Historical Books Joshua

Building an Altar as a Reminder

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Commander Joshua 21-22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 210 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለእኔ ከኢያሱ ጥናታችን የምወስደው ለእኛ የሚዋጋ የእግዚአብሄር ጦር አዛዥ እንዳለን ነው ፤ በምንሄድበት ሁሉ ኢየሱስ “ ከእናንተ ጋር ነኝ ከእናንተም ጋር እሆናለሁ “ ይላል ፡፡ ኢያሱ ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደ ሄደ የነበረው በራስ መተማመን ያ ነበር ፡፡ ኢያሱ በዉጊያ እና ከዉጊያ ዉጪ እስራኤላዊያንን ሲመራ ታላቅ አዛዥ እና ጦረኛ ነበር እንዲሁም ለህዝቡም የሚጠነቀቅ እንጂ ፤ በኢያሱ 22 የኢያሱን የእንክብካቤ ጎን እናያለን ፡፡

ትምህርት

ኢያሱ (22፡ 1-8)፡ ኢያሱ የሮቤልን፣ የጋድን እና የምናሴን ግማሽ ነገድ በእርሱ ፊት ጠራቸው (ቁጥር 1) ፤ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ በመስማት ሌሎቹን ነገዶች በመርዳታቸውአመሰገናቸው (ቁጥር 2-3) ፤ በሌላ ቋንቋ በሚገባ አጠናቀዉ ነበር ፡፡ ሁሉንም ነገር እንዲያደርጉ ተጠይቀዉ እንደ ነበር ሰርተዉ ነበር (ቆላ 3፡ 23-24) ፤ በቁጥር 4 ኢያሱ በትክክልየሚያስከብር ተግባር በመስጠት ወደ ቤታቸዉ እንዲመለሱ ላካቸው (ሮሜ 5፡ 1) ፡፡ እንደ ክርስቲያን በአለም ጦርነት ላይ አንቆይም በክርስቶስ ማረፍ እንችላለን ፡፡

ቁጥር 5 የዚህ ምዕራፍ ቁልፍ እና ዋና ነው ፡፡ ኢያሱ እነዚህን ነገዶች ርስታቸዉን እንደ ተቀበሉ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ እና መመሪያ መታዘዝን እንዲቀጥሉ አበረታታቸዉ - በሙሉነት እግዚአብሄርን እንዲወዱ፣ በመንገዱ እንዲጓዙ፣ ትዕዛዙን እንዲጠብቁ፣ በእርሱ የታመኑ እንዲሆኑና በፍጹም ልባቸዉ እና ነፍሳቸዉ እንዲያገለግሉት ፡፡ የታመኑ እንዲሆኑ አበረታቸዉ ምክንያቱም ተመልሰዉ ዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ድል ባልተደረጉ ሰዎች ወደ ሚከበቡት ስለ ሚሄዱ ፤ ወንዙ በነገዶቹ መካከል መልከዓ ምድራዊ መከፋፈል ፈጥሯል ፡፡ ኢያሱ ባርኳቸዉ ቤታቸዉ ላካቸው (ቁጥር 6) ፡፡ በተለምዶ ታላቁ ካህን በረከትን ይሰጣል (ዘኁ 6፡ 22-27) ነገር ግን በዚህ ጊዜ ኢያሱ አደረገው ፤ ከዚያም ኢያሱ ከጦርነት ከተወሰደ እቃ ድርሻቸዉ ጋር በመንገዳቸዉ ላይ ላካቸው ፡፡ ቤታቸዉ እንደ ተመለሱ በሚያስገርም ተባርከዉ ነበር ምክንያቱም ስራቸዉን ፈፅመዉ ስለ ነበር (ቁጥር 7-8) ፡፡

ኢያሱ (22፡ 9-12)፡ ሁለቱ ነገዶች እና ግማሹ ነገድ ቤታቸዉ እንደ ተጓዙ በመቆም ትልቅ የድንጋይ መሰዊያ ሰሩ (ቁጥር 10) ፤ በዮርዳኖስ ምዕራብ በኩል ላይ ያሉ እስራኤላዊንያን ስለ መሰዊያዉ በሰሙ ጊዜ የምስራቅ ነገዶች ለምን ይህን አድርገዉ እንደ ነበር ጠየቁ (ቁጥር 11) ፡፡ ዋይርስቤ የዚህን አዲስ መሰዊያ ተፅዕኖ ለምስራቅ ነገዶች “ ትክክለኛ ሀሳብ “ እንደ መፍጠር ይገልፃዋል ፤ በዚህ መረጃ መሰረት እስራኤላዊያን ከምስራቅ ነገዶች ጋር ሄደዉ ለመዋጋት በሴሎ(የእግዚአብሄር መገኘት በነበረበት) ተሰበሰቡ ፡፡

