Historical Books Judges

The Progression of Sin

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Judge Judges 17-18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 220 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለመሳፍንት መፅሀፍ ቃላችን ደኛ ሲሆን ወደ ባሪያ የመጣዉ ኢየሱስ እንደ ዳኛ አገለገለ ፤ እንደ ዳኛ ኢየሱስ ፍርድ እንደሚገባን ያዉቃል ነገር ግን በዚያ ፈናታ መታደግን መረጠ ፡፡ ከ300 አመታት የመሳፍንት ጊዜያት በላይ መሳፍንት ከመሳፍንት በኋላ የእስራኤልን ሰዎች ለማዳን እና ነፃ ሊያወጡዓቸዉ ሞከሩ ፤ ነገር ግን ሙከራቸዉ ሂደቱን አልጨረሰዉም ፡፡ መሳፍንት 17 ከእናቱ ወስዶ የነበረዉን 1100 ብር ባለቤት የነበረዉን የሚካን ታሪክ ይሰጣል ፤ የተቀረፀ ምስል በማድረግ በብር ሸፍና ለአሰራችዉ ለእናቱ መለሰላት ፡፡ የብሩ ምስል እንደ ተቀደስ አካል በሚካ ቤት በማስቀመጥ ከልጆቹ አንዱን ለራሱ እንደ ካህን ሰየመ(አቆመዉ) ፤ መሳ (17፡ 6) የሚለው “ በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉስ አልነበረም ፤ ሰዉም ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየዉን ያደርግ ነበር “ ፡፡ ሌዋዉያን በሚካ አካባቢ በተጓዙ ጊዜ ሚካ ካህን እንዲሆነዉ እራሱ ቀጥሯል ፤ ለምዕራፍ 18 መነሻችን ይህ ነው ፡፡

ትምህርት

የዳናዊያን ነገዶች “ ለግዛታቸዉ ለመያዝ ይመለከታሉ “ ፤ ይህ የሚያምታታ ነዉ ምክንያቱም የዳን ነገድ በ11 ሌሎች የእስራኤል ነገዶች መካከል ተስማሚ ምድር (ኢያ 19፡ 47) የመረጡትን ተሰጥቶአቸዉ ነበር ፡፡ በግልፅ አሁን ደግሞ ጎሳዉ ተጨማሪ ምድር ፈለገ ፤ በዳን ነገድ ኃጢዓት ዉስጥ እንጓዛለን ፡፡

መሳፍንት (18፡ 1-2)፡የቅናት ፍላጎት(ከፍተኛ ጉጉት) ፤ ቀድሞ ተሰጥቷቸዉ ከነበረዉ ሌላ ነገር ፈለጉ ፤ በመሳ (1፡ 34) አሞራዊያን ዳናዊያን ተሰጥቷቸዉ የነበረዉን ምድር በመዉሰድ ተቃርኖን አደረጉባቸዉ ስለዚህም ወደ ሌላ ስፍራ ሄዱ ፤ አሁን በመሳፍንት 18 ምድሪቱን እንዲያጠኑ ሰላዮችን ላኩ ፤ ለሌሎች ነገዶች ደርሶ ወደ ነበረበት ምድር ብቻ ሄዱ ፡፡ ወደ ሚካ ቤት መጡ በሜካ ቅዱስ ቤት ሌዋዉያንን አገኙአቸው ፤ ሰላዮቹም ምሽቱን በዚያ ቆዩ ፡፡

