Historical Books Judges

The Strength of the Spirit

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Judge Judges 15-16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 219 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ወደ ክፍል 20 ስንጓዝ በጉ ወደ ሚመስለዉ ነገር ግን በእዉነታው ለራሱ ለብዙ ነገሮች ምክንያት ለነበረው ወደ ሳምሶን የህይወት አለም ወደ ተዘበራረቀዉ አለም እንመጣለን ፡፡ ሳምሶን እንደ ጀግና እና ነፃ አዉጪ እንዲሁም ተበቃይ የተገለፀ ነው ፤ ይሁን እንጂ የተሳሳተዉ ሳምሶን ለማስተካከል የነበረዉ ምክንያት እራሱ ነው ፡፡ ቻርለስሱፐርጎን “ የሳምሶን ጠቅላላ ህይወቱ በጊዜጣት የተከፋፈለ እና ተከታታይ የሆነ ተዓምራት እና ጅልነት እንደ ሆነ “ ተናግሯል ፡፡

የሳምሶን ችግር የጀመረዉ ገና ከመጀመሪያዉ ነው ፤ እግዚአብሄር ከማይከተሉ ሰዎች የሆነች አንዲት ፍልስጤማዊ ሴት ለማግባት አገኘ (መሳ 14፡ 1) ፤ ቤተሰቦቹ ሊያሳምኑት ቢሞክሩም ሳምሶንም ሄዶ ለእርሱ ሊያገኛት ፈለገ ፡፡ “ እፈልጋታለሁ “ የሚለዉ ንግግር ትርጉሙ ቃል በቃል “ በአይኖቼ ትክክል ነች “ ማለት ነው ፤ ይህ ሀረግ ሁልግዜ “ ሰዉን ወይም ድርጊትን ለመግለፅ በእግዚአብሄር አይን ትክክል ለነበረ “ የሚጠቀም ነው ፡፡ ( መዝ 25፡ 13) ፤ የሳምሶን አይን በእግዚአብሄር ላይ ሆኖ በነበር ይህ ጉዳይ አይሆንም ፤ ነገር ግን ሳምሶን ለስጋዉ ፈለገ እንጂ እንደ እግዚአብሄራዊ አይደለም (ቆላ 3፡ 1-2) ፡፡

ትምህርት

መሳፍንት (15፡ 1-5)፡ ሳምሶን ለሚስቱ እንደ ስጦታ አንድ ወጣት ፍየል ወሰደ ነገር ግን አባቷ እርሷን እንዲያይ አልፈቀደለትም (ቁጥር 1) ፤ በዚህ ልምድ ስጦታዉ ከወሲባዊ ግንኙነት በፊት የሚሰጥ ነበር ፡፡ ሳምሶን ይሁዳ በትዕማር አድርጎት በነበረው ተመሳሳይ ነገር እያደረገ ነበር (ዘፍ 38፡ 17) ፤ አቧቷም የሳምሶንን ሚስት ቀድሞ ለሌላ ሰዉ ሰጥቷት እንደ ነበር በመናገር በሷ ፋንታ ትንሻን ልጁን ለሳምሶን አቀረበለት (ቁጥር 2) ፤ በምላሹም ሳምሶን በፍልስጤም ላይ ለሚያደርሰዉ ጉዳት ተጠያቂ እንደ ማይሆን አሳወቀ (ቁጥር 3) ፡፡ ብሎክ ሳምሶንን “ በመፅሀፍ ከሌሎቹ ነፃ አዉጪዎች በሚበልጥ የተጠራ ሰዉ እንደሆነ ነገር ግን የራሱን ነገር በማድረግ ህይወቱን ያሳለፈ እንደ ነበር ይገልፀዋል “ ፡፡ በእግዚአብሄር የሚጓዙ ሰዎች የሚያስደንቅ ትልቅ ጥሪ እንዳላቸዉ አስባለሁ ነገር ግን ብዙዎች ልክ እንደ ሳምሶን የራሳቸዉን ነገር ማድረግ ይመርጣሉ ፡፡

