Faith Even In Weakness
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Judge Judges 7-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የሚንዴስ ስዕል ስለ መሳፍንት መፅሀፍ በቃላት አገላለፅ ብቻ ሳይሆን የመሳፍንትን ጊዜ ቆይታ የሚያሳይ የሚያስደንቅ ስራ ነው ፡፡ ባለመታዘዝ ኡደት እና በእግዚአብሄር ላይ በማመፅ እንዲረዳቸዉ ወደ እርሱ እስኪጮኹ ድረስ የእግዚአብሄርን ፍርድ በመቀበል ያየነዉ በእስራኤል የመባዘን 300 አመት ነበር ፡፡ እግዚአብሄር በመስማት ወደ እራሱ እንዲመልሱ ያያቸዉን የህዝቡ ነፃ አዉጪ እንዲሆኑ አስነሳላቸው ፤ ከዚያም እንደ ገና ዝብርቅርቁ ሂደት ጀመረ ፡፡ እግዚአብሄር ያስነሳቸዉ መሳፍንቶች የክርስቶስ ጥላ ነበሩ ፡፡ ጌዴዎን ከጎቶንያል፣ ከናዖድ፣ ከሰሜጋር እና ከድቦራ በኋላ አምስተኛዉ መሳፍንት ነበር ፤ በምዕራፍ 6 ጌዴዎን ምንድን እንዲሰራ እግዚአብሄር ጠርቶት እንደ ነበር በጥንቃቄ ተመለከተ ምክንያቱም እንደ ማይችል ተሰምቶት ስለ ነበር ፤ ሁለት ጊዜ ለህይወቱ በእግዚአብሄር ሀሳብ እርግጠኛ ለመሆን የበግፀጉር አስቀመጠ ፤ እንደ ማንችል በተሰማን ጊዜ እግዚአብሄር ምን እንድንሰራ እንደፈለገ እርግጠኛ ለመሆን እንዲሁ በኑሮአችን የበግ ፀጉር ያስፈልገን እንደ ሆነ ይህ ጥያቄ ያመጣል ፡፡ በመሳፍንት 6 ከቅድመ ክርስቶስ ጋር ጌዴዎን መገናኘት ነበረው በዚህም ሁል ጊዜ ለእግዚአብሄር የተሰጠ ነበር እግዚአብሄርም ለብዙ እያዘጋጀዉ ነበር ፡፡ የጌዴዎን ቅሬታዎች፣ ጥያቄዎች እና ጥርጣሬዎች እያሉ እግዚአብሄር እንዲያደርግ ጠርቶት በነበረው በመሄድ ጨረሰ ፤ ሁሉም ነገር እያሉ እግዚአብሄር አሁንም ጌዴዎንን መጠቀም ይችል ነበር ፡፡
ትምህርት
መሳፍንት (7፡ 1-4)፡ዋይርስቤ ለዚህ ምዕራፍ ቀላል ሰዎስት መግለጫዎቹን ይጠቀማል፡ “ እግዚአብሄር እምነታችን ይፈትናል “፣ “ እግዚአብሄር እምነታችንን ያበረታታል “ እና “ እግዚአብሄር እምነታችንን ያከብራል “ ፡፡ የጌዴዎንም ጦር በሐሮድ ሚንጭ አጠገብ ሰፈረ እግዚአብሄርም ጌዴዎንን ጦርህ ብዙ ከሆነ እስራኤላዊያን በራሳችን አሸነፍን ይላሉ በማለት ነገረው (ቁጥር 1-2) ፤ እግዚአብሄር በእርሱ ላይ ፍፁም መተማመን(መደገፍ) እንዲኖረን ይፈልጋል (2ቆሮ 12፡ 9) ፡፡ እግዚአብሄር ጌዴዎንን የፈሩትን ወደ ቤታቸዉ እንዲልካቸዉ ነገረው 22,000 ተመለሱ (ቁጥር 3) ፤ 2/3 የጌዴዎን ጦር ተመለሰ ፡፡ ዋይርስቤ ይህን እንደ “ መጀመሪያ መመርመሪያ “ ይጠቅሰዋል ፤ 22,000 ወታደሮች ሲለቁ ማየት አያስጨንቅም ፤ የሚገጥሙት ጦር 135,000 ወታደሮች ነበሩት (መሳ 8፡ 10) ፡፡ ኢንሪንግ “ እግዚአብሄር ድል ማድረግን መስጠት ብቻ አይፈልግም ፤ መታመንን በማስተማር ያተኮረ ነው ፤ በእርግጥ ድሎቻችን በራስ መተማመን ያለን ቢያደርጉንም በመጨረሻ ከማሸነፍ በላይ አጥፊዎች እንደ ሚሆኑ ይናገራል “ ፡፡ የእግዚአብሄር ጥያቄ “ ነገሮች ጠንካራ በሆኑ ጊዜ በእኔ ትታመናላችሁ ?” የሚል ነበር ሰዎች ሁል ጊዜ ያ ይገጥማቸዋል ፡፡
