Asking for Inheritance
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Commander Joshua 15-16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ ስለ ምድሪቱ አከፋፈል እናወራለን ፤ ትናትና ስለ ተስፋ ምድሩ ኬብሮን የካሌብን ጥያቄን ተመልክተናል ፡፡ ኢያሱ 13-19 ለእያንዳንዳቸዉ ለእስራኤል ነገዶች ስለ ምድሪቱ ክፍፍል ላይ ያተኩራል ፡፡ በምዕራፍ 15 የይሁዳ ነገድ ድርሻ በጣም ዉድ ነበር ፤ ትልቁ ልጅ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ጋር በመተኛት በመቆሸሹ የብኩርናዉን መብት አጥቷል ፤ ተከታዮቹ ሁለት ወንድ ልጆች ስምዖን እና ሌዊም ሴኬማዊያንን በገደሉ ጊዜ ቆሽሸዋል ፤ ዘፍጥረት 34 ድርጊቱን “ ምድሪቱ ላይ እንዳለ ክርፋት “ መዝግቦታል ፡፡ አራተኛዉ ልጅ ይሁዳ ቀጣዩ መስመር በመሆን እንዲመራ መብት ተሰጠው (ዘፍ 49፡ 8-12) ፤ የይሁዳ የንግስና መሪነት መሲሁ እስኪመጣ ለዘላለም ይሄዳል ፡፡
ትምህርት
ኢያሱ (15፡ 1-12)፡ ድንበር አስፈላጊ ነበር ምክንያቱም የባላደራነት ገዳይ ስለ ነበር - ተሰጥቶአቸዉ የነበረዉን ምድር በመከባከብ እና ምድሪቱን ከዉጪ ከሚመጣ ወራሪ በመከላከል ፡፡ የይሁዳ ደቡባዊ ድንበሩ የሙት(ጨዉ) ባህር ሰሜናዊ ጫፍ በመሆን በግብፅ ድንበር እስከ አብዛኞቹ ደቡብ የእስራኤላዊያን ነገድ ደቡብ ድረስ ይወርድ ነበር ፤ የምስራቅ ድንበሩ ደግሞ በሙት(ጨዉ) ባህር አጠገብ ይደርስ ነበር ፤ የሰሜን ድንበራቸዉ ደግሞ ከዮርዳኖስ በር(መግቢያ) በመጀመር ሜደትራሊያን ባህር የሚያበቃ ነበር ፡፡
ኢያሱ (15፡ 13-19)፡ ካሌብ ለእርሱ ተስፋ ስለተገባለት አሁንም ረጃጅሞች የነበሩባትን ምድር ጠየቀ ( ኢያሱ 14) ፤ ካሌብ ረጃጅሞቹን በማስወጣት በዳቤር ላይ ዘመት ፡፡ ካሌብ ቂርያትሴፍርን(የአኔቅን አባት) ለሚይዘለት ሰዉ ሴት ልጁን እንደሚያጋባዉ ቃል ገባ ፤ ጎቶንያ የካሌብ የወንድሙ ወይም የታናሹ ልጅ ችግሩን በመዉሰድ ቂርያትሴፍርን ያዛት ከዚያም የካሌብን ሴት ልጅ ዓክሳን አገባት ፡፡ ቆይቶም ጎቶንያ የእስራኤል ዳኞ ሆነ ፤ በአንዳንድ ትርጉም በህግ የካሌብ ልጅ ከኢያሱ በኋላ መሪ እና ነፃ አዉጪ ሆነ (መሳ 3፡ 9) ፡፡ የካሌብ ሴት ልጅ ዓክሳ ስለ ምንጭ ዉሃው መባረክ ካሌብ እንዲጠይቀዉ ባሏል እንዲከታተለዉ አደረገችዉ ፡፡
ሄስ ስለ ምንጩ የዓክሳን ጥያቄ ከይሳቅ ቃር የርብቃን መገናኘት የሚያስታውስ እንደ ሆነ ፅፏል ፤ እነዚህን ተመሳሳይነቶች ተመልከቱ፡
- ሁለቱም እንስሳት ላይ በመሆን (በመጋለብ) ቀረቡ ፡፡
- ሁለቱም ወረዱ ፡፡
- ሁለቱም ለሆነ ነገር ጠየቁ ፡፡
- ሁለቱም የጤቁትን ነገር ተቀበሉ ፡፡
በዚህ የምንረዳዉ በጠየቅን ጊዜ በክርስቶስ ርስታችንን እንደማናጣ የሚያረጋግጥ ነው ፤ ርስታችን ከመሬት የበለጠ ነው፣ ከምንጭ ዉሃ የበለጠ ነው - በኢየሱስ ሙሉ ነው ፡፡ ሁልጊዜ ርስትን እየተሰጠን ነው ነገር ግን ስለ ርስት መፈጸም ሁልጊዜ አንጠይቅም ፡፡
ኢያሱ (15፡ 20-32)፡ በቁጥር 20-32 የይሁዳን ነገድ በዉጭ የሚያዋስኑ 29 ከተሞች የተሰጡ ናቸው ፡፡
ኢያሱ (15፡ 33-47)፡ በእነዚህ ጥቅሶች በቆላማው አገር 39 ከተሞች እና መንደሮቻቸው የተዘረዘሩ ናቸው ፡፡
