Historical Books Judges

Lawlessness or Righteousness

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Judge Judges 11-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 217 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መሲሁ ኢየሱስ ያለፊት ቀናት የብሉይ ኪዳን እና የሚመጡት ቀናት የአዲስ ኪዳን ዳኛ ነው ፤ በሜንዲይ ስዕል በዱር ቀይ አበባ በኩል ሰላምን ታሳያለች ጠላቶች ደግሞ በእስራኤላዊያን ጣዖቶች ለመስረቅ፣ ለመግደል እና ለማጥፋት ይፈልጋሉ ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዳቸዉ መሳፍንቶች ላይ በመጣ ጊዜ እስራኤልን በሞገስ ደረጃ ከፍ ያደርጋል ፤ ደግሞ ደግሞ በመሳፍንት መፅሀፍ ዉስጥ የተካሄዱ መጥፎ ጊዜያትን እናያለን - የዥዋዥዌ ዘመንን “ ከስርዓት ኑሮ “ ወደ “ ቅድስና ለዉጥ “ ከዚያ እንደ ገና “ ስርዓት የሌለዉ(ህግ የሌለዉ) ኑሮ “ መወዛዘወዝ ፡፡ ጣዖት አምላኪነት ከሰባቱ ከተለያዩ ህዝቦች አምላኮች እና ጣዖቶች ጋር የነበር ክፉ ልምድ (በሽታ ነበር) (መሳ 10፡ 11) ፡፡ ሰባት እስራኤላዊያን በምድራቸዉ ቀርተዉ በነበሩት በሁሉም አህዛቦች እርግማን ስር ተጋልጠዉ የነበሩበትን የሚያሳይ የመፈፀም ምልክት ነው ፡፡

ትምህርት

መሳፍንት (11፡ 1-11)፡ ዮፍታሔ ታላቅ ጦረኛ ነበር ነገር ግን የጋለሞታ ሴት ልጅ ነበር (ቁጥር 1) ፤ ቀድሞ ማራገፍ ባልቻላቸዉ ነገሮች ምክንያት ብዙ ጓዝ ነበረው ፤ ወንድሞቹም እንኳን ወደ እርሱ ዞሩበት (ቁጥር 2) ፡፡ እስራኤላዊያን ሴተኛ አዳሪነትን ነቅፈዋል ፤ በአምልኮ ቤት ዉስጥ ገለሞታነት የተፈቀደ አልነበረም እናም የጋለሞታ ልጆች ያፈሩ እና በአምልኮ ቤት ዉስጥ መግባት የማይችሉ ነበር ፤ የቤተሰቦቹ ድርጊት ልጆቹን በኑሮአቸዉ ተከትሏቸዋል ፡፡ ዮፍታሄ ኃይለኛ ጦረኛ ነበር ነገር ግን ከእናቱ ድርጊት የተነሳ እፍረትን ተሸክሟል ፡፡ ለዛሬዉ ትምህርት የሚገፋፋን የቀድሞ ስራችን ምንም ይሁን እኛን አይገልፀንም ፤ መፅሀፍ ቅዱስ በኢየሱስ ክርስቶስ ላሉት ኩነኔ የለባቸዉም ይላል (ሮሜ 8፡ 1) ፡፡

ዮፍታሄ ወደ ጦብ ምድር(ስሙ ርህራሄ ማለት ነው ) ሸሸ ስርዓት የሌላቸዉም ሰዎች ተቀላቀሉት (ቁጥር 3) ፤ በሌላ ትርጓሜ እነዚህ ሰዎች ወሮበላ እና ጮሌ በመባል ይጠሩ ነበር ፡፡ ጃይ ቬርኖን ሜክግዝ በዮፍታሄ ላይ ሰብኳል እንዲሁም ዮፍታሄ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ የሄደበትን ሂደት ገልጧል፡ የተሰደደ፣ የተደሰተ እና ስሜቱ የተቀሰቀሰ ነበር፡፡ ዮፍታሄ የተሰደደ መሆኑን ቀድመን አይተናል ፡፡