በኦሪት ጥናታችን ወታደሮች ዉጊያን ትተዉ መሄድ የሚችሉበት እና በፍርሀት የማይዋጉባቸዉ ብዙ ምክንያቶች እንደ ነበሩ እናስታውሳለን፡ አዲስ ቤት ገንብተዉ ከነበር፣ ለማግባት ታጭተዉ ከነበር ወይም ደግሞ የወይን አትክልት ተክለዉ ከነበር ፡፡
መሳፍንት (7፡ 4-8)፡ እግዚአብሄር ሁለተኛ ጊዜ ከምንጭ ዉሃ በሚጠቱበት መንገድ በምላሳቸዉ አጎንብሰዉ የሚጠጡትን ወይም በአፋቸዉ ዉሃ ለመጠጣት እጃቸዉን የሚጠቀሙትን ወታደሮቹን በመመልመል 10,000 ወታደሮቹን ወደ 300 ቀነሳቸው ፤ ይህ እዉነተኛ የእምነት ፈተና ነበር ፤ ይህ ከሁለተኛዉ የአለም ጦርነት በኋላ ዊንስተን ቸርችል “ በሰዎች ግጭት ሜዳ ላይ በጥቂቶች ለብዙዎች በጣም ብዙ ምስጋና በፍፅሙ አልነበረም “ ካለዉ ጋር የሚመሳሰል ነው ፤ ይህ የዚያ ንግግር ጥሩ ምሳሌ ነው ፡፡ በምድያማዊያን ላይ ድል ማድረግ በሚኖረዉ ነፃ አዉጪዊ ጌዴዎን መሪነት ስር እግዚአብሄር እነዚህን 300 ሰዎች ፈለገ ፡፡
መሳፍንት (7፡ 9-14)፡ እምነታችን በመፈተን ሂደት ዉስጥ እግዚአብሄር እምነታችንን ያበረታል ፡፡ ብዙ ሰዎች በፈተናዉ ጊዜ ተስፋ በመቁረጥ እስከ ቁጥር 9 በፍፁም አላደረጉትም ፤ ደካሞች፣ ልጆች እና ትንሽ ቻዮች በሆነ ቁመና ለመኖር እናዘነብላለን ፤ እግዚአብሄር ጌዴዎንን ቀድሞ ድል ሰጥቶት እንደ ነበር ቃል ገባለት (ቁጥር 9) ፡፡ እግዚአብሄር ያን ተስፋ ሲያደርግ ሰዎስተኛዉ ጊዜ ነበር ደግሞም ጌዴዎንን ሰዎስት ምልክቶች ሰጥቶትም ነበር (መሳ 6፡ 20-21 ፣ 36-38፣ 39-40) ፤ እግዚአብሄርም አሁንም ፈርቶ ከነበር ጌዴዎንን ከአጠገቡ እንዲሄድ አገልጋዩን ፉራን እንዲወስድ ነገረው (ቁጥር 10) ፡፡ ዳቪስ እና ዋይትኮም የጌዴዎንን አቋም “ ጌዴዎን በሁሉም ድፍረት የለዉም - ቀድሞ ለመከላከል፣ ጠቅላላ ትጥቆች ባለመኖር እና ዮሐንስ ዋይኒ አንድ የእዉነተኛ አለት ትልቅ ወደ ሆነ ኳስ ተንከባለለ “ ፡፡ 135,000 የጠላት ወታደሮች ጋር ለመዋጋት እየሄደ ነበር ፡፡
ቁጥር 12 የጠላቶቹን ወታደሮች “ እንደ አንበጣ መንጋ “ እና ግመሎቻቸዉን ደግሞ “ ቁጥር እንደ ሌለዉ የባህር አሸዋ “ ይገልፀዋል ፡፡ ጌዴዎን አንድ የምድያማዊያን ሰው ለባልንጀራዉ አንድት የገብስ እንጀራ ከላይ ስትወድቅ ድንኳኑ ወደ ላይ ተገለበጠ ብሎ ስለ ህልሙ ሲነግረዉ ሰማ (ቁጥር 13) ፤ ህልም ተተኝቶ ተካሂዶ የነበር ሲሆን ራዕይ ደግሞ ተነቅቶ ተካሂዶ የነበር ነው ፡፡ ባልንጀራውም ጌዴዎንን እግዚአብሄር በምድያማዊያን ላይ ድል ሰጥቶት እንደ ነበር መለሰለት (ቁጥር 14) ፤ በአሁኑም ጊዜ ከእግዚአብሄር ህልም እንደ ሚሆን አንዳንድ ሰዎች በስነ መለኮታዊ ያስተባብላሉ (1ነገ 3፡ 5፣ ኢዩ 2፡ 28፣ ማቴ 2፡ 13፣ ሐዋ 2፡ 17) ፡፡ የመጨረሻዉ ቀን መጥቷል ? አልመጣም ከሆነ ህልሞች አሁንም አስፈላጊ ናቸዉ ፤ እግዚአብሄር በህልም ሊናገረን ይችላል ፡፡ የምንሰማዉ ከእግዚአብሄር ቃል ጋር የማይፃረር ከሆነ እግዚአብሄር ተናግሮናል ሊሆን ይችላል ፤ እንዲሁም እግዚአብሄር በማያምኑት ህልም በኩል ሊናገር ይችላል ፡፡