ኢያሱ (15፡ 48-60)፡ በእነዚህ ቁጥሮች በተራራማዉ አገር 38 ከተሞች እና መንደሮቻቸዉ የተሰጡ ናቸው ፡፡
ኢያሱ (15፡ 61-62)፡ የምድረበዳዉ ስድስት ከተሞች እና መንደሮቻቸዉ የተሰጡ ናቸው ፡፡
ኢያሱ (15፡ 63)፡ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳዊያንን የይሁዳ ዘር ግን አላስወጡዓቸውም ፤ ይህ በይሁዳ እና በቢኒያም ድንበር መካከል ቀኝ ላይ ነበር ፡፡ በህይወት የተረፉት ወደ ተመሸጉ ከተሞች አምልጠዋል ከዚያም ተመልሰዉ በኢየሩሳሌም ታዩ (ኢያ 10፡ 20) ፤ ቁጥሩም “ ኢያቡሳዉያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ዉስጥ ተቀምጠዋል “ በማለት ይቀጥላል ፤ ያም በአሁኑ ጊዜ በኢየሩሳሌም ላለዉ ችግር ምክንያት የሆነ ይመስላል ፡፡ እስራኤላዊያን ቤታቸዉን ባለማንፃታቸዉ ምክንያት እስካሁን ድረስ ዛሬም በእስራኤል ሰላም የለም ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ እስራኤላዊያን ከመድረሳቸዉ በፊት በኢየሩሳሌም የሚኖሩት ኢያቡሳዊያን በከተማዋ መፅናት ችለዉ የነበሩበትን “ ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት በሚለዉ ግዴታቸው የይሁዳ ነገዶች አለመከተላቸዉ ነበር ፤ እግዚአብሄር ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር እስራኤልን ሰላም ማድረግ አልፈለገም ይልቁንም እንዲያስወጡዓቸዉ እና እስከ መጨረሻዉ እንዲያጠፉአቸዉ እንደ ሆነ ይገልፃል “ ፡፡ መጀመሪያ ላይ ኢየሩሳሌም ከይሁዳም ወይም ከቢኒያም ነገድ ስር አልነበረችም ፡፡
መሳ (1፡ 8)፡ “ የይሁዳም ልጆች ኢየሩሳሌምን ተዋግተዉ ያዙዓት በሰይፍ ስለትም መቱዓት ከተማይቱንም በእሳት አቃጠሉዓት “ ፡፡
መሳ (1፡ 28)፡ “ እስራኤልም በበረቱ ጊዜ ከነዓናዊያንን አስገበሩዓቸው ፈጽመዉም አላወጡዓቸውም “ ፡፡
እስከ ዳዊት ጊዜ ድረስ የኢያሩሳሌም ከተማ በኢያቡሳዊያን ስር ነች - ሁሉንም ይሁዳ እና ቢኒያም ታዘዉ እንደ ነበረው ስላላስወጡዓቸው ፡፡
መዝጊያ
ከእነዚህ ከተሞች በአንዷ ከካሌብ ሴት ልጆች አንዷ ስለ ብዙ ጠይቃለች ፤ ይህ ለእኛ ሁሉንም እንደ ምንችል እና ለብዙ እግዚአብሄርን ….በብዙ መንፈሱን፣ በብዙ መገኘቱን እንዲሁም በብዙ ፀጋውን እንጠይቃለን ፡፡
2 Richard S. Hess, Joshua: An Introduction and Commentary, Tyndale Old Testament Commentaries series. (Leicester, England, and Downers Grove, Ill.: Inter-Varsity Press, 1996), p. 245; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Joshua, p. 77.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Joshua–Esther (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2003), p. 70.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 295.