ዮፍታሄ የእግዚአብሄርን ርህራሄ ተረድቶታል ብዬ አላምንም ምናልባት ያህዌ (እግዚአብሄር) ማን እንደ ነበር ቀድሞ የመረዳት ችሎታ ነበረው ፤ ነገር ግን አሞራዊያን በእስራኤላዊያን ላይ ጦርነት ባደረጉ ጊዜ የገለዓድ ሽማግሌዎች እንደ ጦራቸዉ አዛዥ አድርገዉ በመመለስ ሊያመጡት ወደ ጦብ ዮፍታሄን ለማግኘት ሄዱ (ቁጥር 4-6) ፤ ዮፍታሄ ባለመቀበል መንፈስ መለሰላቸው (ቁጥር 7) ፤ ሽማግሌዎቹም ሌላ አማራጭ እንዳልነበራቸዉ ገለፁለት (ቁጥር 8) ፡፡ ዮፍታሄ እግዚአብሄር ድል ይሰጠዉ እና የገልዓድ መሪ ያደርገዉ እንደሆን በሁኔታዉ ለመሄድ ተስማማ (ቁጥር 9) ፤ እግዚአብሄርን እንደ ምስክር እንዲሆን በመማል ተስማሙ (ቁጥር 10) ፡፡ ዮፍታሄም ከእነርሱ ጋር በመሄድ በእግዚአብሄር መገኘት በህዝቡ ሁሉ ፊት ቃሎቹን ደገመ (ቁጥር 11) ፤ በመጨረሻም ዮፍታሄ በመደሰት እግዚአብሄር የተራዉ መሪ ለመሆን የተዘጋጀ ነበር ፡፡

ዮፍታሄ የሚለዉ ስም መክፈት፣ መልቀቅ ማለት ነው ፤ እንደ ገና የድልን በር እንዲከፍት፣ ነፃነት እና ለህዝቡ መለቀቅን እንዲያመጣ እግዚአብሄር ዮፍታሄን እያስነሳዉ ነበር ፡፡

መሳፍንት (11፡ 12-22)፡ ዮፍታሄ ለአሞናዊያን ንጉስ ለምን በምድሩ ሊዋጉት መጥተዉ እንደ ነበር መልዕክት ላከ (ቁጥር 12) ፤ አሞናዊያንም እስራኤላዊያን ምድራቸዉን ወስደዉባቸዉ እንደ ነበር መለሱለት (ቁጥር 13) ፡፡ ይህ ግማሽ እዉነት ነበር ፤ ቻርለስ ኢሊኮት “ ይህ በጣም የሚያሳምን የሚመስል ክስ ነበር ነገር ግን ከነባራዊዉ ሀቅ ጋር የሚጣጣም አልነበረም ፤ እስራኤላዊያን ከሞአባዊያን እና አሞናዊያን ጋር ግልፅ ጦርነት እንዳያደርጉ የተከለከሉ ነበር ነገር ግን የአሞራዊያን ንጉስ ሲዎን በሰላም በምድሩ በኩል በሰላም እንዲያሊፉ ፍቃዱን እምቢ ባለ እና ከእነርሱ ሊዋጋ በወጣ ጊዜ አሸንፈዉት ግዛቱን ያዙት ፤ በዚህ ግዛት ትልቅ አዉራጃ ሲጀመር በሞዓብ እና በአሞናዉያን ስር መሆኑ የነበረው ፍፁም እዉነት ነበር በሲዎንም ከእነርሱ ጋር ታግለዉ ነበር ፤ ነገር ግን እስራኤላዊያን የሚያደርጉት ምንም ነገር አለመኖሩ እና በጠላትነት በዘረዘሩዓቸዉ ላይ ለህዛባቸዉ ለማደስ ለግላቸዉ አላማ ማረፊያን ለማሸነፍ ደማቸዉን ማፍሰሳቸዉ ለመገመት የማይመስል መሆኑ ያ ጥያቄዉ እንደ ነበር ይገልፃል “ (ዘኁ 21፡ 21-26፣ ዘዳ 2፡ 19) ፡፡ ዮፍታሄ እስራኤላዊያን ከአሞናዊያን ጋር ለመዋጋት የተለዩ እንዳልነበሩ መለሰ ታሪካዊ ክስተቶችንም አስታወሳቸው (ቁጥር 14-22) ፡፡