መሳፍንት (18፡ 3-6)፡እግዚአብሄራዊ ያልሆነ ምክር ፤ በሚካ ቤት ዋይርስቤ “የእግዚአብሄር ያልሆነ ምክር “ ብሎ የጠቀሰዉን ተቀበሉ ፡፡ ሰላዮቹም የሌዋዊዉን ንግግር ስላወቁ በዚያ ለምን እንደ ነበር ጠየቁት (ቁጥር 3) ፤ ሌዋዊዉ ከገለፀላቸዉ በኋላ ጉዞአቸዉ የተሳካ እንደ ሆነ እግዚአብሄርን እንዲጠይቅላቸዉ ጠየቁት (ቁጥር 4-5) ፡፡ ሰላዮቹ ያለማስተዋል ሌዋዊዉ የነገራቸዉን ተቀበሉ ምንም እንኳን በሌላ ነገድ የተከፈለዉ ቢሆንም (ምሳ 12፡ 26፣ 16፡ 16)፡፡ ብዙ ሀተታ ሰጪዎች ይህ ሌዋዊ የሙሴ የልጅ ልጅ “ የጌርሳም ልጅ ዩናታን “ እንደ ነበር ይስማማሉ (ቁጥር 30) ፤ ስለ መዋቅሮቹ ሲታሰብ የሙሴ የልጅ ልጅ የሚካ የግል ካህን በመሆን ይከፈለዉ ነበር ፤ በቅዱስ ስርዓቱ ላይ ይህ እርምጃ ነው ፡፡

መሳፍንት (18፡ 7-13)፡ተቃዉሞ እና ግድያ - ክፍል 1 ፤ ሰላዮቹ ወደ ሌሳም ሄዱ ከሚካ ቤት 125 ማይል እና ከሜዴትራሊያን ባህር ምስራቅ በኩል 30 ማይል ርቀት ያክል ይሆናል ፤ በዚያም “ ፀጥ እና ያልተጠረጠሩ “ ለመያዝም ቀላል የሚመስሉ የሲዶናዊያንን ሰዎች አገኙ (ቁጥር 7) ፡፡ በአዲስ ኪዳን ጊዜ ይህ በሜዴትራሊያን ምስራቅ ጫፍ የሚገኝ ወደብ እና ከተማ ነበር ፡፡ ሰላዮቹ ወደ ዳን በመመለስ ሰዎቹን ምድሪቱ ምልካም እንደ ነበረች እና ለመያዝም ቀላል እንደሚሆን ነገሩዓቸው (ቁጥር 8-9) ፤ በሙሴ መሪነት ስር ሰላዮቹ ወደ ምድሪቱ በገቡ ጊዜ ዳናዊያን ሰላዮች ፈርተዉ እንደ ነበር እና ምድሪቱን አለመዉሰድን እንደ መረጡ አስታዉሱ ፤ እነዚህ ሰላዮች ህዝቡን “ እግዚአብሄርም በምድር ካለዉ ነገር ሁሉ አንዳች የማይጎድልበትን ስፍራ በእጃችሁ ሰጥቶአል አሉ “ (ቁጥር 10) ፡፡

ስድስት መቶ ዳናዊያን የእነርሱ ወዳልነበረዉ ምድር ለመሄድ ቀረ (ቁጥር 11) ፤ የሆነ ጊዜ ላይ በዳን ከዚህ የሚበልጡ ብዙ ወታደሮች ነበሩ (ዘኁ 1፡ 38-39፣ 26፡ 42-43) ፤ ምናልባትም ይህ ብቸኛዉ ትንሽ ጦር ነበር ወይም ደግሞ ከወታደሮቹ ብዙዎቹ አልነበሩም ፡፡ ጦሩም መንገዱን ወደ ሚካ ቤት አደረገ (ቁጥር 12-13) ፤ እነዚህ ቁጥሮች ወደታች የምንሸፍነዉን ብጥብጥ እና ግድያን ያስቀምጣል ፡፡

