Historical Books Judges

The Appearance of the Pre-Incarnate Christ

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Judge Judges 13-14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 218 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ ስንጀምር ማሳሰቢያ ማድረግ እፈልጋለሁ ፤ ይህ የእግዚአብሄር ቃል ነው - አልሰራሁትም ፡፡ በቀሩት መሳፍንቶች ዉስጥ በእዉነት የእብደት(ከባድ) የሆኑ ታሪኮች አሉ ፤ ለዚህ ነዉ የእግዚአብሄርን ቃል ለማጥናት በጣም አስደሳች የሆነው ፡፡ ፀሎታችን በመሳፍንት መፅሀፍ ባሉ አስቸጋሪ ነገሮች መከል ላይ አይኖቻችንን በእግዚአብሄር ላይ እንድናደርግ ይህ ጥናት የሚያድስ እንዲሆን ነው ፡፡

ትምህርት

መሳፍንት (13፡ 1-5)፡ እንደ ገና እስራኤላዊያን በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር አደረጉ ለፍልስጤማዉያንም ለ40 አመታት አሳልፎ ሰጣቸው (ቁጥር 1) ፡፡ መጀመሪያ ላይ እንዳለዉ ሌላ በእስራኤላዊያን አለመታዘዝ፣ መቀጣት፣ በመሳፍንት በኩል ነፃ መዉጣት እና መታደስ ላይ ተመልሰን እንመለከታለን ፡፡ ዳኛዉ በሞተ ጊዜ ኡደቱ እንደ ገና ይጀምራል ፤ ለምሳሌ በብዙ መሳፍንቶች ይህን ኡደት ስለነዋል (አይተነዋል) እነሱም፡ ጎቶንያል (መሳ 3፡ 7-9)፣ ናዖድን ( 3፡ 12-15)፣ ሰሜጋር (3፡ 31)፣ ድቦራ (መሳ 4፡ 1-4) እና ጌዴዎን (መሳ 6፡ 12) የመሳሰሉት ናቸዉ ፡፡ ከዳን ነገድ ሚስቱ መሀን የነበረች አንድ ሰዉ ነበር (ቁጥር 2) ፤ የእግዚአብሄር መለዓክም ማኑሄ ለሚባለዉ ሰዉዬ ሚስት በመገለጥ ከዉልደቱ ጀምሮ ለእግዚአብሄር ናዝራዊ የሆነ አንድ ልጅ እንደ ምትፀንስ ነገራት ፤ ስለዚህም የማኑሄ ሚስት ወይን ወይም ቢራ ወይም ደግሞ ንፁኅ ያልሆነ ምንም አይነት ነገር መብላት አትችልም (ቁጥር 3-5) ፡፡ በተጨማሪም የልጇንም ፀጉር በፍፁም መቁረጥ አትችልም ምክንያቱም ከፍልስጤማዉያን እስራኤልን ማድን ስለሚጀምር ፡፡

የእግዚአብሄር መልዓክ የነበረዉ ቅድመ ክርስቶስ እንደ ነበር እናምናለን ፡፡ ፈጣሪዉ በማኑሄ ሚስት ፊት ልጅ እንደ ሚኖራት ሊነግራት ቆሞ ነበር ይህ ማለት ትርጉሙ ልጁ በእርሱ በኩል እንደ ሚፈጠር የሚፈጠር እንደ ሆነ ነው (ዮሐ 1፡ 1-4፣ ቆላ 1፡ 15-16) ፡፡ በብሉይ ኪዳን ዉስጥ ቅድመ ክርስቶስ (ክርስቶስ ቀድሞ) ታይቶባቸዉ የነበሩ ሁኔታዎች አሉ፡

