Historical Books Judges

All About the Name

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Judge Judges 5-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 214 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በስም ምንድን ነው ? እግዚአብሄር ሰዎችን ለሰጣቸዉ ስም በጣም የሚያተኩር ነው ፤ በዚህ ክፍል በጣም በሚያስደንቅ በእስራኤል አራተኛ እና አምስተኛ ፈራጆች ባህሪያት ላይ ስለ ሚያስደንቁ ሁኔታዎች እናወራለን ፡፡ ድቦራ ላይ መመልከት እንቀጥልላለን ከዚያም ጌዴዎንን እናገኛለን ፤በጌዴዉን በኩል የስሙ ትርጉም ላይ እንመለከታለን ….” ኃይለኛ ተዋጊ “ እና “ እግዚአብሄር ያድናል “ ፡፡ ምዕራፍ 5 የድቦራን ዝማሬ ያካትታል ፤ እግዚአብሄር በእናቴ ማህፀን ላይ እጁን ሲያስቀምጥ በማሳየት ይህ የእርሱ ኃይለኛ ጦረኛ መሆኑን መናገሩን የሰጠኝን ራዕይ በሰጠኝ ጊዜ ያን ጊዜ አስታዉሳለሁ ፤ ራዕዩ በጣም ስለጎዳኝ ማልቀስ እና ማዘን ጀመርኩ ፡፡ ስለ ራዕዩ ለአባቴ በነገርኩት ጊዜ በቱርክ አንድ ሰዉ መጥቶ በእናቴ ሆድ ላይ እጁን በማስቀመጥ ስለ ኃይለኛ ተዋጊነት እያለቀሰች እንደ ነበር ተናግሮ የነበረበትን ጊዜ ከእኔ ጋር አጋራኝ ፤ ሳድግም ሁል ጊዜ እንደ ኃይለኛ ተዋጊ ይጠቅሱኛል፡፡ በሚያስጨንቅ መጥፎ ጊዜያት ስለ ተወለዱ ሰዎች ነገር ግን እግዚአብሄር እንዳለ ለሆነ ጊዜ ምልክት አድርጓቸዉ እንደ ነበር እናወራለን ፡፡ ይህንን እያዳመጣችሁ ካላችሁት ከእናንተ ዉስጥ እያንዳንዳችሁ በእግዚአብሄር ምልክት የተደረጋችሁ እና በመንግስቱ የሚያስፈልግ የሆነ ነገር እንድታደርጉ የተጠራችሁ ናችሁ ፡፡

ትምህርት

መሳፍንት (5፡ 1)፡ ድቦራና ባርቅ በዝማሬ ድላቸዉን አከበሩ (ቁጥር 1) ፡፡ በዘጸዓት ማሪያም እና ሙሴ መዝሙር ለመዘመር መሳሪያዎቻቸዉን ማንሳታቸዉን እና እስራኤል የኪዳኑን ታቦት መልሶ በያዘ ጊዜ ንጉስ ዳዊት ማክበሩን እናያለን ፡፡ የድቦራ ስም ቃል በቃል ትርጉሙ “ ንብ “ ማለት ነው ፡፡ እግዚአብሄር ድቦራን በእግዚአብሄር ጠላቶች ላይ ነደፋን ለማምጣት እንደ ፈራጅ ተጠቀማት ፤ ድቦራ ባለ ቅኔ እና ነቢይት ነበረች ፡፡ የባርቅ ስም “ ብርሃን “ ማለት ነው ፤ የባርቅ በዕብራዊ ለምስጋና የሚሆን ቃል ነው ፡፡ መዝ (34፡ 1) የሚለው “ እግዚአብሄርን ሁል ጊዜ እባርከዋለሁ ምስጋናዉም ዘወትር በአፌ ነው “ ፤ የቃሎች መሳሳብ ማምለክ እና መስገድ ማለት ነው ፤ መዝ (95፡ 6) የሚለው “ ኑ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ ፤ በእርሱ ባደረገን በእግዚአብሄር ፊት እንበርከክ ፤ እርሱ አምላካችን ነዉና “ ፡፡