መሳፍንት (18፡ 14-26)፡ መስበር እና መግባት፣ ዝርፊያ እና ዛቻ ፤ ሰላዮቹ ወንድሞቻቸዉን ስለ ሁሉም ጣዖቶች እና በሚካ ቤት ዉስጥ ስላለዉ መልካም ነገሮች ነገሩዓቸዉ የዳናዊያን ወታደሮች በመግቢያዉ በር ላይ በመጠበቅ ወደ ቤቱ መንገዳቸዉን በመቀየር አደረጉ (ቁጥር 14-16) ፡፡ ሰላዮቹም ወደ ቤቱ በመሄድ በብር የተሸፈነዉን ስዕል፣ በድንጋዮች የተሸፈነዉን ኢፉድ እና የቤት ዉስጥ ጣኦቶቹን ወሰዱ (ቁጥር 17) ፤ የሌዋዊዉ ካህን እያደረጉ የነበሩትን ጠየቃቸው (ቁጥር 18) ፤ ዝም እንዲል ነገሩት እንዲሁም ለጠቅላላዉ ነገድ ካህን አለመሆን ከአንድ ሰዉ ካህን ከመሆን አይሻልም በማለት ጠየቁት (ቁጥር 19) ፤ ይህ ተገቢ(ህጋዊ) ጥያቄ ነበር ምክንያቱም ጥያቄዉ ታማኝነቱ የትን እንደ ነበር ስለ ሆነ ፤ ጥያቄዎ ስለ ቁጥር አልነበረም ፡፡ በአሜሪካ ልንጠነቀቅ ያስፈልገናል ምክንያቱም በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የቤተ ክርስቲያንን ስኬት በህዝብ ቁጥር ለመለካት ስለምናዘነብል ፡፡

ሌዋዊዉም በመስማማት ኢፉዱን፣ ጣዖቶቹን እና የተቀረፀዉን ስዕል ከእነርሱ ጋር ወሰደ (ቁጥር 20) ፤ ትንሽ ልጆችን፣ እንስሳቶችን እና ንብረቶችን ለደህንነታቸዉ ሲሉ በወታደሮቹ ፊት አስቀመጡዓቸው “ ምክንያቱም ብዙ ጥቃቱ ከኃላ ስለሚመጡ “ ፡፡ ስለ ዳን ነገድ የያዕቆብ ትንብያ ስለ ነበረዉ በትክክል በዳን ነገድ ምንድን እየሆነ ነበር (ዘፍ 49፡ 17)፡ “ ዳን በጎዳና ላይ እንደ እባብ ይሆናል በመንገድም እንደ ቀንዳም እባብ ፤ ፈረሱን ከሰኮናዉ ይነክሳል “ ፤ በምዕራፍ 18 ይህ ትንቢታዊ ነገር ስለ መምጣቱ ለማየት እየጀመርን ነው ፡፡ ሚካ ቤት በተመለሰ ጊዜ ምንድን ተፈጥሮ እንደ ነበር አወቀ በቤቱ አጠገብ ያሉትን ሰዎች ከዳናዊያን ኃላ እንዲሄዱ ጠራቸው (ቁጥር 22) ፤ በዳናዊያንም ላይ ደረሱባቸዉ ዞረዉም ሚካን ለምን እያሳደዳቸዉ እንደ ነበር ጠየቁት (ቁጥር 23) ፡፡ ሚካም ከቤቱ ሁሉንም ነገር ለምን ወስደዉበት እንደ ነበር ጠየቃቸው (ቁጥር 24) ፤ ዳናዊያን ሚካን በእነርሱ ላይ እንዳይጮህ ወይም እርሱን እና ቤተሰቦቹን በማጥቃት እንደ ሚገድሉዓቸዉ ነገሩት (ቁጥር 25) ፡፡ ዳናዊያን በመንገዳቸዉ ቀጠሉ ፤ ሚካም ቤቱ ተመለሰ ምክንያቱም ዳናዊያን እርሱ ከነበረዉ ጠንካራ እንደ ነበሩ ስላወቀ (ቁጥር 26) ፡፡