መሳፍንት (7፡ 15-25)፡ እግዚአብሄር እምነታችንን ያከብራል ፡፡ ጌዴዎን የምድያማዊዉን ህልም በሰማ ጊዜ ለዊጊያ ወታደሮቹን ጠራቸው ፤ ለእያንዳንዱም ሰዉ በአንድ እጃቸዉ መለከት በሌለኛዉ ደግሞ በዉስጡ ችቦ ያለበት አንድ ማሰሮ ሰጣቸው ከዚያም ምን እንደሚያደርጉ እንዲያዉቁ በጥንቃቄ እንዲአጡኑት ነገራቸው ፤ ጌዴዉን ልክ እንደ ጦር መሪ አክት እያደረገ ነበር ፡፡ ከሰፈር ዉጪ ባዩት ጊዜ መለከቶቻቸዉን በመንፋት መብራታቸዉንም ለማሳየት ማሰሮቻቸዉን ሰበሩ ፤ በመጮኽ እርስ በእርሳቸዉ ላይ በመነሳት በምድያማዊያን ሰይፍ እርስ በእርሳቸዉ እንዲገዳደሉ የምድያማዊያንን ወታደሮች አሳደዱዓቸው ፡፡ እስራኤላዊያን ከራሳቸዉ ከአንድ በላይ የሆኑ ነገዶችን በመጥራት ምድያማዊያንን ተከታተሉዓቸው ማንምም አላመለጠም ፡፡
መደምደሚያ
ዕብ (11፡ 6) የሚለው “ ያለ እምነት ደስ ማሰኘት አይቻልም ፤ ወደ እግዚአብሄር የሚደርስ እግዚአብሄር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና “ ፤ ሁላችንም ጌዴዎኖች ነን ፡፡ እግዚአብሄር ጌዴዎንን ስለ ዘለለ(ትንሽ ) እምነቱ አከበረው ስኬታማም ሆነ ፡፡
4 John J. Davis and John C. Whitcomb, A History of Israel, reprint ed. (Grand Rapids: Baker Book House, 1980), pp. 106-107; quoted in Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes, available online at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/judges.pdf, p. 65.
Warren W. Wiersbe, The Bible Expositional Commentary: Judges (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), pp. 119-123.
Wiersbe, p. 120.
Gary Inrig, Hearts of Iron––Feet of Clay (Grand Rapids: Discovery House, 1979), p. 125.
ጥያቄዎች
-
እግዚአብሄር የጌዴዎንን ጦር ከ32,000 ሰዎች ወደ 300 ለምን ቀነሰው ?
-
ጌዴዎን ምድያማዊያንን እንዲያጠቃቸዉ ብርታት ሲሰጠው ምንድን ተፈጠረ (መሳ 7፡ 13-15) ? ለድርጊታችሁ ብርታት የሰጣችሁ ከእግዚአብሄር የሆነ ህልም ነበራችሁ ? እንዴት በማህበረሰቡ ዉስጥ መስማት ይሆናል ካበረታችሁ እግዚአብሄርስ ሌሎች እንዴት ይሰማሉ ?
