Caleb's Unaltering Confidence
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Commander Joshua 13-14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በኢያሱ መፅሀፍት ዉስጥ ስንጓዝ ብዙ ግድያዎችን እና መታዘዞችን አይተናል ፡፡ እስራኤላዊያን “ እንዲበረታ እና እንዲጠነክር “ ለኢያሱ በእግዚአብሄር ትዕዛዝ እየኖሩ ነበር ፤ ሙሴ ኢያሱን ምድሪቱን እንዲወስድ አዘጋጀው ህዝቡም የኢያሱን መሪነት አገዙት ፤ በእነዚህ ሁሉ ነገር በመካከል ላይ እግዚአብሄር ጣልቃ መግባቱን ቀጥሏል ስለሆነም እስራኤላዊያን አሸናፊነት ይኖራቸዋል ፡፡ ኢያሱ 13 ኢያሱ እያረጀ እንደ ነበር እና አሁን ያልተወረሰ ምድር እንደ ነበር ይናገራል (ቁጥር 1-7) ፤ በምዕራፉ ሌሎች ክፍሎችድል ተደርገዉ የነበሩት ምድሮች ለሮቤል ነገድ፣ ለጋድ ነገድ እና ለምናሴ ግማሽ ነገድ እንደ እርስታቸዉ ተሰጣቸው ፡፡ በምዕራፍ 14 ለሌሎቹ የእስራኤል ነገዶች ምድሪቱን መስጠት ቀጠለ ፡፡ ኢያሱ በኢየሱስ በኩል ስለ ሚመጣዉ የድነት ስጦታ ምስል ነው ፡፡
ትምህርት
ኢያሱ (14፡ 1-5)፡ ታላቁ ካህን አልዓዛር፣ ኢያሱ እና በእያንዳንዱ ነገድ ቤተሰብ መሪዎች እግዚአብሄር ሙሴን እንዲያደርገዉ ነገሮት እንደ ነበረው ምድሪቱን በእጣ አስረከቡ (ቁጥር 1-2) ፤ ሙሴ ተስፋይቱ ምድር ከመግባታቸዉ በፊት ለሁለቱ ነገዶች እናለግማሹ ርስትን ሰጥቶ ስለነበር ይህ ቡድን ለዘጠኙ እና ለግማሹ ርስትን ሰጠ (ቁጥር 3) ፡፡ ሌዋዊያን (የክህነት ነገዶች) የተቀበሉት ምድር የለም ነገር ግን ለከብቶቻቸዉ እና ለእንስሳቶቻቸዉ ከተሞችን እና ማሰማሪያ ምድርን ተሰጥተዋል ፡፡ ዉርሱን በኢያሱ እና በእስራኤላዊያን በኩል መታዘዝ ዉስጥ ተቀበሉ ፡፡
ኢያሱ (14፡ 6-9)፡ በቁጥር 6 ታሪኩ ትክክለኛ መመለስን ለማድረግ ይመስላል ፤ የይሁዳ ዘር ኢያሱን በመቅረብ ቃሌብ እርሱን ተናገረው ፤ ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዉ የነበሩት ከመጀመሪያዎቹ ሰላዮች ኢያሱና ካሌብ ብቻ እንደ ነበሩ አስታወሰው ፡፡ ካሌብ የእስራኤል ካልሆነ ቡድን ከኤሳው ዘር በቀኔዛ በኩል የቄኔዛዊዉ የዮፎን ልጅ እንደ ሆነ የተገለፀ ነው (ዘፍ 15፡ 19፣ 36፡ 11፣ 15) ፤ አንዳንድ ምሁራን መጀመሪያ ደረጃ ላይ ራሳቸዉን ከይሁዳ የሚያዛምዱ ቡድኖች እንደ ነበሩ ያመለክታሉ (ዘኁ 13፡ 6) ትዉልዱ ካሌብን እስራኤላዊያን ካልሆነ ቤተሰብ አስወገዱት ፡፡ ካሌብ ኢያሱን ስለለዉት የነበሩትን ተስፋይቱን ምድር ሁሉንም እንዳለፉበት አስታወሰዉ (ቁጥር 6-9)፡፡
ካሌብ እንደ ሌሎቹ ሰላዮች ሳይሆን “ ትክክለኛ ሪፖርት “ ተመልሶ ይዞ መምጣቱን አመለከተ (ቁጥር 7) ፤ እንዲሁም ሌሎቹ ሰላዮች ለህዝቡ መፍራት ምክንያት በሚሆን ሪፖርት ተመልሰዉ መጥተዉ እንደ ነበር ነገር ግን እርሱ ለአምላኩ ታማኝ እንደ ነበር ገለፀ (ቁጥር 8)(ዘኁ 13፡ 30) ፡፡ በትክክለኛ ሪፖርቱ ምክንያት እርሱና ወገኖቹ የተለየ ርስት ተስፋ እንደ ተገባላቸዉ ኢያሱን እስታወሰው (ቁጥር 9) ፤ ዘኁ (14፡ 24) የሚለው “ ባሪያዬ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ ከእርሱ ጋር ስለ ሆነ ፈጽሞም ስለ ተከተለኝ እርሱ ወደ ገባባት ምድር አገባዋለሁ ፤ ዘሩም ይወርሳታል “ ፡፡
