Historical Books Joshua

Completing God's Plan

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Commander Joshua 11-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 205 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በተጨማሪም ወደ ኢያሱ መፅሀፍ ስንጓዝ አዛዡ ኢያሱ ህዝቡን ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲመራ እንመለከተዋለን ፡፡ ብዙ ጊዜ እስራኤላዊያን እቅዱን በሚከተሉ ጊዜ እግዚአብሄር ስራን እየሰራ ነበር ፤ በኢያሱ 11 ከደቡብ ወደ ሰሜን ድል ማድረግ እንጓዛለን ፡፡

ትምህርት

ኢያሱ (11፡ 1-5)፡ ኢያቢስ ከ30,000 እስከ 40,000 ሰዎች የሚኖሩባት የአሶር ንጉስ ነበር ፡፡ የእስራኤላዊያን ወደ ሰሜን ተጉዘዉ ነበር የሚለዉ ቃል በደረሰዉ ጊዜ ለሌሎች የሰሜን ነገስታቶች ቃል በመላክ እስራኤላዊያንን ለማጥቃት ተሰበሰቡ (ቁጥር 1-3) ፡፡ በአንድ ላይ መጥተዉ የነበሩት ዝርዝር ዉስጥ እዚያ ያልነበሩት ኢያቡሳዊያንም ነበሩ ፤ አስታዉሱ አምልጠዉ ከነበሩት ጥቂቶች በቀር ቀድመዉ በእስራኤላዊያን ተጠርገዉ ነበር (ኢያ 10፡ 20) ፡፡ ቁጥር 4 የጦራቸዉን መጠን ይገልፃል፡ “ እነዚህም ከሰራዊቶቻቸው ሁሉ ከእጅግም ብዙ ፈረሶች እና ሰረገሎች ጋር ወጡ “ ፤ ታሪክ ፀሀፊዉ ጆሴፍስ “ የከነዓናዊያን ነገድ የተጣመረዉ ጦር በጠቅላላ 300,000 እግረኛ ጦር፣ 10,000 ፈረሰኞች እና 20,000 ሰረገሎች እንደ ነበሩ ገምቷል “ ፡፡ የኔልስን ማብራሪያ “ በኢያሪኮ እና በጋይ ጦርነት ብቻ እስራኤላዊያን ድርጊት እንዳነሳሱ ያመለክታል “ ፡፡ በጅማሮዉ(በጅማሬዉ) እግዚአብሄር የእስራኤላዊያንን ኃይል ብዛት በማሳነስ ኃይሉን አሳዬ ፤ የሰሜኑ ህብረት(ጥምረት) በማሮን ዉሃ ላይ በሚያጠቁበት ፊት ሰፈሩ (ቁጥር 5) ፡፡

ኢያሱ (11፡ 6-11)፡ እግዚአብሄር ኢያሱን በሰሜኑ ጥምረት የሚያስፈራዉ ምንም እንዳልነበር አሳሰበው ፤ ኢያሱ የፈረሶቹን ቋንጃ እንደ ሚቆርጥ እና ሰረገሎቻቸዉን እንደ ሚያቃጥል ተነገረው (ቁጥር 6) ፡፡ እስራኤላዊያንም በድንገት የተጣመረዉ ጦር ላይ ደረሱ እግዚአብሄርም ዉጊያዉን ሰጣቸው ፤ እስራኤላዊያንም በህይወት የሚያመልጡትን ጦሮች በሁሉም አቅጣጫ ተከተሉዓቸው በህይወት ያመለጠ አንድም የሌ (ቁጥር 7-9) ፡፡ ደግሞም ኢያሱ የአሶርን ከተማ ያዘ፣ ንጉሷንም ገደለ፣ ሁሉንም ህዝብ በመግደል ከተማዋን አቃጠለ (ቁጥር 10-11)፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ15 ክፍለ ዘምን የአሶር መጥፋት የስነ ቅርስ ማስረጃዎች አሉ ፡፡

