The Cycle of Disobedience
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Judge Judges 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የመጀመሪያዉን የታሪክ መፅሀፍ ኢያሱን ሸፍነናል አሁን ወደ መሳፍንት እተጓዝን ነው ፤ የመጀመሪያዉ የመሳፍንት ኢያሱ ሞቶ እንደ ነበር ይገልፃል ስለዚህም እግዚአብሄር ለእስራኤላዊያን አዲስ ወቅት ያቀርባል ፡፡ የመሳፍንት መፅሀፍ ትንሽ መዘበራረቅን እንዲሰማ ያደርጋል ፡፡ የሜንዲይ አዲስ ስዕል በእባብ እና በራስ ቅል ትንሽ የጨለመ ነው ነገር ግን በመሳፍንት መፅሀፍ የምናወራዉ ያን ነው ፤ መሳፍንት ስለ ብዙ መሪዎች ወይም መሳፍንቶች ነው ፡፡
የመፅሀፉ ፀሀፊ ሳሙኤል እንደሆነ ይታመናል (1ሳሙ 10፡ 25) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ የእስራእል መሳፍንት “ ቅሬታዎችን ለመቀበል የፍርድ ወንበርን የያዙ ወይም ህጋዊ ዉሳኔ የሚያደርጉ እንዳልነበሩ (ከድቦራ በስተቀር) ፤ ይልቁንስ ከዉጪ ከሚመጡባቸዉ አስፈሪዎች እና አስጨናቂዎች እስራኤልን ነፃ የሚያወጡ እንደ ነበሩ ተናግሯል “፡፡ መፅሀፉ ከዳዊት ዘመን በፊት ከሳዖል የንጉስነት ሹመት በኋላ የተፃፈ ነበር ፤ በሚያስደንቅ ሁኔታ መሳፍንት ለሁለቱም የመፀሀፍ ቅዱስ መፅሀፍ ወይም እስራኤል በፍርስርስ ዘመን በነበረች ጊዜ መሳፍንት በተቀመጡበት ለ300 አመት ጊዜያት ያክል ማጣቀስ ይችላል ፡፡ የመሳፍንት መፅሀፍ የኢያሱ መፅሀፍ ተከታታይ ነው ፤ በዚህ መፅሀፍ ዉስጥ 15 መሳፍንት የተጠቀሱ ናቸው ፡፡
ቸክ ሲዊንዶል በመሳፍንት ጊዜ በእስራእል ታላቅ የኃይማኖት ክህደት የነበረበትን እነዚህን ምክንያቶች ያስቀምጣል፡
- እጅግ ብዙ ፖለቲካዊ እና ሀይማኖታዊ ብጥብጥ ነበር ምክንያቱም እስራኤላዊያን ሙሉ በሙሉ ይዘዋቸዉ ያልነበሩትን የተስፋይቱን ምድር ለመያዝ ያለሟቋረጥ እየሞከሩ ስለ ነበር ፡፡
የእስራእል ነገድ እርስ በእርሳቸዉ መዋጋት ስለ ጀመሩ ፤ በእርግጥ የምናሴ ነገድ (መሳፍንት 12) እና የቢንያም ነገድ (መሳፍንት 20-21) እየተባረሩ ነበር ፡፡
የኃጢዓት፣ የቅጣት፣ የንስሀ እና የይቅርታ ኡደት እየተካሄደ ነበር ፤ የእግዚአብሄር ሰዎች በጣዖት አምልኮ እና ባለማመን አመፁ ስለዚህም እግዚአብሄር በሌሎች ሰዎች የማስጨነቅን ፍርድ አመጣባቸው ፤ ከዚያም እግዚአብሄር ህዝቡን በንስሃ ወደ እግዚአብሄር መልሰዉ የሚያመጡ ነፃ አዉጪ ወይም መሳፍንት አስነሳላቸው ፤ ይሁን እንጂ በጥቂት ምዕራፍ ዉስጥ ህዝቡ ወደ ኃጢዓት ዉስጥ ተመልሶ ወደቀ ኡደቱም እንደገና ጀመረ ፡፡
