Taking A Stand Against Evil
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Judge Judges 9-10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ስለ መሳፍንት መፅሀፍ የምወደዉ ነገር እነዚህ ሰዎች በመጥፎ ነገር ቆሽሸዉም ቢሆን እግዚአብሄር እንዴት ሊጠቀምባቸዉ እንደ መረጣቸዉ ማየት ነው ፤ በመሳፍንት መፅሀፍ ስትጓዙ እናንተንም እግዚአብሄር እንዴት ሊጠቀምባችሁ እንደ ሚችል ተስፋ እንድታገኙ ነው የምፀልየዉ ፡፡ ዛሬ የይሩበኣል(ጌዴዎን ተብሎ የሚታወቀዉ) ልጅ አቤሜሌክ ላይ እንመለከታለን ፤ በጠቅላላዉ አቤሜሌክ ዳኛ (መሳፍንት) አልነበረም የእግዚአብሄር ጠላት ነበር እንጂ ፡፡
እግዚአብሄር በጠራዉ ጊዜ ጌዴዎን ከጠላቶቹ እየተደበቀ በብዙ ጦር ላይ ትንሹን የእስራኤላዊያንን ጦር እየመራ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ተከተለ ፤ በመሳ (8፡ 22) ጌዴዎን እና የልጅ ልጁ በእስራኤል ላይ እንዲገዙ ተጠየቁ ፤ ነገር ግን ጌዴዎን እግዚአብሄር ብቻ በእነርሱ ላይ እንደ ሚገዛ መለሰላቸው (መሳ 8፡ 23) ፡፡ እግዚአብሄር በጌዴዎን በኩል ነፃ መዉጣትን አመጣ ፤ ሰዎቹ ይህን ሰዉ እንዴት ለመከተል እንዳጋደሉ አስታዉሉ ፤ ንጉሳቸዉ ሊያደርጉት ዝግጁ ነበሩ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሆኑ ሰዎች በኃይል በእግዚአብሄር በተጠቀሙ ጊዜ ኩራታቸዉ ሊቀርና ሊያበቃ ይችላል ፡፡ ጌዴዎን ለእግዚአብሄር ታዛዥ እና ትሁት ሆነ ፤ ነገር ግን ከዘረፉት ለእያንዳንዱ ወታደሮቹ ጥቅም(እቃ/ጉትቻ) እንዲያገኙ ጠየቀ ፤ ጉትቻዎቹ አምላክ የሌላቸዉ ሰዎች ይጠቀሙባቸዉ የነበሩ ናቸዉ ነገር ግን ጌዴዎን ልልጁ ለክህነት ልብስ ለኢፉድ መስሪያ ተጠቀመባቸው ፡፡ ኤፉዱ የአምልኮ ሀሳብ ሆነ ፤ መሳ (8፡ 27) ዉጤቱን መዝግቧል፡ “ እስራኤልም ሁሉ ተከትሎ አመነዘረበት ፤ ለጌዴዎንና ለቤቱም ወጥመድ ሆነ “ ፡፡ በጌዴዎን የህይወቱ መጨረሻ ላይ ሰዎቹ ወደ ከእግዚአብሄር ርቀዉ የነበሩበትን ስህተት ማድረግ ጀመሩ ፡፡
ትምህርት
