Historical Books Judges

Facing God's Tests

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Judge Judges 3-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 213 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ በመሳፍንት 3-4 ላይ እንመለከታለን እንዲሁም እስራኤላዊያን ፈተናዎቹን እንዴት እንዳለፉ እንመለከታለን ፡፡ እንዴት አድርገዉ የኢያሱን መሪነት አልተከተሉም ?

ትምህርት

መሳፍንት (3፡ 1-4)፡ ቁጥር 1 ለእኛ አድስ ነገር የሚያመጣ ይመስላል ፤ ኢያሱ ሁሉንም ምድር እንዲይዙ ነግሯቸዉ ነበር ነገር ግን መሳ (3፡ 1) እግዚአብሄር ለአንዳንድ ህዝቦች እስራኤልን እንዲፈትኑ እንደፈቀደላቸዉ ያወራል ፡፡ በዚህ ፈተና እስራኤል እንዴት እንዳደረገ እናያለን ፡፡ የእግዚአብሄር ደረጃ በተለያዬ መስፈርት እኛ ከምንረዳዉ በላይ እንደሆነ አስታዉሉ ፤ ይህ የእስራኤልን ትንሹን ትዉልድ በጦርነት እንዲዋጉ ያስተምራል (ቁጥር 2) ፡፡ እነዚህ ወጣት ትዉልዶች ከዚህ በፊት ጦርነት ለምደዉ አያዉቁም ነበር ስለዚህም ይህ እዉነተኛ ማረጋገጫ ሰጥቷል ፡፡ ለስላሶች ስለ ነበሩ ጠንኳሮች ለማድረግ እግዚአብሄር አስፈለጋቸው ፡፡

በጣም የእዉነት ማረጋገጫ ስለ ሚያስፈልገን እናስብ ፤ ዛሬ በምሰራበት ስፍራ ለመቆም ዋጋ ያስከፈለንን እረስተነዋል ?

ከፍልስጤማዊያን ክፍሎች፣ ከነዓናዊያን፣ ሲዶናዉያንም እና ኤዊያዉያንየዚህ ፈተና እንደ አካል ቀርተዉ ነበር (ቁጥር 3-4) ፤ አሁንም እግዚአብሄር እኛን ይፈትናል ?

  • ዘጸ (13፡ 17-18) እግዚአብሄር እስራኤላዊያን ቅርብ በነበረዉ በፍልስጤማዊያን መንገድ አልመራቸዉም በዚህም ምክንያት ሀሳበቻዉ በመቀየሩ ወደ ግብፅ ለመመለስ መፈለጋቸዉን ይናገራል፡፡

ዘዳ (8፡ 1-2) በእግዚአብሄር ይታመኑ እንደ ሆነ ለማየት የምድረበዳ ጉዞዉን እንደ ፈተና ይገልፀዋል ፡፡

2ቆሮ (13፡ 5)፡ “ በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ ፤ ራሳችሁን ፈትኑ ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ዉስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታዉቁምን ? “

ኢያሱ (3፡ 5-8)፡ እነዚህን ህዝቦች ከማስወገድ ይልቅ እስራኤላዊያን በእነርሱ መካከል መኖርን መረጡ (ቁጥር 4) ፡፡ የጣዖት አምላኪ ሴት ልጆችን አገቡ የራሳቸዉን ሴት ልጆች ደግሞ ለጣዖት አምላኪ ወንድ ልጆች አጋቡ በተጫማሪም የአምላክ የለሽ አምላኮቻቸዉን አመለኩ (ቁጥር 5-6) ፡፡ በተለይም ከከነዓናዊያን እና ከሌሎች አምላክ የለሽ ቡድኖች ጋር ተጋቡ ፤ ቤተሰቦቻቸዉን በመደባለቅ በሌሎች አምላኮች አምልኮ ላይ ተሳተፉ ፡፡ በትዳራቸዉ አንድ መሆን ከራሳቸዉ እምነት ዉጪ በማግባት አመቻመቹ ፡፡ ከዝምድና ወደ ማመቻመች ከዚያም ወደ ጣዖት ከዚያም ወደ ምርኮነት ተጓዙ ፤ ትንሽ ነገር እንዳደረጉ ቢመስላቸዉም “ በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር ነበር “ ፤ ባዖሊም እና አስታሮትን ማምለክ በመጀመር በጣዖት ጨረሱ (ቁጥር 7) ፤ በዚህ ኃጢዓታቸዉ ምክንያት እግዚአብሄር በመበሳጨቱ ለመስጴጦምያ ንጉስ ለባርነት ሰጣቸው (ቁጥር 8) ፡፡

