Under the Spirit of the Lord
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Judge Judges 21 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
አንዳንድ ሰዎች የመሳፍንትን ጊዜ እንደ እስራኤላዊያን የጨለማ ጊዜ ጠቅሰዉታል ፤ ይህ የተጣራ 300 አመት የክፉነት ጊዜ ነበር ፡፡ በጊዜዉም ዉስጥ ለትንሽ ጊዜ ወደ እግዚአብሄር እንዲመለሱ በመምራት የሚናገሯቸዉን መሳፍንትን አስነሳላቸው ፤ እግዚአብሄር እያንዳንዳቸዉን መሳፍንቶች ለሆነ ጊዜ ያክል ተጠቀመባቸው ፡፡ የሚንዴ ስዕል በመሳፍንት መፅሀፍ ጊዜ ህይወት ምን ይመስል እንደ ነበር የሚያሳይ እንደ ቅፅበታዊ ፎቶ ነው ፡፡ እያንዳንዳቸዉ መሳፍንቶች የእግዚአብሄር መንፈስ በእነርሱ ላይ በመጣ ጊዜ ይጀምራሉ ፤ እያንዳንዳቸዉ የእግዚአብሄርን ህዝብ ነፃ እንዲያወጡ እና እንዲያድኑ ተጠርተዋል ፡፡ ግባችን የመፅሀፍ ቅዱስ እያንዳንዱ መፅሀፍ በይበልጥ እንዴት የመሲሁን የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት እንደሚያመለክቱ መመልከት እንደ ሆነ አስታዉሱ ፤ በጣም በመቆሸሻችን ምክንያት በብዙ ነፃ አዉጪ ያስፈልገናል ፡፡ በምዕራፍ 20 በጦርነቱ አብዛኛዎቹ ቢንያማዊያን ተገድለዋል ፤ በምዕራፍ 21 የቢንያምን ነገድ መልሶ ለመገንባት እስራኤላዊያን ሚስቶችን ተመለከቱ ፡፡
ትምህርት
መሳፍንት (21፡ 1-4)፡ በመፅሀፍ ያልተመዘገበዉን መሀላ ባደረጉ ጊዜ (ቁጥር 1) ነገር ግን ከጀርባዉ ያለዉ ምክንያት አስፈላጊ ነው - እስራኤላዊያን የቢኒያም ነገዶች እንዲኖሩ አለመፈለጋቸው ፤ ይሁን እንጂ የእስራኤል ሰዎች በቤቴል በመሰብሰብ በቢኒያም አለመገኘት ምክንያት አዘኑ (ቁጥር 2-3) ፡፡ ህዝቡ በሀዘን ወደ እግዚአብሄር በመመለስ መሰዊያን በመስራት የሚቃጠል መስዋዕት እና የደህንነት መስዋዕት አቀረቡ (4) ፤ የሚቃጠለዉ መስዋዕት የኃጢዓቱን አይነት እዉቅና በመስጠት ከእግዚአብሄር ጋር የታደሰ ግንኙነትን ያሳወቀ የማስተሰሪያ መስዋዕት ነበር (ዘሌ 1፣ 6፡ 8-13 ) ፡፡ የደህንነት መስዋዕት ስለ ጥበቃዉ እና ስለ ነፃ ማዉጣቱ ለእግዚአብሄር የሚሰጥ የማመስገኛ መስዋዕት ነበር (ዘሌ 7፡ 11-21) ፤ ይህ እስራኤላዊያን ወደ እግዚአብሄር ለመመለስ እያሳዩት የነበረዉን የተስፋ ብልጭታ ይሰጣል ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር መስዋዕት ከመስጠት ያለፈ ይጠይቃል ፡፡ ኢዩ (2፡ 12-13) የሚለዉ ልባችንን እንድንቀድ እንጂ ልብሳችንን እንድንቀድ አይደለም ፤ ከዉጨኛዉ ሀዘን ምልክት በይበልጥ በልባቸዉ እንዲያዝኑ እያስረዳቸዉ ነበር ፡፡ በኃጢዓት ምክንያት አንዳንድ ዉጫዊ ሀዘንን የሚያወሩ፡ ዘፍ (37፡ 34) ያዕቆብ ልብሱን በመቅደድ ማቅ ለበሰ፣ 2ሳሙ (1፡ 11) ዳዊት በሀዘን ልብሱን ቀደደ፣ ኢዮ (1፡ 20) ኢዮብ ካባዉን በመቅደድ ራሱን ተላጨ ፡፡
