The Horrific Sin of Benjamin
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Judge Judges 19-20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በመሳፍንት በመጫረሻዎቹ ሁለት ጥናቶች ስንሄድ መጥፎነት በመቀጠል ወደ ባሰ መጥፎነት ይሄዳል ፡፡ በዚህ መፅሀፍ ለመሲሁ ያለን አንዱ ቃላችን ዳኛ ነዉ ፤ መሲሁ ለማዳን የመጣ ዳኛ ነው ! እስካሁን ለብሉይ ኪዳን ለጥናታችን ቃላችንን እስኪ እንከልሰዉ፡ ዘፍጥረት- ዘር፣ ዘጸኣት - ነፃ አዉጪ፣ ዘሌዋዉያን - አስተሰሪይ፣ ዘኁልቁ - አለት፣ ዘዳግም - ነቢይ፣ ኢያሱ - አዛዥ እና መሳፍንት - ዳኛ ፡፡
ትምህርት
መሳፍንት (19፡ 1-4)፡ ምዕራፍ 19 “ በእስራኤል ንጉስ ባልነበረ ጊዜ “ በሚል ፅሁፍ ይጀምራል ፤ በመሳፍንት 17-18 ወደ ተራራማዉ ኤፍሬም አገር የተጓዘ አንድ ሌዋዊ ከቤቴልሄም ነበረን ፡፡ በምዕራፍ 19 ያልተጠቀሰ ሌዋዊ ከኤፍሬም ወደ ቤቴልሄም ተጓዘ ፤ ይህ ሌዋዊ ካህን ጉዳይ ነበረው …. በመጋበዝ ወይም ከእርሱ ጋር ከማይሆኑ ሰዎች ጋር መፍጠሩ ችግር አልነበረው (ቁጥር 9-14) እንዲሁም ቁባቷን ያየበትም መንገድ ችግር የሌዉም ፤ ይህ ክስተት በእስራኤል ቀዝቃዛ ጦርነትን አመለከተ ፡፡
በደንብ በመቅረብ ሌዋዊዉ ካህን ላይ ስንመለከት ፤ ዘሌ (21፡ 7) አንድ ካህን ያገባ ወይም ያላመነዘረ ወይም ያልፈታች ሴት መሆን እንዳለበት ይናገራል ፤ ካህኑ ከራሱ ሰዎች ድንግል ሴት ያገባ ነበር (ዘሌ 21፡ 13-14) ፡፡ አንድ ቁባት ሚስት በዚያን ጊዜ በባህሉ ተቀባይነት ነበረዉ ነገር ግን ለእግዚአብሄር ተቀባይነት አልነበረውም ፡፡
ቁባቷ ለሌዋዊዉ የታመነች አልነበረችም ለአራት ወራትም በአባቷ ቤት ለመኖር ትታዉ ሄደች (ቁጥር 2) ፤ የብሉይ ኪዳን ህግ በዝሙት ጥፋተኝነት የተገኙት አካላቶች እንዲገደሉ ይጠይቃል (ዘሌ 20፡ 10) ፡፡ ህጉ እንዲፈፀም ከሚጠይቀዉ ይልቅ ሌዋዊዉ እንድትኖር ፈቀደላት ቆይቶም “ በመልካም ለመናገር “ ፍለጋዋን ተከትሎ ሄደ (ቁጥር 3) ፤ አሁንም በጣም ስለሚወዳት አለመታመኗን ለመተዉ ፍቃደኛ ነበር ፡፡ የቁባቷም አባት ሌዋዊዉን በደስታ ወደ ቤቱ ተቀበለው መናልባትም ሌዋዊዉ የሴት ልጁ ነፃ አዉጪ በመሆን አገልግሎት ስለ ነበር (ቁጥር 4) ፤ ለሰዎስት ቀናት ሌዋዊዉ በዚያ በመቆየት በአንድ ላይ አከበሩ ፡፡