ኢያሱ (11፡ 12-15)፡ በአሁኑ ጊዜ በእስራኤል ከተሞቹ በቀድሞዎቹ ከተሞች ላይ እንደ ተገነቡ ብዙ “ ነገሮች “ ወይም ኮረብቶች አሉ ፤ እስራኤላዊያን የአሶርን ከተማ ብቻ እንዳጠፉ አስታዉሉ ስለዚህም እነዚህ ሌሎች ከተሞች ከእነዚህ ከብዙ ነገሮች ስር ምናልባትም ይሆናሉ (ቁጥር 12-13) ፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ከተሞች እስራኤላዊያን ለራሳቸው እሴቶቻቸዉን እና ከብቶቻቸዉን ወስደዋል ፡፡ በህይወት ማንንም አላስቀሩም እግዚአብሄር ሙሴን እንዳዘዘው ኢያሱንም አዘዘዉ (ቁጥር 14-15) ፡፡

የሁሉም ቡድን ሰዎች ድምሰሳው የተመቻቸን አያደርገንም በተለይምስለ ሰብዓዊ መብት ለሚያስቡ ሰዎች ፤ አስፈላጊ ነበር ? ወይስ በሂደቱ ኢያሱ ደም የጠማዉ ሆኖ ነበር ?የኔልሰን ማብራሪያ እግዚአብሄር ሙሴን የከነዓንን ጥፋት ነግሮታል ምክንያቱም “ ከነዓናዊያን ስለ እርጉመነታቸዉ በእግዚአብሄር እንደ ተፈረደባቸው “ ይገልፃል (ዘዳ 20፡ 16-20) ፡፡ እግዚአብሄር ህዝቡን መለየት በፈለገ ጊዜ ኃይለኛ አምላክ ነው ፤ ለልጁ ያደረገዉን ተመልከቱ በዚህም በእርሱ መሆን እንችላለን ፡፡

ኢያሱ (11፡ 16-23)፡ እነዚህ ቁጥሮች የኢያሱን ድል ማድረግ ማጠቃለያን ይሰጣሉ - ተራራማዉ አገርን፣ ጎሶምንም ምድር፣ የእስራኤልን ተራራማ አገርን እና ቁላዉን (ቁጥር 16-17) ፤ ኢያሱ ሁሉንም ወስዷል በጣም በርሃ የሆነዉን የእስራኤል ተራራማዉን አገር ሁሉ ፡፡ ለረጅም ጊዜ ኢያሱ የድርጊት ሰዉ ነበር (ቁጥር ቁጥር 18) ፤ ዋይርስቤ ይህ ረጅም ጊዜ በቃዴስ በርኔ(ዘዳ 2፡ 14) ካሌብ 40 አመቱ ነበር ከዚያም ከ38 አመታት በኋላ ዮርዳኖስ ወንዝን ተሻገሩ (ኢያ 14፡ 7) በዚህ እዉነት መሰረት ላይ ለሰባት አመት እንደ ቆየ ይገልፃል ፡፡ ካሌብ 85 አመቱ ነበር (ኢያ 14፡ 10) የእስራኤላዊያን ተስፋይቱን ምድር ድልማድረግ ተጠናቀቀ ( ስለዚህ 40 + 38 = 78 ድል ማድረግ መጀመራቸዉ ላይ የካሌብ እድሜ ነበር እና 85 መጨረሻዉ ነበር ስለዚህ 85-78 = 7 አመት) ፡፡

ከገባዖን ዉጪ ማንም ከተማ ከእስራኤላዊያን ጋር ሰላም አለደረገም እግዚአብሄር እንዳዘዘዉ ሌሎቹ ሁሉም ተደምስሰዋል (ቁጥር 19-21) ፡፡ በቁጥር 22 ከዔናቅዋያን (የእስራኤል ሰላዮች የፈሩዓቸዉ ግዙፎች ከነበሩት) በጋዛ፣ በጌትም እና በአዛጦንም ከቀሩት በቀር አንድም አልቀረም ነበር ( ቁጥር 22) ፡፡

ጋዛ ለፍልስጤማዉያን ቤት ነው ፡፡ በኢያሱ ትዕዛዝ የጡሩ መጠን እና ጠላቶቹ ጉዳይ አልነበረም ፤ ሁሉም ነገር የአምላኩ መጠን ጉዳይ ነበር ፡፡ ኢያሱ ሁሉንም ምድር ወሰደ ምክንያቱም እግዚአብሄር እንደ ሚያደርግ ስለ ተናገረው (ቁጥር 23) ፤ በአምላኩ ስላመነ ፤ “ ምድሪቱም ከሰልፍ አረፈች “ (ቁጥር 23) ፡፡

1 Richard S. Hess, Joshua: An Introduction and Commentary (Tyndale Old Testament Commentaries series) (Leicester, England, and Downers Grove, Ill.: Inter-Varsity Press, 1996), p. 208; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Joshua, p. 66.

