God Sent the Hornet
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Commander Joshua 23-24 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በኢያሱ ይህ የመጨረሻ ትምህርታችን ነዉ ሚያስደንቅም ነው ፡፡ በኢያሱ መፅሀፍ ዉስጥ በ12 ክፍሎች አልፈናል(አይተናል) ፤ ይህ እንደ ድብድብ ፊልም ይመስላል ወደ መሳፍንትም ጥናታችንም ላይ ይቀጥላል ፡፡ ለኢያሱ መፅሀፍ ያተኮርንበት ቃል አዛዥ የሚል ነው ፡፡ የሚንዴስ ስዕል ለእኛ በአዲስ መሪነት በኢያሱ ስር ሰፈርን በመስበር ከዚያም ወደ ተስፋይቱ ምድር ወደ መጓዝ ትኩረት ያመጣናል ፡፡ በሄዱባቸዉ በሁሉም ዉጊያዎችከእነርሱ ጋር አዛዥ እግዚአብሄር ነበራቸው ፤ በመፅሀፉ መጨረሻ ላይ ለእነርሱ እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረዉን እንደ ቋሚ ማስታወሻነት የመታሰቢያ ድንጋዮችን እንዲገነቡ አበረታታቸዉ ፡፡ በኢያሱ 23 እና 24 ሁለት ንግግሮች አሉ ፤ መጀመሪያ የኢያሱ የስንብት ንግግር ኢያሱ እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረዉን ሲያስታዉሳቸዉ በመስጠት የደረሰዉ ነበር (ኢያሱ 23) ፤ በመሰረቱ ይህ በዘፍጥረት ለአብርሃም የእግዚአብሄርን ተስፋ መፈፀምን ያሳያል ፡፡ ህዝቡ እንዲጠነክሩ እና ለእግዚአብሄር ታዛዥ እንዲሆኑ አበረታቸዉ ምክንያቱም ሁሉም ነገር እግዚአብሄር ተስፋ ገብቶት የነበረዉ ስለ ተፈፀመ (ኢያሱ 23፡ 14) ፡፡ ሁለተኛዉ ንግግር በኢያሱ 24 ላይ ይገኛል ፡፡
ትምህርት
ኢያሱ (24፡ 1-5)፡ ኢያሱ በዚያን ጊዜ የድንኳኑ ማደሪያ እና የእግዚአብሄር መገኘት በነበረበት በሴኬም (ዘፍ 12፡ 6-7) በአንድ ላይ 12ቱን ነገዶች፣ መሪዎችን እና ፈራጆችን አመጣቸው (ቁጥር 1) ፡፡ ኢያሱ እግዚአብሄር በእቅዱ ጣዖት የሚመልኩትን(ታራን እና ናኮር) ተጠቅሞ እንደ ነበር ገለፀ ፤ ከእኛ ዉስጥ ማንኛችንም እግዚአብሄር ሊጠቀምብን ይችላል ፡፡ የመጀመሪያዎቹ አምስት ቁጥሮች ዘፍጥረትን በዘጸዓት 15 በመሸፈን ታሪካቸዉን ይከልሳሉ ፤ ጆርጅሳንታያና “ የቀድሞዉን ማስታወስ የማይችሉ በንስሃዉ ይኮነናሉ “ ብሏል ፤ እንዲሁም ፀሀፊ ኖርማን ኮሳይን ታሪኩን “ እንደ ሰፊ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት “ ይገልፀዋል ፤ በሚያናድድ ሁኔታ የመሳፍንት መፀሀፍ የኃጢዓት ኡደት እና አለመታዘዝ ነው ምክንያቱም ህዝቡ የኢያሱ 24 የመጀመሪያዎቹን አምስት ቁጥሮች አላከበሩም ፡፡
ኢያሱ በእስራኤላዊያን ላይ የእግዚአብሄርን ጣልቃ ገብነት በታራን፣ በኖኮር እና በአብርሃም በኩልእንዲሁም ከኤፍራጠስ ወንዝ አልፎ ወደ ከንዓን ባለዉ ጉዞ በኩል እና በአብርሃም ዘር በኩል ያለዉን መዘርዘር ጀመረ (ቁጥር 2-3) ፡፡ ኢያሱ የታሪኩን ለዉጥ (እድገት) በይስሐቅ፣ በያዕቆብ እና በኤሳዉ በኩል አስቀመጠ (ቁጥር 3-4) ፤ ቁጥር 4-5 ወደ እስራኤላዊያን ወደ ግብፅ የሚጓዙበት ጊዜ ያካትታል ፤ ኢያሱ ህዝቡን ያዉቁት ስለ ነበረዉ ነገር እየነገራቸዉ ነበር ፤ ታሪካቸዉን ያውቃሉ ነገር ግን ያውቃሉ ማለት ቀምሰዉት የነበረዉን እና ለእነርሱ እግዚአብሄር አድርጎት የነበረዉን ያስታዉሳሉ ማለት አይደለም ፡፡ በአንዳንድ ምክንያቶች “ የመታሰቢያ ድንጋዮቹ “ በልባቸዉ ዉስጥ ሊቀመጥ አይችልም ፤ የኢያሱ የመጨረሻዉ መልዕክት የነበረው “ ሁሉንም እንዳትረሱ ! “ ምን እንደ ሚመጣ ኢያሱ ቀድሞ ስለ ሚያውቅ