መሳፍንት (19፡ 5-13)፡ ከሰዎስት ቀን በኋላ ሌዋዊዉ ለመሄድ ሞከረ ነገር ግን አባትዬው ምግብ በመስጠት እና ሌላ አዳር እንዲቆይ በመለመን አቆየው (ቁጥር 5-7) ፡፡ አምስተኛዉ ቀን ላይ ሌዋዊዉ እንደ ገና ለመሄድ ሞከረ ነገር ግን አባትየዉ እንዲቆይ እና እንዲበላ አሳመነው ፤ ከሰዓትም መጣ አባትየዉም ሌላ ምሽት እንዲቆይ ለማድረግ እንደ ገና ሞከረ (ቁጥር 8-9) ፤ ሌዋዊዉ በዚህ ጊዜ ለመቆየት እምቢ አለ ፤ እሱ፣ ቁባቱ እና አገልጋዮቹ ሄዱ ፡፡
ሌዋዊዉ ፣ ቁባቱ እና አገልጋዮቹ የይሁዳን አካባቢ በመተዉ ወደ ቢኒያም ምድር ገቡ ( ቁጥር 10) ፤ አገልጋዮቹ በኢያቡሳዉያን ከተማ ኢያቡስ እንዲቆዩ ጠየቁ ነገር ግን ሌዋዊዉ እምቢ አለ ወደ ጊብዓም መጓዛቸዉን ቀጠሉ (ቁጥር 11-13) ፡፡ ኢያቡሳዉያን ሁልጊዜ ችግር ነበሩ ምክንያቱም እስራኤል ምድሪቱን መያዝ እና ጣዖቶችን ማስወገድ በፍፁም ስላልጨረሱ ፤ ሌዋዊዉ በኢያቡስ መቆየትን እምቢ አለ ምክንያቱም በዚያ እስራኤላዊያን ስላልነበሩ ፡፡
መሳፍንት (19፡ 14-21)፡ በቢንያም ምድር ጊብዓ እስኪደርሱ ድረስ ቀጠሉ (ቁጥር 14) ፤ ሁሉም የከተማዋ መሪዎች ወደ ሚሰባሰቡበት ወደ ከተማዋ አደባባይ ሄዱ (ቁጥር 14) ፡፡ ሌዋዊዉ ምሽቱን የሚቆይበት እንግዳ ተቀባይነት ሊሰጠን ይችላል ብሎ በመጠበቅ በዚያ ሄደ (ቁጥር 15) ፤ በዚህ ማህበረሰብ ዉስጥ ኃጢዓት ነበር ፤ ዘፍ (4፡ 7) የሚለው “ መልካም ባታደርግ ግን ኃጢዓት በደጅህ ታደባለች “ ፤ ያዕ (1፡ 14) የሚለው “ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል “ (ያዕ 1፡ 14-16) ፡፡ በጊብዓ ያሉት ሰዎች ወደ እነርሱ ኃጢዓት እንዴት እየቀረበ እንደ ነበር ሀሳቡ አልነበራቸዉም ፤ በመጨረሻም ከኤፍሬም የሆነ(ግን ከቢንያም ያልሆነ) አንድ ትልቅ ሰዉ አደባባዩ ላይ አያዉ ከየት መጥቶ እንደ ነበር እና ወዴት እየሄደ እንደ ነበር ጠየቀው (ቁጥር 16-17) ፡፡ ሌዋዊዉም ወደ እግዚአብሄር ቤት(በሰሊሆ) ተመልሰዉ እየሄዱ እንደ ነበር መለሰ ፤ እንዲሁም ደግሞ የሚያስፈልጋቸዉ ሁሉ ነበራቸዉ ለመቆያ ግን መልካም ስፍራ አልነበራቸዉም (ቁጥር 18-19) ፤ ሽማግሌዉም ለእነርሱ ሁሉንም ነገር እንደሚያደርግለት ለማረፊያም ቦታ እንኳን ሳይቀር እንደሚያደርግለት ነገረው (ቁጥር 20) ፡፡ ሽማግሌዉም ቤት ወስዶ የምስራቅን እንግዳ ተቀባይነት አሳያቸዉ - እግራቸዉን በማጠብ መገባቸው (ቁጥር 22) ፡፡