ጥያቄዎች
-
የካሌብ እምነት በቤተሰቦቹ ላይ እና በህግ ልጆቹ ላይ እንዴት አድርጎ ተጣበቀ (ኢያ 15፡ 13-19፣ መሳ 3፡ 7-11) ? የካሌብ ሴት ልጅ ለመጠየቅ ምንድን በማድረግ ነበር እምነት ያላት ?
-
በቤተ ክርስቲያን ትንሹ ትዉልድ እንዴት አድርጎ ትልቁን ትዉልድ እንደ ሚያገለግለዉ ምን ታስባላችሁ ?
-
በኢያ (15፡ 20-62) የይሁዳ ነገድ ርስታቸዉን እየተቀበሉ ነበር ፤ በክርስቶስ ርስታችንን ስለ ተቀበልን እንደ አማኝ በምንድን ልንጠይቅ እንችላለን ? ወደ ፊት የምንጠብቀዉ ርስት ምንድን ነው ? (ኤፌ 1፡ 3፣ 1ጴጥ 3-6)
-
በኢያሱ (15-16) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Joshua 15:19
“She replied, ‘Give me a blessing. Since you have given me land in the Negev, give me the springs of water also.’ So he gave her the upper and lower springs.”
ካሌብ በዳቤር ሕዝብ ላይ ዘመተ፡፡ ቂርያትሤፍርን ለሚይዝ ሰው ልጁን አክሳን ለመዳር ቃል ገባ፡፡ ጎቶንያል ቂርያትሤፍርን ያዛት እና መታት፥ እናም አክሳን ለሚስትነት ተቀበለ፡፡ አክሳ አዲሱ ባሏ ከአባቷ የእርሻን መሬት እንዲጠይቅ አሳመነችው፡፡ አክሳ አባቷ አዲስ ለተጋቡት ጥንዶች ተጨማሪ የሚሰጠው እንደነበረው ታውቃለች፥ ስለዚህ ተጨማሪ ጠየቀች፡፡ በረከትን እና የውሃ ምንጭን ጠየቀች፡፡ ሳያመነታ፥ አባቷ ሁለቱንም የላይኛውን እና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት፡፡
በተመሳሳይ መንገድ፥ የሰማዩ አባታችሁ ለእናንተ የበለጡ ስጦታዎች አሉት፡፡ ከእርሱ ጋር በታማኝነት ስትራመዱ፥ መልካም ነገሮችን አይከለክላችሁም፡፡ ከምታስቡት በላይ፥ ብዙ የሚሰጠው ኃይል፥ ፀጋ፥ ጥበብ እና ደስታ አለው፡፡ ኢየሱስ የዕየለት የውሃ ምንጭ ነው፡፡ እርሱን ስታምኑት፥ በውስጣችሁ ውስጥ ይኖራል፡፡ ጌታ በእርሱ በመኖር፥ የምትፈልጉትን ሁሉ ስትጠይቁ፥ እንደሚደረግላችሁ ተናግሯል፡፡ ዛሬ፥ በእምነት ጌታን እንዲጨምርላችሁ ጠይቁት፡፡ የህይወት ውሃ ምንጭ በውስጣችሁ በዛሬው ዕለት ይፍለቅ!
“ካሌብም፦ ምን ፈለግሽ? አላት። እርስዋም፦ በረከትን ስጠኝ በደቡብ በኩል ያለውን ምድር ሰጥተኸኛልና አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ አለችው። እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት።”
—መጽሐፈ ኢያሱ 15:19
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 84:11 — “እግዚአብሔር አምላክ ምሕረትንና እውነትን ስለ ወደደ፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም። ”
- የዮሐንስ ወንጌል 15:7 — “በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ”
- የዮሐንስ ራእይ 21:6 — “አለኝም፦ ተፈጽሞአል። አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ። ’”
የመሲሁ ሙሉ ስዕልበታሪክ መፅሀፍት፡ ክፍል 8
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።