መሳፍንት (18፡ 27-29)፡ተቃዉሞ እና መግደል - ክፍል 2 ፤ ዳናዊያን ወደ ሌሳ ሄዱ ህዝቡንም በመግደል ከተማዋን አቃጠሉ (ቁጥር 27) ፤ የሌንሳ ሰዎች ከማንም ጋር አንድነት ስላልነበራቸዉ ማንም ሊረዳቸዉ አልቻለም (ቁጥር 28) ፡፡ ዳናዊያንም ከተማዋን እንደ ገና በመስራት ዳን በማለት በዚያ ኖሩ (ቁጥር 29) ፤ የእነርሱ በማይሆነዉ ቦታ ሰፈሩ ፡፡ ዋይርስቤ “ በዛሬዉ አለም ሰዎስት የህይወት ፍልስፍዎች ብቻ እንዳሉ “ 1) የእኔ የሆነዉን እጠብቃለሁ፣ 2) የእናንተ የእኔ ነዉ እወስደዋለሁ እና 3) የእኔ የእናንተ ነው እካፈላለሁ “ ይናገራል ፤ የዳን ነገዶች በሁለተኛዉ ፍልስፍና ስር ተገበሩ ፤ በአይኖቻቸዉ ጀመሩ - ያዩትን ፈለጉ ፡፡

1Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Judges (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p.159.

መሳፍንት (18፡ 30-31)፡ጣዖት አምላኪነት ፤ ዳናዊያን የጌርሳም ልጅ ዮናታን እና ልጆቹ ለዳናዊያን እንደ ካህን እስኪያገለግሉ ከሚካ ወስደዉት የነበረውን የተቀረፀ ምስል በመትከል አመለኩት (ቁጥር 30-31) ፡፡ ዋይርስቤ “ የዳን ነገድ በእስራኤል የኃይማኖት ስርዓት ጣዖት አምላኪነትን በአደባባይ በማምለክ የመጀመሪያዉ ነገድ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፤ (1ነገ 12፡ 25-33) ፡፡ ማክአርቱር “ የእግዚአብሄር ታቦት ከዳናዊያን የራቀ ነበር ስለሆነም ከቀሩት እስራኤላዊያን ባለዉ እርቀታቸዉ ጣዖት አምላኪነታቸዉን ምክናያታዊ እንደ ሚያደርገዉ ይገልፃል “ ፡፡

መዝጊያ

በራዕ (7፡ 5-8) 144,000 በአሁኑ ጊዜ ኃይማኖተኞች አይደሉም ነገር ግን ከእስራኤል ነገድ የሚመጡ ወንጌላዊያን ናቸው ፤ ከ12 ነገዶች አይሁዶች ለኢየሱስ በወንጌላዊነት ያገለግላሉ ፡፡ ራዕ (7፡ 5-8) በምናነብ ጊዜ የ144,000 ከእያንዳንዱ ነገድ ዝርዝር በተጠቀሰው የዳን ነገድ እንዳልተጠቀሰ እናያለን ፤ በእስራኤል ዉስጥ የመጀመሪያዉን የኃይማኖት የጣዖት አምልኮ የዳን ነገድ በማቋቋሙ ምክንያት እንደ ሆነ ላረጋግጥ እችላለሁን ? አልችልም ነገር ግን ያ ነገር ትልቅ እንዳለዉ አስባለሁ ፡፡ ሌሎች የነበራቸዉን በመመኘት ሁሉም ነገር ጀመረ ፤ መመኘት ለሌሎች አይነት ጉዳዮች ይመራል ፤ ይህ አይኖቻችሁን በእግዚአብሄር ላይ እንድታደርጉ እንደሚያበረታታችሁ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡

  1. Wiersbe, p. 159.

  2. Wiersbe, p. 160.

  3. Wiersbe, p. 160.

  4. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publications, 2005), p. 286.

ጥያቄዎች

  1. በመሳ (17፡ 5) ሚካ የእግዚአብሄር ቤት ነበረዉ ማለት ምን ማለት ነው ? ሚካ ተሰርተዉ የነበሩ ብዙ እቃዎች ነበሩት እንዲሁም ፤ እንዲህ አይነት ሌላ ቦታ የት አይታችኋል (ዘጸዓት 39) ? በዚህ አሰራር ሚካ ስህተት ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይም ለምን አላሰባችሁም ?
  2. ሌዋዊዉን ሚካ እንዲቆይ እና ካህኑ እንዲሆን ለምን እንደ ጠየቀዉ ምን ታስባላችሁ ? (መሳ 17፡ 7-13)
  3. በመሳ (18፡ 11-21) ሌዋዊዉ የሚልካ እቃዎች ሲሰረቁ ለምን በተቃራኒ ቆመ ? ሌዋዊዉ ከዳን ጦረኞች ጋር ለምን ሄደ ?
  4. በመሳፍንት (17-18) በትምህርት ወይም በትናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Judges 18:5-6

“Then they said to him, ‘Please inquire of God so we will know if we will have a successful journey.’ The priest told them, ‘Go in peace. The Lord is watching over the journey you are going on.’”