መሳፍንት (9፡ 1-6)፡ አቤሜሌክ ሌላዉ ስሙ ይሩበኣል ማለትም “ ባዖልን ለምዳደር ፈቀደ “ የሆነዉ የጌዴዎን ልጅ ነበር ፤ የአቤሜሌክ እናት ከጌዴዎን ቁባቶች ዉስጥ የሆነች ከነዓናዊት ነበረች ፡፡ እንደ አንድ ቁባት ልጅ አቤሜሌክ ከጌዴዎን ከ70 ዎቹ ልጆች ዉስጥ አልነበረም ከጌዴዎንም ዉርስ አልነበረው ፤ 70 ልጆች በደህና እየኖሩ ነበር አቤሜሌክ ግን አልነበረም ፡፡ አቤሜሌክ ለስልጣን በቅናት በመፈለግ ታገለ ፤ ለስልጣን በመፈለጉ አቤሜሌክ በእግዚአብሄር ህግ ስርዓት ላይ ተረማመደ ፤ የእናቱን ከነዓናዊት ወገኖች ለማዉራት ወደ ሴኬም ሄደ በጌዴዎን 70 ልጆቹ መመራት የሚፈልጉ እንደሆን ወይም ደግሞ ከእነርሱ በሆነ በአንዱ -በእርሱ እንደሆነ ጠየቃቸው (ቁጥር 1-2)፡፡ ከነዓናዊያን ወገኖችም በሴኬም የቀሩትን ጌቶች አቤሜሌክ የእነርሱ ቤተሰብ አካል በመሆኑ ለመምራት ትክክለኛዉ ሰዉ እንደ ነበር አሳመኑዓቸው (ቁጥር 3) ፤ አቤሜሌክ ከባዖልብሪትም ቤት በአንድ ድንጋይ ላይ 70 ወንድሞቹን ለመግደል ለነፍሰ ገዳይነት ለመቀራየት የሚጠቀምባቸዉን 70 ቁርጭ ብር ተሰጥቶት ነበር (ቁጥር 4-5) ፤ በአንድ ድንጋይ መሰዊያ ላይ 70 ሰዉነቶች ሲሰዉ ማየት ምን እንደ ሚመስል አስባችሁታል ? ከዚያም የሴኬም ሰዎች አቤሜሌክን ንጉሳቸዉ አደረጉት (ቁጥር 6) ፡፡ ንጉሳቸዉ አድርገዉ ሾሙት ነገር ግን የእግዚአብሄር ንጉስ አልነበረም ፡፡ የጌዴዎን ከሁሉም የሚያንሰዉ ልጅ ኢዩአታም በመሸሸግ ከጭፍጨፋዉ ዳነ (ቁጥር 5) ፤ የእርሱ ማምለጥ የእግዚአብሄርን ልዓላዊነት ያሳያል ፡፡
መሳፍንት (9፡ 7-21)፡ ኢዩአታም አቤሜሌክ ንጉስ ሆኖ ባገኘዉ ጊዜ ከገሪዛን ተራራ ራስ ላይ በመሆን ስለ ዛፎች ምሳሌን ተናገረ (ቁጥር 7) ፤ በምሳሌዉ ዉስጥ፡
ዛፎቹ አንድ ሰዉ እንዲመራቸዉ ይፈልጉ የነበሩትን አምራች ሰዎች የሆኑትን የሴኬምን ሰዎች ይወክላሉ ፡፡
የወይራ ዛፍ ዘይት ያመነጫል እናም ንጉስ ለመሆን እንዲያደርግ ተፈጥሮበት የነበረዉን ማድረጉን ለማቆም እምቢ አለ ፡፡
የበለስ ዛፍ ጣፋጭ ፍሬ ያመነጫል እናም ንጉስ ለመሆን እንዲያደርግ ተፈጥሮበት የነበረዉን ለማቆም እምቢ አለ ፡፡
የወይን ጠጅ የወይን ፍሬ ያመነጫል እናም ንጉስ ለመሆን እንዲያደርግ ተፈጥሮበት የነበረዉን ለማቆም እምቢ አለ ፡፡
አስታዉሉ ሁሉም ሰዉ በራሳቸዉ ኑሮ ትክክል የነበረውን እያደረጉ ነበር (መሳ 17፡ 6) ፤ በአሜሪካ ይህ እዉነት አይደለም ? በእኛ ላይ ለመግዛት በዙሪያችን አረመቾ ከፍ ከፍ በማለታቸዉ ላይ በማትኮር በጣም ተጠምደናል ፡፡
አረም ምንም አያመነጭም ነገር ግን ንጉስ ለመሆን ፍቃደኛ ነበር እንዲሁም ንጉስ የማያደርጉት ከሆነ የዛፎችን ደህንነት ያስፈራራ ነበር ፡፡