ኢያሱ (14፡ 10-12)፡ እግዚአብሄር ይህን ቃል ለሙሴ በሚናገር ጊዜ ካሌብ 40 አመቱ ነበር አሁን ደግሞ ከ45 አመት በኋላ በዚህ ተስፋ ላይ አሁንም የተፈፀመ እንዲሆን ከእግዚአብሄር እየጠበቀ ነበር (ቁጥር 10) ፤ 85 ላይ ካሌብ መፈፀሙን ለመቀበል ዝግጁ ነበር ፡፡ ለዉጊያ እና ለስራ ጥንክሬዉ ልክ 40 አመት እንደ ነበረው ጠንካራ ነበር (ቁጥር 11) ፤ ስለሆነም ካሌብ ከ45 አመት በፊት እግዚአብሄር ተስፋ የገባለትን ተራራማዉን አገር ጠየቀ (ቁጥር 12)፡፡
ካሌብ የጠየቀው ምድር የረጃጅሞቹ የኤናቅን ምድር ነበር ፤ ካሌብ በእግዚአብሄር እርዳታ መሄድ ፈለገ ፡፡ ኤፍ.ቢ.ሜየር “ በዘመቻዉ እና ዘመቻዉን በመቋቋም ፣ ለመቁጥር በሚያስቸግረዉ ሞት፣ በህዝቡ ሀዘን እና አመፅ መካከል ላይ ካሌብ ሌላ መሪ እንደ ሌለ በማወቅ እና ሌላ ድምፅ እንደ ሌለ በማስተዋል እግዚአብሄርን ለማመስገን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ብቻ ለማድረግ በመፅናት ባለመወላወል ቆመ ….የማሪያምን መጥፎ ቅናት ተካፋይ አይሆንም ፤ በሞዓብ ሴቶች ማታለል የሚማረክ አይሆንም ፡፡ በሚቀየር ባህር ዉስጥ እንዳለ አለት፣ በደመና እና በጎርፍ እና በፀሀይ መቀየር እንዳለ ጫፍን እንደ ሸፈነ በረዶ ሁልጊዜ ጠንካራ እና እዉነተኛ እና ንፁህ እንዲሁም ባለበት የቆመ ሆነ ፡፡ በአንድ ሰዉ በተፈጥሮ ጥንካሬው ደካማ ሰዎች ሊደበቁ ይችላሉ እንዲሁም በእስራኤል መጥፋት ባዶ ቦታ ለመሙላት ለሚያድጉት አድስ እና ወጣት ትዉልድየጥንካሬ ማማ ይሆናል ፡፡ በዕብራዊያን ሰፈር አማካሪ በእርሱ በትልቅ እድሜዉ ፍሬ እንደ ሚሸከም የመዝሙራት ቃላት የማይጠበቅ ነበር እንዲሁም በመጨረሻ ስብ እና የበለፀገ እንደ ነበር ተናግሯል “ ፡፡
ይህ አስደናቂ መልክ ነው ፤ ህይወቱ መካከል ላይ ካሌብ ፀና ፤ ህይወት መካከል ላይ ካሌብ እና ኢያሱ እንዲያደርጉት በጠጠሩት ፍራት አልተሰማቸውም ፡፡ ካሌብ ለእርሱ የእግዚአብሄርን ተስፋ ለመፈፀም ቀጣዩን እርምጃ ለመራመድ ዝግጁ ነበር ፡፡ ጃኮብሰን ካሌብ ለመኖሪያነት ቦታ ለምን “ መልካም “ ወይም ቀላል እንዳልተመለከተ ይጠይቃል ፤ ገለፃዉም “ ለካሌብ መልካም ቦታ ጥቂት አትክልቶችን ወይም አበቦችን በማሳደግ ቀሪ ህይወቱን ሊያሳልፍበት የሚችልበትን ቦታ ቀድሞ የተያዘዉን የምድሪቱን ክፍል መጠየቅ ቀላል (ተፈጥሮ) ነዉ የሚሆነው ፤ ይልቁንስ 85 አመቱ ላይ በአስሩ ሰላዮች ልቦች ዉስጥ አስፈሪነትን ጥለዉ የነበሩትን የምድሪቱን ክፍል እንደ ጠየቀ ይናገራል “ ፡፡ እየጠበቀ ስለ ሚቀበላቸዉ በረከቶች ካሌብ ስለ ነበሩት እነዚህ ክስተቶች አደንቀዋለሁ - በእግዚአብሄር ቃልም ይዟቸዋል !