ሳምሶን ሄዶ 300 “ ቀበሮችን “ ያዘ ፤ የዕብራዊ ቃል ለቀበሮ(ለተኩላ) እንዲሁም ለቀበሮ የሚጠቅም ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ተኩላዎች ብቸኛ እንሰሳቶች ቀበሮች ግን በመንጋ የሚሮጡ እንደ ሆኑና ለመያዝ ቀበሮች ቀላል እንደ ሆኑ በማመልከት ይናገራል ፡፡ ከዚያም በእያንዳንዱ ጥንድ እንስሳት ጅራት ላይ ችቦ በማሰር ችቦዎቹን በመለኮስ ወደ ፍልስጤም የእህል ማሳ ላካቸው ፤ እንደ ተበቃይ ሳምሶን የእህል ክምሮችን፣ የእህል ማሳዎችን፣ የወይን ተክሎችን እና የወይራ ዛፎችን አቃጠለ (ቁጥር 4-5) ፤ የሚፈልገዉን ካላገኘ ሳምሶን እንደ ዘራፊ ልጅ በመተግበር ፍልስጤማዊያን የነበራቸዉን ሁሉንም ነገር አቃጠለ ፡፡ ሳምሶን ህዝቡን ከፍልስጤማዊያን ነፃ እንዲያወጣ ኃላፊነት ተሰጥቶት ነበር ነገር ግን ፍርድ በራሱ ፍላጎት የተሸፈነ ነበር ፤ ከእግዚአብሄር በተጠራበት ምንም አላደረገም ነገር ግን በስጋዊነት ለመበቀል ፈለገ ፡፡

መሳፍንት (15፡ 6-8)፡ ፍልስጤማዉያን ሳምሶን እህላቸዉን ለምን አቃጥሎት እንደ ነበር በሰሙ ጊዜ አባትየዉን እና ለሳምሶን የምትገባዉን ሙሽራ በመዉሰድ እንዲሞቱ አቃጠሉዓቸው (ቁጥር 6) ፤ የጀመረዉ ቢሆንም እንኳን ሳምሶን በፍልስጤማዉያን ላይ በቀልን ተመለከተ (ቁጥር 7) ፡፡ ጭን ጭናቸዉን በመምታት “ በታላቅ አገዳደል ገደላቸው “ (ቁጥር 8) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ ይህ ማለት ሳምሶን ፍልስጤማዉያንን ገነጣጠላቸዉ ማለት እንደሆነ ይናገራል ፤ ከዚያም በኤጣም አለት ወዳለዉ ሸለቆ ሄደ ፡፡

መሳፍንት (15፡ 9-13)፡ ፍልስጤማዉያን ከሰሜን በመምጣት የራሳቸዉ ምድር ባልሆነዉ በይሁዳ ምድር በመስፈርበሌሂን ከተማ በድንገት ያዙዓት ፤ የይሁዳ ሰዎች ለምን ብለዉ በጠየቁዓቸዉ ጊዜ ፍልስጤማዉያን ሳምሶንን ለማሰር መጥተዉ እንደ ነበር እና ወደ ፍልስጤም ሊወስዱትም እንደ ሆነ መለሱላቸው (ቁጥር 9) ፤ ስለሆነም የእስራኤላዊያን የይሁዳ ጦር (3,000 ሰዎች) ሳምሶንን ለፍልስጤማዉያን ለማምጣት ሄዱ (ቁጥር 11-12)፡፡ ሳምሶን ተስማማ ነገር ግን እስራኤላዊያን እንደ ማይገድሉት እንዲምሉለት ጠየቀ ፤ ምሁራን ለምን ሳምሶን ይህን ዋስትና መጠየቅ አስፈላጊ ሆኖ ተሰምቶት በነበረው ክርክር አላቸው ፤ ምናልባትም የራሱን ሰዎች ማጥቃት አለመፈለጉ ይሆናል ፡፡ እስራኤላዊያንም ቃል በመግባት አዲስ ገመዶች በመዉሰድ ሳምሶንን አሰሩት (ቁጥር 13) ፤ “ ገመዶቹ ከቆዳ፣ ከፀጉር ወይም ከዕፅዋት የተሰራ ነበር …. ምናልባትም አዲስ ስለሆኑ ገመዶቹ ከሁሉም በሚበልጥ ጠንካሮች ነበሩ “ ፡፡