በቁጥር 16 ኢዩአታም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ ፤ የሴኬም ሰዎች አቤሜሌክን ንጉሳቸዉ በማድረግ ከእምነታቸዉ ዉጪ አድርገዉ ከነበር በይሩበአልና በቤተሰቡ መልካም ነገር አድርገዉ ከነበር በአደረጉት ነገር ደስ ሊላቸዉ ይችላል (ቁጥር 17-19) ፤ ነገር ግን ከእምነታቸዉ ዉጪ አድርገዉ ከነበር እና በይሩበአልና በቤተሰቡ ትክክል ነገር አድርገዉ ካልነበር አንዱ ከሌላዉ በእሳት የሚበሉ ይሆናሉ (ቁጥር 20) ፡፡ በቀላሉ ሲቀመጥ ለእግዚአብሄር ተግብረዉ ካልነበር በዚህም መጓዙን ከቀጠሉ እርስ በእርሳቸዉ ይጠፋፋሉ ፡፡ በአለመስማማታቸዉ ወደ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሄር እሳት እየመጣ ነበር ፡፡
መሳፍንት (9፡ 22-55)፡ አቤሜሌክ ለሰዎስት አመት ንጉስ ከሆነ በኋላ እግዚአብሄር በሴኬም ጌቶች እና በንጉስ መካከል ክፉ መንፈስን ላከባቸው ፡፡ የሴኬም ሰዎች በተራሮች በኩል ላይ ሲያልፉ የደፈጣ ጦር ለመዝረፍ በማስቀመጥ በአሜሌክ ላይ አመፁ (ቁጥር 22-25) ፤ አቤሜሌክ ግብር እና ቀረጥ እንዲሁም የማጥቃት ዝናዉን አጣ ፤ አንድ ሰዉ ገዓል የሚባል (የስሙ ትርጉም “የሆነ አስጠሊታ”) ከአቤሜሌክ ስልጣን ለመዉሰድ እድሎችን አየ፡፡ በአምላካቸዉ ቤት ሊያከብር እና ወይን ሊለቅም ከሴኬም ጌቶች ጋር ሄደ (ቁጥር 26-27) ፤ ገዓል አቤሜሌክን ለመግደል ማሴር ጀመረ (ቁጥር 28-29) ፡፡ የከተማይቱ ገዢ ዜቡል ስለ ገዓል እቅድ በመስማቱ አቤሜሌክ እንዲያዉቅ ፈቀደ በገዓል እና በተከታዮቹ ላይ ድብቅ ጦር በማደራጀት ተራዳ (ቁጥር 35-36) ፤ በመካከላቸዉም ጦርነት ተጀመረ ፤ በዉጊያዉ አቤሜሌክ ጋዓልን ገደለዉ ገዓልን ይከተሉ የነበሩ የሴኬምም ሰዎች ተገደሉ (ቁጥር 37-45) ፡፡
ከዉጊያዉ በኋላ የሴኬም ጌቶች እና ሰዎች ወደ ኤልብሪት ቤት ምሽግ ዉስጥ ገቡ ፤ አቤሜሌክ በዚያ በአንድ ላይ እንደ ተሰበሰቡ በሰማ ጊዜ ከዛፍ ላይ ቅርጫፎቹን ለመቁረጥ ምሳር ተጠቀመ ከእርሱም ጋር ለነበሩት ሰዎች ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ ነገራቸው ፡፡ በምሽጉም ዉስጥ ቅርንጫፎቹን በመዉሰድ አቃጠሉዓቸው ፤ 1,000 ያክል ወንዶች እና ሴቶች በምሽጉ ዉስጥ ሞቱ (ቁጥር 46-49) ፡፡ የኢዮአታም እርግማን ከገሪዛን ተራራ በዚህ እሳት ተፈፀመ ፡፡