ሴኬም በመሆን የመጨረሻ ንግግሩን ለማድረስ አሰውፈላጊ ነበር ፤ ክላረሲይ ማክአርቲኒይ የሴኬምን አስፈላጊነት “ በመጀመሪያ እና በመጨረሻ በተዋጋችሁበት በነፃነት በአንድ ላይ በመሰብሰብ ምልክትን የምታስቀምጡ ከሆን ሴኬም ለእስራኤል ምን እንደሆነች አታዉቁም ማለት ነዉ “ በሚል መንገድ ገልፆታል ፡፡ ለእስራኤል ሴኬም የእግዚአብሄር ትንቢታዊ ቃል ነበረችይህም ክስተት በዚያ ትንቢት እየተጓዙ እንደ ነበር ያሳያል ፤ እግዚአብሄር በተናገረን ጊዜ ሁላችንምእነዚህ ክስተቶች አሉን በዚያን ጊዜ ያለንበት ስፍራ “ ሴኬማችን “ ይሆናል ፡፡ ሴኬም ላይ የተሰጠዉ የኢያሱ ቃል በራሳችን ኑሮ ላይ ያሉትን ንብረቶች እንድናስታውስ ያሳስበናል ፡፡
ኢያሱ (24፡ 6-13)፡ ይህ ከዘጸ 12 እስከ ኢያሱ 22 (በትንሽ የታሪካዊ የኃላ መስመር) የሚሸፍን ሌላ ታሪካዊ መዝገብ ይሰጣል ፡፡ ኢያሱ የሚሰሙትን(አብዛኞቹ ሲከሰት በዚያ አልነበሩም) ቀይ ባህርን በመክፈል ከግብፃዊያን ጦር እስራኤላዊያንን ስለ እግዚአብሄር ማዳን አሳሰባቸው(አስታወሳቸው) (ቁጥር 6-7) ፤ በእነዚህ ቁጥሮች ኢያሱ ለሰዎስተኛ ወገን የሚሰሙትን በማካተት ቀምሰዉት በነበረው አበራላቸው ፤ በቁጥር 8 ኢያሱ ወደ ተስፋይቱ ምድር የሚገቡት በዚያ የነበሩትን ሰዎች እንዲያጠፉም እንደ ነበር አሳሰባቸው ፤ ኢያሱ አሞራዊያንን፣ የሞዓብ ንጉስ ባላቅ እና ኢያሪኮን ከሌሎች የህዝብ ጋር አካትቷቸዋል (ቁጥር 9-11) ፡፡
ቁጥር 12 እግዚአብሄር በፊታቸዉ “ተርብ “ እንደ ላከባቸዉ ይናገራል (ዘጸ 23፡ 28) ፤ በእስራኤላዊያን ፊት የእግዚአብሄር መሄድ በኢያሱ ቋሚ ጭብጥ ነው ፡፡ ተርቦቹ የሚያመለክታቸዉ አማራጮች እነዚህ ናቸው፡ “ 1) ምልክቱ ንብ ወይም ተርብ የነበረዉን የግብፁን ፈርዖንን ለመወከል፣ 2) የእግዚአብሄር አስፈሪነት ምልክት ወይም አስፈሪነትን በከነዓናዊያን መካከል፣ 3) ትክክለኛዉን ተርብ “ ፤ (ኢያ 2፡ 9-11፣ 24፣ 5፡ 1፣ 6፡ 27) ፡፡ የትኛዉም አማራጭ ትክክል ይሁን እግዚአብሄር በግልፅ ለእስራኤል መንገድ እያዘጋጀ ነበር ፡፡
መልሱ በዘጸዓት 23 መልሱ የሚገኝ ነው፡
- ዘጸ (23፡ 28)፡ “ በፊትህ ተርብ እሰድዳለሁ ኤዊያዊዉንም ከነዓናዊዉንም ኬጢያዊዉንም ከፍትህ አባርራለሁ “ ፡፡
ዘጸ (23፡ 20-23)፡ “ በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልዓክን በፊትህ እሰድዳለሁ ፡፡ በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢዓት ብትሰሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት ፡፡ አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ ፡፡ መልዓኬ በፊትህ ይሄዳልና ወደ አሞራዉያንም ወደ ኬጢያዉያንም ወደ ፌርዛዉያንም ወደ ከነዓናዉያንም ወደ ኤዊያዉያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ያገባሃል ፤ እኔም አጠፋቸዋለሁ “ ፡፡