መሳፍንት (19፡ 22-28)፡ ነገር ግን የከተማዋ ወስላታ ወንዶች ወንዱን እንግዳ እንዲወጣ ፈለጉ በዚህም ከእርሱ ጋር ሊገናኙ ይችላሉ (ቁጥር 22) ፤ ይህ በሲዶም እና በገሞራ ሁሉም እንደ ገና የዘፍ (19፡ 4-5) ሁኔታ ነበር ፤ እናም ይህ በቢንያም ነገድ ሆነ በጣዖት አምላኪዎች አይደሉም ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የእግዚአብሄር የሆነ ምንም ነገር አልነበረም ፡፡ ሽማግሌዉም “ ለወንድሞቹ “ ነገራቸዉ - በግል ያውቃቸዋል እናም ይህን አስቀያሚ ነገር እንዳያደርጉ ለመናቸው - ግንኙነት (የተመሳሳይ ፃታ ግንኙነት) ከሰዉዬዉ ጋር (ቁጥር 23) ፡፡ ሽማግሌዉም ለእነርሱ በዚያ ፋንታ የራሱን ድንግል ሴት ልጅ እና የሌዋዊዉን ቁባት እንደ ሚያወጣላቸዉ ነገራቸው (ቁጥር 24) ፤ ሽማግሌዉ ሰዉዬው አስከፊዉን የተመሳሳይ ወሲብ ከማየት ይልቅ ሴት ልጁ ስትደፈር ያያል ፡፡ አንድኛዉም ሁኔታ ሁሉም ስህተት እና ኃጢዓት ነው ፤ ከቢኒያም የሆኑት ወንዶች ባልሰሙት ጊዜ ሌዋዊዉ ካህን ቁባቱን ወደ ዉጪ በመዉሰድ ለእነርሱ ሰጣት (ቁጥር 25) ፡፡ በመልካም አስተሳሰብ ያን እንዴት ሊያደርግ ይችላል ? ሰዎቹም ምሽቱን ሁሉ ደፈሩዓት አመነዘሩባትም ፤ የተመሳሳይ ወሲብ ኃጢዓት ወደ መድፈር እና ትክክል ወዳልሆነ ወሲብ እየመራ ነበር ፡፡
ሲነጋም ሰዎቹም ቁባቷን ትተዋት ሄዱ ፤ መንገዷንም ተመልሳ ወደ ሽማግሌዉ ቤት አደረገች ወደቀችም (ቁጥር 26) ፤ ባል ለዚህ ሚስቱን አሳልፎ ሰጥቶ ተመልሶ ሲተኛ አስባችሁታል ? ሌዋዊዉ ለመሄድ ሁሉንም ነገር በማዘጋጀት ጉዞዉን ቀጠለ፤ ለመሄድ በሩን በከፈተ ጊዜ ቁባቷ በር ላይ ወድቃ አገኛት (ቁጥር 27) ፡፡ ትቷትም እየሄደ ነበር 1 እንድትነሳም ነገራት ነገር ግን ምላሽ አልነበረም እናም አካሏን ቤት ወሰደዉ (ቁጥር 28) ፡፡
መሳፍንት (19፡ 29-30)፡ ሌዋዊዉ እቤቱ ቁባቷን 12 ቦታ በመቆራረጥ ቁራጮቹን ወደ ሁሉም እስራኤል ግዛቶች ላካቸዉ (ቁጥር 29) ፤ በ 1ሳሙ (11፡ 6-7) “ የእግዚአብሄር መንፈስ በወረደበት ጊዜ “ ሁለት በሬዎችን በመዉሰድ ወደ ቁርጥራጭ በመቁረጥ በመለዉ እስራኤል በመላክ ሳዖል ተመሳሳይ ነገር አደረገ ፡፡ የእግዚአብሄርም ማስፈራት በህዝቡ ላይ ወረደ ሳዖልንም ተከተሉት ፤ የእስራኤልም ነገዶች የቁባቷን ቁራጭ በተቀበሉ ጊዜ ሰዎቹ ስላዩት እና ተፈጥሮ ስለ ነበረው አወሩ ፡፡ እስራኤላዊያን ከግብፅ ከወጡበት ቀን ጀምሮ እንደዚህ አይነት አልተፈጠረም (ቁጥር 30) ፡፡