የተዘረዘሩት በኃጢዓት ምክንያት ዉስጣዊ መግለጫዎች ናቸው፡
- ሆሴ (6፡ 6) - እግዚአብሄር ከመስዋዕት ይልቅ ታማኝነትን ከሚቃጠል መስዋዕት ይል እግዚአብሄርን ማወቅን ይወድዳል ፡፡
- መዝ (51፡ 17) - እግዚአብሄር የተሰበረ መንፈስን እና ትሁት እና የተሰበረን ልብ ይፈልጋል ፡፡
- 2ቆሮ (7፡ 10) - እግዚአብሄር ምህረትን የሚያመጣን እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ የሆነ ኃዘን ይፈልጋል ፡፡
መሳፍንት (21፡ 5-9)፡ እስራኤላዊያን የቢኒያም ነገድ ከእነርሱ ጋር ስላልነበረ እና የሚቃወመዉ ሁሉንም መግደል የተባለ መሀላ አድርገዉ ስለ ነበር አዘኑ (ቁጥር 5) ፡፡ በኃዘናቸዉም በመራራት ጠቅላላ የቢኒያምን ነገድ ከድምሰሳ ለማዳን ፈለጉ ( ቁጥር 6-7) ፤ ከቢኒያም ሴት ልጆቻቸዉ ወንዶችን እንዳያገቡ መሀላ አድርገዉት እነበረዉ ላይ አትኩረዉ ነበር ፤ ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ስብሰባዉ ማንም እንዳልመጣ አወቁ (ቁጥር 8-9) ፡፡
“ ገለዓዳዊያን የራሄል የልጅ ልጅ የሆነዉ የምናሴ ዘር ነበሩ ስለዚህም ከራሄል ልጅ ከቢኒያም ዘር ጋር የደም ትስስር ነበራቸው ፤ በተከታዩም ታሪክ በቢኒያም ነገድ እና በኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች መካከል በጣም የቀረበ ትስስር ነበር ፡፡ “
መሳፍንት (21፡ 10-18)፡ እስራኤላዊያን በአንድ በመሰብሰብ ከድንግል ሴቶች ዉጪ የኢያቢስ ገለዓድ ነዋሪዎችን ሁሉ እንዲገድሉ 12,000 ሰዎችን ላኩ (ቁጥር 11) ፤ 400 ደናግልትን አገኙ ወደ ሰሊሆም አመጡዓቸው (12) ፡፡ ከጦርነቱ የተረፉ 600 ቢኒያማዊያን ነበሩ (መሳ 20፡ 47) ስለዚህም ለእነዚህ ለተረፉት አሁንም 200 ደናግልት ያስፈልጋቸዉ ነበር ፤ እስራኤላዊያን ከዉጊያው ተረፈዉ ለነበሩት ቢኒያማዊያን የሰላም መልዕክት ላኩ (ቁጥር 13) ፡፡ የቢኒያም ነገዶች መለሱ እስራኤልም ለእነርሱ 400 ድንግሎቹን ሰቷቸው (ቁጥር 14) ፤ ህዝቡ በቢኒያም ነገድ ላይ ርህራሄ ስለ ነበራቸዉ ለቢኒያማዊያን ሙሽራ እንዲሆኑ ተጨማሪ ድንግሎች እንደሚሰጡዓቸዉ ወሰኑ ስለዚህ አይጠፉም (ቁጥር 15-17) ፤ ነገር ግን የራሳቸዉን ሴት ልጆች መስጠት አይችሉም ምክንያቱም መሀላ አድርገዉ ስለነበረ (ቁጥር 18) ፡፡