መሳፍንት (5፡ 2-6)፡ በቁጥር 2 ባርቅ እንደ ገና ተጠቀመ፡ “ በእስራኤል ዉስጥ መሪዎች ስለ መሩ ሕዝቡም ነፍሳቸዉን በፈቃዳቸዉ ስለ ሰጡ እግዚአብሄርን አመሰገኑ “ ፤ ድቦራና ባርቅ እያደረጉት የነበረዉን ስማቸዉ እያረጋገጠዉ ነበር - በስማቸዉ እየኖሩበት የነበረ ትንቢታዊ ድርጊትን የሚያሳይ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ልክ እንደ ንብ በመንደፍ ወታደሮችን እንድትመራ ድቦራን እንዲሁም ደግሞ በማብራት እንዲገድሉ ወታደሮቹን ባርቅን ተጠቀመ ! አሁን ደግሞ እግዚአብሄርን እያመሰገኑ (ባርቅ) ነበር ፡፡ በቀጥታ ባርቅ ማለት መባረክ፣ መንበርከክ፣ በተትረፈረፈ መባረክ፣ ሰላምታ መስጠት፣ ማመስገንመኩራት እና በረከትን ማወጅ ማለት ነው ፡፡ በቁጥር 3 ለምስጋና የተለያዩ የዕብራዊያን ቃላቶች ይጠቅማሉ - ዝማሬ ሙዚካ መስራት ወይም በዝማሬ ማመስገን ማለት ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን እግዚአብሄርን እናመሰግነዋለን እንላለን ለሁሉም አይነት ምስጋናም ያን ቃል እንጠቀማለን ፡፡ በዕብራዊያን ለምስጋና ብዙ ቃላቶች አሉ ፡፡ ሰዎስተኛዉ ፈራጅ (መሳፍንት) ሰሜጋር የተሰየመ ነው (ቁጥር 6) ፡፡

መሳፍንት (5፡ 7-9)፡ ድቦራ “ በእስራኤል እንደ እናት “ተነሳች (ቁጥር 7) ፤ እግዚአብሄር ወደ ኑሮአችን የሚናገሩ እግዚአብሄራዉ አባት እና እናቶች አስነስቶልናል (1ቆሮ 4፡ 15-17) ፡፡ ቁጥር 8 በእስራኤል ተፈጥሮ የነበረውን መዝግቧል - በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር አድርገዉ ስለ ነበር በከነዓናዊያን ንጉስ በኢያቢስ አገዛዝ ስር ወደቁ (መሳ 4፡ 1-3) ፤ ቁጥር 9 የእግዚአብሄር አመራርነት መዴል ነው ፡፡ በመሪነት ልባቸው ከህዝቡ ጋር ነበር ፤ አንዱ ለአንዱ የሚታዘዝበት የትህትና አመራርነት ነበር (ኤፌ 5፡ 19-21) ፡፡ የህዝቦች መልስ ለእግዚአብሄር መሆን ያለበትን ባርቅ እና ድቦራ ይህን እንደ ማስተማሪያ ክስተት ተጠቀሙት ፡፡

መሳፍንት (5፡ 10-11፣ 21፣31)፡ ለምስጋና ሌላዉ ዕብራዊ ቃል - ሲንች ሲሆን መመልከት፣ መቀየኝት፣ መናገር ወይም ማዉራት ማለት ነው (ቁጥር 10) ፤ ቁጥር 11 ምስጋና ለሚለዉ ቃል ሌላ ዕብራዊ ቃል ይጠቀማል - ዳባር ሲሆን መናገር፣ ማረጋገጥ፣ ማወጅ፣ መስበክ፣ መናገር ወይም ማሰማት ማለት ነው ፡፡ የድቦራ እና የባርቅ ስም ትንቢታዊ ነበር ፡፡ ዳባር የሚለዉ ቃል ደቢር ከሚለዉ የዕብራዊ ቃል መሰረትነት የመጣ ሲሆን ትርጉሙም በመናገር ልክ ድቦራ እንደ ሚለዉ ስም በመታራት በሚያስቀይም መዝጋት ማለት ነው ፡፡ ድቦራ እንደ ተናጋሪ እና ለእስራኤል እንደ እናት ትንቢታዊ መድረሻዋን ኖረች ፤ ድቦራ (ዳባር፣ ደቢር) “ አዲስ መዝሙር እየዘመረች “ እንድትኖር በምትጠራው ኖረች ፤ ይህ እንዱ የተቀራረበ ጥቅስ ነው - “ ነፍሴ ሆይ በኃይል እርገጪ “ (ቁጥር 21) ፡፡ ምድሪቱም ለ40 አመታት ሰላም ነበረች ፤ ድቦራና ባርቅም የሰላም ሰራተኞች ነበሩ (ማቴ 5፡ 9) ፡፡

