጤት የነበረባችሁን ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ ?
  3. በኢያ (10፡ 13) እግዚአብሄር ፀሀይ አለችበት ላይ እንድትቆም አደረገ ፤ ለምን ? ዉጤቱ ምን ነበር ?
  4. በተያዙት ነገስታቶች ላይ ኢያሱ አዛዦቹ አንገታቸዉ ላይ እግራቸዉን ለምን እንዲያደርጉ አደረገ ? ምንድን ነገራቸው ? (ኢያ 10፡ 25፣ መዝ 110፡ 1፣ ሮሜ 16፡ 20)
  5. በኢያሱ (9-10) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Joshua 9:24b–25

“We greatly feared for our lives because of you, and that is why we did this. Now we are in your hands. Do to us whatever you think is right.”

እስራኤላውያን ኢያሪኮን እና ጋይን ካሸነፉ እና ካጠፉ በኋላ፥ የገባዖን ሰዎች ለህይወታቸው ፈሩ፡፡ ህይወታቸውን ለማዳን ሲሉ፥ ተንኮል ያለበት ዕቅድ በማምጣት ኢያሱን እና እስራኤላውያንን አታለሉ፡፡ ዕቅዱ ሰራ፥ እስራኤላውያንም ፥ የጌታን ጥበብ ሳይፈልጉ፥ የገባዖን ሰዎች በምድራቸው እንዲኖሩ በመፍቀድ ቃለ መሃላ ገቡ፡፡ በመጨረሻም፥ ኢያሱ እና እስራኤላውያን እውነቱን ተማሩ፥ እና የገባዖን ሰዎች የፈለጉትን ነፃነት ሳያገኙ ቀሩ፡፡ በዚያ ፋንታ፥ በማታለል መንገዳቸው የተነሳ፥ እንጨት ቆራጭ እና ውሃ ቀጂ ሆኖ በማገልገል ቀሪ ዘመናቸውን ኖሩ፡፡

በጊዜው፥ ውሸት እና ማታለል ቀላሉ ምርጫ ይመስላል፡፡ ልክ እንደ ገባዖን ሰዎች፥ ከፊታችሁ ያለውን ነገር መፍራት ሥጋችሁ ውሸት ከሁሉ የተሻለ እና ብቸኛ ምርጫ ነው ብሎ እስከማሰብ ሊያደርሳችሁ ይችላል፡፡ ስጋችሁ እንዲህ ሊል ይችላል፥ " ትንሽ ውሸት ነው፡፡ ይህ ቀላል መንገድ ነው ፥ በተጨማሪም ደግሞ ማንም ሰው መቼም አያውቅም፡፡" በመጨረሻም አንድ ሰው እውነቱን ያጋልጥ እና ፥ ከዚያም ውጤቱን ትጋፈጣላችሁ፡፡ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከተራመዳችሁ፥ እንደ ውሸት እና ማታለል ላሉ፥ የሥጋ ስራዎች እጅ አትሰጡም፡፡ በታማኝነት ስትኖሩ፥ በሰላም ትኖራላችሁ፡፡ ምርጫ ስታደርጉ ፥ አስታውሱ፥ ጌታ በታማኞች ደስ ይሰኛል፡፡

“ስለዚህም ከእናንተ የተነሣ ስለ ነፍሳችን እጅግ ፈራን፥ ይህንንም ነገር አድርገናል። አሁንም፥ እነሆ፥ በእጅህ ውስጥ ነን፤ ለዓይንህም መልካምና ቅን የመሰለውን ነገር አድርግብን አሉት። ”

—መጽሐፈ ኢያሱ 9:24ለ–25

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መጽሐፈ ምሳሌ 10:9 — “ያለ ነውር የሚሄድ ተማምኖ ይሄዳል፤ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይታወቃል። ”
  • መጽሐፈ ምሳሌ 12:22 — “ውሸተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አሰጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው። ”
  • ወደ ገላትያ ሰዎች 5:16 — “ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ።”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበታሪክ መፅሀፍት፡ ክፍል 5