መሳፍንት 20፡ ከእስራኤል ካህን የሆነዉ የአንዱን የሌዋዊዉን ድርጊት ለመቀበል በጣም ከባድ ነው ፤ ይሁን እንጂ በእነርሱ ዉስጥ ስላለዉ ኃጢዓት ለእስራኤል ህዝቦች ምናልባትም ለእርዳታ ነበር ፡፡ በምዕራፍ 20 የእስራኤል ሌሎቹ ነገዶች የቢኒያ ነገዶች አድርገዉት በነበረዉ ቁጣቸዉ በእነርሱ ላይ ነደደ ፤ ይህ የቢኒያማዊያንን ኃጢዓት ለማጥፋት በአንድ ላይ እንዲመጡ ለህዝቡ ጥሪ ነበር ፤ በዚህም “ ሁሉም እስራኤላዊያን “ (400,000 እግረኛ ወታደር) በምጽጳ በእግዚአብሄር ፊት በአንድ ላይ መጡ (ቁጥር 1-2) ፡፡ ሌዋዊዉ ድርጊቱ በእስራኤል አስደንጋጭ እፍረት ምክንያት እንደ ነበር ገለፀ (ቁጥር 3-6) ፡፡ የተሰበሰቡት እስራኤላዊያን ከእያንዳንዱ ነገድ ከ100 ሰዎች 10፣ ከ1000 ሰዎች 100 እና 10,000 ደግሞ 1,000 ሊቀጡዓቸዉ ወደ ቢንያም የተሰባሳበ ጦር ለመላክ ለመዉሰድ ወሰኑ ፡፡ የእስራኤል ጦር ቢኒያም በደረሱ ጊዜ ስለ ጊብዓ ወስላታ ሰዎች ጠየቁ ነገር ግን ቢኒያማዊያን ግን ባለመመለስ ወጥተዉ 26,000 የራሳቸዉን ጦር ሰበሰቡ (ቁጥር 13-15) ፡፡
መደምደሚያ
እስራኤላዊያን(ከቢንያማዊያን ዉጪ) 400,000 ተቆጠሩ ፡፡ ወደ ቤቴል በመሄድ በቢኒያማዊያን ላይ ጦራቸዉን ምን መምራት እንዳለበት እግዚአብሄርን ጠየቁ ፤ እግዚአብሄርም “ይሁዳ “ ብሎ መለሰላቸው (ቁጥር 17-18) ፡፡ ዉጊያዉ የቢኒያምን ነገድ ለማጥፋት ተካሄደ ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publications, 2005), p. 286.
MacArthur, p. 286.
ጥያቄዎች
-
ሌዋዊዉ በጊብዓ በቀረ ጊዜ ለምሽቱ መቀመጫ የሚረዳዉ ማንንም ሊያገኝ አልቻለም ፤ አንድ ሽማግሌ ለእርሱ እንዳደረገለት ጥቂት የከተማዋ ሰዎች ሽማግሌዉን እንግዳዉን ወደ ዉጪ እንዲያስወጣዉ ፈለጉ ፤ እንዲወጣ ለምን ፈለጉ (መሳ 19፡ 22) ? ይህ ባህሪይ ሌላ የት ላይ ተከስቷል ? (መሳ 19፡ 5)
-
በሰዉየዉ ቁባት ላይ ምን ተፈጠረ ? ሌዋዊዉ በእርሷ አካል ምን አደረገ ? ያን ለምን እንዳደረገ ምን ታስባላችሁ ?
-
በመሳ (20፡ 13) የሌዋዊዉን ሚስት ክፉ ያደረጉባትን ሰዎች የቢኒያም ልጆች ለምን አለቀቁም (አልሰጡም)? ዉጤቱ ምን ነበር ?
-
በመሳፍንት (19-20) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Judges 20:28
“Phinehas son of Eleazar, son of Aaron, was serving before it. The Israelites asked: ‘Should we again fight against our brothers the Benjaminites or should we stop?’ The Lord answered: ‘Fight, because I will hand them over to you tomorrow.’”