2 Flavius Josephus, The Works of Flavius Josephus, trans. William Whiston (London: T. Nelson and Sons, 1866; reprinted ed. Peabody, Mass.: Hendrickson Publishers, 1988), 5:1:18; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Joshua, p. 67.

5 Douglas Petrovich, “The Dating of Hazor’s Destruction in Joshua 11 by Way of Biblical, Archaeological, and Epigraphical Evidence,” Journal of the Evangelical Theological Society

51:3 (September 2008):489–512; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Joshua, p. 67.

መዝጊያ

የትንቢቱ መፈፀም በኢያሱ መሪነት በኩል እየሆነ ነበር ፡፡ ያዕቆብ ሞንቶጎመሪ ቦይሴ የኢያሱን የመሪነት ጥራት የሚከተሉትን ለይቷል፡

  1. ኢያሱ ትልቅ ከሆነው አላማዉ እንዲያግዱት ለትንሽ ጥቅሞች አልፈቀደም ፤ አምስት ነገስታት አገኘ ጦራቸዉንም በማሸነፍ ንጉሶቹን ገደለ ፡፡
  2. ኢያሱ ስለ ሚታይ ማበረታታት ሌሎች እንዲኖራቸዉ እንደ ሚያስፈልግ ተረድቷል ፤ የነበሩትን አዛዦቹን ለማበረታታት በንጉሶቹ አንገት ላይ እግራቸዉን አስቀመጡ ፡፡
  3. ኢያሱ አቋራጮችን አልወሰደም ነገር ግን ሰባት አመት በወሰደ ለዉጥ ደረጃ በደረጃ ዘመቻዉን ተከታተለ ፡፡
  4. ኢያሱ የጅማሬዉ ስህተት እንዳይረጋጋ ወይም እንሺነፍ አልፈቀደም አንደ ጋይ አይነት ሽንፈቶች እና በሰፈር እንዳለዉ ኃጢዓት (ፊል 3፡ 13-14) ፡፡
  5. ኢያሱ የእግዚአብሄርን የሚያቅተዉ አለመኖሩን(ሁሉን ቻይነት) አምኗል - ጠንካራ እና ጀግና ነበር ፡፡
  6. ኢያሱ ሙሉ ለሙሉ ታዝዟል (ኢያ 11፡ 15) ፡፡

በመሪነት ለእግዚአብሄር ለሁሉም እነዚህ ጡሩ ጥራት ናቸው ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 292.

  2. Nelson’s Commentary, p. 292.

  3. Nelson’s Commentary, p. 292.

  4. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2003), p. 67.

  5. James Montgomery Boice, Expositional Commentary: Joshua (Grand Rapids: Baker Books, 2006), n.p.

ጥያቄዎች

  1. ኢያሱ 11 መጀመሪያ ላይ ብዙ ነገስታቶች እና ጦራቸው ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ተሰብስበዉ ነበር ፤ ከእናንተ ጋር ለመዋጋት በዙሪያችሁ ተሰብስበው ከበዋችሁ እንደ ነበር ተሰምቷችሁ ያውቃል ?
  2. ኢያ (11፡ 4-5) እና ራዕ (19፡ 19) አንብቡ ፤ ምንድን ተመሳሳይነቶችን ታያላችሁ ?
  3. ኢያ (11፡ 9፣ 12 እና 15) ከህግ መፅሀፍት(ከኦሪት) (ዘጸ 39፡ 42፣ 40፡ 16፣ 19፣ 21፣ 23) ምንድን ያስታውሳችኋል ? በእነዚህ ከተሞች ዉስጥ ሁሉንም እንዲገድሉ እስራኤላዊያንን ያዘዘበት የእግዚአብሄር ምክንያት ምን ነበር ? (ዘዳ 20፡ 16-18. ኢያ 11፡ 11)
  4. እግዚአብሄር የከነዓናዊያንን ልብ አደነደነ (ኢያ 11፡ 20) ፤ ሌላ የት ላይ እግዚአብሄር ልብን ስለ ማደንደን አንብበናል ? (ዘጸ 9፡ 12፣ 10፡ 1፣ ዘዳ 2፡ 30፣ ዮሐ 12፡ 40)
  5. በምዕራፍ 12 እግዚአብሄር የሴዎን እና የዐግ፣ በዮርዳኖስ በምስራቅ በኩል የአሞራዊያንን ንጉሶች እና የተዘረዘሩት የ31 ነገስታቶች መሸነፍ እና ከተሞቻቸዉ እስራኤላዊያን ድል እንደወሰዱዓቸዉ እንደ ገና ተናገረ ፤ ይህን ለምን እንዳደረገ ምን ታስባላችሁ ? (ዘዳ 8፡ 2፣ መዝ 77፡ 11፣ 105፡ 5)
  6. በኢያሱ (11-12) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Joshua 11:6, 8a