መሳፍንት (6፡ 1-10)፡ እንደ ገና እስራኤል በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር አደረገ ፤ ስለሆነም እግዚአብሄር ለሰባት አመታት ለምድያም አሳልፎ ሰጣቸው (ቁጥር 1) ፡፡ በህግ የሙሴ አባት ለምድያማዊያን ካህን እንደ ነበር አስታዉሱ ፤ የአብርሃም ቁባት ኬቱራ ዘሮች ነበሩ ፤ ምድያም የሚለዉ ስም ፍርድ ማለት ሲሆን እግዚአብሄር በእስራኤላዊያን ላይ ፍርድን ለማምጣት ምድያማዊያንን ተጠቀመ ፡፡ በጣም አስቸጋሪ(መጥፎ) ስለነበር በተራራ እና በዋሾች ላይ ከምድያማዊያን ጥቃት እስራኤላዊያን ራሳቸዉን ይደብቃሉ (ቁጥር 2-5) ፤ በእስራኤላዊያን አለመታዘዝ ላይ ምድያማዊያን ጥፋት እንዲያመጡ ፈቀደላቸው ፡፡ በጥቃቱ ምክንያት እስራኤል በጣም ድሀ ሆነ - የተራበም ሆነ ወደ እግዚአብሄርም ጮኹ (ቁጥር 6-7) ፤ እግዚአብሄር ከግብፅ ምድር ነፃ አዉጥቷቸዉ እንደ ነበር እና ምድራቸዉን እንደ ሰጣቸዉ የሚያሳስብ ያልተጠቀሰ ነቢይን እግዚአብሄር ላከላቸው (ቁጥር 8-9) ፡፡ በጌዴዎን መነሳት እና በኢያሱ ሞት መካከል 130 አመታት ነበሩ እንዲሁም ከግብፅ የእስራኤል ነፃ መዉጣት ጀምሮ 220 አመት ያክል ነበር ፡፡ በእነዚህ ከ200 አመታት በላይ ጉዞ ዉስጥ ሰዎች በእግዚአብሄር ነገሮች ዉስጥ ሲገቡ እና ሲወጡ ማየት ትችላላችሁ፡፡ ነቢዩም እግዚአብሄር የአሞራዊያንን አምላኮች እንዳይፈሩ ነግሯቸዉ እንደ ነበር አስታወሳቸው ነገር ግን እርሱን አልታዘዙም ነበር (ቁጥር 10) ፡፡

መሳፍንት (6፡ 11-21)፡ ተደብቆ በወይን መጭመቂያዉ ዉስጥ ስንዴዉን እየወቃ የእግዚአብሄር መልዓክ ጌዴዎንን ሲያገኘው ጊዜዉ በጣም ተስፋ የቆረጠበት ነበር (ቁጥር 11) ፤ መለዓኩም “ፅኑ ኃያል “ በማለት ጠራው (ቁጥር 12) ፡፡ ሮሜ (4፡ 17) የሚለው “ የሌለዉን እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነዉ “ ፤ በቁጥር 13 ጌዴዎን በምሬት እግዚአብሄር ለምድያማዊያን አሳልፎ ስለ ሰጣቸዉ በመክሰስ መለሰ ፡፡ እግዚአብሄር ሙሉ ለሙሉ ከጌዴዎን ፍላጎት እና ቅሬታ በተቃራኒ “ ሂድ “ አለው (ቁጥር 14) ፤ በቤተ ክርስቲያን እግዚአብሄር በእኛ የምቾት ስፋራ በእዉነት ራሱን አያሳስብም ፤ ወደ አለም ትክክለኛ ስርዓትን እና ፍትህን እንድናመጣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንድንጓዝ ይፈልጋል ፤ ነገር ግን ጌዴዎን የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ጠየቀ (ቁጥር 15) ፤ እግዚአብሄርም “ከአንተ ጋር እሆናለሁ “ በማለት መለሰለት (ቁጥር 16) ፡፡ ጌዴዎን የሚለዉ ስም ከዕብራዊያን ጋዳ ከሚለዉ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ቆረጠ፣ ሰባበረ፣ ፈለጠ ወይም ወደ ትናንሽ ቆራረጠ ማለት ነው ፡፡ እነዚህ ቃሎች ጌዲዎን እንዲያደርጋቸዉ የተጠራበት ትንቢቶች ነበሩ ፡፡ ጌዴዎን እየሰማ የነበረዉ ከእግዚአብሄር እንደ ነበር ለማረጋገጫነት ምልክትን ጠየቀ (ቁጥር 17-18) ፤ ጌዴዎን ምግቡን ለእርሱ እስኪያመጣለት ድረስ የእግዚአብሄር መለዓክ መጠበቁ አስቂኝ(የሚያስቅ) ይመስላል ? በዚህ ድርቅ አስገዳጅ በሆነበት ጊዜ ይህ የምግብ ቁርባን ጌዴዎን ብዙ ወጪ ያስወጣዋል (ቁጥር 19) ፡፡ በተዘጋጀዉ ምግብ ምንድን እንደ ሚያደርግ መለዓኩ ጌዴዎንን ነገረው ከዚያም ከአለቱ በሚመጣዉ እሳት የተቃጠለዉን ዳቦ እና ስጋ በብትር ጫፍ ነካው (ቁጥር 20-21) ፡፡