እግዚአብሄር ለምን ፍትህ ፈለገ ? አንዳንድ ሰዎች ይህን በመመልከት እሚወዳቸዉን እግዚአብሄር በፍቅር መቅጣት እንዴት እንደ ሚችል ያደንቃሉ ፤ ይህ በጊዜ ላይ የነበረ የህብረት (የህዝብ) ኃጢዓት ነበር ፤ አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ የተፈጠረ አንድ ኃጢዓት አልነበረም ፡፡ ዳኛዉ ፍትህ የሚያመጣዉ አንዱ እንደ ሆነ እንረዳለን ፍትህ ደግሞ ነፃነትን ታመጣለች ፡፡ በኃጢዓት ለመቀጠል ብንፈቅድ እንኳን እግዚአብሄር በጣም ይወደናል ፤ እግዚአብሄር የተበሳቸ ሊሆን እና መሆን ወደ ሚገባን ስፍራ እንድንመለስ ሊቀጣን ይችላል በፍፁምም የፍቅሩን ትንሽ መጠን አይቀንስም ! እግዚአብሄር በፍፁም ከፍትህ ሊመለስ (ሊተዉ) አይችልም ፡፡ ኃጢዓት ከትክክል መስፈረት ዉጪ ያወጣል ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ያን ትክከል መስፈረት መለስ ያመጣል ፤ ለምን ? ምክንያቱም ስለሚወደን - አንዳንድ ጊዜ እንኳን በጠንካራ ፍቅር ማለፍ የሚያስፈልግ ነው ፡፡

መሳፍንት (3፡ 9-11)፡ የእስራኤል ሰዎችም ወደ እግዚአብሄር ጮኹ እግዚአብሄርም ነፃ አዉጪ የካሌብን ታናሽ ወንድም ልጅ ጎቶንያን አስነሳላቸው (ቁጥር 9) ፡፡ ገቶንያን እንደ ሰዉ ነፃ አዉጪ አልነበረም እግዚአብሄር ነበር ነፃ አዉጪዉ ፤ የእግዚአብሄር መንፈስም በጎቶንያን ላይ መጣበት የእስራኤልም መሳፍንት ሆነ ከመስጴጦምያ ጋር ለጦርነት ወጣ (ቁጥር 10) ፤ የእግዚአብሄር መንፈስ ያደረገዉን እንዲያደርግ ጎቶንያን አበረታው ፡፡ ለስምንት አመታት በምርኮ ነበሩ (ቁጥር 8) ከዚያም ለቀጣዮቹ 40 አመታት በሰላም ይጓዛሉ (ቁጥር 11) ፡፡

መሳፍንት (3፡ 12-31)፡ እንደ ገና እስራኤላዊያን ኃጢዓት አደረጉ (ቁጥር 12) ለ18 አመታትም እግዚአብሄር በሞአብ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው (ቁጥር 13-14) ፤ አሁንም እንደ ገና ህዝቡ ወደ እግዚአብሄር ጮኹ እንደ ቀጣይ ፈራጅም ናዖድን አስነሳላቸው ፡፡ ናዖድ የሞዓብን ንጉስ በመግደል የእስራኤል ሰዎችን አስለቀቀ ፤ ከዚያም እስራኤል 80 አመታት የሰላም ነበራት (ቁጥር 30) ፤ ከዚያም ሰሜጋር ፈራጅ ሆነ ፍልስጤማዊያንን በመምታትም እስራኤልን ነፃ አወጣ (ቁጥር 31) ፡፡

ነፃ አዉጪን ባሰብን ጊዜ (የዘጸዓት ቃላችንን) ሁል ጊዜ ስለ ኢየሱስ እናስባለን ፡፡ እነዚህ ፈራጆች (መሳፍንቶች) ነፃ አዊጪዓችን ሆኖ የመጣዉን የክርስቶስን ስዕል ይሰጣሉ ፡፡