“The LORD said to Joshua, ‘Do not be afraid of them, for at this time tomorrow I will cause all of them to be killed before Israel. You are to hamstring their horses and burn up their chariots . . . The LORD handed them over to Israel, and they struck them down.”

የእስራኤላውያን የጦርነት ድሎች ዜና በተስፋይቱ ምድር ውስጥ ባሉ መላው የሰሜን ከተሞች ተስፋፋ፡፡ በዚህም ምክንያት፥ የአሦር ንጉስ ፥ኢያቢስ፥ እስራኤልን በአንድነት ለመውጋት የጎረቤቶቹን ነገስታት እና ሠራዊቶቻቸውን ሁሉ ሰበሰበ፡፡ የሠራዊቶቹ ጥምር በባሕር ላይ እንዳለ የአሸዋ ቅንጣት ያህል ብዙ ነበር፡፡ ኢያሱ ሊመጣ ስላለው ጥቃት ሰማ፥ ጌታም እንዳይፈራ አስታወሰው፡፡ ከዚያም ለኢያሱ የድል ስልትን ሰጠው፡፡ የእግዚያብሔር የውጊያ ስልት እግዚያብሔርን እና ሰውን ያካትታል፡፡ እግዚያብሔር ሠራዊቱን ለእስራኤል አሳልፎ ይሰጣል፥ ቢሆንም ግን ለእስራኤላውያን የውጊያ ዕቅድ ሰጣቸው፡፡

ጌታ ጦርነት እንደሚያጋጥማችሁ ተናግሯል፡፡ ነገ ምን እንደሚያጋጥማችሁ በማሰብ፥ ማታ አልጋ ላይ ተኝታችሁ ይሆናል፡፡ ጌታ ያያችኋል ስለዚህ የምትጋፈጡትን ውጊያ ያውቃል፡፡ ስለነገ አትጨነቁ ይላችኋል— አትፍሩ፡፡ ለእናንተ አላማ ስላለው ከፊት ይቀድማችኋል፡፡ በዕቅዱ ታመኑ፡፡ ዕቅዱ ያልተለመደ ቢመስል እንኳን፥ ተከተሉት፡፡ እግዚያብሔር ኢያሱን ፈረሶቹን እንዲገታ እና ሰረገሎቸሁንም እንዲያቃጥል ነገረው ፥ እናም እስራኤላውያን ድልን አገኙ፡፡ የጌታን መንገድ ተከተሉ እና፥ በጦርነት ውስጥ ድልን ታገኛላችሁ፡፡

“እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን እንደ ሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፤ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቈርጣለህ፥ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ አለው። . . . እግዚአብሔርም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ መቱአቸውም”

—መጽሐፈ ኢያሱ 11:6, 8ሀ

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ኦሪት ዘዳግም 20:4 — “ከእናንተ ጋር የሚሄድ፥ ያድናችሁም ዘንድ ጠላቶቻችሁን ስለ እናንተ የሚወጋ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነውና። ”
  • መጽሐፈ ምሳሌ 21:31 — “ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤ ድል ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። ”
  • 1ኛ ቆሮንቶስ 15:57–58 — “ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ። ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበታሪክ መፅሀፍት፡ ክፍል 6