The Tribe of Asher
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Commander Joshua 19-20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሁላችንም እያወራን ያለነዉ ልክ እንደ ጋራ መኖሪያ አካባቢ እንደ ሆነ ይሰማኝል ፡፡ እስከዚህ ሰዓት ድረስ እስራኤላዊያን ምድራቸዉን አልተሰጡም ነበር ፤ በመጨረሻም የተስፋይቱ ምድር ተሰጠቻቸዉ ፡፡ ካሌብ እና ኢያሱም በመጨረሻ ወደ ተስፋይቱ ምድርን መግባት አገኙ ! የምድሪቱን ሀብት ተቀብለዉ ያልነበሩ ሰባት ነገዶች ነበሩ ፡፡ ዛሬ ስለ እስራኤላዊያን ተጨማሪ ርስት ከምድር ብቻ ይበልጥ ስለ ነበረው እናወራለን ፤ በምድሪቱ ዉስጥ ብዙ አካሎች ነበሩ ፡፡ ዛሬ ስለ አሴር ነገድ እናወራለን ፤ በትንቢት የሚያስደንቅ ሀብታም ነገድ ነው ፡፡
ትምህርት
ኢያሱ (19፡ 1-9)፡ የመጀመሪያዉ እጣ ለቢኒያም ነገድ ወጣ ሁለተኛዉ እጣ ደግሞ ለስምዖን ነገድ ወጣ ፤ የምድሪቱን ርስት መረዳት በጀመራችሁ ጊዜ ሁሉም ነገር በብሉይ ኪዳን ዉስጥ ትርጉም ይሰጣል ፡፡
ኢያሱ (19፡ 10-16)፡ ሰዎስተኛዉ እጣ ለዛብሎን ነገድ ወጣ ፤ እንዲሄዱ፣ እንዲያጠኑ፣ እንዲመዘግቡ እና ተመልሰዉ እንዲመጡ የተነገራቸዉን 21 ሰዎች ታስታዉሳላችሁ ? እነዚህ ሰዎች የስራቸዉን ዉጤት እያዩ ነበር ፡፡
ኢያሱ (19፡ 17-23)፡ አራተኛው እጣ ለይሳኮር ነገድ ወጣ ፤ ርስታቸዉ ከገሊላ ባህር ወደ ደቡብ የተቀመጠ ነበር ፡፡
ኢያሱ (19፡ 24-31)፡ አምስተኛዉ እጣ ለአሴር ነገድ ወጣ (ሕዝ 47፡ 21-23) ፤ የአሴር ምድር በሜደትሪሊያን ባህር አጠገብ ጠባብ ትልቅ ቁራጭ ምድር ነበር ፡፡ ከአብዛኞቹ ሌሎቹ ነገዶች ግዛት በተለየ የአሴር ድንበር ከተሞች ከሌሎቹ የተሰመረ አልነበረም፤ አዲሱ የአሜሪካን መፅሀፍ ቅዱስ ማብራሪያ የአሴርን ግዛት “ እንደ ሚያንፃባር ሙሉነት ይህም የሁለቱ የተለያዩ እቃዎች ያልተጣራ መደበላለቅ በግዛቱ ላይ ሀገራዊ ይገባኛል ባይነት ከሆነዉ መነሳትን ያሳያል ሁለቱም የድንበር ከተሞቹ እና የዉስጠኛ ከተሞች ተመሳሳይ ተግባርን እንደ ሚያገለግሉ “ ይገልፃል ፡፡ ስለሆነም ድንበሩን ለመለየት አስቸጋሪ ነበር (መሳ 1፡ 29-31) ፤ ድንበሩ በቋሚነት የሚጓዝን ይመስላል ፡፡ በኢያ (21፡ 30-31) የሌዋዉያን ከተሞች የተዘረዘሩ ናቸው (1ነገ 9፡ 11-13) ፡፡ የአሴርን ድንበሮች ለመለየት እንዴት አስቸጋሪ እንደ ሆነ ይህ ስዕልን ይሰጣል፡
- አሴር በልያ አገልጋይ ዘለፉ የተወለደ የያዕቆብ ስምንተኛ ልጅ ነበር ፤ ዘለፉ ለያዕቆብ የወለደችለት ሁለተኛ ልጅ ነበር ፤ አሴር የሚለዉ ስም “ ደስታ “ ማለት ነው ፡፡
በዘዳ (27፡ 13-16) መሰረት የአሴር ተወካይ በሌሎቹ አምስት ነገዶች ተወካዮች ላይ በሙሴ ትዕዛዝ ስር በእስራኤላዊያን ላይ ርግማን ተናግሯል ፡፡ ይህ ነገድ በእስራኤላዊያን ላይ የተናገራቸዉ 12 ርግማኖቹ ነበሩ፡፡
በዘዳ (33፡ 24) ያዕቆብ አሴር በጣም የተባረከ እና ሞገስ ያለዉ እንደ ሚሆንተናግሯል (ዘፍ 49፡ 20) ፤ ለአሴር ያዕቆብ ከሰጣቸው አንዱ በረከት ከእግዚአብሄር የሆነዉን ብልፅግና እና በረከት ለማመልከት እግሮቹን በወይራ ዘይት ዉስጥ ያጠልቃል(ያስገባል) የሚል ነበር ፡፡
የአሴር ነገድ ከነዓናዊያንን ማስወጣት አልተቻለዉም (መሳ 1፡ 31-32) ፤ እግዚአብሄር እንዲያደርጉት የነገራቸዉን አላደረጉም ፡፡ በረከታቸዉን ተቀብለዉ ነበር ወይስ ባለመታዘዛቸዉ ዉጥረት (ስጋትን) (መሳ 5፡ 17)?