የእርግማኑ ሌለኛዉ አካል የነበረው በብዙ አቤሜሌክ በእሳት የሚበላ ይሆናል ፤ አቤሜሌክ ወደ ቴሴብ ሄደ በዚያ ያሉትም ሰዎች በሌላ ምሽግ ተሸሸጉ ፤ አቤሜሌክም እንደ ለመደዉ ለማቃጠል ምሽጉን ተጠጋ ነገር ግን አንዲት ሴት በአሜሌክ ራስ ላይ በማረፍ ራሱን የፈነከተዉን የወፍጮ መጅ ከላይኛዉ መስኮት ጣለችበት ፡፡ አቤሜሌክ በሰይፍ እንዲገድለዉ ጋሻ አዣግሬዉን ጠራዉ በዚህም ማንም በሴት ተገድሏል አይለዉም ፤ ጋሻ አዣግሬዉም ነግሮት እንደ ነበረው አደረገ አቤሜሌክም በሞተ ጊዜ ህዝቡ ወደ ቤት ተመለሱ (ቁጥር 50-55) ፡፡
መሳፍንት (9፡ 56-57)፡ የእግዚአብሄር እቅድ እና አላማ በሰዎች ሊታገድ አይችልም ፡፡ ሁል ጊዜ የእግዚአብሄር እጅ የፍትህን ደረጃ (ከፍታ) ሲያመጣ እናያለን ፡፡
መሳፍንት (10፡ 1-6)፡ እግዚአብሄር “ እስራኤልን ነፃ ማዉጣት የጀመረ “ እንደ ፈራጅ የፎሐን ልጅ ቶላን አስነሳ ፤ ለ23 አመትም ፈረደ (ዳኘ) (ቁጥር 1-2) ፡፡ ከቶላ በኋላ እግዚአብሄር ለ22 የፈረደ ገለዓዳዊዉን ኢያዕርን አስነሳ (ቁጥር 3-5) ፡፡
ያም እንዲያደርጉ ተነግረዉ የነበረዉን እያደረጉ እስራኤላዊያን በመሳፍንት ስር የነበሩበት የ45 አመት ጊዜ ነው ፤ ነገር ግን ከዚያ በኋላ እስራኤላዊያን በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር አደረጉ (ቁጥር 6) ፡፡ እስራኤላዊያን ከእግዚአብሄር በሚመለሱበት በእያንዳንዷ ጊዜ የኃጢዓታቸዉ ጥልቀት የጠለቀ እና ያመለኩዓቸዉ ጣዖት አምላኮች ዝርዝርም ረዝሟል (በዝቷል) ፤ በሂደት ኃጢዓታቸዉም ከፋ ፡፡
መደምደሚያ
በአሁኑ ጊዜ ለዕኛ ምን ይመስላል ? በዚህ አለም ለስልጣን የሚቀኑ እና የተራቡ ሁል ጊዜ አቤሜሌኮች ይኖራሉ ፤ ሁል ጊዜ ለስልጣን የተራቡ እና ሌሎች ባላቸዉ የሚቀኑ ሰዎች ይኖራሉ ፤ ግን በዚያ የምንጓዝ ነን ? ልክ እንደዮናትን በመቆም በዚህ ላይ የእግዚአብሄርን መልዕክት የምንናገር ነን ? እግዚአብሄር ለእኛ በአለማችን መዘበራረቅ ላይ ለመቆም (ለማስተካከል) የተመለከተ(ያተኮረ) ነው ፡፡
የኔ ሙግት በዳኛ በኩል ስንጓዝ እግዚአብሄር ያለዉን እዉነት አንስተዉም የሚል ነው ፤ እናም በእርሱ ፍትህ የምንጓዝበት ምህረት እን ፍቅር አለ ፡፡
ጥያቄዎች
-
አቤሜሌክ በአባቱ 70 ወንድሞቹን ለምን ገደላቸው ? የሴኬም ዜጎች በዚያ የተስማሙ የሚሆኑበት ለምን ነበር ? (መሳ 9፡ 1-6)
-
በኢዩአታም የተነገረዉን ምሳሌ አንብቡ ፤ እንዴት ትተረጉሙታላችሁ ? ለጥቂት ተረጋግታችሁ የተቀመጣችሁበትን ጊዜ ማስታወስ ትችላላችሁ ?