ኢያሱ (14፡ 13-15)፡ የኢያሱ ምላሽ ለካሌብ ጥያቄዎች በቁጥር 13 ይጀምራሉ ፤ ኢያሱ ካሌብን በመባረክ ኬብሮንን እንደ ርስት ሰጠው ፡፡ ኬብሮን በአሁኑ ጊዜ ጥቂት አይሁዶች የሚገኙባት አንዷ አስፈሪ ቦታ ነች (ዘኁ 13፡ 21-22) ፡፡ ያዕቆብ እና ካሌብ እንደ ሰላይ ቀድመዉ ወደዚች ምድር ሄደዉባት ነበር ፤ አብርሃም ይዟቸዉ ከነበሩት ምድር ብቸኛዋ ነበረች እንዲሁም እርሱ እና ሚስቱ ሳራ በዚያች ተቀብረዋል በተጨማሪም ይስሐቅ፣ ርብቃ እና ያዕቆብ ተቀብረዉቧታል ፤ በመጨረሻም ዮሤፍ አካሉ በዚህ እንዲቀበር ጠይቋል ፤ በዚያን ጊዜ ለአይሁዶች አስፈሪ ቦታ የሆነበት የቀረበዉ ነገር እና “ለእግዚአብሄር የታመነ በመሆኑ ምክንያት “ (ቁጥር 14) ለካሌብ የተሰጠ የሆነበት ምክንያት ይህ ነው ፡፡
ያዕቆብ ሞንትጎመሪይ ቦይኬ ኒፍሊሞች ግዙፎች እንደ ነበሩ (ዘፍ 6፡ 4) እና ኤናቅአዊያን ደግሞ የኒፍሊሞች የዘር ሀረግ እንደ ነበሩ ይገልፃል ፡፡ ሰዎስት ኤናቅአዊያን (የኤናቅ) የዘር ሀረጎች በኬብሮንን ይኖራሉ፡ አኪመን፣ ሴሲ እና ተላሚ (ዘኁ 13፡ 22) ስለዚህ በምድሪቱ እስካሁን ትልልቆች ነበሩ ፤ ምንም እንኳን እስራኤላዊያን ቢይዟትም አሁንም የሚሰሩት ስራ ነበር ፤ እንዲሁም የሰላምም ተስፋ ነበር - “ ከጦርነት አረፈች “ (ቁጥር 15) ፡፡
1 Donald K Campbell, “Joshua.” In The Bible Knowledge Commentary: Old Testament, p. 357, ed. John F. Walvoord and Roy B. Zuck (Wheaton: Scripture Press Publications, Victor Books), 1985; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Joshua, p. 75.