ስዕሉ ህዝቡን ሊያድናቸዉ ስለ መጣዉ አንዱ እንጂ ወደ መታዘዝ ስለ ሚቀጠቅጣቸዉ አይደለም ፤ ይህ ስለ ሚመጣዉ አዳኝ ስዕል ነው ፡፡ በእርሷ ስዕል ሜንዲይ ሁላችን በዘፍጥከር ከወደቅነው የእስራኤላዊያንን የኃጢዓት ኡደት ለመወከል የተቀመሰችዉን ፍሬ ተጠቅማለች፣ እባቡ ሁል ጊዜ ኋጢዓት ከኛ ኋላ እንደ ሚመጣ ይወክላል እራሱ ደግሞ ሞትን ይወክላል ፤ እያንዳንዱ የመፅሀፉን ጭብጥ ይደግፋል - እግዚአብሄር ኃጢዓት ሳይቀጣ እንዲሄድ አይፈቅድም ፡፡
የዘፀዓት መፅሀፍ እንዴት እስራኤል የእግዚአብሄር ህዝብ እንደሆኑ እና በምድረበዳ እንደ ተከተሉት ይገልፃል ፤ በኢያሱ መፅኀፍ የተስፋይቱን ምድር እንዲይዙ መራቸዉ መፅሃፉም እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረዉን እንዳይረሱ በኢያሱ የማስጠንቀቂያ ንግግር ይጨርሳል (ኢያሱ 24) ፡፡ በመሳፍንት ደግሞ እግዚአብሄር ህዝቡን ሌሎች አማልክት በመከተላቸው፣ ህጉን ባለመታዘዛቸዉ እና ስርዓት በማጣታቸዉ ይቀጣቸዋል ፡፡
ትምህርት
መሳፍንት (1፡ 1-18)፡ መሪነት ወደ ይሁዳና ስምዖን የተመለሰ ነበር (ቁጥር 1-3) ፤ በቁጥር 4-5 አሁንም እስራኤላዊያን ከተስፋይቱን ምድር የቀረውን ለመያዝ እየሞከሩ ነበር (ኢያ 3፡ 10) ፡፡ አዶኒቤዜቅንም ተከታትለዉ ያዙት የእግሩን እና የእጁን አዉራጣቶች ቆረጡዓቸው በዚህም ሰይፍ ይዞ ሊቆይ ወይም በዉጊያዉ ሊሮጥ አልቻለም ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ ድል የተደረጉትን ጠላቶች አካል የመጉዳት ተግባር በቀድሞ ምንጮች የተመዘገበ እንደሆነ…..እንዲሁም በራሱ በአዶኒቤዜቅንም ተፈፅመዉ የነበሩትም እንደነበር “ ይገልፃል ፤ አዶኒቤዜቅም ከቁስል የተነሳ ሞተ (ቁጥር 6-7) ፡፡ ኢየሩሳሌምን ያዙዓት ነገር ግን ሁሉም አልሞተም ነበር (ቁጥር 8)(ኢያ 15፡ 63) ፤ መሳፍንት ከኢያሱ ማስረጃዎች ዉጪ ሙሉ ያልሆነዉን የኢየሩሳሌምን ስዕል ሰጡ ፤ ከዚያም ይሁዳ በኬብሮን ሰዎስቱን ግዙፎች - ሴሲንን፣ አኪመንንና ተላሚንን ገደላቸው (ቁጥር 10) ፡፡ ካሌብ ጎቶንያል የነበረችዉን ምድር ነፃ ለሚያወጣ እንደ ሽልማት ከሴት ልጁ ጋር ያለዉን ተዳር እንደተጠቀመ ያሳስባል (ቁጥር 11-14) ፤ በደቡብ ምድረበዳ በኩል ያለዉን የምንጩን እጥፍ ክፍል ለመቀበል ጠየቀች (ቁጥር 15-16) ፡፡ ጎቶንያ የመጀመሪያዉ መሳፍንት ሆነ ፤ በቁጥር 17-18 ብዙ ከተሞች ተያዙ ፡፡