አንድ ሌዋዊ ከቁባቱ ጋር ሲጓዝ በብንያም በምትገኘው ጊብዓ ከተማ እንግዳ ተቀባይነትን አየ ፡፡ ሌዋዊውን ማንም ማረፊያ ቦታ ሊሰጣው ባልፈቀደ ጊዜ አንድ ሸማግሌ ሰው ምሽቱን ሁሉ ያርፉ ዘንድ ወሰዳቸው ፡፡ ነገር ግን በጊብዓ የሚኖሩ ብንያማውያን ቤቱን ከበቡ ሌዋዊዉንም አስጨነቁ ፡፡ ቁባቱንም ወስደው ሌሊቱን ሙሉ አመነዘሩባት ስለዚህም ሞተች ፡፡ ሌዋዊውም ባሰቃቂ መንገድ ሰውነቷን ለአስራ ሁለት ቦታ ቆራርጦ የተቆረጠውንም አካል ወደ አሰራ ሁለቱም የእስራኤል ነገዶች ላከ ፡፡ ይህም አስራኤላውያንን በብንያም ነገድ ወስጥ ሰለ ተፈፀመው ካባድ ሀጢአት አሳወቀ ፡፡ እስራኤላወያንም አይኖቻቸውን ከአግዚአብሔር ላይ በማንሳታቸው አዘኑ ተፀፁትም ፡፡ እነርሱም ከዚህ ክፉ ነገር ነፃ ያወጣቸው ዘንድ መስፍን እንድሚያስፈልጋቸው አወቁ ፡፡ እግዚአብሔርም አንደገና ድልን ያቀዳጃቸው ዘንድ እንድዋጉ አዘዘ ፡፡
እንግዳን አለመቀበል ፣ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ፣ አሰገድዶ መድፈር ፣ ሰድብ ፣ መግደል - ምናልባት አነዚህን ብንያማውያን አይኖቻቸወን ከእግዚአብሔር ላይ ባነሱ ጊዜ ያደረጉዋቸውን ሀጥያቶች ዝርዝር ማንበብ ይከብድህ ይሆናል ፡፡ እነርሱ በራሳቸው አይን ትክክል የሆነውን ነበር ያደረጉት ይህም ወደ ተበላሸና ከፉ ወደ ሆነ ባህል መራቸው ፡፡ ዛሬ አንተ የምትኖርበት ባህል ከብንያማወያን ጋር ተመሳሳይ ድምፅ ያለው ይሆን ? በዚህ ዘመን ብዙዎች አይናቸውን ከኢየሱስ ላይ አንስተዋል ደግሞም በራሳቸው መንገድ ሄደዋል ፡፡ አሁንም ግን ተስፋ አለ የክርስቶስ ፍቅር ስላላለቀ ፡፡ ለብንያማውያን እንደ ሆነው ሁሉ ድነትና የሚያድን ፀጋ ላንተና በዙሪያህ ላሉት አለ ፡፡ ኢየሱስ ወደ እርሱ የሚመለሱትን ሁሉ ይቀበላቸዋል ፡፡ ዛሬ ይህ ትውልድ አይኑን ወደ ኢየሱሰ እንድመለስና በእርሱ ድነት ውስጥ እንድኖር ፀላይ ፡፡
“ በዚያም ዘመን የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊነሀሰ በፊቱ ይቆም ነበርና የእሰራኤል ልጆች እግዚአብሔርን ከወንድሞቻችን ከብንያም ልጆች ጋር ለመዋጋት ዳግመኛ እንውጣን ወይስ እንቅር ? ብለው ጠየቁ ፡፡ እግዚአብሔርም ነገ በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጡ አለ ፡፡
መሳፍንት 20 ፡ 28
ተጨማሪ ጥቀስ
- መዝሙር 43 (44)፡6-8 –“ በቀሰቴ የምታመን አይደለሁምና ሰይፌም አያድነኝምና አንተ ግን ከጠላቶቻችን አዳንኸን የሚጠሉንንም አሳፈርሃቸው ሁልጊዜ በእግዚአብሔር እንከብራለን ሰምህንም ለዘላለም እናመሰግናለን ፡፡ “
- ኢሳያስ 40፡28 – “ አላወቅህምን ? አልሰማህምን ?እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው አይደክምም አይታክትም ማስተዋሉም አይመረመርም ፡፡ “
- ያዕቆብ 4፡9-10 –“ ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም ሳቃጭሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ ፡፡ በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል ፡፡ ”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።