መሳፍንት (21፡ 19-22)፡ እስራኤላዊያን በሚመጣዉ አመታዊ በዓል (ምናልባትም የዳስ ወይም የፋሲካ በዓል) የሚያስፈልጋቸዉን ያነሰዉን የሴቶች ቁጥር ለማስተካከል እድሉን እንደሚሰጡዓቸዉ ወሰኑ (ቁጥር 19) ፡፡ ቢኒያማዊያን የሲሎሆን ወጣት ሴቶች ለመዝፈን በሚመጡበት ጊዜ ለመመልከት በወይኑ ስፍራ እንዲደበቁ ነገሩዓቸው ፤ ከዚያም እያንዳንዳቸዉ ሚስት እንዲሆኗቸዉ አንዷንድ በመያዝ ተመልሰዉ ወደ ቢኒያም ይወስዷቸዋል (ቁጥር 20-21) ፡፡ በዚያ መንገድ አባቶቻቸው (ወይም ወንድሞቹ) ሴት ልጆቻቸዉን ለመመልከት በመጡ ጊዜ አባቶቻቸዉ መሀላቸዉን እንዳልሰበሩ መናገር ይችላሉ ነገር ግን ቢኒያማዊያን ከነበሩት በላይ ተጨማሪ ሚስቶች ያስፈልጓቸዉ ነበር (ቁጥር 22) ፡፡
መሳፍንት (21፡ 23-25)፡ ቢኒያማዊያን ነግረዋቸዉ እንደ ነበረዉ አደረጉ ፤ ሴቶቹንም በመዉሰድ ወርሰዋት በነበረዉ ምድር በመመለስ ኑሮአቸዉን እና ቤተሰባቸዉን እንደ ገና መሰረቱ (ቁጥር 23) ፤ ሁሉም የተሰበሰቡትም እስራኤላዊያን ቤታቸዉ ተመለሱ (ቁጥር 24) ፡፡ እንዲሁም “ በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉስ አልነበረም ፤ ሰዉ ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የጣየዉን ያደርግ ነበር “ (ቁጥር 25) ፡፡
ወደ ዚህ ጥናት መጨረሻ ላይ ስንመጣ በመሳፍንት መፅሀፍ ላይ ትልቅ ስዕሎችን እስኪ እንመልከት ፤ መሳፍንት (17፡ 6፣ 18፡ 1፣ 19፡ 1፣ 21፡ 25 ) ሁሉም ተመሳሳይ ነገር ነዉ የሚሉት፡ “ በእዚህ ቀናት በእስራኤል ንጉስ አልነበረም” ፡፡ ደግሞ ደግሞ እንደ ገና ንጉስ ባለመኖሩ ምክንያት ህዝቡ የሚፈልገዉን አደረገ ፤ የጊብዓ ወንዶች እንዷን ሴት ምሽቱን ሁሉ ደፈሯት ፡፡ የቢኒያም ሰዎች ክፉን በመከላከል ችግር አልነበረባቸዉም ፡፡ በእስራኤል የንፁሀን ጭፍጨፋ፣ የንፁሀን ሰዎች እገታ፣ ቋሚ የሆነ ህግን አለመታዘዝ እና አይናቸዉን ከእግዚአብሄር ላይ ማንሳት ነበር ፡፡
መደምደሚያ
እዉነታዉ ተመሳሳይ ነገር እንደምናደርግ ነው ፤ ልዩነቱ ንጉስ አልነበራቸዉ እኛ ደግሞ በንጉሱ ኢየሱስ እናደርጋለን ፡፡ በመሳፍንት ንጉስ በመፈለግ የሆነ ሰዉ መጥቶ እንዲያድናቸዉ ጠበቁ ፤ ሁሉም መሳፍንቶች እግዚአብሄር ተጠቅሞባቸዉ የነበሩት ታላቅ ሰዎች ነበሩ ነገር ግን በአጭር ወደቁ ! ለምን ?ምክንያቱም በመምጣት ከእነዚህ ሁሉ ነፃ ያወጣን እዉነተኛ ንጉስ ስላለ ፡፡ እዉነቱ በእነዚህ ክፉ ጊዜያት ሁላችንም ኖረንበት እንደ ነበር ነዉ፡
ሮሜ (3፡ 23)፡ “ ሁሉ ኃጢዓትን ሰርተዋልና የእግዚአብሄርም ክብር ጎድሎአቸዋል “ ፤ ከእኛ ዉስጥ ሁላችንም በአጭር ወድቀናል
ሮሜ (6፡ 23)፡ “ የኃጢዓት ደመወዝ ሞት ነዉና ፤ የእግዚአብሄር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው “ ፤ ሁል ጊዜ ኃጢዓት ወደ ሞት ይመራል ፤ ምን እንደሆናችሁ ወይም ምንም አድርጋችሁ እንደሆነ ችግር የለዉም !