መሳፍንት (1፡ 19-34)፡ ተራራማዉን አገር ተቆጣጠሩ ነገር ግን “ የብረት ሰረገሎች “ የነበራቸዉን የሸለቆ አገር የነበሩትን ህዝቦች ማስወጣት አልቻሉም ቑጥር 19) ፤ በእስራኤላዊያን በኩል ላይ በሙሉ እምነት አለመኖር ምክንያት ወደቁ ፡፡ ኢያ (1፡ 3) የሚለው እግዚአብሄር ህዝቦቹን ያስወጣቸዋል ፤ በኢያ (1፡ 3-7) እግዚአብሄር የተናገረው ወደ ሚሄዱበት ሁሉም ቦታ ከእነርሱ ጋር እንደ ሚሆን እና ምድሪቱን እንደ ሚሰጣቸዉ ነው ፡፡ ዉድቀት ለይሁዳ አልሆነም ፤ አብዛኞቹ ነገዶች ወድቀዋል፡ ቢኒያም (ቁጥር 21)፣ ምናሴ (ቁጥር 27)፣ ኤፍሬም (ቁጥር 29)፣ ዛብሎን (ቁጥር 30)፣ አሴር (ቁጥር 31)፣ ንፍታሌም (ቁጥር 33) እና ዳን (ቁጥር 34) ፤ እነዚህ ነገዶች ወድቀዋል ምክንያቱም በእግዚአብሄር ስላልታመኑ ፡፡ የምድሪቱን ነዋሪዎች ሙሉ ለሙሉ እንዲያጠፉ ተነግሯቸዉ ነበር እምነታቸዉም ከእግዚአብሄር የሚስብ አይሆንም ወደቁ እንጂ (ዘዳ 20፡ 16-18) ፡፡ በሙሉ ልባቸዉ ባልታዘዙ ጊዜ ዘዳ (20፡ 18) ወደ እዉነት መጥቷል (ኢያ 6፡ 17፣ 11፡ 14፣ መሳ 2፡ 11-12) ፡፡
መደምደሚያ
በመሳ (2፡ 1-4) የእግዚአብሄር መለዓክ (ኢየሱስ ክርስቶስ) በመምጣት ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ኪዳን እንዳያደርጉ ህዝቡን ነገራቸው ፤ እስራኤላዊያንን ካለመታዘዝ እና ከአመፅ ኡደት ለማዳን በቂ አልነበረም (መሳ 2፡ 16) ፤ ያም ለዚህ ጥናት ወደ ጥናታችን ይመራናል - መሳፍንት ወደ ሚለው ፡፡ በመሳፍንት መፅሀፍ እነዚህ እግዚአብሄር የቀባቸዉ መሳፍንቶች ወደ መሳፍንት(ዳኛው) ያመለክታሉ (ይመራሉ) ፡፡
የዳኛችን ጥቅም በቆላስይስ (1፡ 13-14) ይገኛል፡ “ እርሱ ከጨለማ ስልጣን አዳነን ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢዓትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት አፈለሰን “ ፡፡
ከኃጢዓት ኡደት ለመዉጣት ከፈለጋችሁ ወደ ዳኛዉ ተመልከቱ - ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 309.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes: Judges, p. 3; available online at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/judges.pdf.
Chuck Swindoll, Judges: Why Was Judges So Important? Available online at https://www.insight.org/resources/bible/the-historical-books/judges.
Nelson’s Commentary, p. 306.
ጥያቄዎች
-
ኢያሱ ከሞተ በኋላ ከከነዓናዊያን ጋር ለመዋጋት መጀመሪያ ይሁዳ መሄድ እንዳለበት እግዚአብሄርን ለምን እንደ ተናገረ ምን ታስባላችሁ ? (ዘፍ 49፡ 8-9፣ ራዕ 5፡ 5)
-
የካሌብን ልጅ አክሳን መሬትን ስለ መሰጠት ካሌብን ለመጠየቅ ከማን ጠየቀች ? ለመዋጋት እርሱን ማን ጠየቀው ? የካሌብ እንዴት መለሰ ?