መሳፍንት (11፡ 23-40)፡ ካሞሽ የአሞናዊያን እና የሞዓባዊያን ሀገራዊ አምላክ ነበር ፤ የሚያጠፋ፣ የሚቆጣጠር እና የአሳ አምላክ ማለት ነበር የስሙ ትርጉም ፡፡ ንጉስ ሰለሞን ለእስራኤል የኬሞሽን አምልኮ ያስተዋዉቃል ቆይቶም በንጉስ ኢዮስያስ አመታት ከእስራኤል ተግባሩን ያጠፋል ፡፡ ዮፍታሄ አሞናዊያን ለምን አምላካቸዉ ኬሞሽ ሰጥቷቸዉ ያልነበረዉን እንደ ፈለጉ እና መልሰዉ ለማግኘት ለምን ከ300 አመት በላይ እንደ ጠበቁ ጠየቀ (ቁጥር 24፣ 26) ፤ ነገር ግን በአሞራዊያን ምድር አካባቢ ዉስጥ በሚጓዘዉ በዮፍታሄ ላይ የእግዚአብሄር መንፈስ መጣበት (ቁጥር 29) ፡፡ ዮፍታሄም ደስታዉ በማደጉ እግዚአብሄር በአሞናዊያን ላይ ድል የሚሰጠዉ ከሆነ መጀመሪያ ከቤቱ የሚወጣዉን እንደ ሚቃጠል መስዋዕት እንደ ሚያቀርብ ለእግዚአብሄር ተሳለ (ቁጥር 30-31) ፤ አስታዉሉ እግዚአብሄር ስለዚህ አልጠየቀዉም ዮፍታሄም ይህን መጥፎ ዉሳኔ አደረገ ፡፡ እግዚአብሄር የሰዉ መስዋዕት አልፈለገም አይፈልግም ፤ አምላካችን ያን አያደርግም ምክንያቱም በእርሱ ተፈጥሮ ዉስጥ ስለሌለ ፡፡ ዮፍታሄ በአካባቢዉ ባሉ አምላኮች ፍላጎት ለሁሉን ቻዩ እግዚአብሄር በመሳል ኃይማኖትን እየቀላቀለ ነበር ፤ ከአሞናዊያን ድል በኋላ (ቁጥር 32-33) በመመለሱ ሴት ልጁ ሰላም ልትለዉ ከቤት ወጣች (ቁጥር 34) ፡፡ ዮፍታሄ መሃላዉ (ስለቱ) የሴት ልጁን ነፍስ እንደ ሚወስድ እና የተናገረዉም ስለት መልሶ ሊወስደዉ እንደ ማይችል ሲያዉቅ በኃዘን ልብሱን ቀደደ (ቁጥር 35) ፡፡ እንደ ገናየዩፍታሄ እግዚአብሄር ፍቅርን፣ መጠንቀቅን እና የእግዚአብሄር ይቅር ባይነትን አለመረዳት አስታዉሉ ፡፡