  • ዘፍ (12፡7) - ከአብርሃም ጋር
  • ዘፍጥረት 16 - ከአጋር ጋር
  • ዘፍጥረት 18 - ከአብርሃም እና ከሳራ ጋር
  • ዘፍጥረት 21 - ከአጋር ጋር
  • ዘፍ (22፡ 11-14) - በአብርሃም እና በይሳቅ ላይ ጣልቃ ሲገባ
  • ዘፍጥረት (24፡ 7, 40) - ከአብርሃም አገልጋይ ጋር
  • ዘፍ (31፡ 11) - በህልም ለያዕቆብ ፤ ዘፍ (32፡ 24-43) - ከያዕቆብ ጋር በመታገል
  • ዘጸ (3፡ 2-22) - በሚነድደዉ ቁጥቋጦ ዉስጥ ከሙሴ ጋር
  • ዘጸ (13፡ 21፣ 14፡ 19፣ 23፡ 20-23፣ 32፡ 34፣ 33፡ 2) - በደመና እና በእሳት አምድ በእስራኤላዊያን ፉት ሲሄድ
  • ዘጸ (24፡ 9-11) - ለእስራኤል ሽማግሌዎች ተገለጠ
  • ዘጸ (33፡ 9-23፣ 40፡ 38) - ለሙሴ
  • ዘኁ (22፡ 22-35) - ለበለዓም በአህያዋ በኩል
  • ኢያ (5፡ 14) - እንደ እግዚአብሄር ጦር አዛዥ

መሳ (2፡ 1-3፣ 5፡ 23) - ለእስራኤል

መሳ (6፡ 11-24) - ለጌዴዎን

የቅድመ ክርስቶስ መልክ በብሉይ ኪዳን ዉስጥ ሁሉም ታይቷል ፡፡

መሳፍንት (13፡ 6-11)፡ ሴትየዋም “ የሚያስደነግጥ የእግዚአብሄር መልዓክ “ ስለ ሚመስለዉ ሰዉዬ እና ነግሯት ስለነበረው ለማኑሄ ነገረችዉ (ቁጥር 6-7) ፡፡ ሌሎች አይተዉት የማያዉቁትን እና አዉርተዉት የማያዉቁትን የእግዚአብሄር መልዓክ እንደ ሚመስል እንዴት ያውቃሉ ? ለሚስቱ ዜና በምላሹ ማኑሄ በመፀለይ ልጃቸዉን እንዴት እንደሚያሳድጉ እንዲያስተምራቸዉ የእግዚአብሄርን መልዓክ መልሶ እንዲልክ እግዚአብሄርን ጠየቀዉ (ቁጥር 8) ፡፡ ምን አይነት የሚገርም የአባት ፀሎት ነው ! የእግዚአብሄር ሰዎች እንደ አባት ተግባራቸዉን ለመያዝ(ለማግኘት) ምንድን እንዲያደርጉ እግዚአብሄርን ሲመለከቱ አስቡት ! ሮጣ ባሏን ላገኘችዉ ሴት እግዚአብሄር መልሶ መልዓኩን ላከላት (ቁጥር 9- 11) ፡፡ ወደ እርሱ በምንፀልይ ጊዜ እግዚአብሄር ሊሰማን እና ሊመልስልን ይፈልጋል (መዝ 145፡ 18፣ ሰቆ ኤር 3፡ 57፣ ያዕ 4፡ 8) ፡፡ ለሚስቱ ተናግሯት የነበረው ሰዉ እርሱ እንደ ነበር ማኑሄ ጠየቀ ( ቁጥር 11) ፤ የማኑሄ ፀሎት ተመልሶ እንዲመጣ ለእግዚአብሄር መልዓክ ነበር አንድ ፀሎት ዛሬም ለእስራኤል የሚያነሳ ከሆነ ለአማኞች ፀሎት ትንቢታዊ እንደ ሆነ አምናለሁ ፡፡ አሁን እስራኤል ችግር ዉስጥ ነች እና የእርሱ እርዳታ ያስፈልገናል ፤ ይህ አስቸጋሪ ነገር ነው - የእግዚአብሄር መለዓክ በእኛ በመጠበቅ ብዙ ሰዎችን በመጠበቅ ወደ እርሱ እንድናመጣቸዉ ይጠብቃል ፡፡