-
በመሳፍንት 2 የእስራኤል ሰዎች ከጌታ መለዓክ ከሰሙ በኋላ ለምን አለቀሱ ? ይህን ቃል ከሰሙ በኋላ ምን አደረጉ ?
-
ከኢያሱ በኋላ የአዲሱ ትዉልድ ጥቂት ኃጢዓቶች ምን ነበሩ ?
-
በእስራኤላዊያን የአመፅ ጊዜ እንኳን ለእነርሱ እግዚአብሄር እንዴት አድርጎ ርህራሄዉን አሳያቸው ? ከምድሪቱ ወጥተዉ ባልነበሩት አህዛቦች ላይ አላማዉ ምን ነበር ?
-
በመሳፍንት 1-2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Judges 2:18
“Whenever the LORD raised up a judge for the Israelites, the LORD was with him and saved the people form the power of their enemies while the judge was still alive.”
ምንም እንኳ እያሱ ሌላ አማልክቶች እንዳይኖሩና እግዚያብሔር ብቻ እንዲመለክ ቢያሰጠነቅቃ ቸዉም ፤ እስራኤላዉያን አልሰሙም ነበር ፡፡ የአባቶቻቸዉን አምላክ በመተዉ በእግዚአብሄር ፊት ክፉ የሆነዉን በማድረግ ባዖልንና ሌሎች አማልዕክቶችን አመለኩ ፡፡ እግዚያብሔርን ባለመታዘዝ ኖሩ ፤ አይኖቻቸውንም በእርሱ ላይ አላደረጉም ፡፡ በዚህም ምክንያት በጦርነት ተሸነፉ ፤ ራሳቸውንም ለውድቀት ዳረጉ ፡፡ ሆኖም ግን ሀጥያት ቢሰሩም ፤እግዚያብሔር ህዝቡን ከጠላቶቻቸው ይታደጉ ዘንድ መሳፍንትን አስነሣላቸው ፡፡ እግዚያብሔር ከጨለማ አዳናቸው ፡፡
በተመሳሳይ መንገድ እግዚያብሔር አባት የአለምን ጭንቀትና ሀጥያት አይቶ ፤ አንተን ያድን ዘንድ ልጁን ኢየሱስን ላከው ፡፡ ኢየሱስ አንተን ከጨለማ እንድሁም ከሀጥያት ባርነት ሊያድን መጥቷል ፡፡ እርሱ ህይወትንና ተስፋን ሊሰትህ መጥቷል ፤ በጭንቅ ውስጥ ሆነህ ሳለ ፡፡ ወደ ኢየሱስ ትመለሳለህ ደግሞስ እንድያድንህ ትፈቅዳለህ ? ወይስ በረስህ ጥንካሬ ፡ ጥበብ ትደገፋለህ እንድሁም በራስህ ሀይል ልታደርገው ትሞክራለህ ፡፡ ጓደኛዬ ኢየሱስ እንድያግዝህ ፍቀድለት ፡፡ ዛሬ እመንና የእርሱን ፍቅር ፀጋና ሀይል ተቀበል ፡፡ እርሱም ይገኝልሃል ምክንያቱም ስለሚወድህ ፡፡
“ እግዚያብሔርም መሳፍንትን ባስነሣላቸው ጊዜ እግዚአብሔር ከመስፍኑ ጋር ነበረ እግዚያብሔረም ስለሚገፉአቸውና ስለሚያስጨንቋቸው በጩኸታቸው ያዝን ነበርና በመስፍኑ ሁሉ ከጠላቶቻቸው እጅ አዳናቸው ፡፡”
- መሳፍንት 2 ፡ 18
ተጨማሪ ጥቅስ
- 1ኛ ቆሮንቶስ 10 ፡ 13 – “ ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው ፤ ትታገሱም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውቻዉን ደግሞ ያደርግላችኋል ፡፡ “
- ቆላስያስ 1 ፡ 13-14 – “ እርሱ ከጨለማ ስልጣን አዳነን ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢኣትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት አፈለሰን ፡፡ “
- 1ኛ ተሰሎንቄ 1 ፡ 10 – “ እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ ከሙታንም ያስነሳውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቁጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ ፡
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።