በሚያናድድ ሁኔታ የልጁ እግዚአብሄርን መረዳት ከአባቷ ከዮፍታሄ የተሸለ አልነበረም ስለሆነም ስለቱን ከመፈፀሙ በፊት ስለ ድንግልናዋ በተራሮች ላይ ለሁለት ወር እንድታዝን አባቷ እንዲፈቅድላት ብቻ ጠየቀችዉ (ቁጥር 37) ፤ ተስማማ ሁለት ወሩም ካለቀ በኋላ ትመለሳለች ዮፍታሄም ስለቱን ይፈፅማል (ቁጥር 38-39) ፡፡ የእስራኤልም ወጣት ሴቶች ለአራት ቀናት የዮፍታሄን ሴት ልጅ በየአመቱ ያስቧታል (40) ፡፡

ይህ ለእኛ ለልጆቻችን በትክክል እግዚአብሄር ማነው የሚለዉን የሚያስተምሩ ቤተሰቦች ማን እንደሆኑ ያስታውሳል - የፍቅራችንን ስዕል፣ የእግዚአብሄርን ትክክለኛ ምህረት ለመሳል ፡፡

መሳፍንት (12፡ 1-6)፡ የኤፍሬም ነገድ ሰዎች ወደ ዮፍታሄ መጡ ምክንያቱም ከእርሱ ጋር አሞናዊያንን እንዲዋጉ ጠይቋቸዉ ስላልነበር በእርሱም ላይ ቤቱን ሊያቃጥሉት አስፈራሩት (ቁጥር 1) ፡፡ ከዉጊያዉ ኤፍሬም ከተሰረቀዉ እቃ ድርሻ ፈለጉ ፤ ዮፍታሄ ጠይቋቸዉ እንደ ነበር ነገር ግን አልሄድም እንዳሉት ገለፀ ስለሆነም ከእነርሱ ዉጪ ተዋጋ (ቁጥር 2-3) ፡፡ በሚያናድድ ሁኔታ ገለዓድ እና ኤፍሬም እርስ በእርስ ወደ ጦርነት ገቡ ገለዓድም ኤፍሬምን አሸነፈው ፤ በዉጊያዉም ከኤፍሬም 42 ሺህ ወታደሮች ተገደሉ ፡፡

መደምደሚያ

ይህን ክፍል እንዴት አድርገን እንደምንይዝ ለማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው ፤ ሁሉም አስደንጋጭ ነገሮች፣ እግዚአብሄርን የተሳሳተ መረዳት፣ በእስራኤል ነገዶች መካከል የእርስ በእርስ ዉጊያው - ሁሉንም ለመያዝ አስቸጋሪ ነው ፡፡ ከዚህ ልንወስደዉ የምንችለዉ አንድ ነገር በነፃነት እና ከአሮጌዉ አስተሳሰብ መንገድ፣ ከአሮጌዉ ትምህርት እና እግዚአብሄር ማን እንደ ሆነ ካሰብነዉ አሮጌ ሀሳብ ራሳችንን የምናስለቅቅ ሰዎች መሆን ያስፈልገናል ፡፡ እግዚአብሄር ሰዎችን ለመምታት የሚጠብቅ አይደለም ፤ እርሱ የእግዚአብሄር ፍቅር ነው ፡፡ ፀሎቴ በትልቁ ስዕል ላይ የሚያተኩረዉን፣ ትክክል የሆነዉን የሚለየዉን እና በፅድቅ እና በፍትህ የሚገዛዉን እግዚአብሄርን እንደ ዳኛ እንድናየዉ ነው ፡፡

  1. Jay Vernon McGee, “07 Judges 11-15 – J Vernon McGee – Thru the Bible”; available on youtube.com.

  2. Charles J. Ellicott, Ellicott’s Bible Commentary for English Readers: Judges 11:13; available at www.studylight.org/commentaries/ebc/judges-11.html.