መሳፍንት (13፡ 12-18)፡ ቁጥር 12 እግዚአብሄር ትግስተኛ አምላክ እንደ ሆነ ያንፀባርቃል ምክንያቱም ማኑሄ ቀድሞ ተነግሯቸዉ ስለ ነበረዉ ነገር ነበር የጠየቀው ፤ የእግዚአብሄር መለዓክ ሚስቱ ምንድን እንደ ምታደርግ በመመለስ እንደ ገና ጠቀሰዉ (ቁጥር 13-14) ፡፡ ከዚያም ማኑሄ ለእርሱ ምግብ እስኪያዘጋጁ መለዓኩ ከእነርሱ ጋር እንዲቆይ ጠየቀው (ቁጥር 15) ፤ ማኑሄ የእግዚአብሄር መልዓክ እንደ ነበር አላወቀም ነበር ነገር ግን እንግዳ ተቀባይነትን አቀረበ ፡፡ ለማይታወቁ መለዓክቶች እንግዳ ተቀባይነትን ሰጥተዋል ብሎ ስለ ጠቀሰዉ ዕብ (13፡ 1) ሊሆን ይችላል ? መለዓኩም ምግቡን እምቢ በማለት ማኑሄን ለእግዚአብሄር የሚቃጠል መስዋዕት ማቅረብ እንደ ሚችል ነገረው (ቁጥር 16) ፡፡ ማኑሄ የእግዚአብሄርን መለዓክ ስም ጠየቀ ስሜ “ ድንቅ ነዉ “ በማለትም መለሰለት (ቁጥር 18) ፤ ኢሳ (9፡ 6) የሚለው “ ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል “ ፤ ስሙ “ ድንቅ “ ነው ፡፡

መሳፍንት (13፡ 19-24)፡ ማኑሄ ፍየል እና እህል ቁርባን በመዉሰድ እንደ ሚቃጠል መስዋዕት በአለት ላይ ለእግዚአብሄር አቀረባቸው (ቁጥር 19) ፡፡ ከመስዋእቱ ዉስጥ ነበልባሉ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ መለዓኩ በነበልባሉ ዉስጥ አረገ (ሄደ) ፤ ከዚያም ማኑሄ እና ሚስቱ የእግዚአብሄር መልዓክ እንደ ነበር አወቁ በግንባራቸዉም ተደፉ (ቁጥር 20) ፡፡ ብዙ ጊዜ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር እንደ ሚባላ እሳት ተገልጧል፡ ዘጸ (3፡ 2) - መልዓኩ በሚቃጠለዉ ቁጥቋጦ ዉስጥ፣ ዘጸ (14፡ 19) - መለዓኩ በእሳት አምድ ዉስጥ፣ መሳ (6፡ 21) ለጌዴዎን በስጋ እና በእሳቱ ፡፡

የእግዚአብሄር መለዓክ ለማኑሄና ለሚስቱ እንደ ገና አልተገለጠላቸዉም (ቁጥር 21) ፤ ማኑሄ እግዚአብሄርን አይቶ እንደ ነበር ባወቀ ጊዜ እንደ ሚሞት ጠብቋል (ቁጥር 22) ፡፡ ሚስቱ ምክንያቱን መናገር ትችል ስለ ነበር ወደ ህይወቱ እምነት አስገባች (ቁጥር 23) ፤ ከዚያም የማኑሄ ሚስት አንድ ወንድ ልጅ ስሙ ሳምሶን የሚባል ወለደች ( ትርጉሙም “ ትንሽ ፀሀይ “ ወይም “ ፀሀያማ ልጅ “ ማለት የሚቻል ነው ) ፡፡ ልጁም አደረ በእግዚአብሄርም የተባረከ ነበር (ቁጥር 24) ፤ ይህ ቃል በጣም ሉቃ (2፡ 52) ኢየሱስ በጥበብ፣ በሞገስ እና በእምነት እንዳደገው ተመሳሳይ ድምፅ ነው ፡፡ ሳምሶን የክርስቶስ ጥላ ነበር ፤ ዋይርስቤ የሳምሶንን ስም እንደ “ፀሀያማ “ ወይም “ ብርሃናማ “ ይተረጉመዋል “ በእርግጠኝነት ለማኑሄ እና ለሚስቱ ብርሃን እና ደስታ አምጥቷል ……እንዲሁም በፍልስጤማዊያን ጭቆና ጨለማ ቀናቶች ጊዜ ለእስራኤል ብርሃን ማምጣት እንደ ጀመረ “ ይተረጉመዋል ፡፡