ኢያሱ (22፡ 13-20)፡ እስራኤላዊያን ካህናትን እና አስር የጎሳ መሪዎችን ወደ ምስራቅ ነገዶች ላኩ (ቁጥር 13-15) ፤ በቁጥር (15-16) የምስራቅ ነገዶችን ምንድን እያደሩ እንደ ነበር ጠየቁዓቸው ምክንያቱም በእግዚአብሄር ላይ ኃጢዓት እያደረጉ ስለ ነበር ፡፡ ቁጥር 17 አሁንም እስራኤላዊያን የኃጢጢዓቱ ፀፀትን እንደ ተሸከሙ የሚያመለክተዉን በጎፌር አምላክ የተደረገዉን ኃጢዓት ይጠቅሳል ፤ እስራኤላዊያን እነዚህ ሁለት እና ግማሽ ነገዶች አሁን በማመፅ ከእግዚአብሄር እየተመለሱ እንደ ነበር እየጠየቁዓቸዉ ነበር ፤ በቁጥር 20 መልዕክተኞቹ የምስራቅን ነገዶቹን ስለ አካን ኃጢዓት አሳታወሱዓቸው (ኢያሱ 7) ፡፡

ኢያሱ (22፡ 21-25)፡ የምስራቅ ነገዶች ምላሽ ያልተጠበቀ ነበር ፤ ዋይርስቤ ምላሻቸዉን እንደ “ ትህትና መታዘዝ “ ይገልፃዋል ፡፡ ምንም የተሳሳተ ነገር ባላደረጋችሁ ጊዜ ምንም ነገር አለመደበቃችሁ የሚያስገርም ነው ? የምስራቅ ነገዶች ምንም ደብቀዉ ስላል ነበር በትህትናና በታማኝነት መለሱ ፡፡ በእግዚአብሄር ላይ አምፀዉ ከነበር ወይም ለመስዋዕት መሰዊያ ሰርተዉ ከሆነ የተቀጡ እንዲሆነ ተናገሩ (ቁጥር 22-23) ፤ መሰዊያም ሰርተዉ የነበረው በወንዙ በሁለቱም በኩል የወደፊቱ ትዉልድ የጋራ እምነታቸዉን እንዲያስታዉሱ እንደ ሆን ገለፁ (ቁጥር 24) ፡፡ በተጨማሪም የዮርዳኖስ ወንዝ በሁለቱ መካከል መከፋፈልን በመፍጠሩ በእያንዳንዳቸዉ በኩል የሌለኛዉን እምነት ሊጠይቁ እንደ ሚችሉ አስተዋሉ (ቁጥር 25) ፡፡

ኢያሱ (22፡ 26-29)፡ የምስራቅ ነገዶች (ሮቤል፣ ጋድ እና የምናሴ ግማሹ) መሰዊያዉን “ ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል ከእኛም በኋላ በትዉልዳችንና በትዉልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መስዋዕትና በቁርባን በደኅንነትም መስዋዕታችን እግዚአብሄርን እናመልክ ዘንድ በሚመጣዉ ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻችንን በእግዚአብሄር ዘንድ እድል ፈንታ የላችሁም እንዳይሉ ምስክር ይሆናል “ (ቁጥር 27) ፡፡

ኢያሱ (22፡ 30-34)፡ ዋይርስቤ ይህን እንደ “ አስደሳች ስምነት “ ይገልፀዋል ፤ መሰዊያዉም “ እግዚአብሄር አምላክ እንደ ሆነ በመካከላችን ምስክር ነው “ ብለዉ ሰየሙት ፡፡ በዮርዳኖስ ወንዝ በምዕራብ በኩል ያሉት እስራኤላዊያን ደስ አላቸው በምስራቅም በኩል በሌሎቹ ነገዶች ላይ ለጦርነት አልሄዱም ፡፡ ኮንስታብል ያመለከተው “ ምናልባትም እሳራኤላዊያን እንደማይነሱ “ ምክንያቱም “ እግዚአብሄር ይህን አዝዞ ስላልነበር “ ፤ በእርግጥ “ ሌሎች ሰዎች ስለመኖሩ አይረዱም- ቀድመዉ አንዳንዶች አድርገዉ እንደ ነበረው ….. መሰዊያ የመገንባት ተግባር ከሚያጠነክራቸዉ ይልቅ ለያህዌ ያለን ታማኝነት እና ወገናዊ መተሳሰር በመዳከም የሚመጣ ነው “ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ሰላም እንዲኖራቸዉ በማንኛዉም መንገድ ይሄዳሉ ፤ ሰላም ከንፁህነት የሚመጣ ነው (መዝ 3፡ 17) ፡፡ ሰላም የተሸወደ ወይም ምድር ላይ የተመሰረተ ሊሆን አይችልም ፡፡ ማቴዎስ ሄነሪይ እንደ ተናገረው “ ሰላም እዉነት የሆነዉን ነገር ሁሉ የምሰጠው የከበረ ጌጥ አይነት እንደ ሆነ ነው “ ፡፡

በኢያሩሳሌም ለሰላም ስንፀልይ (መዝሙር 122) በማስመሰል ሊሆን አይችልም ፤ ከመሲሁ ብቻ ሊመጣ ይቻለዋል፡፡

መዝጊያ

ከሰላም ኋላ በምትሄዱ ጊዜ ከእግዚአብሄር የመጣ መሆኑን እና ንፁህ መሆኑን እርግጠኛ ሁኑ ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Joshua–Esther (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2003), p. 76.

