The Pentateuch Genesis

Joseph's Brothers Return to Egypt

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Seed Genesis 43-44 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 23 ከ730
ማውረዶች

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Genesis 44:33

“Now please let your servant remain here as my lord's slave, in place of the boy. Let him go back with his brothers.”

ይሁዳ ዮሴፍን በቢንያም ፋንታ አገልጋዩ እንዲሆን እንዲፈቅድለት አጥብቆ ለመነዉ። ይሁዳ ወንድሙን ለማዳን ጥሯል። ወንድማቸዉ ቢንያምን ይዘዉ ካልተመለሱ፥ እንዴት አባታቸዉ ያዕቆብ በኃዘን እንዲሚሞት ለዮሴፍ ገለጠለት። ይሁዳ ራሳ ወዳድነት የሌለበት፥ ዋጋ የሚያስከፍል ፍቅር አሳየ። ዮሴፍም የዚህኛዉን ወንድም ልብ እንዲያይ በር ከፈተለት።

ይሁዳ፥ ከራስ በላይ ስለሆነ ስጦታዉ እና ዋጋ ስለሚያስከፍል ፍቅር ምሳሌ የሆነንን፥ የክርስቶስ የዘር ግንድ ተሸካሚ ነበር። ክርስቶስ እንደወደደ ሌሎችን እንድትወድ ተጠርተሃል! ዛሬ፥ እግዚዓብሔር በህይወትህ ዉስጥ ይህንን ከራስ በላይ የሆነን እና ዋጋ በሚያስከፍል ፍቅር አንድን ሰዉ እንድትወድ እየጠየቀህ ይሆን?

"ስለዚህም እኔ ባሪያህ በጌታዬ ዘንድ ባሪያ ሆኜ በብላቴናው ፋንታ ልቀመጥ፤ ብላቴናውም ከወንድሞቹ ጋር ይውጣ።"

ኦሪት ዘፍጥረት 44:33

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የዮሓንስ ወንጌል 15:13፦ "ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።"

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:3-5፦ "ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ። በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።"

1ኛ የዮሓንስ መልዕክት 3:16፦ "እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል።"