መሳፍንት (15፡ 14-20)፡ እስራኤላዊያን ፍልስጤማዉያን እርሱን እየጠበቁበት በነበረው ወደ ሌሂ(አሁንም በይሁዳ) ወሰዱት ፤ በእርሱ መያዝ ተደስተዉ ወይም በመበሳጨት እየጮኹ መጡ ፤ ነገር ግን የእግዚአብሄር መንፈስ ሳምሶንን ሲቆጣጠረው እጆቹን ይዘዉት የነበሩት ገመዶች በእሳት እንደ ተበላ ፈትል እግር (ከገመዶች ሁሉ እንደ ደካማዉ) ሆነ ፡፡ ሳምሶንም የአንድ አህያ መንጋጋ በማንሳት 1000 ፍልስጤማዉያንን ለመግደል ተጠቀመበት (ቁጥር 15) ፡፡ መንጋጋዉ አዲስ ስለ ነበር ሳምሶን እርኩስ የሆነን ነገር እየነካ እና የናዝራዊነቱን ስርዓት አንዱን መስፈርት እየጣሰ ነበር ፤ ይሁን እንጂ የእግዚአብሄር መንፈስ በእርሱ ላይ ስለመጣ ምናልባትም ችግር የለዉም ፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ በመሳፍንቶች ላይ የመጣበት ሌሎቹ ጊዜያት፡ መሳ (3፡ 10፣ 6፡ 34፣ 11፡ 29፣ 13፡ 25፣ 14፡ 6, 19፣ 15፡ 14) እነዚህ ናቸው ፡፡ ሮሜ (8፡ 14) ስለ እግዚአብሄር ልጅ ያወራል ፡፡

እግዚአብሄር ጨለማዉን፣ ክፉዉንና መዘበራረቁን በመሳፍንቱ በኩል ለመጣስ መንፈሱን ተጠቅሟል ፤ ከእኛም ጋር ተመሳሳይ ነገር ያደርጋል ፡፡

ሳምሶን አድርጎት የነበረዉን በአህያ መንጋግ እንደ ገደላቸዉ ተናገረ - አካላቸዉንም በክምር ከመራቸዉ (ቁጥር 16) ፤ ከዚያም ሳምሶን መንጋጋዉን በመወርወር ቦታዉን ራማትሌሒ ወይም የመንጋጋ ተራራ ብሎ ጠራው (ቁጥር 17)፡፡ ዋይርስቤ “ በመፅሀፍ ብዙ ጊዜ ፈተና የድል ደስታዎችን እንደ ሚከተል “ ያብራራል ፡፡ ሳምሶን ዉሃ በማጣቱ በጥም ሊሞት ስለ ነበር እግዚአብሄርን ተጣራ (ቁጥር 18) ፤ እግዚአብሄር ለሳምሶን ዉሃ ከመሬት ሰጠው ፡፡ ሳምሶን ከጠጣ በኋላ ቦታዉን ዓይንሀቆሬ ብሎ ጠራዉ ትርጉሙም “ የጥሪ ምንጭ ማለት ነው “ ምክንያቱም ለዉ እግዚአብሄርን ስለ ተጣራ (1ቆሮ 10፡ 4) ፡፡ በዘጸዓት ጊዜ ስለ እግዚአብሄር ዉሃ ሰጪነት ሳምሶን ስለ ማወቁ አናዉቅም ነገር ግን እግዚአብሄር ጥሪዉን ሊሰማ እንደ ሚችል እና ለፍላጎቶች እንደ ሚሰጠዉ አዉቋል ፡፡ ሳምሶን እስራኤልን ለ20 አመት ዳኘ (ቁጥር 20) ፡፡