አላን ሪድፓዝ ይህን የምድሪቱን መተላለፍ፡ “ አብዛኛዎች ከራሳቸዉ ጥንካሬ አንፃር ረጃጅሞችን ገመቱ ካሌብ እና ኢያሱ ደግሞ ከእግዚአብሄር አንፃር ረጃጅሞቹን ተመለከቱ ፤ አብዛኛዎች ተንቀጠቀጡ፣ ሁለቱ ደግሞ ድል አደረጉ ፤ አብዛኞቹ ታላቅ ረጃጅሞች ነበራቸዉ ነገር ግን ትንሽ እግዚአብሄር ፤ ካሌብ ታላቅ እግዚአብሄር ነበረው ነገር ግን ትንሽ ረጃጅሞች “ በማለት ያጠቃልላል ፡፡ ኢያሱ ካደረገዉ በላይ ካሌብ አምኗል ፤ በካሌብ ሙሉ እምነት ምክንያት ካሌብ የተምታታ አልነበረም ፡፡ ለመፈፀሙ ሚና እንደ ነበረው ስለተረዳ አይሁን በእግዚአብሄር ላይ እንጂ በረጃጅሞቹ ላይ አላደረገም ፡፡
መዝጊያ
ዮሐንስ ካዉድ በካሌብ መሪነት አራት ጥራቶችን ለይቷል፡
- “ የማይወላዉል እምነት “ - ለ45 አመታት ካሌብ እግዚአብሄር ሰጥቶት ስለ ነበረዉ ተስፋ ፀና ፡፡
- “ ያልተገደበ ትጋት “ - ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሄር የተሰጠ ነበር ፡፡
- “ ያልተቀየረ ድፍረት(ብርታት) “ - በእግዚአብሄር ላይ ባለዉ መደገፍ በኩል ድፍረት አግኝቷል ፡፡
- “ ያልተቀየረ (ያልተሸረሸረ) በራስ መተማመን “ - በእግዚአብሄር ያለዉን መተማመን በፍፁም አላጣም ፡፡
ከሌብ ተስፋዉን ተቀብሎ ባይሆን ምንድን ይሆን ነበር ? የሚያም ነው፣ በመፅሀፍት ብዙ ሰዎች ተስፋቸዉን በፍፁም አላዩም (ዕብ 11፡ 32-40) ነገር ግን እምነታቸዉ በፍፁም አልተሸረሸረም ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 280.
Frederick B. Meyer, Joshua and the Land of Promise (New York: Fleming H. Revell, n.d.; reprint ed., Fort Washington, PA, Christian Literature Crusade, 1977), p. 2; available online at http://www.baptistbiblebelievers.com/LinkClick.aspx?fileticket=l7VECJdnV9U%3d&tabid=306&mid=1008.
Henry Jacobson, Claiming God’s Promises, New ed. Bible Knowledge series (Wheaton: Scripture Press, 1963, p. 100; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Joshua, p. 76.
James Montgomery Boice, Joshua: Expositional Commentary (Grand Rapids, MI: Baker Books, Pbk. Ed., 2006), n.p.
Alan Redpath, Victorious Christian Living (Grand Rapids, MI: Baker Books, 2003), pp. 197–198.
Boice, n.p.
John Cawood, “The Godly Features of Caleb,” Confident Living, 44:10 (November 1986): pp. 53–55; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Joshua, p. 76.
ጥያቄዎች
-
በኢያ (13፡ 6) መሰረት በእስራኤላዊያን ተይዞ ያልነበረዉን ምድር የምድሪቱን ነዋሪዎች ማስወጣት የነበረበት ማን ነበር ? የእናንተ የሆነዉን “ጋዛታችሁን “ የያዙባችሁን ጠላቶቻችሁን እንደ ሚያስወጣላችሁ እግዚአብሄርን ታምኑታላችሁ ?
-
በኢያ (13፡ 22) ያለዉ ምልክት ከዮርዳኖስ በምስራቅ በኩል እስራኤላዊያን የቢዖርን ልጅ በለዓምን መግደላቸዉን ያስታውሰናል ፤ ይህ ለምን እንደ ተጠቀሰ ምን ታስባላችሁ ? (ዘኁ 31፡ 16፣ 2ጴጥ 2፡ 15፣ ራዕ 2፡ 14)
-
ስለ ኤናቅ ምን ታውቃላችሁ ? (ዘፍ 6፡ 4፣ ዘኁ 13፡ 33፣ ዘዳ 9፡ 2)
-
ካሌብ በሙሴ ተስፋ እንደ ተገባለት ስለርስቱን ኢያሱን ጠየቀ ለእርሱም ኬብሮን ተሰጠችው ፤ ቀድሞ ሆኖ የነበር ክስተት ምን ነበር ? (ዘፍ 23፡ 2፣ 35፡ 27)
-
የምዕራፍ 14 የመጨረሻዉ ቁጥር የኬብሮን የቀድሞ ስም እንዴት ቂርያትአርባቅ እንደ ነበር ይገልፃል ፤ እንደዛ ትጠራ የነበረዉ ለምን ነበር ? አርባቅ ማን ነበር ? (ኢያ 15፡ 13)
-
በኢያሱ (13-14) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።