የዳንም ልጆች ከወገናቸው አምስት ጽኑዓን ሰዎች ምድሪቱን እንድሰልሉና እንዲመረምሩ ላኩ ፡፡ እነርሱም ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም አገር ወደ ሚካ ቤት መጥተው በዚያ አደሩ ፡፡ በሰለላ ጉዟቸውም እነርሱ ጣዖት አምለኮን ወሸትንና ማጭበርብርን ተመለከቱ ፡፡ ምንም እንኳ የዳን ዘሮች ኢያሱ እንዳዘዘው አይኖቻቸውን በእግዚአብሔር ላይ ባያደርጉም ነገር ግን እነርሱ በመንገዳቸው እውነቱን ያውቁ ነበር ፤ እግዚአብሔርን መጠየቅ እንዳለባቸው ደግሞም እግዚአብሔር በመንገዳቸው ያለውን ሁሉን ነገር እንድያወቅ ያውቁ ነበር ፡፡

አንድ ሰው ወዳንተ/ች ህይወት ሲመለከት ምን ይሆን የሚያው ? እግዚአብሔርን ለማከበር ትኖሩ ይሆን ነገር ግን ደግሞ የተደበቀ ሀጢአት በጓዳህ ይኖር ይሆን ? ይህንን አወቅ ምንም ይሁን ምን በህይወትህ የሚታየው እግዚአብሔር ግን ሁሌም መንግድህን ጉዞህን ያያል ይህ የእግዚአብሔር መልካምነት ነው ፡፡ እርሱ ካንተ ጋር ነው ደግሞም ያለ ምክንያት ይወድሀል ፡፡ ምንም ያህል ርቀት ከእረሱ እርቀህ ብትሄድ ወይም ደግሞ ምንም ያህል የጠለቀ ግነኙነት ከውሸት አማለክትና ጣዖታት ጋር ቢኖርህ ፤ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው ይመለከትህማል ፡፡ የዳን ልጆችን እንዳትመስል ፤ የዳን ልጆች እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር እንደነበረ ያወቁ ነበር ነገር ግን የጣዖት ባርያ መሆናቸውን ቀጠሉ ፡፡ እግዚአበሔርን ነፃ እንድያወጣህ ጠይቀው ፤ ጠይቀው በመንገድህ በጉዞህ እንድያግዝህ እርሱም ለሌሎች አማልክት ከመሰገድ እንድሁም ደግሞ በሀጥያት ውስጥ ከመኖር ነፃ ያወጣሀል ፡፡

“ እነርሱም የምንሄድበት መንገድ የቀና መሆኑን እናውቅ ዘንድ እባክህ እገዚአብሔርን ጠየቅልን አሉት ፡፡ እርሱም የምትሄዱበት መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ነውና በደኅና ሂዱ አላቸው ፡፡ “

- መሳፍንት 18፡5-6

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ዘፀአት 20፡23 –“ በአጠገቤ ምንም አታድርጉ የብር አማልክት የወርቅም አማልክት ለእናንተ አታድርጉ ፡፡ “
  • መዝሙር 90 (91 ) ፡11 –“ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና ፡፡ “
  • 1ኛ ዮሐንስ 1፡6 –“ እነርሱም በማኅበር ፊት ሰለ ፍቅርህ መስክረዋል ለእግዚአብሔር እንደሚገባ አድርገህ በጉዞአቸው ብትረዳ መልካም ታደርጋለህ ፡፡ “