-
አለቆቿ በሱኮት ጌዴዎንን ጦሩን ከመመገቡ በፊት በመጀመሪያ ዛብሄልን እና ስልማናንን እንዲይዝ ለምን እንደ ነገሩት ምን ታስባላችሁ ? ምን አይነት ቅጣት ተቀበሉ ?
-
ከእያንዳንዳቸዉ ሰዎች ምርኮ ጌዴዎን አንድ ወርቅ እንዲያገኝ ለምን ጠየቀ ? ይህ ጥሩ ነገር በመሆን አብቅቷል ? ለምን አበቃ ወይስ አላበቃም ?
-
በመሳፍንት (7-8) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Judges 7:2
“The Lord said to Gideon, ‘You have too many people for Me to hand the Midianites over to you, or else Israel might brag: I did it myself.’”
ጌዴዮንም የእግዚአብሔርን ጥሪ በመቀበል ኃያል ሰራዊትን ገነባ ምድያማውያንንም ለመውጋት ተዘጋጀ ፡፡ በዝግጅቱም መካከል እግዚአብሔር ጦሩ እጅግ እንደበዛ ለጌድዮን ተናገረው ፤ እግዚአብሔርም ከ 32000 ሰራዊት 300 ሰዎች ብቻ እንድቀሩ አደረገ ፡፡ እግዚአብሔርም ለጌድዮን 300 ሰዎችን ብቻ በመጠቀም ምድያማውያንን አሳልፎ በእጁ እንደሚሰጠው ቃል ገባለት ፡፡ ጌዴዮንም የእግዚአብሔርን ኪዳን በህይወቱም ውስጥ ያለውን ጥሪ በማመን በእምነት ተራመደ ፡፡ ጌድዮን በመንገዱ ያለውን ጥርጣሬና ፍርሀት ያስወግድ ዘንድ እግዚአብሔር ለእርሱ ማፅናቱንና እርሱን ማስታጠቁን ቀጠለ ፡፡ በዚህ ሁሉ በጌድዮን ድካም እግዚአብሔር ከበረ ፡፡
የእግዚአብሔር ኀይል ባንተ ድካም ውስጥ ይታያል ፡፡ እርሱ በአንተ ድካም ውስጥ ኃያል መሆኑን ተናግሯልና በራስህ ሳይሆን በእርሱ ኃይል ልትመካ ይገባሃል ፡፡ ሁልጊዜም ጥሪህን ስትፈፅም ይህን አስታውስ ለእግዚአብሔር ትልቅ የሆነ ተራራ ፤ በእግዚአብሔር የማይፈርስ ኪዳን ፤ ለእግዚአብሔር የከበደ ስራ ወይም ደግሞ ከእግዚአብሔር በላይ የሆነ ህመም እንደሌለ ፡፡ እንደ ጌዴዮን ሁሉ እግዚአብሔር አንተም በእርሱ እንድታምን ይፈልጋል ፡፡ በድካምህ በከባዱ ላይ እምነት ይኑርህ የእርሱንም መንገድ ተከተል ከእርሱ ጋርም ጀምር እርሱም ከመድረሻህ ያደርስሀል ፡፡ ታመን ታመን ታመን ፡፡
“ እግዚአብሔርም ጌዴዎንን ከአንተ ጋር ያለው ህዝብ በዝቶአል ስለዚህ እስራኤል እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም ፡፡ “
- መሳፍንት 7፡2
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መሳፍንት 7፡7-8 – “ እግዚአብሔርም ጌዴዎንን በእጃቸው ውኃ በጠጡት በሦስት መቶ ሰዎች አድናችላሁ ምድያማውያንንም በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ የቀሩት ህዝብ ሁሉ ግን ወደ ስፍራቸው መለሱ አለው ፡፡ የህዝቡንም ስንቅና ቀንደ መለከት በእጃቸው ወሰዱ የቀሩትንም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ድንኳናቸው ሰደዳቸው ሦስቱን መቶ ሰዎች ግን በእርሱ ዘንድ ጠበቃቸው የምድያምም ሰፈር ከእርሱ በታች በሸለቆው ውስጥ ነበረ ፡፡
- 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9 –“ እርሱም ፀጋዬ ይበቃሃል ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ ፡፡ እንግድህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እዋዳለሁ ፡፡ “
- ዕብራውያን 11፡6 –“ ያለ ዕምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰትጥ የምን ዘንድ ያስፈልገዋልና ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።