ኢያሱ (19፡ 32-39)፡ ስድስተኛዉ እጣ ለንፍታሌም ወጣ ፡፡
ኢያሱ (19፡ 40-48)፡ ሰባተኛዉ እጣ ለዳን ወጣ ፡፡
መዝጊያ
የአሴር ሰዎች እግዚአብሄር እንዲሰሩት የሚፈልገዉን ባለማድረጋቸዉ ምክንያት በረከታቸዉን እንዳጡት ብዙ ጊዜ ይሰማኝል ፤ በእግዚአብሄር ስንጓዝ በረከቱን ያፈስስብናል ፡፡ እግዚአብሄር እንድታደርጉት የሚፈልገዉን አድርጋችኋል ?
David M. Howard, The New American Bible Commentary (Nashville: Broadman & Holman, 1998), p. 372
ጥያቄዎች
-
ምድሪቱን ስትከፋፈል “ እንደ ቤተሰባቸዉ “ የሚለዉ ሀረግ ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ?
-
በኢያ (19፡ 9) እንደ ቤተሰቡ የተሰጣቸዉ የይሁዳ ልጆች ድርሻ በጣም ትልቅ የነበረዉ ለምን ነበር ?
-
የመማፀኛ ከተሞች ተብለዉ የተሰየሙት መሪ ማን ነበር ?
-
ዳን በግዛቱ ያልነበረችዉን ሌሼምን ለመዉሰድ የፈቀደዉ ለምን ነበር ? (ኢያ 19፡ 47)
-
በኢያሱ 19-20 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Joshua 19:47
“When the territory of the Danites slipped out of their control, they went up and fought against Leshem, captured it, and struck it down with the sword. So they took possession of it, lived there, and renamed Leshem after their ancestor Dan.”
የእስራኤል ነገዶች የመሬት ርስታቸውን ምልክት ማድረጋቸውን ቀጠሉ፡፡ እያንዳንዱ ነገድ ወሰን የነበረው መሬት ነበረው፡፡ እያንዳንዱ ድርሻ የተለያየ ነበር ደግሞም እያንዳንዱ ነገድ የተሰጠውን መሬት የመንከባከብ ኃላፊነት ነበረበት፡፡ የዳን ነገዶች ርስታቸው ከቁጥጥራቸው ውጪ ሆነ፡፡ ለመሬታቸው መዋጋት እና መውረስ ነበረባቸው፡፡
ጌታ መሬት ፥ ቤት ፥ግንኙነቶችን ወይም ደግሞ ልጆችን ሲሰጣችሁ ፥ የመንከባከብ ኃላፊነት አለባችሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ፥ ልክ እንደ ዳን ነገድ፥ እግዚያብሔር በአደራ አምኖ የሰጣችሁ ነገር ከቁጥጥራችሁ ውጪ ሊሆን ይችላል፡፡ በህይወታችሁ ውስጥ እናንተ ባለቤት የሆናችሁበት ወይም ኃላፊነት ኖሯችሁ ከቁጥጥራችሁ ውጪ እንደሆነ የሚሰማችሁነገር አለ? ምናልባት ከባድ ግንኙነቶች ይኖራችኋል ወይም ልጆችን ለማሳደግ እየታገላችሁ ነው፡፡ ምናልባት፥ ቤታችሁ እየፈረሰ ነው፥ እናንተም ለመቀጠል የሚያስችል ግብአት የላችሁም፡፡ ቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ አታውቁም ይሆናል፡፡ አስታውሱ፥ ጌታ ይንከባከባችኋል፥ የሰጣችሁን እንድትንከባከቡ አደራ ሰጥቷችኋል፡፡ በሁከት መካከል እሱን ፈልጉት እና እነርሱን በጥሩ ሁኔታ እና በብቃት እንድትጠብቁ ጥበብን እንዲሰጣችሁ ለምኑት፡፡ ተስፋ አትቁረጡ! የዳን ነገዶች ለመሬት ድርሻቸው መዋጋት ነበረባቸው፡፡ መጽናት፣ ብዙ መጸለይ እና በፊታችሁ ያሉትን ጦርነቶች መዋጋት ሊኖርባችሁ ይችላል፡፡ አስታውሱ፥ ጌታ ከእናንተ ጋር ይሆናል፡፡ በእርሱ ድል አላችሁ!
“የዳንም ልጆች ዳርቻ አልበቃቸውም፤ የዳንም ልጆች ከሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ ያዙአትም፥ በሰይፍም ስለት መቱአት፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም፤ ስምዋንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት።”
—መጽሐፈ ኢያሱ 19:47
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ወደ ገላትያ ሰዎች 6:9 — “ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት። ”
- የያዕቆብ መልእክት 1:5 — “ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።”
- 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:10 — “ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕልበታሪክ መፅሀፍት፡ ክፍል 10
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።