መሳፍንት (4፡ 1-10)፡ ሂደቱ ቀጠለ ፤ እስራኤል ኃጢዓት አደረገ እግዚአብሄርም ለከነዓን ንጉስ ሰጣቸው (ቁጥር 1-2) ፡፡ እንደ ገና እስራኤል 900 የብረት ሰረገሎች ከነበሩት እና ለ20 አመታት አስጨንቆአቸዉ ከነበረዉ ከንጉሶ ጦር አዛዥ ከሲሳር ነፃ ስለ መዉጣት ጮኹ (ቁጥር 3) ፤ እግዚአብሄርም የእርሱ 4 ፈራጅ በማድረግ የእግዚአብሄርን ፍቃድ በመለየት ለሎሎች መናገር የምትችለዉን ኒቢይ ድቦራን አስነሳ (ቁጥር 4) ፡፡ እስራኤላዊያን ለፍርድ ወደ እርሷ ይመጣሉ (ቁጥር 5) ፤ 10,000 እስራኤላዊያን ወታደሮችን ወደ ታቦር ተራራ እንዲወስድ ባርቅን አዘዘችው (ቁጥር 6) ፤ እግዚአብሄርም የከነዓናዊያንን አዛዥን ሲሳርን ለእርሱ እንደ ሚሰጠው ተስፋ ሰጥቶታል (ቁጥር 7) ፡፡ ባርቅ ድቦራ ከእግዚአብሄር እየሰማች እንደ ነበር ያውቃል ስለ ነበር አብራዉ የምትሄድ ከሆነ ለመሄድ ተስማማ(ቁጥር 8) ፤ ድቦራ ለመሄድ ተስማማች ነገር ግን ክብር እንደ ማያገኝ ባርቅን ነገረችዉ ምክንያቱም እግዚአብሄር ሲሳርን ለመግደል ሴት ስለ ሚጠቀም (ቁጥር 9) ፡፡ ባርቅ እና ድቦራ ከንፍታሌም እና ከዛብሎን ነገድ የሲሳርን ጦር ለመግጠም ለማለማመድ 10,000 ወንዶችን ወሰዱ (ቁጥር 10) ፡፡

መሳፍንት (4፡ 11-24)፡ ከሲሳር ጋር ለመዋጋት ወደ ጦርነት ሄዱ በጭቃ ምክንያት የሲሳርን የብረት ሰረገሎችን ለማቆም እግዚአብሄር በደረቅ ወቅት ዝናብን ላከ (መሳ 5፡ 4) ፤ የሲሳር ጠቅላላ ጦርም በሰይፍ ተቆረጡ ከጦርነቱ ሸሽቶ ከነበረዉ ከሲሳር በስተቀር የተረፈ አልነበረም ፡፡ ሲሳር በሄቤር ድንኳን ተደበቀ ፤ ሲሳርም በተኛ ጊዜ የሄበር ሚስት ኢያኤል የድንኳኑን ካስማ በጆረግንዱ ላይ ቸነከረችበት (አጠለቀችበት) ፤ ሲሳርም በሞተ ጊዜ በሰዎስቱ ሰዎች ድርጊት በኩል - በባርቅ፣ በድቦራና በኢያኤል እስራኤል ነፃ ሆነች ፡፡ ከእነርሱ ማንም ድርጊት አልወሰዱም ምክንያቱም ክብር ስለፈለጉ ፤ ባርቅ በሴት መሪነት ስር እንደ ሚያገለግል አላሰበም ወይም ክብርን አልተቀበለም ፡፡ ምንም ክብር ወይም እዉቅና ሳንቀበል እግዚአብሄር እንድናደርግ የሚነግረንን ለማድረግ ፍቃደኛች ነን ?

መደምደሚያ

እግዚአብሄር የሰጣቸዉን ፈተና እንዴት እስራኤላዊያን አለፉ ? ፍቃዱን እንዲያደርጉ እግዚአብሄር ሰዎችን ተጠቅሟል ፤ ኢየሱስ ነፃ አዉጥቶናል ፤ በማህበረሰባችን ዉስጥ እና በህዝቦች ላይ ነፃ አዉጪዎች እንድንሆን እግዚአብሄር እንደ ጠራን አምናለሁ ፡፡