-
እግዚአብሄር አቤሜሌክን እና የሴኬምን ህዝቦች እንዴት ቀጣቸው ? ተገቢ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ?
-
እስራኤልን እንደ ገና ለፍልስጤማዉያን እና አሞናዉያን እግዚአብሄር ለምን መልሶ ሰጣቸው ? (መሳ 10፡ 6-8)
-
ከቀደሙት እስራኤላዉያንን ያዳናቸዉ ማን እንደ ሆነ እግዚአብሄር ማንን አላቸው (መሳ 10፡ 11-12) አሁን አልረዳችሁም ለምን አላቸዉ ? (መሳ 10፡ 13)
-
መሳፍንት (9-10) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Judges 9:56-57
“In this way, God turned back on Abimelech the evil that he had done against his father, by killing his 70 brothers. And God also returned all the evil of the men of Shechem on their heads. So the curse of Jotham son of Jerubbaal came on them.”
የጌዴዮን ልጅ አቤሜሌክ በህዘቡ ላይ እርሱ ያሰበውን ስልጣን አለገኘም ነበርና ቤተሰቦቹን በቅናት ተመለከታቸው በጭካኔ የተሞላም ነገር አደረገባቸው ፡፡ እርሱም ወንደሞቹ የሆኑትን የጌዴዮን ሰባ ልጆች አረዳቸው ኢዮአታም ግን ሸሽቶ ነበርና ተረፈ ፡፡ ነገር ግን አቤሜሌክ እግዚአብሔርን በመተው ክፉ የሆነውን ማድረግ ቢቀጥልም እንኳ እግዚአብሔር ሉአላዊ ነውና እጁ ከእስራኤል ጋር ነበረች ፡፡ አቤሜሌክም በውጊያ ሙሀል በወፍጮ ድንጋይ ተመትቶ በከባዱ ተጎዳ ፡፡ እግዚአብሔርም ክእስራኤላውያን ጋር በውጊያ ነበር ድልንም ያቀዳጃቸው ነበር ፡፡
ይህ ስለ ሳተና ሙሉ ለሙሉ ከእግዚአብሔር ሀሳብ ውጭ ስለሚንቀሳቀሰ ሰው የሚያወራ ታሪክ ነው ፡፡ ቢሆንም ግን እግዚአብሔር በዙፋኑ ነውና የተሳሳተውና በራስ ወዳድነት የተሞላው የሰው ሀሳብ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን ሀሳበ ሊያሸንፍ አይችልም ፡፡ ዛሬ ይህን መስማት ይኖርብህ ይሆናል በእስራኤላውያን ላይ ተሰፋ ቆርጦ እንደማያወቅ ሁሉ እግዚአብሔር ባንተም ተስፋ እንደማይቆርጥ ፡፡ እርሱ በማይታዩት ከባድ በሆኑት የትግል ጊዜያት ሳይቀር እርሱ በዚያ አለ እናም እርሱ ደግሞ አሸናፊ ነው ፡፡ አንተ በጭንቀት ወስጥ ሳለህ እንኳ ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር አምላክ ባንተ ዙሪያ አለ ፡፡
“ እንድሁ ሰባ ወንድሞቹን በመግደል አቤሜሌክ በአባቱ ላይ ያደረገውን ክፋት እግዚአብሔር መለሰበት ፡፡ እግዚአብሔርም የሴኬምን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ መለሰባቸው የይሩበኣልም ልጅ የኢዮአታም እርግማን ደረሰባቸው ፡፡
- መሳፍንት 9፡56-57
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 134 (135) ፡ 6 –“ በሰማይና በምድር በባህርና በጥልቆች ሁሉ እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ አደረገ ፡፡ “
- ምሳሌ 16 ፡ 4 –“ እግዚአብሔር ሁሉን ለእርሱ ለራሱ ፈጠረ ኃጥአን ደግሞ ለክፉ ቀን ፡፡ “
- ቆላስያስ 1፡17 –“ እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።