መሳፍንት 16 ከደሊላ ጋር እና ሌሎች ፍልስጤማዉያን ጋር የሳምሶንን መገናኘት ይናገራል ፡፡ በእርሷ ፍቅር በመዉደቁ የጥንካሬዉን ሚስጥር ለእርሷ እንዲነግሯት ስሜቱን ለመጠቀም ሞከረች ፤ ሁለት ጊዜ ለእርሷ ዋሻት በእያንዷንዷ ጊዜ በማሰር ለፍልስጤማዉያን አሳልፋ ልትሰጠዉ ሞከረች ፡፡ በመጨረሻም ቢወዳት ኖሮ እንደሚነግራት በማለት አለቀሰች ፤ ስለሆነም የጥንካሬዉ ምንጭ ያልተቆረጠዉ ፀጉሩ እንደሆነ ገለጠ ፡፡ እንደ ተኛም ፀጉሩን ቆረጠችዉ ፍልስጤማዉያንም አሰሩት ፤ አይኖቹንም በማዉጣት እህል ወደ ሚፈጭበት በጨለማ ስፍራ አስቀመጡት ፡፡ በጨለማዉ ቤት ፀጉሩ ተመልሶ ማደግ ጀመረ ፤ አንድ ቀን ፍልስጤማዉያን በአንድ ላይ ተሰብስበዉ በኃይል እየጠጡ ነበር ፤ በሰከሩም ጊዜ በእነርሱ ፊት የመጣ ሳምሶን ነበራቸው ቤቱን ደግፈዉ በያዙት ምሰሶዎች መካከል ቆሟል ፤ ስምሶን እዉር ስለ ነበር የቤቱ ምሰሶዎች ያሉበትን መረዳት የሚችልበትን ስፍራ ጠየቀ ፤ ከዚያም ሳምሶን ለመጨረሻ ጊዜ ጥንካሬዉን እንዲሰጠዉ እግዚአብሄርን ጠየቀ ይህ ከሆነ የአይኑን እይታ ስለ ወሰዱበት ፍልስጤማዉያን ላይ በቀልን ማግኘት ይችላል ፡፡ የአይኑ እይታ መወሰዱ አስደናቂ ነው በጣም ብዙ ችግር እንዲያገኘዉ ስላደረገው ፡፡ ሳምሶን በሙሉ ኃይሉ ገፋቸዉ ምሰሶዎቹም በመዉደቅ ከ3,000 ወንዶችና ሴቶች የሚበልጦ ገደሉ ፤ ቁጥር 30 ሳምሶን በህይወቱ ካደረገዉ የሚበልጥ በሞቱ ብዙ ሰዎችን እንደ ገደለ ያወራል ፡፡

መዝጊያ

ሳምሶንን የምንመስል ብዙዎች ነን ፤ በቀናት ዉስጥ ስህተትን በማድረግ እንሄዳለን ፡፡ ጥሪ አለን ነገር ግን አቆሽሸነዋል ፤ ለእኛ በፍፁም የማይደርቅ ዉሃ አለን ፤ ዮሐንስ 7 የሚለው በእኛ ዉስጥ ህያዉ ዉሃ እንዳለ ነው ፤ ስለዚህ በዉስጣችን እና በእኛ በኩል በሚንቀሳቀሰዉ መንፈስ ቅዱስ ላይ መደገፍ አለብን ፡፡ ሳምሶን ያን በመርሳት ሁልጊዜ በእግዚአብሄር ከመደገፍ ይልቅ በራሱ ላይ ተደገፈ ፡፡ የህይወታችሁ መጨረሻ ከጥሪአችሁ ዉጪ እስኪሄድ ድረስ አትጠብቁ ፤ አሁኑ መጓዝ ጀምሩ ፡፡

  1. Warren W. Wiesrbe, The Bible Exposition Commentary: Judges (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 149.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 328.

  3. Nelson’s Commentary, p. 328.

  4. Nelson’s Commentary, p. 306.

  5. Nelson’s Commentary, p. 329.

  6. Nelson’s Commentary, p. 329.

  7. Nelson’s Commentary, p. 329.

  8. Nelson’s Commentary, p. 329.

  9. Wiersbe, p. 151.

ጥያቄዎች

  1. ሳምሶን ምን ያክል ቀበሮዎችን ያዘ (መሳፍንት 15) ? በዚያ የሚያደርገዉ አላማዉ ምን ነበር ?
  2. ከሳምሶን እና ከፍልስጤማዊያን ከበቀል አንፃር ከሁለቱም ምን ልትማሩ ትችላላችሁ ? (ማቴ 5፡ 38-42፣ ሮሜ 12፡ 19)
  3. ሳምሶን ለደሊላ የነገራቸዉ ሰዎስት ዉሸቶች ምንድን ናቸው ? በመጨረሻ ደካማ ስለሚያደርገው እዉነቱን ለእርሷ ለምን እንደ ተናገረ ምን ታስባላችሁ ?
  4. መፅሀፍት ልባችንን ስለ መጠበቅ ይናገራሉ ፤ ሳምሶን ልቡን ያልጠበቀባቸዉ ጥቂት መንገዶች ምንድን ናቸው ? (ምሳ 4፡ 23፣ ገላ 5፡ 16)
  5. የሳምሶን ጥንካሬ ከየት መጣ ? ሳምሶን እግዚአብሄር ከእርሱ እንደ ተለየዉ ለምን አላወቀም ? መንፈስ ቅዱስ በፍፁም እንደ ማይተወን እንዴት አረጋገጥን ? (ዮሐ 14፡ 16፣ ኤፌ 1፡ 13-14)
  6. በመሳፍንት (15-16) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Judges 15:19