ጥያቄዎች

  1. እግዚአብሄር አህዛቦችን በእስራኤላዊያን መካከል ለምን አላማ እንዲቀሩ አደረገ (ኢያ 23፡ 12-13፣ መሳ 2፡ 21-22፣ 3፡ 1) ? ይህ “ ፈተና “ በማቴ (25፡ 14-30) ካለዉ ምሳሌ ጋር ንፅፅር አለዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? እስካሁን በእግዚአብሄር እንደ ተፈተናች ተሰምቷችሁ ያዉቃል ?
  2. በመሳ (3፡ 5-6) በፍፁም መጥፋት በነበረባቸዉ ህዝቦች መካከል እስራኤላዊያን ኖሩ (ኢያ 11፡ 14-15) ፤ ዉጤቶቹ ምንድን ነበሩ ? የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ባላከበራችሁ ጊዜ ምንድን ዉጤቶችን አያችሁ ? የእነዚህ ዉጤቶች አላማ ምንድን ነው ?
  3. በመሳ (3፡ 9) መሰረት ሄኔታዎቻቸዉ (ችግሮቻቸዉ) እንዴት ተቀየሩ ? ይህን ነፃ አዉጪ ምንድን ኃይለኛ አደረገው (መሳ 3፡ 10) ? በትክክል እስራኤልን ድል የሰጠዉ ማነው ?
  4. በመሳፍንት መፅሀፍ ቀድማችሁ ምንድን ሂደት ወይም ኡደት እያያችሁ ነው ? ፈተናዉ እስካሁን የሄደበትን እንዴት ታዩታላችሁ ? (መሳ 3፡ 1)
  5. በምዕራፍ ሰዎስት እና አራት ስለ ማን መሳፍንቶች ምንድን ተፅፏል ? እርስ በእርሳቸዉ እንዴት ነበር የሚመሳሰሉት ? እንዴት ነበር የሚለያዩት ? ለአላማዉ እንዲያገለግሉት ሲጠራቸዉ እግዚአብሄር የሆነ ጥራት አይቶባቸዋል ? አዎ ከሆነ ጥራቶቹ ምንድን ነበሩ ?
  6. በመሳፍንት (3-4) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Judges 3:9

“The Israelites cried out to the LORD. So, the LORD raised up Othniel son of Kenaz, Caleb’s youngest brother, as a deliverer to save the Israelites.”

ኢያሱ ከህዝቡ ጋር በሌለበት ዘመን ፤ በእስራኤላውን ዘንድ እንድህ ሆነ ፡፡ በመጀመርያ እስራኤላውያን እግዚያብሔር አምላካቸውን በመተው በእርሱ ፊት ክፉ የሆነውን ሌሎች አማልክትን አመለኩ ከዚያም ጣላት ተነስቶ ጨቆናቸው ፡፡ ስለዚህም ወደ እግዚያብሔር ጮኸው አለቀሱ ፤ እግዚአብሔርም ለቅሶቸውን ሰምቶ ራራላቸው ፤ ከጦርነትም ያድኑዋቸው ዘነድ መሳፍንትን አስነሳላቸው ፡፡ ይህም ለብዙ ግዜ ሆነ ፡፡ መሳፍንቱ ስለ ራሳቸው ዝናና ክብር አይጨነቁም ነበር ይልቁንም እስራኤላውያን በነፃነት ይኖሩ ዘንድ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ላስቀመጠው ጥሪ ምላሽ ይሰጡ ነበር እንጅ ፡፡

እግዚያብሔር አብዚቶ ይወድሀል ፡፡ አንተ በሀጥያት ውስጥ እየኖርክ ወይም ከእግዚብሔር ይልቅ የዓለምን ነገር በምትፈልግበት ጊዜ እንኳ ኢየሱስ ከአንተ ጋር ነው ፡፡ ዛሬ አንተ በውድቀት ውስጥ እንዳለህ ከተሰማህ ወደ እግዚአብሔር ጩኽ ኢየሱስም ነፃ እንድያወጣህ ፍቀድ ፡፡ ከዚያም አንተ በነፃነት ወስጥ መኖር ስትጀምር የእግዚአብሔር መንፈስ ሌሎችን ለማዳን አንተን ይጠቀማል መሳፍንቱን በጥንት ጊዜ እንደተጠቀመ ፡፡

“የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብን የታናሽ ወንድሙን የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን አስነሳላቸው ፡፡

- መሳፍንት 3፡ 9

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 31 (32) ፡ 7 –“ አንተ ለእኔ መሸሸግያዬ ነህ ከጣርም ትመብቀኛለህ ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ ፡፡ “
  • መዝሙር 33(34) ፡17 –“ ጻድቃን ጮኹ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው ፡፡ “
  • 1ኛ ቆሮንቶስ 15 ፡ 57 –“ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሳትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ፡፡ “