የዕብራዊያን ቃል “ተርብ” ለሚለው ለቅድመ ክርስቶስ እንደ ማሳያ ሊሆን ይችላል ፤ ኢያ (5፡ 13-15) ኢያሱ “ እንደ እግዚአብሄር ጦር አዛዥ ሆኖ “ የሚመጣዉን አንድ ሰዉ እየደረሰ እንደሆነ መዝግቧል ፡፡ ሙሴ እግዚአብሄር ስለ ሚልካቸዉ ተርቦች አዉርቷል (ዘዳ 7፡ 17-22) ፤ ሂደቱ እግዚአብሄር ቆይቶ ተርብ ብሎ የጠራዉን ምናልባትም ቅድመ ክርስቶስን የላከዉን መለዓክት ያሳያል ፡፡
ይህ መልዕክት በጣም አስፈላጊ ነበር ምክንያቱም ኢያሱ የእስራኤል ሰዎች እግዚአብሄር እንጂ ኢያሱም እንኳን ከእነርሱ ጋር እንደ ማይሆን እንዲረዱ ፈለገ ! የእግዚአብሄር ጦር አዛዥ - ተርቡ - ከእነርሱ ጋር ይሆናል ፡፡
ይህ በሪቫይቭ ት/ቤት በመፅሀፍት ጥናታችን ቀስ በማለት በጥልቀት እንድንሄድ ያሳስበናል ፤ በጥልቀት በምንሄድ ጊዜ በብዙ የተዘጋጀን እንሆናለን ፤ በዚህ ጊዜ ኢያሱ አንድ ጭብት ለማድረግ(ለመስራት) ሁሉንም የተለያዩ መልዕክቶች እያቀረበ ነበር - እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር መሆኑን ፡፡
ኢያሱ (24፡ 15)፡ ይህ በግድግዳዎች እና በልብስ ቁራጮች ላይ የምናየው እና ከኢያሱ የምንወስደዉ ጥቅስ ነው፡ “ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሄርን እናመልካለን “ ፤ የቑጥሩ ያ ክፍል ኢያሱ ህዝቡን ማንን መከተል እንዳለባቸዉ - ያህዌን ወይስ የቀድሞ አባቶቻቸዉን ጣዖት አምላኮችን እንዲወስኑ ከነገራቸዉ በኋላ ይመጣል ፤ ከዚያም ኢያሱ ጥያቄዉን ራሱ መለሰው …. እሱና ቤተሰቡ ያሕዌን እንደ መረጡ ፡፡
ኢያሱ (24፡ 26-33)፡ ኢያሱ እግዚአብሄር አድርጎት የነበረዉን ለማስታወስ የመታሰቢያ ድንጋዮች አስቀመጠ (ቁጥር 26-27) ፤ ከዚያም እስራኤላዊያንን በመላክ በ110 አመቱ ሞተ (ቁጥር 28-29) ፡፡ የዮሴፍ አካል ከግብፅ መጥቷል (ቁጥር 32) እንዲሁም የአሮን ልጅ አልዓዛር ሞተ (ቁጥር 33) ፤ ሁሉም መሪዎች አሁን ሞተዋል እናም ማንም ስፍራዉን(ስልጣኑን) ለመቀበል የቀረ የለም ፡፡
መዝጊያ
ጠንቃቆች ካልሆንን ቤተ ክርስቲያን ሌሎች አስፈላጊ ያልሆኑትን እነዚህን ሁሉ ነገሮች መልዕክቱ ላይ ትጨምራለች ፤ በኢያሱ ህይወት መጨረሻ ላይ አንድ ነገር እንዲያደርጉ ፈለገ……አምላካቸዉን እግዚአብሄርን እንዲያመልኩ ፡፡ ካለዉ ዉጪ ለኢያሱ ምንም ነገር አስፈላጊ አልነበረም እናም ለእስራኤላዊያን የመጨረሻ ቃሉ ይህ መልዕክት ነበር ፡፡
Clarence Macartney, The Greatest Texts of the Bible (Nashville: Abingdon,1947), pp. 74–75; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes: Joshua, p. 94.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 301.
ጥያቄዎች
-
በኢያሱ (23፡ 1) እንደ ተገለፀዉ እስራኤል ከሁሉም ጠላቶቿ ረፍትን ለምን ተቀብላ ነበር ? (ኢያ 1፡ 13፣ 21፡ 44፣ 22፡ 4)
-
ኢያሱ እግዚአብሄር ለእነርሱ አድርጎት የነበረዉን አይተዉ እንደ ነበር በተናገረ ጊዜ እስራኤላዊያንን ስለ ምን እያስታወሳቸዉ(እያሳሰባቸው) ነበር ? በሁኔታዎቻችሁ(በችግሮቻችሁ) ይህ እንዴት ያበረታታችኋል ?
