Historical Books Joshua

Division of Land

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Commander Joshua 17-18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 208 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የምናደርገዉ ሁሉም ስለ ምድር ያወራል ! እግዚአብሄር ከመጀመሪያው ከአብርሃም ጋር ምድርን እና እጣ ተስፋ መስጠቱን ቀጠለ ፡፡ በመጨረሻም እስራኤላዊያን በኢያሱ መሪነት ስር ወደ ተስፋይቱ ምድር ገቡ ፤ ስለ ምድርም ከሰዎች ጋር ዉጊያ ነበራቸው ፡፡

ትምህርት

ኢያሱ (17፡ 1-13)፡ ኢያሱ ለምናሴ ነገድ ምድሪቱን አከፋፈለ ፤ የምዕራብ ምናሴ ቡድና እና የምስራቅ የምናሴ ቡድን ነበር ፤ የምዕራብ እና የምስራቅ ለምን ነበር የነበረው ? ወንዙ ምድሪቱን ስለ ከፈላት እና ግማሹ ነገድ ተስፋይቱ ምድር ከመግባት ይልቅ ከዮርዳኖስ በስተምስራቅ በኩል ለመኖር ወስነው ነበር ፡፡

ኢያሱ (17፡ 14-18)፡ እነዚህ ቁጥሮች ለምናሴ እና ለኤፍሬም ነገድ ተጨማሪ ዉርሶችን ያስቀምጣሉ ፡፡

ኢያሱ (18፡ 1)፡ ይህ ቁጥር በብዙ በመሰብሰብ መኖርን ይጀምራል ፤ ጠቅላላ ማህበሩ በሴሎ ተሰበሰቡ ፡፡ በሴሎ ከሁሉም ስፋራ መካከል ላይ ነበረች እንዲሁም እስራኤላዊያን የመገናኛ ድንኳኑን ተክለዉበት የነበረ ስፋራ ነበር ፡፡ አስታዉሱ የመገናኛው ድንኳን ተንቀሳቃሽ እንደ ነበር እና እንደ ድንኳን ማደሪያ እንደ ይጠቀስ እንደ ነበር ፡፡ እስራኤላዊያን የእግዚአብሄርን መገኘት መቅመስ (ማግኘት) እንዲችሉ ፈለጉ ፤ በጊዜው የድንኳኑ ማደሪያ ወደ ቤተ መቅደስ ይመራል ቤተ መቅደስ ደግሞ ወደ ኢየሱስ ይመራል (1ሳሙ 4፣ መዝ 78፡ 60፣ ኤር 7፡ 14) ፡፡

በዚህ ታሪክ በኩል መጓዝ እፈልጋለሁ ፤ በሴሎ ሁለት ሰዎች የመገናኛውን ድንኳን ሰሩ (ዘጸ 31፡ 2-3፣ 6) ፤ እነዚህ ሁለት ሰዎች ጠቅላላ ሰራተኞች ነበሩ ፡፡ ድንኳ ከተጠናቀቀ በኋላ በተስፋይቱ ምድር ዉስጥ በሂደት ነበር የተወሰደው፡

  • ጌልጌላ (ኢያ 5፡ 10) ፡፡
  • ጌልጌላ (ኢያ 10፡ 15፣ 43) ፡፡
  • ሴሎ (ኢያ 18፡ 1) ፡፡
  • ቤቴል (መሳ 20፡ 27-28) ፡፡
  • ሴሎ (1ሳሙ 1፡ 3) ፡፡
  • ምጽጳ (1ሳሙ 7፡ 9-11) ፡፡
  • ጌልጌላ (1ሳሙ 10፡ 8) ፡፡
  • ገባዖን (1ዜና 16፡ 39-40) ፡፡

ይህ ድንኳን ቆይቶ ሰለሞን በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ በመስራቱ አብቅቷል ፤ ድንኳኑ የሚንቀሳቀስ ስለ ነበር ለህዝቡ ለመትከል እና ለመንቀል ብዙ ስራ ነበር ፡፡ የእግዚአብሄርን መገኘት ለመቅመስ አንዳንድ ጊዜ ለእርሱ ከራሳችን መንገድ መዉጣት አለብን ፡፡

ኢያሱ (18፡ 2)፡ አምስት ነገዶች ቀድመዉ ርስታቸዉን ተቀብለዉ ነበር ፤ ተጨማሪ ርስታቸዉን ያልተቀበሉ ሰባት ነበሩ ፡፡ ይህ ለማድረግ እየመረጡ እንዳልነበር ነበር ፡፡

ኢያሱ (18፡ 3)፡ ኢያሱም “ እስከ መቼ ችላ ትችላላችሁ ?” ብሎ ጠየቃቸው የኔልሰን ማብራሪያ “ የምድሪቱን ነዋሪዎች ማሸነፍ ብቻ በቂ አይደለም ንብረቷንም መዉሰድም እንደ ሚገባቸዉ “ ይናገራል ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ ይህ ስንፍናበኢያ (13፡ 1) የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ባለማክበር በተስፋዉ እምነት እንደሌላቸዉ ማሳየታቸዉ “ ላይ በመሄድ አመልክቷል ፡፡ ተጨማሪዎቹ ሰባት ነገዶች ከምድሪቱ በኋላ ሄደዉ አልነበረም ! ምድሪቱ ላይ ያልኖሩትን(ያልሰፈሩ) ነገዶች ስንጠራቸው፡