መሳፍንት (13፡ 25)፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ወደ ሳምሶን ህይወት መምጣት ጀመረ ፡፡

መደምደሚያ

በመሳፍንት ለሳምሶን የተሰጡ አራት ምዕራፎች አሉ ፤ ነገ አስገራሚ ጥንካሬዉን እንዴት ሲጠቀምበት እንደ ነበር እና ለእግዚአብሄር እያደረገ የነበረው በመልቀቅ ለሴት እንዴት ደካማነቱን እንደፈቀደ እንመለከታለን ፡፡

ከዚህ ክፍል የምንወስደው ከዕብ (11፡ 32) ምንም እንኳን ህይወቱ የቆሸሸ ቢሆንም ሳምሶን በዕብራዊያን የእምነት አባትነት ቦታ የተዘረዘረ መሆኑን ነው ፤ በማንኛዉም በተሰጠ ጊዜ እግዚአብሄር ከእኛ ዉስጥ ማንኛችንንም ሊጠቀም ይችላል ፤ እንደ “ ሳምሶን “ ቤተሰቦች ወይም ደግሞ በተመሳሳይ እንደ “ ሳምሶን “ ሊጠቀምብን ይችላል ፡፡ ሰዎችን ወደ እርሱ የማመልከት እድል አለን ፡፡

  1. Thomas Constable, Dr. Constables Expositional Bible Study Notes: Judges, p. 147; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/judges.pdf.

  2. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Judges (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 146.

ጥያቄዎች

  1. እግዚአብሄር የማኑሄን ሚስት ወይን እና ጠንካራ መጠጥ እንዳትጠጣ አዘዛት ምክንያቱም ፀንሳ አንድ ወንድ ልጅ ስለ ምትወልድ ፤ ተመሳሳይ ትዕዛዝ የተቀበለ ወደ አይምሯችሁ የሚመጣ ሌላ አለ (ሉቃ 1፡ 15)? ስለ ዚህ ልጅ ምንድን ነዉ የተናገረችዉ ? (ዘኁ 6፡ 1-8፣ መሳ 13፡ 4-5፣ 7)
  2. የእግዚአብሄር መለዓክ ስለ ህፃኑ ወደፊት የማኑሄን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ቀድሞ ለማኑሄ ሚስት ሰጥቷት የነበረዉን ትዕዛዝ ብቻ (መሳ 13፡ 12-14) ለምን እንደ ደገመ ምን ታስባላችሁ ?
  3. ከፍልስጤማዊያን ነፃ ለማዉጣት ሲል እግዚአብሄር የሳምሶንን ህግ አለመታዘዝ (ዘዳ 7፡3) መጠቀሙ አስገርሟችኋል ? ዛሬስ እግዚአብሄር ከኛ አለመታዘዝ መልካም ያመጣል ? (ኢሳ 61፡ 3፣ ሮሜ 8፡ 28)
  4. በኃጢዓተኝነት ምርጫዉ ሳይሆን ሳምሶን እንደ እምነት ሰዎች ምሳሌ በዕብ (11፡ 32) ተዘርዝሯል ፤ በዚያ(በዚህ) የእግዚአብሄርን ፀጋ ታያላችሁ ? በቀድሞ ህይወታችሁ የኃጢዓተኝነት ምርጫ ቢኖራችሁም እንደ እምነት ወንድም ወይም እህት ራሳችሁን ማየት ትችላላችሁ ?
  5. አንድ ደቦል አንበሳ አጥቅቶ ሊያሸንፈዉ ወደ ሳምሶን መጣ በባዶ እጁም በመገነጣጠል ገደለዉ ፤ ይህን ለማድረግ የቻለዉ እንዴት ነበር (መሳ 14፡ 6፣ 16፡ 17) ? ሳምሶን የሚጮኸዉን አንበሳ ሰይጣንን ያሸነፈዉ የክርስቶስ ጥላ ነበር ? (ዕብ 2፡ 14፣ 1ጴጥ 5፡ 8፣ 1ዮሐ 3፡ 8)
  6. በመሳፍንት (13-14) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Judges 13:8-9a

“Manoah prayed to the Lord and said, ‘Please Lord, let the man of God you sent come again to us and teach us what we should do for the boy who will be born.’ God listened to[a] Manoah, and the Angel of God came again to the woman.”