-
የኢያሱ ስኬት ሚስጥሩ ምንድን ነበር ? (ኢያ 23፡ 6፣ 14)
-
በሴኬም የኢያሱ “የመጨረሻ ንግግር “ መስጠቱ አስፈላጊነቱ ምን ነበር ? (ዘፍ 12፡ 6-7፣ 33፡ 18-20)
-
በኢያሱ 24 እስራኤላዊያን ፍላጎታቸዉ እግዚአብሄርን ማገልገል እንደ ሆነ ምን ያክል ጊዜ አረጋገጡ (ኢያ 24፡ 16-18፣ 21፣ 24) ? ከህዝቡ በዚህ ማረጋገጫ መሰረት ኢያሱ ምንድን አደረገ ? እግዚአብሄርን ማገልገል ማለት ምን ማለት ነው ?
-
በኢያሱ (23-24) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Joshua 24:14, 15b
“Therefore, fear the Lord and worship Him in sincerity and truth. Get rid of the gods your fathers worshiped beyond the Euphrates River and in Egypt, and worship Yahweh . . . As for me and my family we will worship Yahweh.”
ኢያሱ ከመሞቱ በፊት በአመታት ውስጥ የእግዚያብሔርን ብርቱ ታማኝነት በማስታወስ ለእስራኤላውያን ተናገራቸው፡፡ ዳግመኛ፥ እንዴት እንደሚኖሩ በመናገር አበረታታቸው— እግዚያብሔርን ፍሩት፥ በቅንነት እና በእውነት አምልኩት፥ሌሎች አማልክትን አስወግዱ፡፡ በአጭሩ፥ ያህዌን ታዘዙ፡፡ ከዚያም ኢያሱ የመዳን አለት የሆነውን ጌታ እግዚያብሔርን እንዳይክዱት ምስክር ይሆን ዘንድ ትልቅ ድንጋይ ወስዶ ከአድባር ዛፍ ስር አስቀመጠ፡፡ ኢያሱ እንዲህ እያለ ነበር፥ "እባካችሁ አይኖቻችሁን በአለቱ ላይ አድርጋችሁ ቆዩ፡፡"
ወደ አንድ ቤት ሄዳችሁ ፥ " እኔ እና ቤቴ ግን እግዚያብሔርን እናመልካለን " የሚል ጽሑፍ ያለው የተቀረፀ ጌጥ አይታችሁ ታውቃላችሁ? ወይም እነዚህ ቃላት በቤታችሁ ስላሉ በዕየዕለቱ ታልፏቸው ይሆናል፡፡ እንደ ቤተሰብ ጌታን ማምለክ ማለት ለእናንተ ምን ማለት ነው? ዛሬ፥ ጌታን ጠይቁት፤ " ጌታን በእውነት እና በመንፈስ ከማምለክ ርቄ ይሆንን? አንዱ እና ብቸኛው የመዳን ዓለት ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ ሌሎች አማልክቶች አሉኝ? እየታዘዝኩህ ነው? " መንፈስ ማናቸውንም ነገር ወደ አይምሮአችሁ ካመጣ ፥ ከእርሱ ተመለሱ እና አይናቸሁን ኢየሱስ ላይ አድርጉ፡፡ ጌታ ኢየሱስን ዳግመኛ በማየት በፍጹም ልባችሁ፣ነፍሳችሁ፣ ሀሳባችሁ፣ እና ኃይላችሁ ፈልጉት፡፡ ይወዳችኋል፥ እርሱ ብቻ ነው የሚያስፈልጋችሁ!
“አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ፥ በፍጹምም በእውነተኛም ልብ አምልኩት፤ አባቶቻችሁም በወንዝ ማዶ በግብፅም ውስጥ ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፥ እግዚአብሔርንም አምልኩ። የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።”
—መጽሐፈ ኢያሱ 24:14, 15ለ
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መጽሐፈ ምሳሌ 4:25–27 — “ዓይኖችህ አቅንተው ይዩ፥ ሽፋሽፍቶችህም በቀጥታ ይመልከቱ።የእግርህን መንገድ አቅና፥ አካሄድህም ሁሉ ይጽና።ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤ እግርህንም ከክፉ መልስ። ”
- የሉቃስ ወንጌል 10:27 — “እርሱም መልሶ፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።”
- 1ኛ የጴጥሮስ 1:22 — “ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ። ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕልበታሪክ መፅሀፍት፡ ክፍል 12
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።