ቢኒያም (ኢያ 18፡ 11-28)

ስምዖን (ኢያ 19፡ 1-9)

ዛብሎን (ኢያ 19፡ 10-16)

ይሳኮር (ኢያ 19፡ 17-23)

አሴር (ኢያ 19፡ 24-31)

ንፍታሌም (ኢያ 19፡ 32-39)

ዳን (ኢያ 19፡ 40-48)

እየመጣ ስለ ነበረዉ ሂደት(ለዉጥ) ማየት ትችላላችሁ ነገር ግን እንደ ነበር አስባለሁ ምክንያቱም ኢያሱ ስለጠራቸው፡፡

በ 2ነገ (5፡ 8-11) ነዕማን ሄዶ ዉሃዉ ዉስጥ ሰባት ጊዜ በመግባት ከለምፅ እንዲፈወስ ተነገረው ፤ ተበሳጭቶ እና አዝኖ ነቢዩን ትቶት ሄደ ፤ ከነቢዩ ከራሱ ፈጣን የሆነ ተዓምራት ስለ ፈለገ ፡፡ እስራኤላዊያን ርስታቸዉ እንዲሰጣቸዉ ፈለጉ ፤ ከእግዚአብሄር ጋር ባለን ግንኙነት የምንጫወተው ድርሻ አለን ፤ ለዚያም ነዉ ግንኙነት ተብሎ የሚጠራው፡፡ እግዚአብሄርን እንድናዉቀው እንዲሁ ወደ እርሱ መፍሰስ አለብን ፡፡

ዮናስ (1፡ 1-3) ተመልከቱ ፤ አንዳንዴ ጊዜ የሆነን ነገር የተወሰነን ነገር ሊመለከት ይችላል ነገር ግን እግዚአብሄር የራሱ መንገድ እንደ ሚኖረዉ ሊያሳየን ይቀጥላል ፡፡ በሉቃ (6፡ 46-48) ኢየሱስ “ ለምን ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ትሉኛላችሁ የምለዉንም ግን አታደርጉም ? “ አላቸው በራሱ ጊዜ እግዚአብሄር ያለንን ባላደረግን ጊዜ ያለመታዘዛችንን ዉጤት ይገጥመናል ፡፡

ኢያሱ (18፡ 4)፡ ኢያሱ እንዚህን የእስራኤላዊያንን ሰባት ወገኖች ከእያንዳንዱ ወገን ሰዎስት ሰዎች እንዲሾሞ በአጠቃላይም 21 ሰዎችን አዘዛቸው ፤ እነዚህ ሰዎች ምድሪቱን በማጥናት ምልከታቸዉን በመፃፍ ያገኚትን መለስዉ ሪፖርት ለማድረግ ይላካሉ ፡፡ ኢያሱ ጥሩ መሪ ነበር ምክንያቱም እነዚህ ነገዶች የዘገዩ ስለ ነበሩ የእርሱ አቅጣጫ አስፈለጋቸው ፡፡

ኢያሱ (18፡ 5)፡ ምድሪቱ ወደ ሰባት ክፍል ትከፋፈላለች ፡፡ ይሁዳ በደቡብ የሚቀመጥ ሲሆን የዮሴፍ ቤተሰብ ደግሞ በሰሜን በኩል ይሆናሉ ፡፡

ኢያሱ (18፡ 6-7)፡ ኢያሱ 21 ሰዎች ያገኙትን ተመልሰዉ ሪፖርት እንዲያደርጉ አዘዛቸዉ ከዚያም ኢያሱ በእግዚአብሄር ፊት ለእያንዳንዳቸዉ ነገዶች እጣዎችን ያወጣል ፤ እነዚህ እጣዎች እያንዳንዱ ነገድ የትኛዉን የምድሪቱን ክፍል እንደ ሚወርስ ይወስናሉ ፡፡ እንዳትረሱ ሌዋዊያን መሬትን አይቀበሉም ምክንያቱም እንደ ርስታቸዉ የክህነት አገልግሎትን ስለ ተቀበሉ ፡፡

ኢያሱ (18፡ 8-10)፡ ሰዎቹ ለመሄድ እንደ ተዘጋጁ ኢያሱ አቅጣጫዉን ደገመላቸው ፤ በዋናነት ለሚሄዱበት እንዲያተኩሩ እና ተመልሰዉ እንዲመጡ ፡፡ 21 ሰዎችም በመሄድ አሳይመት ተሰጥቷቸዉ የነበሩትን ከተሞች ምልከታቸዉን ፃፉ ፤ በአንድ ላይ ተመልሰዉ በመጡ ጊዜ በአንድ ላይ መረጃዉን ወደ ሰባት በመከፋፈል አስቀመጡት ፤ ኢያሱም በሴሎ ለሰባቱ የእስራኤላዊ ነገዶች እጣዎችን አወጣ ከዚያም በዚያ መሰረት ምድሪቱን ተከፈለች ፡፡