መሳፍንት (6፡ 22-28)፡ ይህ በጌዴዎን እና በእግዚአብሄር መካከል አስደናቂ መገናኘት ነው ፡፡ በቀጣዮቹ ጥቂት ቁጥሮች እግዚአብሄር ጌዴዎንን የባዖልን መሰዊያ እና የማምለኪያ አፀድ እንዲያጠፋ ከዚያም ከአባቱ በሬ ሰባት አመት የሆነዉን በሬ እንዲወስድ ነገረው (ቁጥር 25) ፡፡ እግዚአብሄር ጌዴዎንን የአባቱን የጣዖት አምልኮ እርግማን የሚቆረጠዉን የመጀመሪያዉን በሬ የሚቆርጥበትን ትንቢታዊ የመሰዊያ ቦታ እየወሰደዉ ነበር በተጨማሪም የሁለተኛዉ በሬ መስዋዕት የምድያማዊያንን የሰባት አመት እርኩሰት ያስወግዳል ፡፡ የጌዴዎን አባት የባዖል ፀዳል አምላኪ ነበር ጌዴዎንም የአሴርን አፀድ “ ቆራረጠው “ (ስሙ እንደሚለዉ አደረገ )፣ የባዖልንም መሰዊያ አፈራረሰ (ቀዳደደ) ከዚያም ለእግዚአብሄር በሰራው አዲስ መሰዊያ በሬዉን ሰዋ (ቁጥር 27-28) ፡፡

መደምደሚያ

ስማችሁ በጣም ትርጉም አለው ለእንደዚህ አይነት ጊዜ አይነት ጊዜ ተወልዳችኋል ፤ ስህተት የለም - ለአላማ ተወልዳችኋል ፡፡ ስለ ባዖል መሰዊያዎች እና ስለ አሴር አፀዶች እንድትቆራርጧቸው በመጠራታችሁ ደስ ብሎኛል ፤ በአለም ላይ የኃጢዓትን ሞት ለማስተካከል እና ለማስነሳት ፃድቃን ወንዶች እና ሴቶች ያስፈልጉናል ፡፡

ጥያቄዎች

  1. የድቦራን እና የባራቅን ዝማሬ በተነበበ ጊዜ ስለ ኢያዔል እና የሴይርን ማሸነፏን ዘመሩ ፤ መሳ (5፡ 26-27) ዘፍ (3፡ 15) ወደ አይምሮ ያመጣል ? ለምን ?
  2. መሳ (6፡ 1) የእስራኤል ልጆች እንደ ገና በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ማድረጋቸዉን እና እግዚአብሄር በምድያማዊያን እጅ አሳልፎ እንደ ሰጣቸዉ መዝግቧል (ዘዳ 31፡ 16-18) ፤ በዚህ ጊዜ ወደ እግዚአብሄር በጮኹ ጊዜ እግዚአብሄር እንዴት መለሰላቸው (መሳ 6፡ 7-10) ? እግዚአብሄር ነፃ እንዲያወጣቸዉ በፊቱ እንዲጀምር ነብዩን ለምን እንደ ላከላቸዉ ምን ታስባላችሁ ?
  3. ምድማዉያን እና አማሌቃዉያን እስራኤላዊያን ሰብላቸዉን ሲተክሉ ይፈቅዱላቸዋል ነገር ግን በመምጣት ምርታቸዉን ይወስዱባቸዋል ወይም ያጠፉባቸዋል (መሳ 6፡ 3-4) ፤ በኢያ (24፡ 13) የዚህን ምድር ንብረት በወሰዱ ጊዜ ከነበረዉ እንዴት ይወዳደራል ?
  4. የእግዚአብሄር መለዓክ ለጌዴዎን በተገለጠለት ጊዜ ጌዴዎን “ እግዚአብሄር ከአንተ ጋር ነዉ “ በሚለዉ ሀረግ ችግር ነበረበት ፤ ያ ለምን ነበር ? በዘዳግም 32 ጌዴዎን የሙሴን መዝሙር ሰምቶ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ? እግዚአብሄር በእምነት ይመለክበት የነበረው ቦታ ላይ ጌዴዎን በቤቱ አምጥቶት ነበር ? (መሳ 6፡ 25)
  5. ለእግዚአብሄር ምንድን እንደ ሚቀርብ ጌዴዎን እንዴት እንዳወቀ ምን ታስባላችሁ (መሳ 6፡ 19) ? ከአለት የወጣዉ እሳት መስዋዕቱን መብላቱን ምን ያመለክታል ? ጌዴዎን የሰራዉን መሰዊያ “ እግዚአብሄር ሰላም ነዉ “ ብሉ ለምን እንደ ሰየመዉ ምን ታስባላችሁ ? (ዘሌ 26፡ 6፣ መሳ 6፡ 24)
  6. በመሳፍንት 5-6 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Judges 6:15-16