ጥያቄዎች

  1. ዮፍታሄ በአባቶቹ ልጆች በወንድሞቹ ተሳደደ ነገር ግን ጦርነቱ በተጀመረ ጊዜ ሽማግሌዎች ተመልሶ እንዲረዳቸዉ እና እንዲገዛቸዉ ጠሩት ፤ በእናንተ የግል አስተያየት ዮፍታሄን ወንድሞቹ ያልሆኑት እንዲረዳቸዉ እና እንዲገዛቸዉ ለምን ጠየቁት ?
  2. የኤፍሬም ነገድ በመምጣት ዮፍታሄን ለመርዳት እምቢ ለምን እንዳለ ምን ታስባላችሁ ? በመበሳጨትለምን ሊገድሉት አስፈራሩት ? (መሳ 12፡ 1-6)
  3. የኤፍሬም ሰዎች ለማምለጥ እንዴት ሞከሩ ? ዉጤቶቹስ ምንድን ነበሩ ? ምን ያክሎቹ ህይወታቸዉን አጡ ?
  4. በመሳ (11፡ 27) እግዚአብሄር እንዴት ነበር የጠቀሰው ?
  5. በመሳፍንት (11-12) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Judges 11:1

“Jephthah the Gileadite was a great warrior, but he was the son of a prostitute, and Gilead was his father.”

ዮፍታሄም የእስራኤላውያን መሪና ታላቅ ተዋጊ ሆነ ፡፡ የዕብራውያን መጸሀፍት ጭምር ስለ እርሱ እምነት ያወሳሉ ፡፡ ዮፍታሄ እሰራኤላውያን አሞናውያንን ያሸንፉ ዘንድ በድፍረትና በተለየ መንገድ መርቷል ፡፡ ምንም እንኳ ዮፍታሄ የጋለሞታ ልጅ ቢሆንም የትላንት ታሪኩ እርሱን ይገልፀው ዘንድ አልፈቀደም ፡፡ እርሱ በከባድና በማይመቹ ሁኔታዎች ውሰጥ ሁሉ ለእግዚአብሔር የገባውን ክዳን ያከብር ነበር ፡፡ በእምነትም ውስጥ ሁኖ እስራኤላውያንን በውጊያ ይመራ ነበር ፡፡

የትላንት ታሪክህ አንተን አይገልፅህም ምናልባት አንተ ትላንት በሱስ ህይወት ወስጥ አልፈህ ይሆናል ወይም ደግሞ ከተፋቱ ባልና ሚስትም ልትገኝ ትችላለህ ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ይመስገን የቤተሰቦችህ ታሪክ አንተን አይገልፅህም ፡፡ ኢየሱስን ስታምንና ከእርሱ ጋር ስትራመድ ይህንን አስታውስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን ፡፡ አንተ አድስ ፍጥረት ነህ አሮጌው ነገር አልፏል አድሱ ደግሞ መጥቷል ፡፡ በእናትህ ማህፀን የሰራህ እርሱ ላንተ ዓላማ አለው ፡፡ በእርሱ ለሚታመኑት ለእነርሱ እርሱ ሁሉን አያይዞ ለመልካም ያደርገዋል ፡፡ አሁን ባለህበት በክርስቶስ ውስጥ ተመላለስ ፡፡

“ ገለዓዳዊውም ዮፍታሔ ጽኑዕ ኃያል ሰው የጋለሞታ ሴትም ልጅ ነበረ ፡፡ ገለዓድም ዮፍታሔን ወለደ ፡፡ “

- መሳፍንት 11፡1

ተጨማሪ ትቅስ

  • ሮሞ 8፡28 –“ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንድደረግ እናውቃለን ፡፡ “
  • 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17 –“ ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው አሮጌው ነገር አልፎአል እነሆ ሁሉም አዲስ ሆኖአል ፡፡ ”
  • ዕብራውያን 11፡32-34 –“ እንግድህ ምን እላለሁ ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሳምሶን ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና ፡፡ እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ ጽድቅን አደረጉ የተሰጠውን የተሰፋ ቃል አገኙ የአንበሶችን አፍ ዘጉ የእሳትን ኃይል አጠፉ ከሰይፍ ስለት አመለጡ ከድካማቸው በረቱ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ ፡፡ “