  2. Wiersbe, p. 77.

  3. Wiersbe, p. 79.

  4. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes, p. 90; available online at http://planobiblechapel.org/constable-notes/.

  5. Constable, p. 90.

ጥያቄዎች

  1. ሌዋዊያን ምንም ግዛት ያላገኙት ለምን ነበር ? በዚያ ፋንታ እንደ እርስታቸዉ ምንድን አገኙ ? (ዘኁ 18፡ 20)
  2. በኢያ (22፡ 8) እየተጠቀሱአቸዉ የነበሩት ወንድሞቻቸዉ እነማን ነበሩ ? (ኢያሱ 1፡ 14)
  3. በኢያ (22፡ 10) የሮቤል፣ የጋድ እና የምናሴ ግማሹ ነገድ ለምንድን መሰዊያ ሰሩ (ኢያ 22፡ 26-28) ? በእነርሱስ ላይ ለጦርነት የእስራኤል ልጆች ለምን ተሰበሰቡ ?
  4. የመሰዊያዉን ምስክርነት ለምን ሰየሙት ?
  5. በኢያሱ (21-22) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Joshua 22:30, 33a

“When Phinehas the priest and the community leaders, the heads of Israel’s clans who were with him, heard what the descendants of Reuben, Gad, and Manasseh had to say, they were pleased. . . . The Israelites were pleased with the report, and they praised God.”

ነገዶቹ ወደ ወረሷቸው ከተሞች ከተበተኑ በኋላ፥ የሮቤል ፥ የጋድ እና የምናሴ ነገድ እኩሌታ በከነዓን ምድር ወሰን ላይ መሠዊያ የመስራታቸው ወሬ ተሰማ፡፡ ከበፊት ኃጢያቶች እና ልምምዶች ምክንያት፥ እስራኤላውያን መሠዊያውን የሰሩት በእግዚያብሔር ላይ ክፉ ድርጊት ለማድረግ ነው ብለው አሰቡ፡፡ ይሁን እንጂ፥ ሄደው ከማጥቃታቸው እና ወደ ጦርነት ከመሄዳቸው በፊት፥ ስለ መሠዊያው በይበልጥ ያውቁ ዘንድ ፊንሐስን እና አስር መሪዎችን ላኩ፡፡ መሠዊያውን የሰሩበት ምክንያት የሚመጡት ዘሮቻቸው ከእስራኤል አምላክ ከእግዚያብሔር ጋር ስላላቸው ግንኙነት አንዲያውቁ ሆኖ ተገኝ፡፡ ፊንሐስ እና የማኅበሩ መሪዎች ለእሰራኤላውያን እውነቱን ሲነግሯቸው፥ ደስ ተሰኝተው እግዚየብሔርን አከበሩ፡፡ ማንም ሰው በድጋሚ ከሮቤል፥ ከጋድ እና ከምናሴ ነገድ ጋር ጦርነት ስለመግባት አላወራም፡፡

ከሰዎች ጋር ግንኙነት ሲኖራችሁ፥ ግጭቶችን ትጋፈጣላችሁ፡፡ ይህ የህይወት ክፍል ነው፡፡ ግጭቶች ሲያጋጥሟችሁ፥ በድርጊት ምላሽ ከመስጠታችሁ በፊት ፥ መረዳትን ፈልጉ፡፡ የተጋጫችሁትን ሰው አድምጡ፡፡ ከዚያም ሙሉ ሁኔታውን ከተረዳችሁ በኋላ ውሳኔአችሁን አድርጉ፡፡ በግምት ምንም አታድርጉ፡፡ እስራኤላውያን እንደዛ አድርገው ቢሆን ኖሮ፥ ምክንያት በሌለው ጦርነት ውስጥ ራሳቸውን ያገኙት ነበር፡፡ በህይወታችሁ በይበልጥ መረዳት የሚያስፈልገው ሁኔታ ይኖር ይሆን? ለመረዳት ጊዜ ስትወስዱ ጌታ ነገሩን እንዴት እንደሚሰራ ይደንቃችሁ ይሆናል፡፡

“ካህኑ ፊንሐስና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱ ጋር የነበሩት የእስራኤል አእላፋት አለቆች፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ልጆች የተናገሩትን ቃል በሰሙ ጊዜ ነገሩ እጅግ ደስ አሰኛቸው።. . . .ነገሩም የእስራኤልን ልጆች ደስ አሰኘ፤ የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን አመሰገኑ”

—መጽሐፈ ኢያሱ 22:30, 33ሀ

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መጽሐፈ ምሳሌ 15:1 — “የለዘበች መልስ ቍጣን ትመልሳለች፤ ሸካራ ቃል ግን ቍጣን ታስነሣለች። ”
  • የማቴዎስ ወንጌል 5:9 — “የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና። ”
  • የማቴዎስ ወንጌል 18:15–16 — “ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕልበታሪክ መፅሀፍት፡ ክፍል 11