ሮሜ (5፡ 8)፡ “ ነገር ግን ገና ኃጢዓተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሄር ለእኛ ያለዉን የራሱን ፍቅር ያስረዳል “ !
ኤፌ (2፡ 8-9)፡ “ ይህም የእግዚአብሄር ስጦታ ነዉ እንጂ ከእናንተ አይደለም ፤ ማንም እንዳይመካ ከስራ አይደለም ፤ እኛ ፍጥረቱ ነንና “ ፡፡
ሮሜ (10፡ 9-10)፡ “ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሄር ከሙታን እንዳነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህና ፤ ሰዉ በልቡ አምኖ ይፀድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና “ ፡፡
የእግዚአብሄር የፍቅርን ስጦታ ያልያዙ ይህን የሚያነቡ ሰዎች አሉ ፤ ይህን ስጦታ ለእነርሱ በመስቀል ላይ ከሞት ከኢየሱስ ክርስቶስ አልያዙትም በዚህም ምክንያት ይህ እብደት እና ክፉነት በእነርሱ ያበቃል ፡፡ በእግዚአብሄር የኢየሱስ ክርስቶስ ስጦታ እምነት ካላችሁ ወደ ህይወት ይመራችኋል ፤ እግዚአብሄር ኢየሱስን ከሞት እንዳስነሳዉ በልባችሁ ብታምኑ ትድናላችሁ ፡፡ ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በምትናገሩ ጊዜ ድነትን ትለምዱታላችሁ (ትቀምሱታላችሁ)፡፡
በመሳፍንት መፅኀፍ ሁሉም የኃጢዓት እና የሞት ኡደት (ድግግሞሽ) ነበር ፤ ከዚህ በኋላ ግን አይኖረንም - የክርስቶስ ፍቅር ስላለን ፡፡ ስለ ሜንዲ ስዕል የወደድኩት አንድ ነገር የመንፈስ ቅዱስን አገላለፅ ነው ፤ መፅሀፍ ለኢየሱስ እሺ ባላችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ዉስጥ እንደ ሚያደር ይናገራል ፤ ሮሜ (8፡ 14) የሚለው “ በእግዚአብሄር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሄር ልጆች ናቸዉና “ ፤ የእግዚአብሄር ልጆች ናችሁ ፡፡ የመሳፍንት መፅሀፍ የሚያደርገዉ ያን ነው ፤ በክርስቶስ እስራኤልን ከገዙት ክፉዎች ነፃ የመዉጣትን ተስፋ ይሰጠናል ፡፡
በህይወታችሁ ኃላፊ(ዋስትና እንዲሆን) ፈልጋችሁት ኢየሱስን በፍፁም ካልነገራችሁት ፤ አሁን ጊዜዉ ነው ! ፤ አሁን አድርጉት እነዚህን ቃላቶች በኃይል በሉ
“ ኢየሱስ ጌታዬ እንድትሆን እፈልጋለሁ ፤ በህይወቴ ከተመላለስኩበት ኃጢዓቴ ይቅር በለኝ ፤ ኢየሱስ በመስቀል ላይ እንደ ሞት እንደ ተቀበርክ ወደ ህይወት እንደ ተመለስክ በዚህም መዳን እንደምችል አምናለሁ ፤ ኢየሱስ አዳኜ እንድት ሆን እፈልጋለሁ ፤ አሜን “ ፡፡
በዚህ ምሽት ከፀለያችሁ www.reviveschool.org ወይም www.timetorevive.com ድህረ ገፅ ሂዱ ከዚያም በዚህ ሂደት እንድታድጉ መርዳት እንችላለን ፡፡
Arthur E. Cundall and Leon Morris, Tyndale Old Testament Commentaries: Judges and Ruth, v. 7 (Downers Grove, IL: IVP Academic, InterVarsity Press, 2015), p. 200, Kindle Edition.