የእስራኤልም ልጆች በእግዚአበሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ እግዚአብሔርም በፍልስጤማውያን እጅ አርባ አመት አሳልፎ ሰጣቸው ፡፡ በዝያን ጊዜም ስሙ ማኑሄ የተባለ ሰወና ሚሰቱ ልጅ መውለድ አይችሉም ነበር ፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ ለሚስቱ ተገልጦ ወንድ ልጅን እንደምትወልድ ነገራት ልጁንም እንደ ናዝራዊ እንዴት እንደምታሳድግ አስገነዘባት ፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ አላት “ ይሄ ልጅ እስራኤልን ከፍልስጤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል “ ፡፡ ሚስቱም የአግዚአብሔር መልአክ የነገራትን በነገረችው ጊዜ ማኑሄ እግዚአብሔር እንድያስረግጥለትና ልጁንም እንዴት እንድያሳድጉ እንድያስተምራቸው ወደ እግዚአብሔር ጠየቀ ፡፡ እግዚአብሔርም የማኑሄን ልመና ሰምቶ መልአኩን ወደ እነርሱ ላከ ፡፡ ከዝያም በኃላ እነርሱ የመጨረሻውን መስፍን ሳምሶንን ወለዱ ፡፡

ማኑሄ መልአኩ የነገራቸውንና ያዘዛቸውን የሰማው በሚስቱ በኩል ነበር የሰማውንም አምኖ ነበር ነገር ግን እርሱ ተጨማሪ ማሰረገጫን ፈለገ ፡፡ ማኑሄም በደንብ ለመረዳትና ለማረጋገጥ ወደ እግዚአብሔር ለመነ ፡፡ እግዚአብሔር ለሆነ ነገር እንደጠራህ ስታውቅ ነገር ግን በዙ ጥያቄዎች ሲኖርህ ወደ እርሱ ተመለስና ለበለጠ መረዳት ጠይቅ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔርን ከመጠየቅ ይልቅ ወደ መገናኛ ብዙሀን ጓደኞቻችን የሚያደርጉትን ወደ ማየት ወይም ደግሞ መፀሀፍትን ልናገላብጥ እንችላለን ፡፡ እግዚአብሔር ይመልስልሀል መንገድህንም ያሳይሀል ፡፡ ማንም ከእርሱ ጥበብን ቢፈልግ እርሱ ያለ ነቀፋ በልግስና እንድሰጠው ተናግሯል ፡፡ እርሱ በጨለማም ውሰጥ ይመራሀል ሀሳቡንም ያስታውቅሀል በመንገዱም ያስተምርሀል ፡፡ ከዚያ ያንተ ድርሻ ነው በእምነት መውጣት እንድታደርግ ወደ ሚመራህም በእምነት መራመድ ፡፡

“ ማኑሄም ጌታ ሆይ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እባክህ እንደገና ወደ እኛ ይምጣ ለሚወለደውም ልጅ ምን እንድናደርግ ያስገንዝበን ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ ፡፡ እግዚአብሔርም የማኑሄን ደምፅ ሰማ የእግዚአብሔርም መልአክ እንደገና ለሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች ተገለጠላት ባልዋ ማኑሄ ግን ከእርሱዋ ጋር አልነበረም “

መሳፍንት 13፡8-9

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 15 (16) ፡ 7-8 –“ የመከረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ ደግሞም በሌሊት ኩላሊቶቼ ይገሰጹኛል ሁለ ጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ በቀኜ ነውና አልታወክም ፡፡ “
  • መዝሙር 24 (25) ፡ 4-5 –“ አቤቱ መንገድህን አመልክተኝ ፍለጋህንም አስተምረኝ አንተ የመድኃኒቴ አምላክ ነህና በእውነትም ምራኝ አስተምረኝም ቀኑን ሁሉ አንተን ተስፋ አድረጌአለሁ ፡፡ “
  • ያዕቆብ 1፡5 –“ ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን ለእርሱም ይሰጠዋል ፡፡ ”