መዝጊያ

ምዕራፍ 18 መጨረሻ ላይ የተስፋይቱ ምድር በእስራኤላዊያን መካከል የተከፈለች ሆነች ፤ በዚህ ጭብጥ ላይ ኢያሱ እስራኤላዊያን እርግጠኛ በመሆን በአብርሃም፣ በይሳቅ እና በያዕቆብ በኩል ያለፈዉን ትንቢት መፈፀሙን እንዲያዉቁት ፈለገ ፡፡ ኢያሱ ጥሩ መሪ ነበር፣ ህዝቡ እንዲያደርጉት በሚያዛቸዉ ግልፅ ነበር ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 297.

  2. Nelson’s Commentary, p. 297.

ጥያቄዎች

  1. የኤፍሬም እና የምናሴ ጥያቄ ስለ ምን ነበር ? ኢያሱ እንዴት አድርጎ መለሰላቸው ?
  2. ኤፍሬም እና ምናሴ ርስታቸዉን በመሚወስዱበት እንዴት እንደ መለሱ እና ካሌብ እንዴት እንደመለሰ በመካከል ያለዉ ልዩነቱ ምን ነበር ? (ኢያ 14፡ 11-12)
  3. እስካሁን ርስታቸዉን ያልያዙ ሰባት ነገዶች ለምን እንደ ነበሩ ምን ታስባላችሁ ? (ኢያሱ 2-3፣ ምሳ 12፡ 27፣ ዕብ 11፡ 6)
  4. ርስት በመኖር እና ያለን ርስት በመያዝ በካከል ያለዉ ልዩነት ምንድን ነው ? (ኢያ 2፡ 6፣ 18፡ 3፣ ማቴ 25፡ 34)
  5. በኢያሱ (17-18) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Joshua 18:3–4

“So Joshua said to the Israelites, ‘How long will you delay going out to take possession of the land that the Lord, the God of your fathers, gave you? Appoint for yourselves three men from each tribe, and I will send them out. They are to go and survey the land, write a description of it for the purpose of their inheritance, and return to me.’”

መላው የእስራኤላውያን ማኀበር በሴሎ ተሰበሰቡ፡፡ ርስትን ገና ያልተከፋፈሉ ሰባት የእስራኤል ነገዶች ነበሩ፡፡ ለመውጣት እና እግዚያብሔር የሰጣቸውን ምድር ለመውረስ ሕዝቡ እስከ መቼ እንደሚዘገዩ ኢያሱ አሰበ፡፡ ስለዚህ ነገዶቹ ሄደው ስለመሬቱ እንዲያጣሩ እና መግለጫ ጽፈው ወደ እርሱ እንዲመለሱ አዘዛቸው፡፡ ኢያሱ እስኪመለሱ ድረስ የመገናኛው ድንኳን ጋር ጠበቃቸው፡፡ ከዚያም፣ በጌታ ፊት እጣ ተጣጣሉ፡፡

በኢየሱስ እንደሚያምኑ ሰዎች፥ ከእርሱ ጋር ህብረት እንዲኖራችሁ፥ የብርታት፥ የሰላም፥ የደስታ፥ እና የምሪት ምንጭ እንዲሆናችሁ በእርሱ ልትኖሩ እድል አላችሁ፡፡ ነገርግን ልክ እንደ እስራኤላውያን፥ ተከትላችሁት መሄድ አለባችሁ፡፡ ጌታ በዕየለቱ ህልውናውን እንድትፈልጉ ይናፍቃል፡፡ ኢየሱስን በይበልጥ ለማወቅ፥ በህልውናው ውስጥ ጊዜ ማሳለፍ፥ ቃሉን ማንበብ፥ ማጤን፥ እና መፃፍ አለባችሁ፡፡ ይህን ከማድረግ የሚከለክላችሁ ምንድን ነው? ለምን ትዘገያላችሁ? ምናልባት ሥራ በዝቶባችሁ ወደ ጎን መሄድ ቀጥላችሁ ይሆናል፡፡ ሂዱ! ዛሬውኑ ጀምሩ! ጌታን እና በህልውናው ውስጥ ለእናንተ ያዘጋጀውን ከመፈለግ አትዘግዩ!

“ኢያሱም የእስራኤልን ልጆች አላቸው፦ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ እስከ መቼ ለመግባት ቸል ትላላችሁ? ከየነገዱ ሁሉ ሦስት ሦስት ሰዎች ምረጡ፥ እኔም እልካቸዋለሁ፤ ተነሥተውም አገሩን ይዞራሉ፥ እንደ ርስታቸውም መጠን ይጽፉታል ወደ እኔም ይመለሳሉ።”

—መጽሐፈ ኢያሱ 18:3–4

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 27:7–8 — “አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ፤ ማረኝና አድምጠኝ። አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ። ”
  • ሮሜ 13:11 — “ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። ”
  • የያዕቆብ መልእክት 4:8 — “ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበታሪክ መፅሀፍት፡ ክፍል 9