ጥያቄዎች
-
በቁጥር 1 የእስራኤል ሰዎች ሴት ልጆቻቸዉን በትዳር ለቢኒያም ነገድ ላለመስጠት ለምን እንደ ማሉ ምን ታስባላችሁ ?
-
በቁጥር 5 የእስራኤል ሰዎች ወደ ምጽጳ የማይመጣዉን ማንኛዉንም ሰዉ ለመግደል ለምን መሀላ አደረጉ?
-
ሚስቶቻቸዉ እንዲሆኑ የሴሎን ሴት ልጆች በጉልበት በመዉሰዳቸዉ ትክክል ነበሩ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አልነበሩም ?
-
በእነርሱ አይን ትክክል የነበረ ሁሉም የሚያደርጉት ስህተት ምን ነበር ? በአሁን ጊዜ ነገሮች እንዴት የሚመሳሰሉ ናቸው ? (ኤር 17፡ 9)
-
በመሳፍንት 21 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Judges 21:25
“In those days there was no king in Israel; everyone did whatever he wanted.”
እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ነፃ ያወጣና ያድን ዘንድ መሳፍንትን ተጠቅሟል ፡፡ የእግዚአብሔር እጅ ስላገዛቸወ ብቻ ነበር የእርሱ ህዘብ የሆኑት እስራኤላውያን ያልጠፉት ፡፡ በመሳፍንት መፀሀፍ ወሰጥ አራት ጊዜ ንጉስ በእስራኤል ስላልነበረ የእሰራኤል ልጆች የፈለጉትን አድርገዋል ፡፡ እግዚአብሔር ለእስራኤል ዓላማ ዕቅድና ኪዳን ሰለነበረው ጣልቃ እንድገቡና ህዝቡን እንድመሩ መሳፍንትን መሾሙን ቀጠለ ፡፡ ቢሆንም ግን የትኛውም መስፍን እውነተኛውን ንጉስ መሆን አልቻለም ፤ እርሱም ኢየሱስ ክርሰቶስ የነገስታት ንጉስ የጌቶችም ጌታ ፡፡
በህይወት የወደቅህባቸው አጋጣሚዎች ይኖራሉ ፡፡ በወሲብ ምሰሎች ሱስ ወስጥ መውደቅ ፤ የመጨረሻ እንደሆነ ተሰፋ በማድረግ እንደገና በህመም ማሰታገሻዎች (የተለያዩ ሱሶች) ውስጥ መወደቅ ፤ በፍርሀት በሰጋት በሀዘን ውስጥ መወደቅ ፤ በወሬ ወይም በማጭበርበር ወጥመድ ውስጥ መወደቅ ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የብንያምን ነገድ እንዳዳነ ማለትም ለመልካም እንዳጠፋቸው ሁሉ እርሱ ኢየሱስ እንድመጣና አንተን እንድያድን ላከው ፡፡ ወድቀትህ ምንም የህል ከባድ ቢሆን እንኳ ኢየሱስ ሰለሚወድህ ሊያድንህ መቷል ፡፡ ይህን በማለት ህይወትህን ሙሉ ለኢየሱሰ ስጥ “ ኢየሱስ ሆይ ህይወቴን ተረከብ እኔ ተማርኬአለሁ አንተም ለዘላለም የህይወቴ ንጉስ እንድትሆን እሻለሁ ፡፡ ”
“ በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንግሥ አልነበረም ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር ፡፡ “
- መሳፍንት 21፡25
ተጨማሪ ጥቅስ
- ዮሐንስ 18፡37 –“ ጺላጦስም እንግድያ ነጉስ ነህን ? አለው ፡፡ ኢየሱስም መልሶ እኔ ንጉስ እንደሆንሁ አንተ ትላለህ ፡፡ እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ ከእወነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው ፡፡ “
- ገላትያ 2፡20 –“ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬለሁ እኔም አሁን ሕያው ሁኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል አሁንም በስጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ሰለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረወ ነው ፡፡ ”
- ራዕይ 17፡14 –“ እነዚህ በጉን ይወጋሉ በጉም የጌቶች ጌታና የነገስታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።