“He became very thirsty and called out to the LORD…So God split a hollow place in the ground at Lehi, and water came out of it. After Samson drank, his strength returned, and he revived. That is why he named it En-hakkore, which is in Lehi to this day.”

የእግዚአብሔር እጅ በሳምሶን ላይ ነበረ ፡፡ ምንም እንኳ የአይሁድ ሰዎች በፍልስጤማውያን እጅ አሳልፈው ቢሰጡትም ከእግዚአበሔር የተቀበለው ሀይል ሳምሶንን አሸናፊ አድረጎታል ፡፡ እርሱ በአንድ የአህያ መንጋጋ አንድ ሺ ሰው የሚገድል ተዋጊ ነበር ፡፡ ምንም እንኳ ሳምሶን እርምጃውን ከአግዜአብሔር ጋር ባያደርግም እግዚአብሔር በወጊያ ድልን ያቀዳጀው ነበር ፡፡ ከድሉ በኋላም ሳምሶን ደከመው ውኃም ተጠማ ፤ በደከመው ጊዜም እግዚአብሔርን ስለ ውኃ ለመነ ፡፡ እግዚአብሔርም ውኃን ሰጠው ሳምሶንም ጠጣ በረታም እንደገናም ተነቃቃ ፡፡ በፍልስጤማውያን ዘመንም ለተጨማሪ ሀያ ዓመታት በእስራኤል ላይ ፈረደ ፡፡

እግዚአብሔር ወደ እርሱ እንድትመለስ ይጠብቅሀል ሰለዚህም ደግሞ ያበረታሀል ፡፡ ከእውነቱ ወተህ የሄድከው ርቀት ወይም ደግሞ በራስህ የኖርከው ህይወት ርዝመተ ለወጥ አያመጣም እግዚአብሔር ፈጽሞ አይተወህም ፡፡ እግዚአብሔር ላንተ ዕቅድ አለው ስለዚህም ወደ እርሱ ለእርዳታ እሰከምትጮኽ ይጠብቀሀል ፡፡ ከህይወት ውጣ ውረድ የተነሳ ልትጠማ ለትደክምም ተችላለህ ፤ ለመታደስ ወደ እርሱ ጩኽ እርሱ የኃይልህና የህይወት ወኃ ምነጭ ነወና ፡፡ እርሱም ነፍሰህን ይመልሳታል ያነቃቃህማል ፡፡ ብቻ ጠይቀው ፡፡

“ እርሱም እጅግ ተጠምቶ ነበርና አንተ ይህቸን ታላቅ ማዳን በባሪያህ እጅ ሰጥተሀል አሁንም በትም እሞታሁ ባልተገረዙትም እጅ እወድቃለሁ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ እግዚአብሔርም በሌሒ ያለውን አዘቅት ሰነጠቀ ከእርሱም ውኃ ወጣ እርሱም ጠጣ ነፍሱም ተመለሰች ተጠናከረም ፡፡ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ዓይንሀቆሬ ብሎ ጠራው የህም እስከ ዛሬ ድረስ በሌሒ አለ ፡፡ “

መሳፍንት 15 ፡ 18-19

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 2ኛ ሳሙኤል 7፡1 –“ እንድህም ሆነ ንጉሡ በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ እግዚአብሔርም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ ባሳረፈው ጊዜ ፡፡ “
  • መዘሙር 118 (119) ፡ 38 –“ በእርሱ ህያው አድርገኸኛልና ፍርድህን ለዘላለም አልረሳም ፡፡”
  • ዮሐንስ 7 ፡ 38 –“ በእኔ የሚያምን መጽሀፍ እንዳለ የሕይወት ወኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ ፡፡ “