“He said to Him, ‘Please, Lord, how can I deliver Israel? Look, my family is the weakest in Manasseh, and I am the youngest in my father’s house.’ ‘But I will be with you,’ the Lord said to him. ‘You will strike Midian down as if it were one man.’”

ከእስራኤላውያን አለመታዘዝ አመታት በኋላ እግዚአብሔር ህዝቡን ነፃ ያወጣ ዘንድ ጌድዮንን አምስተኛ መሳፍንት አድርጎ ጠራው ፡፡ ጌድዮን ከደካማ ቤቴሰብ ፤ በጣም ከተጠቃው የምናሴ ነገድ የተገኘ እንድሁም ደግሞ ባባቱ ቤት ከሁሉም ታናሽ በመሆኑ እግዚአብሔር እንዴት ሊጠቀምበት እንደሚችል አላስተዋለም ነበር ፡፡ እግዜአብሔር ግን ጌድዮንን እንደ ፅኑ ተዋጊ ነበር ያየው ከእርሱም ጋር እንደሚሆን ነገረው ፡፡ ጌድዮንም እግዚአብሔርን ለጥሪው ማስረገጫ ምልክትን ጠየቀው እግዚአብሔርም በምልክትና በድንቅ ጥያቄውን መለሰለት ፡፡

እግዚአብሔር በህይወትህ ላይ ላስቀመጠው ጥሪ በቂ እንዳልሆንክ ከተሰማህ አንተም ከጌድዮን ጋር ተመሳሳይ ነህ ፡፡ አስታውስ እግዚአብሔር በመንግስቱ ለአንተ ዓላማ አለው ይህም ደግሞ እርሱ ውብና ድንቅ አድርጎ ስለፈጠረህ እንጅ በትምህርት ስላገኘኻቸው ድግሪዎች ወይም በንግዱ ዓለም ስላስመዘገብከው ስኬት አልያም ደግሞ ከቤተሰብ ስላገኘኸው ውርስ አይደለም ፡፡ እርሱ ሲጠራህ አላፈረም ባንተ ላይ ዓላማ ስላለው ፤ አንተን ሁልግዜም በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መጠቀም ስለሚሻ እንድሁም ውስጥህ ያለውን መንፈስ ቅዱስ ስትሰማ እርሱ ደግሞ ይልክሀል ፡፡ ነገር ግን አንተም እንደ ጌድዮን ሁሉ የእግዚአብሔርን ምስክርነት የምትፈልግባቸው ጊዜያት አሉ ፡፡ እግዚአብሔር ኃያል ተዋጊ ነውና በእምነት ተራመድ እርሱም ፊቱን በመፈለግ ስትራመድ መንገድህን ሲያፀናልህ ታያለህ እርሱ ሁሌም ካንተ ጋር ነው ፡፡

“ እርሱም ጌታ ሆይ እስራኤልን በምን አድናለሁ ወገኔ ከምናሴ ነገድ ከሁሉ ይልቅ የተጠቃ ነው እኔም በአባቴ ቤት የሁሉ ታናሽ ነኝ አለው ፡፡ እግዚአብሐየርም በእርግጥ ካንተ ጋር እሆናለሁ ምድያምንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ትመታለህ አለው ፡፡ ”

- መሳፍንት 6 ፡ 15-16

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 1ኛ ሳሙኤል 17፡37 – “ ዳዊትም ከአንበሳና ከድብ እጅ ያስጣለኝ እግዚአብሔር ከዚህ ፍልስጤማዊ እጅ ያስጥለኛል አለ ፡፡ ሳኦልም ዳዊትን ሂድ እግዚአብሔርም ከኣንተ ጋር ይሆናል አለው ፡፡ “
  • ኤርምያስ 32 ፡27 – “ እነሆ እኔ የስጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ በውኑ እኔን የሚያቅተኝ ነገር አለን ፡፡ “
  • ዕብራውያን 13፡20-21 – “ በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ስራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን አሜን ፡፡